• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አንድነት ከማን ጋር? አንድነት ለምን? አንድነት መቼ?

June 7, 2017 10:12 pm by Editor 2 Comments

ዐማራው በባህሉ፣ በሥነ-ልቦናውና በፖለቲካ ታሪኩ እንዲሁም በሚጋራቸው የወል ዕሴቶቹ፣ በእሱነቱና በኢትዮጵያዊነቱ መካከል የተሰመረ ልዩነት ባለመኖሩ፣በዘር ጠላትነት ተፈርጆ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሲፈጸምበት ፣ወንጀሉ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚፈጸም ነው በማለት፣ለምን? እንዴት? ብሎ ለመጠየቅ ከሁለት ዓሥርተ ዓመታት በላይ እንደፈጀበት በግልጽ ይታወቃል። ይህም ዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድንና አጋሮቹ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፉ ሠፊ ዕድልና አጋጣሚ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል። ይህን ያህል ቁጥር ያለው ከትግሬ፣ ከሶማሌ፣ ከጉራጌ፣ ከሲዳማ፣ ከወላይታ ቢጠፋ ሁሉም የነገዱ አባሎች ጠፉ ማለት ነበር። ዐማራው ይኸን ያህል ቁጥር የሰው ኃይል ጠፍቶበት፣ ምንም ያልመሰለው ከጣና ሐይቅ በጭልፋ ውኃ የመቀነስ ያህል ሆኖ በመታየቱ፣ የሁሉንም የዐማራውን ነገድ ጆሮ ሊስብ እንዳላስቻለ ይታመናል። ይህ ባይሆን፣ የወያኔው ፓርላማ በራሱ አደባባይ  ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮን ዐማራ ስልታዊ በሆነ መንገድ ጠፍቷል ብሎ ሲነገረን፣ ዐማራው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ሆ! ብሎ በአንድነት ይነሳ ነበር። ያለመነሳቱ ምክንያቶች የመጀመሪያው እንደ ኢትዮጵያዊ እንጂ፣ እንደዐማራነት አለማሰቡ ነው። ሌላው የቁጥሩ ብዛት፣ «ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል» አይነት ሆኖበት እንደሆነ ይታመናል።

ይኸም ሁሉ ሁኖ፣ የትግሬ ወያኔ ቡድን ሥልጣን ከጨበጠ በኋላ፣ እንደ መንግሥት ማሰብ አልቻም። የሁሉም ኢትዮጵያ ነገዶች ገዥዎች መሆናቸውን አለማመኑም። ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ የመግዛት ዓላማ  ዓላማችን ብለው አልያዙትም። ዓላማቸው ኢትዮጵያን መበታተን በመሆኑ፣በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ ነገዶችን፣ ቡድኖችንና ግለሰቦች እያሳደዱ ከምድረ ገጽ ማጥፋት ሥራዬ ብለው ይዘውታል። በአስተሳሰባቸው እሳ እና ይሉታ የሚባሉ ዕሴቶች የሏቸውም። ዐማራን ከቻሉ ከምድረ-ገጽ የማጥፋት፣ ካልሆነ በሁሉም መልኩ አናሳና የበታች አድርጎ የመግዛት ፍልጎታቸው የደነደነ ነው።  በመሆኑም ዐማራውን ከኢኮኖሚ እስከ ሕይዎት ነጠቃ፣ የሥራ ዕድል ከመንፈግ እስከ አገር ማሳጣት፣ ከመሬት መንጠቅ እስከ መዋለድ መክልከል ወዘተ ተደራራቢና ተከታታይ ወንጀል ዓይን ባወጣ መልኩ  ፈጽመውበታል። እየፈጸሙበትም ነው። ይህ ተደራራቢ ወንጀም መበራከት፣ ለካ እንድንጠፋ የተፈረደብን ዐማራነትና ኢትዮጵያዊነትን አዋህደን በመያዛችን ነው? ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት በቅድሚ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነውን ነገድ ማጥፋት የመጨረሻው መጀምሪያ ይሆናል ብለው አስበው ነው? የሚል ጥያቄ የዐማራው ልጆች እንዲያነሱ ግፊት እያሳደረ ነው።

በተፈጠረው ግፊትም ፣ዐማራው ኅልውናውን አስጠብቆ ማንነቱን ለማስቀጠል ያለው ብቸኛ አማራጭ ፣በማንነቱ ዙሪያ መደራጀት የሚለው ሆነ። በዚህ እሳቤ መሠረትም የተለያየ ዕድገት፣ መጠንና የአደረጃጀት ቅርጽ የያዙ ድርጅቶች በየአቅጣጫው ድምፃቸውን ማሰማት ጀምረዋል። ይህ መልካም መነቃቃትና ጅምር ነው። የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ገዥ ሀሳብ በነገድ ዙሪያ የሚሽከረከር በመሆኑ  ዐማራው ከዚህ ነባራዊ ሁኔታ ውስጭ ሊያደርገው የሚችል ግልጽ አመክንዮ ካለመኖሩም ሌላ፣ ሌሎች በነገዳቸው ዙሪያ ስሰባሰቡ በአውራ ጠላትነት ፈርጀው  እያጠፉት ያለው እርሱን በመሆኑ፣ በማንነቱ ዙሪያ  መሳባሰብ ምርጫው ሳይሆን ግዴታው  ሆኗል።  ይህም ዐማራውም፣ ከቁጥሩና ከደረሰበት ግፍና በደል አኳያ፣ ካንድ በላይ ድርጅቶች ቢኖሩት የሚደንቅ አይሆንም። ከአንድ በላይ ድርጅቶች ኖረው፣ ለዐማራው ድምፅ ቢሆኑ፣ በዙ፣ ለምን እንዴት ሆኖ ሊያሰኝ የሚችል አይሆንም። ግፉ በደሉ ብዙ ነውና!

በአንፃሩ የተለያዩ ድርጅቶች በዐማራው ስም መደራጀት፣ በዕውነት፣ ለዕውነት ለዐማራው ብሦት የቆሙ ከሆነ፣ የዐማራውን ችግር በዝምታና በይሁንታ የዓለም ማኅበረሰብ እንዲጠፋ ጆሮውን የነሳውን ክፍል ደጋግሞ በመጮኽ አድማጭ እንዲያገኝ አዎንታዊ ሚና ይጫወታል። ስለሆነም በዐማራው ስም ከአንድ በላይ ድርጅቶች መደራጀት ከዚህ አንፃር የሚደገፍ እንጂ፣ የሚነቀፍ አይሆንም።

ክፋት የሚኖረው እና የሚነቀፈው፣ እነዚህ ድርጅቶች የሚያራምዱት ዓላማ ምንድ ነው? የተደራጁበት መሠረታዊ ምክንያቶች ምንድናቸው?፣ የተደራጁት በራሳቸው አነሳሽነት ለዐማራው ተቆርቁረው ነው? ወይስ ከኋላ የሚገፋቸው ፀረ-ዐማራ ቡድን አለ? የተደራጁት ጠንካሮቹን የዐማራ ተቆርቋሪ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ለማኮስመንና ለማክሰም ነው? ወይስ ሌላ ለሚሉት ጥያቄዎች የሚያስገኙት መልስ አሉታዊ ሲሆን ብቻ ነው።  በዐማራ ስም የተደራጁት ድርጅቶች አንድ ሁኑ ከመባሉ በፊት ለእነዚህ ጥያቄዎች ተገቢና የማያሻማ መልስ መገኘት አለበት። ለጥያቄዎቹ የሚገኙት መልሶች ሁሉም ወይም ጥቂቶቹ በሐቀኞቹ የዐማራ ልጆች የተደራጁ ናቸው፤ ዕውነተኛ የዐማራው ሕዝብ ተቆርቋሪዎች ናቸው፤ የሚለውን መልስ ከጥርጣሬ ውጭ በሆነ መንገድ ማረጋገጥ ከተቻለ፣ ሁለመናዊ ኃይላችሁ ጎልብቶ፣ ወያኔን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ አሽቀንጥሮ ለመጣል መተባበር ሳይሆን፣ አንድ መሆን አለባችሁ የሚለው ከጥርጣሬ ባሻገር፣ በተግባር የሚገለጽ መሆን ይኖርበታል። ማን ምን እንደሆነና ለምን ዓላማ እንደተደራጀ በቅጡ ሳይለዩ፣ በዐማራ ስም ተደራጅተናል ስላሉ ብቻ አንድ ሁኑ የሚለው ግፊት የጤና አይሆንምና ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።

ከፍ ሲል ለመጥቀስ እንደተሞከረው፣ ለተነሱት ጥያቄዎች አዎንታዊ የሆነና ሁሉም ድርጅቶች ዕውነተኛ የዐማራው ኅልውና ተቆርቋሪዎች ከሆኑ፣ የዓላማ ልዩነት ከሌላቸው፣ ካለማንም ተጽዕኖና ጎትጓች አንድ ጠናካራ ድርጅት ለመፍጠር የሚከለክላቸው አንዳች ምክንያት አይኖርም። ይህ ግን የሚረጋገጠው በሂደት በጊዜ ፍሰት፣ በሚሠሩት ተጨባጭ ሥራዎች ነው። ድርጅቶቹ በአማርኛ ቋንቋ ፕሮግራማቸውን በማዘጋጀታቸው፣ ዓማርኛ ቋንቋ በመናገራቸው፣ በዐማራው ስም ነው የተደራጀነው በማለታቸው፣ ዕውነተኛ የዐማራው ኅልውናና ማንነት ጠበቃዎች ናቸው ማለት አይቻልም። ከኢሕአፓ፣ ከመኢሶን፣ ከኢጭአት፣ ወዘተ አመሠራረትና የትግል ጉዞ ብዙ የምናማራቸው ነገሮች አሉ። ሁሉም ስማቸው ተግባራቸውን የሚገልጽ አልነበሩም።

እነዚህ በዐማራ ስም ተደራጀን የሚሉ ድርጅቶች የራሳቸውን ዓላማ ዕውን ለማድረግ የተጨበጠ ሥራ ሠርተው ለዐማራው ያላቸውን ወገንተኛነት ሳያሳዩ፣ ተመሠረትን ባሉ ማግሥት ለአንድነትና ለውኅደት ተደጋጋሚ ጥሪ ከማቅረባቸው ባሻገር፣ ማስፈራሪያና ዛቻ የቀላቀለ ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ይደመጣሉ። ምንነታቸውን በተግባር ሳያሳዩ  የአንድነት ጥያቄ የሚያነሱ ቡድኖች ጥያቄአቸው ላይ ላዩን ሲመለከቱት ተገቢ ይመስላል። አንድነት ለሁሉም ነገር የሚበጅ፣ የጥንካሬና የማድረግ ብቃትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ የሚጠላ አይደለም። ይህም በመሆኑ ለአንድነት ጥያቄ ማቅረቡ መልካም ነው። ግን አንድነት ከማን ጋር? አንድነት ለምን፣ አንድነት መቼ? ለሚሉት ጥያቄዎች ሁነኛና ትክክለኛ መልስ ሳይዙ አንድ መሆን ለውጤት ያበቃል ተብሎ አይታመንም።

እንደዛሬው በነገዶች መካከል ያለው ልዩነት ጦዞ ጣራ ሳይነካ፣ በኢትዮጵያ ተመሥርተው የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ያደረጓቸው የመዋሐድና የአንድነት ሙከራዎች በተደጋጋሚ ተሞክረው ረጅም ርቀት ሳይጓዙ መበታተናቸውን እናውቃለን። ተባበረን፣አንድ ሆን ካሉ በኋላ ረጅም ርቀት ሊጓዙ ቀርቶ፣ የተፈራረሙበት ቀለም ሳይደርቅ በሚያስችል ፍጥነት ተለያይተው በጠላትነት  ግራና ቀኝ ቆመው፣አዳኝና ታዳኝ ሆነው የምናያቸው አያሌ ስብስቦች፣ መሠረትነው ላሉት አንድነት፣ ኅብረት፣ ቅንጅት፣ ውኅደት፣ ጥምረት፣ ትብብር ወዘተ— መፈራረስ መሠረቱ ከላይ ለተነሱት ጥያቄዎች ተገቢ መልሶች ሳይዙ፣ በይሁን ይሁን እና በአንዳንዶች ቀና አመለካከት በሌሎች መሠሪ ተንኮል የተነሳ፣ ውኅደቱ፣ ቅንጅቱ፣ ኅብረቱ፣ ጥምረቱ፣ አንድነቱ ወዘተ—  ውኃና ዘይት በመሆኑ የተነሳ እንደሆን ከሂደቱ መገንዘብ ይቻላል።

በአገራችን ፖለቲካል ታሪክ ውስጥ በዚህ መልክ አንድነት ከማን ጋር? አንድነት መቼ? አንድነት ለምን? የሚሉትን ጥያቄዎች ሳያብላሉ ፣ውኅደት፣ ቅንጅት፣ ኅብረት፣ ጥምረት፣ ትብብር ወዘተ— መሠረትን ብለው ዓመታት ቀርቶ ወራት ሳይጓዙ የተበተኑት ብዙዎች ናቸው። ለአብነት ያህል፦

1 ኢማሌድኅ (የኢትዮጵያ ማርክሲስት ሌኒኒስት ድርጅቶች ኅብረት) ይህ ማኅበር የመኢሶን፣ የወዛደር ሊግ፣ የማሌሪድ፣ የኢጭአት፣እና የአብዮታዊ ሠደድ ድምር የነበረ መሆኑ ይታወቃል።  ተፈጠረ የተባለው ኅብረት ብዙም ሳይጓዝ እርስ በራሳቸው መፋጀታቸውን የምናስታውሰው በሐዘን ነው። አቶ ተስፋዬ መኮንን የተባሉት «ይድረስ ለባለታሪኩ» በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፍ፣ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ለመወያየት ያልቻሉ አብዮታውያን በመንግሥቱ ኃይለማርያም እስር ቤት ባንድነት ታስረው ባንድ ጉድጓድ መቀበራቸውን በቁጭት የገለጹት የሚታወስ ነው።

2 ኢሕአፓ ፦ ኢሕአፓ ፣ የአብዮት ቡድን (የነጌታቸው ማሩ ቡድን)፣ የዴሞክራሲያ ቡድን (ይህ የነፀጋየ ገብረመድኅን፣ዘሩ ክሸን፣ ፀሎተ ሕዝቀየል፣ ተስፋዬ ደበሳይ እና ዮሐንስ ብርሃኔ ቡድን መጠሪያ ነው) ፣ የነሙሄ አብዶ ቡድን እና የነአሰፋ እንደሻው ቡድን} በመዋሐድ የተመሠረተ መሆኑ በግልጽ ይታወቃል። ይህ ቡድን ግን በተከተለው የከተማ ትጥቅ ትግል በደረሰበት የቀይ ሽብር ምት፣ ያስነሳው ክርክር አባላቶቹን ከሁለት መሰንጠቁና የድርጅቱን መሥራቾች ጌታቸው ማሩን፣ ይርጋ ተሰማ (መዝሙር) ወዘተ በራሱ በኢሕአፓ አመራሮች መገደላቸው ይታወሳል። በዚህ ሂደትም ድርጅቱ ከፊሉ ወደ ውጭ ሲሰደድ፣ አብዛኛ «አብዮቴ ማሪኝ» ብሎ ወደ ሰላማዊ ሕዎቱ መግባቱና በፀጋየ ገብረ-መድኅን የሚመራው በቋራ ትግሉን መግፋቱ ይታወቃል። ውጭ የተሰደደውም ኢሕአፓ እና ዴ-ኢሕአፓ ተብሎ ከሁለት መከፈሉ ግልጽ ነው።

3 ኢሠፓአኮ (ኢሠፓ)፦ ይህ ድርጅት ከኢማሌድኅ መበተን በኋላ ሕይዎታቸውን ለማትረፍ በፈለጉ የመኢሶን፣ የወዛደር ሊግ፣ የማሌሪድ እና የፖለቲካ ሥጣኑን የአንበሣውን ድርሻ የያዘው አብዮታዊ ሰደድ ያልተባረከ ጋብቻ የተመሠረተ እንደሆነ ይታወቃል። ኢሠፓ  በዚህ ምክንያት ወጥና ውኅድ ድርጅት  አልነበረም። በመሆኑም በድርጅቱ ውስጥ ታቅፈው የነበሩት ግለሰቦች፣ የየድርጅቶቻቸውን አቋም ይዘው ሲጓዙ የነበሩ እንጂ፣ የኢሠፓ ዓላማ አራማጆች አልነበሩም። ለወያኔ ድል አድራጊነትም፣ ይህ በኢሠፓ አባላትና አመራሮች መካከል የነበረ የመሥመርና መሰል የሥልጣን አጣን ጥያቄዎች አባላቱንና ሕዝቡን በአንድነት አስተባብሮ ለመምራት ያለመቻል ውጤት አንዱና መሠረታዊ ምክንያት ነበር።

4 አማራጭ ኃይሎች ከአሥራ ስድስት በላይ የነገድ ድርጅቶችን አካቶ አዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል በ1985 ዓም የተመሠረተና በዶ/ር በየነ ጴጥሮስ ይመራ የነበረው የድርጅቶች ስብሰብ ነበር። ይህም ስብስብ ለረጅ ጊዜ አለመቆየቱ ይታወሳል። በወቅቱ ጠካራ በነበሩት ድርጅቶች ላይ ወደፊት እንዳይገፉ ጥላውን መጣሉ ግን አይዘነጋም።

5 ኅብረት፣ ኢሕአፓን፣ መኢሶንን፣ ታንድ እና ኦብኮን ጨምሮ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙትን  ከአሥር በላይ ኅብረብሔራዊና ብሔራዊ ድርጅቶችን አካቶ የያዘ ስብስብ እንደነበር ይታወሳል። ይህም ከ1997 ዓም ምርጫ ዘመቻ በኋላ  ዕድሜ እንዳልነበረው ይታወቃል።

6 በኦነግና በቅንጅት መካከል ተመሠረተ የተባለው ኅብረት፣ ከሣምንታት ጩኸት በኋላ ስለመኖሩ ቀርቶ፣ ስለመመሥረቱ መናገር የተቻለበት ሁኔታ እንዳልነበር የሚታወስ ነው።

7 ኢዴኃቅ የተሰኘው በርካታ ድርጅቶችን አሰባስቦ የነበረው ኅብረት ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ የውኃ ሽታ ሆኖ እንደቀረ አይዘነጋም።

8 ግንቦት 7 በከማል ከልቹ ከሚመራው ኦነግ ጋር፣ ከዴምት፣ ከዐማራ ኃይል ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ ወዘተ ጋር ተፈጠሩ የተባሉት ጥምረቶችና ኅብረቶች የት እንደደረሱ በተጨባጭ እያየን ነው። ሁሉም ተስማሙ ከመባሉ ተጣሉ፣ ተበታተኑ የሚለው እየቀደማቸው አንዳችም ለውጤት የሚያበቃ ሥራ ተሠርቶ ሕዝባችን የኅብረትን፣ የቅንጅትን፣ የአንድነትን፣ የውኅደትን ፋይዳ ከንድፈ-ሀሳብ ባሻገር በተግባር ሳያይ ዘመናት መቆጠራቸው ዕውነት ነው። እናም  ተደጋግሞ በተሄደበትና ምንም ዓይነት አዎንታዊ የሆነ ገንቢ ውጤት ባልታየበት መንገድ ደጋግመን እንድንጓዝ የሚገፋፉ ቡድኖች፣ለአንድነችን የጓጉ ሳይሆኑ፣ ልክ እንዳለፉት ሁሉ ውድቀታችን የናፈቃቸው መሆን አለባቸው።

ካሁን በኋላ ለትብብር፣ ለኅብረት፣ ለጥምረት፣ ለቅንጅት፣ ለውኅደትና ለአንድነት የሚቀርቡ ጥያቄዎች ከላይ ለተነሱት ጥያቄዎች አዎንታዊ የሆነ መልሶች ከሚያስገኙት ጋር መሆን እንዳለበት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

አንድነት ከማን ጋር? ለሚለው ጥያቄ፣ በወረቀት ላይ የሰፈረ የዓላማ አንድነት ሳይሆን፣ በተግባር የታዬ መሆን ይኖርበታል። አንድነቱን የምንሻው «ትንሽ አሻሮ ይዘን ወደ ቆሎ በመጠጋት» የሌለ ሥልጣን ለመጋራት መሆን የለበትም። ሥልጣን ወይም ኃላፊነት በድርጅት ሳይሆን፣ በግለሰባዊ ችሎታ፣ ዕውቀት፣ ጽናት፣ ቁርጠኝነት ተመዝኖ ሚዛን የሚደፋው እንዲይዝ እንጂ፣ የድርጅት መሪ በመሆን የሚያዝ መሆን አይኖርበትም። ለመዋኃድ፣ለመተባበር ወዘተ በሚሹት ድርጅቶች መካከል ተመጣጣኝ የሆነ ሕዝቡን የማደራጀት፣ ሁለንተናዊ ዐቅም የመገንባት፣ ሥራ የሠሩ መሆናቸው ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት። በጥቅሉ ለአንድነት፣ ለትብብር በሚፈላለጉት ድርጅቶች ወይም ቡድኖች መካከል የሤራ፣ የማዳከምና የጠነከረውን ለማፍረሻ ስልት መጠቀሚያ ለማድረግ ያላሰቡ፣ የሁሉም ድርጅቶች መሪዎች ቆምንለት ለሚሉት ዓላማ የማያወላውል ቁርጠኝነት ያላቸው፣ ይህም ባለፉት ዘመናት በተግባር ያስመሰከሩ እና ከዋናው ሁሉም ጠላታችን ነው ብለው ከፈረጁት ወገን ጋር ምንም ኦይነት ንክኪ የሌላቸው መሆኑ በተጨባጭ ሥራ ያሳዩ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

አንድነት መቼ? የሚለው ጥያቄ የጊዜን አስፈላጊነት የሚያመላክት ነው። ለሁሉም ነገር ማንነትና ምንነት ጎልቶ የሚታዬው በጊዜ ነው። ጊዜ የሁሉንም ነገሮች ዕውነተኛ ቅርጽና ይዘት፣ ፍሬ ነገርና ክስተት ማሳያ ነው። ስለሆነም ተደራጀን ያሉ ድርጅቶች ማንነትን ለማወቅ ፕሮግራማቸውና እነሱ እንዲህ ነን ማለታቸው በቂ አይሆንም። ዕውነተኛ ማንነታቸውን በጊዜ ሂደት፣ በፈታኝ ሁኔታዎች በሚወስዱት አቋም ሊረጋገጥ ይገባል። ከአቶ ልደቱ አያሌውና ከአቶ አየለ ጫሚሶ የምንማረው ይኸኑ የጊዜን አስፈላጊነት ነው። ከትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር እና ከትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር ውኅደት እና ከተገኘው ውጤት የምንማረው ሌላ አሳዛኝ ጉዳይ እንዳለ ልብ ልንል ይገባል። እንዋሐድ፣ ኅብረት እንፍጠር፣ እንተባበር ከማለታችን በፊት፣ ማንነታችን ሕዝባችን በግልጽ ሊያውቅበት የሚችለው ጊዜ ሊሰጠው ይገባል። «የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ» እንዳይሆን በማስተዋልና በርጋታ ልናየው ይገባል። ኋላ ወጭት ጥዶ ማልቀስ እንዳይሆንብን፣ አስቀድመን ከእርቀት ነገና ከነገ ወዲያ ሊፈጠሩ የሚችሉ ክስተቶችን ካለፉት ጋር በማገናዘብ ወደ ተፈላጊው ግብ ሊያመራን የሚችለውን መንገድ እንድንከተል ለምንሰጣቸው ውሳኔዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።

አንድነት ለምን? የሚለው መልሱ የሚያሻማ አይሆንም። አንድነት የብቃት፣ የሁለንተናዊ ኃይል መገለጫ፣ የማድረግ ብቃት መለኪያ ወዘተ በመሆኑ አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይሆንም። ከዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ አንድነቱን የፈለጉት ኃይሎች እነማን ናቸው? ከኋላቸው ማን አለ? አንድነቱን የፈለጉት በእርግጠኝነት ከአንድነቱ የሚመነጨው ሁለንተናዊ ጉልበት ለተፋጠነ ድል ያደርሰናል ከሚል ነው? ወይስ በአንድነት ስም ገብቶ የጠነከረውን ለማላላት፣ ሰላሙን ለማናጋት፣ ጥቃቅን ልዩነቶችን በማጉላት ነባር አንድነቱን ለማሳጣት? በአንድነቱ ስም በአቋራጭ የሌለ ሥልጣን ባለቤት ለመሆን?  የሚሉት ሊጤኑ ግድ ይላል።

በግልጽ እንደሚታወቀው፣ አንድ ቡድን ከሌላ ይመሳሰለኛ ብሎ ከሚያስበው ጋር የአንድነት፣ የውኅደት፣ የትብብር፣ የቅንጅት ወዘተ ጥያቄ የሚያቀርበው ከሚከተሉት ምክንያቶች አንዱን ወይም ካንድ በላይ የሆኑትን ለማግኘት ነው።

አንደኛ፦ የሚፈጠረው ወይም የሚመሠረተው ውኅደት፣ አንድነት፣ ኅብረት፣ ቅንጅት፣ወዘተ ሼር የሌለበትና በሐቅ ላይ የተመሠረተ ከሆነ፣ ወይም የሚሆን ከሆነ፣ ወደ ተፈላጊው ግብ በአጭር ጊዜ መድረስ የሚያስችል መታለፍ የሌለበት ጉዳይ መሆኑን በማመን፣ ድርድሩ በዓላማ ላይ እንጂ፣ ሌሎች ጉዳዮች በችሎታ ላይ የሚመሠረቱ መሆኑን ሁሉም ሲገነዘቡና ፣ሁሉም የችሎታችን እናገኛለን ብለው ሲረዱ የሚደረግ ስምምነት አዎንታዊና ዓላማን ከማሳካት ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ሁሉም የሚሹትን ሳይሆን የሚችሉትን የሚያገኙበት ነው።

ሁለተኛው፦ ስምምነት፣ አንድነት፣ ወዘተ የሚሹ ቡድኖች፣ በመካከላቸው የኃይል ሚዛን ተፈጥሮ አንደኛው ሌላውን ከጨዋታ ውጭ የማድረግ አቅም የሌላቸው መሆኑን ሁለቱም ሲገነዘቡ፣ ሰጥቶ በመቀበል የጋራ ግባቸው ወደ ሆነው ተግባር በአንድነት ፊታቸውን ማዞር እንዳለባቸው ሲረዱ የሚመሠርቱት ነው። ይህም አቅምን አውቆና ተገንዝቦ ወደ ጋራ ግብ ለመድረስ የሚያስችል በመሆኑ አዎንታዊ ነው። ስምምነቱ ሰጥቶ የመቀበል እና በዓላማ አንድነት ላይ የተመሠረተ ነውና።

ሦስተኛ፦ ለትብብር፣ ለውኅደት፣ ለአንድነት ከሚጠይቁት ቡድኖች አንደኛው በራሱ እንቅስቃሴ ከሚፈልገው ደረጃ መድረስ የማይችል መሆኑን ሲገነዘብ፣ ያለበትን ድክመት በሚመሠርተው ኅብረት ወይም አንድነት ለመወጣት ሲል የሚያቀርበው የአንድነትና የእንተባበር ጥሪ ነው። ይህም  ታይቶ ጠፋ ላለመባል፣ በዚያውም በሚፈጠረው ኅብረት፣ አንድነት ውስጥ የተወሰነ ቦታ አገኝቶ ኅልውናውን ለማስቀጠል በማሰብ፣ የእንተባበርን ጥያቄ አበክሮ ያነሳል። ይህ ከድክመት የሚመጭ በመሆኑ ለሚፈጠረው ኅብረት ወይም አንድነት የችግር ምንጭ ከመሆን አይዘልም። በቅንጅት ውስጥ ከተካተቱት አንዱ የነበረው ቀስተ ዳመና ያደረገው ይኸን ነው። ለጠንካሮቹ መኢአድና ኢዴፓ-መድኅን የውድቀት ምንጭ እንደሆነ ይታወቃል።

አራተኛ፦ አንደኛው ቡድን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑት፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያገኘውን ድርጅት ጠልፎ ለመጣል እንዲያመቸው፣ በእንደራደር ስም ወይም ስበብ የዚያን ድርጅት ልዩ ልዩ መረጃዎች፣ የጥንካሬና የድክመት ምንጮች የሆኑትን ለይቶ ለማወቅ ይጠቀሙበታል። በዚህም ድርጅቱ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊገጥሙት የሚችሉትን መሰናክሎች  ጥሎ ሊያልፍበት የሚችልበት አማራጭ ስልቶች ከሌሉት በተባለው ድርድር ስም በጠላቶቹ  ተጠልፎ እንዲወድቅ ያደርገዋል። ለመኢአድ ውድቀት ዓይነተኛ ምክንያት የሆነው ይህ ዓይነቱ ድርድር ነው።

አምስተኛ፦ ተደራዳሪዎች ለሰላም አልቆሙም፣ አንድነትን አይፈልጉም ከሚለው ክስና ሐሜት ራሳቸውን ለመከላከል እንዲችሉ፣ ለሚቀርቡ የአንድነትና የእንተባበር ጥያቄዎች አፋዊ የሆነ መልሶችን በመስጠት ትብብሩ ወደፊት እንዳይገፋ ዲፕሎማሲያዊ ቋንቋዎችን በመጠቀም ጊዜ  ለመግዛትም የሚጠቀሙበት የትብብር ጥያቄ አለ። ሌላው ጠንካራውን ድርጅት የማዳከሚያና በትብብር ስም ይኸን አለ፣ እንዲህ ተባለ የሚሉትን ወሬዎች በአንድነት አፍቃሪነት ስም፣ አንድነት እንዳይኖር፣በአንፃሩ ተቃዋሚው ኃይል ራሱን አጠንክሮ እንዳይወጣ ጊዜ ማባከኛ የድርድርና የኅብረት ጥያቄዎች እንዳሉ ልብ ልንል ይገባል።

በአጠቃላይ በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ምሕዋር ውስጥ ለአንድነትና ለውኅደት የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ፣ ከላይ የተነሱትን ጥያቄዎች በማንሳት ተገቢና የማያሻሙ መልሶችን መያዝ ብልኅነት ብቻ ሳይሆን ፣ዐዋቂነት ጭምር መሆኑን ማስተዋል ተገቢ ነው።

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ ፤ ሁሉም ዐማራ ለአንድ ዐማራ!
የዐማራው ኅልውና መጠበቅ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ማክሰኛ ግንቦት ፳፱ ቀን ፪ሺህ ፱ዓ.ም.              ቅፅ፭፣ ቁጥር፲፯


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

 

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. kibret Tesemma says

    June 21, 2017 11:57 am at 11:57 am

    The opinions expressed in this article cannot be faulted. There is an object lesson for those who have taken it upon themselves to struggle for Amara Salvation.

    Amaras must be in a position to muster enough strength before consider any alliance with any one.

    Amaras are maligned because of their deeply uncompromising stance on the sanctity of the motherland.
    As Moresh has emphatically narrated, all the previous unity accords between the various groups have crumbled for on reason or another. That is why Amaras must be prepared to bear their own cross first.
    It is far from forging an alliance with anyone at this stage.
    Those who care about Ethiopia and the endangered Amaras, of whom the Tigre/Eritrean occupation force have exterminated over 5 million already, will understand if Amaras just mind their singular plight for the moment.
    Amaras must travel the tortuous journey alone. At least, for the moment. The least, that well-meaning compatriots should do is, to respect this stand.

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    June 23, 2017 03:32 am at 3:32 am

    Guys!!! As I see, the article is jumping or dancing as a tree is touched by storm. The writer is concerned on unity of the country. The unity could bring the equality of her people. All nations and nationalities and even her peoples, should get the right of nations up to separation. This determination could bring to all people trust, confidences, right of speeches, developing their culture, languages, music, dramas, even religion and so on. The Amhara nation, as a chance, his previous kings ruled the whole nations with”unite”; but rejecting other nations rights. Gradually, the conflict started by demands. Those requests went to arm struggle in order to find equality or separation. The arm struggle went thoroughly through out the country. During those periods, the Amhara nation was driven with his rulers against and stood wrongly. Even now, some people couldn’t understand the situations at all. If any movement is created which subjugated the mass requests, then, that ideas would be supportive. More or less, even it takes long period, the demand would be success full. The Amhara nation is among the oppressed nation like other nations. Even though, the equality was preached by his rulers, he was not beneficial economically. What we opposed on the current situation, is that, the Amhara nation is against the equality of others. If it is the Amara’s stands, then, the federal system of the constitution will face a big cloud. Otherwise; no one opposes the unity and the equality of the country. What we should underline or make a remark; our federal government is exercising the equality of the whole nations and nationalities.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእምዬ ምኒልክ አዳራሽ October 30, 2023 10:27 am
  • የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ October 26, 2023 01:30 pm
  • ጥቅምት 15 ለምን? October 26, 2023 01:29 am
  • “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት” October 26, 2023 12:57 am
  • “ውትድርና ሕይወቴ ነው” October 26, 2023 12:13 am
  • መከላከያ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የሚመጥን ኃይል እየገነባ ነው October 20, 2023 05:07 pm
  • “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው” ፕ/ር ብርሃኑ October 20, 2023 04:47 pm
  • 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ታሰሩ October 18, 2023 04:29 pm
  • በተማሪዎች ፈተና ውጤት ለታየው ውድቀት ትምህርት ሚ/ር ኃላፊ መሆን አለበት ተባለ October 18, 2023 04:00 pm
  • ቀይ ባሕር እና ዓባይ “የኅልውና ጉዳይ ናቸው”፤ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” October 13, 2023 10:04 pm
  • ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም October 10, 2023 01:51 pm
  • “አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች October 10, 2023 09:07 am
  • እሸቴ አሸባሪ፤ ቲዲኤፍ/ትሕነግ “ሰማዕት” – የዘመናችን ጉድ! October 7, 2023 06:47 am
  • በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል September 27, 2023 10:42 am
  • በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል September 27, 2023 08:41 am
  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule