ያለፉት 23 አመታት በመንግስትና ተቃዋሚ መካከል ያለው ቅራኔ መፍትኤ አላመጣም። በጦርነት ስልጣን የያዘ መንግስት ዲሞክራሲ ይኸሁላችው ብሎ ይሰጥ ዘንድ አይቻለውም። በጦርነት መንግስት ለመቀየር የሚታገለውም ስልጣኑን ሲይዝ ከዚህ የተለየ አያደርግም። ኢትዮጵያ መውጫ ቀዳዳ ያጣች ትመስላለች። እሺ ብንል እርቅና መግባባት ዲሞክራሲን ለመውለድ ብቸኛ መንገድ ነው። እንዴት ማለት ጥሩ ነው። ሁላችንም የምንጠለልባት፦ በፍቅር ተሳስረን የምንኖርባትን ቤተ ኢትዮጵያን እንዴት እንገንባት?
1ኛ/ ሰላምን ብቻ መምረጥ ላይ መድረስ፦ የቤተ ኢትዮጵያ መሰረት።
የስላሙን ትግል ከትግሎች ውስጥ እንደ አንዱ ሳይሆን እንደ ብቸኛ አማራጭ መውሰድ ይገባል። ኢትዮጵያ ለዚህ አይነት ሰላም ራሳቸውን የሰጡ ሰላማዊ ተቃዋሚ ልጆች አላት። ሰላምን ብቻ መምረጥ ወደ ዲሞክራሲ የሚያደርሰው የእርቅና መግባባት አስተሳሰብ መሰረት ነው። ያለዚህ የመጀመሪያ እርምጃ ንቅንቅ ማለት አይቻልም። በሌላው በኩል ይህ ብቻ በራሱ ዋጋ የለውም። በዚህ መሰረት ላይ መሰራት ያለበት ምሶሶ ያስፈልጋል። ያም ምሶሶ መተማመን ነው።
2ኛ/ መተማመን ላይ መድረስ፦ የቤተ ኢትዮጵያ ምሶሶ።
መንግስት ለሰላም ትግል ነፃነት ሰጥቻለሁ ማለት ብቻ በራሱ ዋጋ የለውም። ተቃዋሚ የሰላም ትግል አካሄዳለው ማለቱ ብቻ በራሱ ትርጉም የለውም። መተማመን ላይ እስካልተደረሰ ድረስ ሁለቱም ውጤት አያመጡም። ለመተማመን ደግሞ ቃል በስራ መተርጎም አለበት። ለምሳሌ መንግስት የሕዝብን ሚዲያዎች በሙሉ ለራሱ መገልገያ ማዋል ብቻ ሳይሆን ለሰላማዊ ተቃዋሚ መድረኩን መክፈት ይጠበቅበታል። ያለበለዚያ እግርን ጥፍር አድርጎ አስሮ ሲያበቃ ለመሮጥ ነፃነት ሰጥቻለሁ እንደማለት ይቆጠራል። በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚው የሰላም ትግልን ከመረጠ የመንግስት ተቃዋሚ ብቻ ሳይሆን የትጥቅ ትግል የመረጡትንም ጭምር መቃወም ይጠበቅበታል። ያለበለዚያ በሁለት ቢላዋ ለመብላት እንደ መሞከር ይቆጠራል።
3ኛ/ መደማመጥ ላይ መድረስ፦ የቤተ ኢትዮጵያ ግድግዳ።
መተማመን ከተጀመረ መደማመጥ መከተል ያስፈልገዋል። ያለበለዚያ ምሶሶ ብቻ ታቅፎ ቤት አለን አይባልም። አንዱ ሌላኛውን ከጨዋታ አውጥቶ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ከመፈለግ ይልቅ በእርቅና በመግባባት የኢትዮጵያን ችግር አብሮ ለመቅረፍ መጣር ያስፈልጋል። ሰላማዊ ተቃዋሚ መሆን ጥቅሙ በጉልህ ይታይ። መንግስት ከሰላማዊው ተቃዋሚ ጋር በመጎራበት ሲሰራ ያየ ሁሉ የትጥቅ ትግል ጊዜ ያለፈበት ያረጀና ያከተመለት መሆኑን በሚገባ ይረዳል። ቤተ ኢትዮጵያም መልክ እየያዘ ይመጣል። ግን ጉዞው ገና ነው። ቤቱ መጠለያ ለመሆን ጣሪያ ያስፈልገዋል።
4ኛ/ ዲሞክራሲን ማዳበር ላይ መድረስ፦ የቤተ ኢትዮጵያ ጣሪያ።
ምሶሶና ግድግዳ ሳይቆም ጣሪያ መስራት እንደማይቻል ሁሉ፤ ዲሞክራሲን ለማዳበር ከዚህ በፊት የተዘረዘሩትን ከቁም ነገር ማስገባትና በስራ መተግበር ያስፈልጋል። መንግስትና ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በመጎራበት ሲሰሩ፦ መንግስትና የትጥቅ ታጋዮች ጡንቻቸውን መጠቀም ሲተው ያኔ ዲሞክራሲ ለማደግ ፋታ ያገኛል። ይህ አማራጭ መንገድ የኛው በኛው ለኛው የሆነ የእርቅና መግባባት ስሌት ነው። ከሌላ ኮርጀን የምናመጣው አይደለም። እንግዲህ መንግስትና ተቃዋሚ አንዱ ያለሌላኛው ለኢትዮጵያ ዜሮ መሆኑን ይረዳ። መንግስትም ንቀቱን ይተው። ተቃዋሚም ጥላቻውን ይተው። ሁለቱም በእርቅና በመግባባት የኢትዮጵያን ውስብስብ ችግር ዲሞክራሲን በማዳበር ለመፍታት ይጣሩ። አዲስ አቅጣጫ ያስፈልገናል። ያለበለዚያ ያንኑ ያረጀ አካሄድ ይዘን አዲስ ምዕራፍ መሻገር አይቻልም። ኢትዮጵያ እንዲታደጓት የምትጠራው ሁለቱም ጎራ ውስጥ ያሉትን ልጆቿን ነው። የእናት ኢትዮጵያን ድምፅ የሚሰማ ይታጣ?
እባክዎን ስለ ብሔራዊ እርቅና መግባባት የተዘጋጀውን የሃሳብ ዳሰሳ (survey)፤ ለዚሁ አገልግሎት ወደ ተዘጋጀው ድህረ ገፅ በመሄድ ድምፅዎን ያሰሙ (እዚህ ላይ ይጫኑ)። ለሌሎችም ይሞሉ ዘንድ ያሳስቡ። አዲሱ አመት የእርቅና የመግባባት ዘመን ይሁንልን። የኢትዮጵያ ጉዳይ ግራ የገባው ሁሉ እጁን ወደ እግዚአብሔር ይዘርጋ፦ ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ እርሱ ፈጣሪያችን ኢትዮጵያን ይታደጋት!አይዞን እግዚአብሔር አለ።
koster says
Is this another Shimagle ala Professor Ephrem Isaac?????????? Do you know the crimes committed by the fascists in the last 23 years and the looting taking place. Do you want a South Africa type of solution – Tigrian fascists like Apartheid South Africa owning everything and the rest as second class citizen in their own country. First the fascists should be defeated and understand that they are not bullet-proof super-men and then after they are defeated and are willing to live like any other ethnic groups in a free and democratic Ethiopia they have the right to do so unless they are criminals and looters. Instead of pushing to bring these criminals to justice the so-called elites/shimagles with a hidden agenda are messing and prolonging the suffering of the Ethiopian people. Are you investor worrying of your investment or condo or do you really care for Ethiopia and Ethiopians? How about the land taken forcefully from Gondar, Wollo, Afar etc by these home grown fascist. TPLF should be dismantelled like the Monarcy and the DERG, I am aware of the material and human losses but there is no other way. 23 years of begging is more than enough. If those criminals face justice and disappear from the Ethiopian politics may be it is possible to negotiate with the rest and the Tigrians should accept even the consequence will be painfull. Forcefully taken land taken should be returned to their rightfull owners, wolqaitis etc. etc.
mes says
ዶክተር ፣እስቲ ተቀዋሚዎች የሚባሉትን የተዋቸውና መንግሥት ራሱ የሚሰራው ድርጊት ከዘረኝነት ወጥቶ ኢትዮጵያዊ ይሆን ዘንድ ምከሯቸው !፣የነሱ ኢትዮጵያነትን መጥላት ነው ህዝቡ በነሱ ላይ ጥላሸት የቀባው እንጂ ምን ተቃዋሚ አለበት ይሄ መንግሥት ፣? መንግሥት እየተጨነቀ ያለው የሚሸጥ ነገር በማጣቱ እንጂ በተቀዋሚ መብዛት አይደለም ። እንደው መምክረ ከቻሉ tplf ን የምከሩ እንጂ ተቃዋሚ ሊያሳስቦት አይገባም ። ለነገሩ በዚህ ሁሉ መከራና ኢሰብአዊ በደል በሕዝቡ ላይ እየተፈፀመ እንደርሶ የሚያስብ ሰው መኖሩ ትንሽም ቢሆን ለሰዉ ተስፋ የሚሰጥ ይመስላል ፣ ግን ዶክተር ወያኔዎች እንዴት እንደሚያስቡ የተረዱ አልመሰለኝም ለነሱ የኢትዮጵያዊነት ምሶሶ፣ የቤተ ኢትዮጵያ ግድግዳ የሚባል ነገር በነሱ መዝገበ ቃላት ውስጥ የለም ። የነሱ አጀንዳ ታላቋ የትግራይ ትግሪኛ ፣ ሞት ለአማራ ሞት ለኢትዮጵያዊነት ነው። እነሱ ካልተመቻቸው ደግሞ አገሯ ትበጣጠስ ነው፣ ይህ ነው አጀንዳው ፣ እርሶም የፈሩት የህንኑ ሳይሆን አልቀረም ፣እኔም እነደርሦ አስፈርቶኛል ።
የሚመከሩ ከሆነ በርትተው የምከሩአቸው።