የቀድሞው ቄስ ታደሰ ሲሳይ የልጆቻቸውን እናት ከፈቱበት (ሰኔ ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. ወይም June 2006) ጀምሮ ለበርካታ ዓመታት የቤተ ክርስቲያኗ ችግር ለተመልካች ሁሉ አሰልቺ፤ እምነታችንንና ባሕላችንን አስተቺና አስነቃፊ ሆኖ ያለ አንዳች መፍትሄ ሲጓተት መቆየቱ ለሁሉም የታወቀ ነው። ችግሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሀፍረት ላይ በመጣሉ፤ በዋሽንግተን ዲሲ: በቨርጅንያና በሜሪላንድ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ተሰባስበው የራሳቸውን የቀድሞው ቄስ ታደሰን ወላጅ እናት በመጨመር በየሳምንቱ የሚታየው ውዝግብ በሽምግልና እንዲያልቅ ብዙ ጥረት አደረጉ። ይሁን እንጅ በቀድሞው ቄስ ታደሰ ሲሳይ በኩል ሽምግልናው ተቀባይነትን ሳያገኝ ቀረ። ይልቁንም “ከሁሉም ገለልተኛ አድርጌ በስሜ ባስመዘገብኩት ንብረት የፈለግሁትን ባደርግ ጠያቂ ሊኖርብኝ አይገባም በማለት እንዲያውም የአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ዶላር ካሣ እፈልጋለሁ” በማለት ሽምግልናውን ረግጠው ወደ ዓለማዊ ዳኛ ሄደው በክርስቲያኖች ላይ ግለሰቡ ክስ መሠረቱ። የቀሩትን ምእመናንና የደብሩን መዘምራን ከሙዳየ ምጽዋቱ በተገኘው ገንዘብ ወታደር ቀጥረው ከቤተ ክርስቲያን ማባረር ጀመሩ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply