ባሳለፍናቸው ሳምንታት የሶስት እስራኤል ታዳጊዎች መጥፋትና ከቀናት በኋላ ተገድሎ ተገኘ። ይህም እስራኤላውያንን አስቆጥቶ በአንድ ታዳጊ ፍልስጥኤማዊ ላይ የበቀል እርምጃ አስወሰደ። ሟች እንጅ ገዳይ አይታወቅም ተባለ። ውጥረቱ ማየል መክረር ያዘ … የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ተፈጸመብን ያሉትን በደል ለመበቀል በአጸፋው በተወንጫፊ ሮኬት ሚሳኤል የእስራኤን መዲና ሳይቀር ማጥቃት ያዙ። ቴል አቢብን፣ እየሩሳሌምና ወደ የተለያዩ ከተሞች ዘልቆ የደረሰው ጥቃት ድንጋጤን ፈጠረ። ጠቅላይ ሚነኒስትር ናታንያሁ ተበሳጩ፣ ተሶረፉ! “እስራኤል አጸፋ ትወስዳለች!” ብለው በተናገሩ ቅጽበት የማጥቃት እርምጃውን አዘዙ! ጥቂቶችን ለማጥቀሰት በጋዛ ፍልስጥኤማውያን ላይ የመከራው ደወል ተደወለ…!
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ ጋዛን መልሰው ለማጥቃት የክተት አዋጅ ጠሩ። ሰኞ አጸፋ የአየር ጥቃት እርምጃም ተጀመረ። ማክሰኞ ሮብ ቀጠለ … በርካታ የጋዛ ግፉአን ንጹሃን ዜጎች ህይወት መቀጠፍ ጀመረ ከስምንት አመት በፊት ጋዛን ካደቀቃትና በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የተቀጠፉበት ወረራ በኋላ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ የቀጠለ ጥቃት ከ500 በላይ በእስራኤል የተጠኑ የፍልስጥኤም ሚሊሽያ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ተነግሯል። ባሳለፍነው ሰኞ በተጀመረው የአየር ድብደባ አቅመ ደካማ ህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንትንቶችን ጨምሮ 75 ፍልጥኤማውያን በጥቃቱ መገደላቸውና 500 ያህል ንጹሃን በጸና መቁሰላቸው እየተሰማ ነው።
ከጋዛ በፍልስጥኤም ሚሊሽያ ታጣቂዎች በኩል የተተኮሱት ከ200 የማያንሱ ተወንጫፊ ሚሳየሎች በሰው ህይወት ላይ ከባድ የሚባል ጉዳት ባያደርሱም ነዋሪውን ስጋት ውስጥ ጥለውታል። ከተተኮሱት ሚሳየሎች መካከል 40 ያህሉ በእስራኤል ሚሳየል መከላከያ መክሸፋቸውም ተጠቁሟል።
የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ የአለም መራሔ መንግስታት ከመግለጫ ያለፈ ስራ ሲሰሩ አልታየም። የንጹሃንና የግፉአን ፍልስጥኤም ተራ ዜጎች ደም ሲፈስ መፍትሔ ማምጣት ያልቻለው የተባበሩት መንግስታት ጸሃፊ ባንኪሙን ሁከቱን እና ድብደባውን ከኮነኑበት መግለጫና የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አልፈው የፈየዱትና የሚፈይዱት አለ አልልም! የማያልቅበት ስብሰባ መፍትሄ ላይሆን ተጠርቷል። የውግዘት መግለጫ ብቻውን መፍትሄ ሆኖ ነፍስን አይታደግ ነገር ንጹሃን በጠራራ ጸሃይ ግፍ እየተፈጸመባቸው አለም ዝም ያለ ይመስላል!
ቀንደኛ የተባሉትን የሃማስ አላቅሳ ሚሊሽያ ታጣቂዎችን ለማጥቃት በሚል የጋዛ ፍልስጥኤም ንጹሃን በጥይት አረር እየተቃጠሉ፣ እየቆሰሉና እየሞቱ ነው። በግፉአኑ ላይ ዛሬም አሳዛኝና ልብ ሰባሪ ግፍ እተፈጸመባቸው ነው! ይህ ሁሉ እየሆነ አለም ዛሬም ይህን የለየለት የንጹሃን ደም መፈረሰስ ለማስቆም የተጋ አይመስልም።
ብቻ … ለጋዛ ጸልዩ!
ነቢዩ ሲራክ
Tazabi says
Nebiyu S
We Ethiopians are living in hell, silent war, our people are being killed quietly for 23 years and still no one knows when it is going to stop. Unfortunately, we have enough destruction not to struggle by being together (united), either by woyane servants, or selfish citizens/so called politicians, could not to stand together and struggle for real freedom of right to live. Now, here you are asking us to cry for Palestine? As human beings we are sorry for them, but they have the whole world to be with them. On the other hand, no country cares about our suffrage. Abused immigrants case by Saudi Government is one good example for Ethiopians horrific problems and no country did care. I think you are enough to do it because you live in the right place to appeal for them. We have full plate of problems that we don’t even know how to solve. Even now, right this moment, citizens are being thrown to jail, being killed at any time, suffering with economic crisis, health issues …, you name it. To cry for your case will be “Yerasua Eyarerebat Yesew Tamasilalch,” for us.
Jarso says
Who the hell you think sypmathise for dead woods who accepts slavery as a matter of right and waiting for devine or rather the invisible one to fight his enemy, the woyane thugs.it is inconcievable to wipe woyane unless fully commited and put up genuine struggle like youths of the 60 &70. Thus until we take up our macheteand lock horns, weyane shall continue to rule with the usual iron hand.