1) መነሻ እውነታዎች፤
በዚህ ቋንቋን መሰረት ባደረ የጎሳ ፌዴራል ስርዓት፦
(ሀ) ጊዜ ያነሳቸው ባለጉልበቶች በጎሳና በቋንቋ ተቧድነው የኢትዮጵያን ህዝብ የጋራ መሬትና የተፈጥሮ ሃብትን ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ አግበስብሰው በመያዝ ከዚህ መስመር አትለፍ፣ ይህ የኔ ክልል ነው አንተን አይመለከትህም፣ መጤዎች ከክልላችንን ለቃችሁ ውጡ፣ መሬቱን እንፈልገዋለን ወደ ሃገራችሁ ሂዱ እያሉ የሃገሪቷን ዜጎች ተወልደው ካደጉበት፣ አድገው ከተዳሩበት፣ ወልደው ከከበዱበት ከሃገራቸው ላይ እንደ ዋዛ ቤተስብ በሚያፈርሱበትና በሚያፈናቅሉበት፣ በተለይም አንዱ የሃገር ባለቤትና አፈናቃይ ሌላው በሃገሩ ላይ ባዳና ሁለተኛ ዜጋ በሆነበት ሁኔታ፣
(ለ) ጥቂቶች የሃገርን ሃብትን ዘርፈውና የንፁሃንን ደም አፍሰው፣ በየእስር ቤቱ ዜጎችን ቶርቸር እያደረጉና እያሰቃዩ ከህግ በላይ ሆነው ሰውንም እግዚአብሔርን ሳይፈሩ በማን አህሎኝነት ደረታቸውን ገልብጠው በሚፎልሉበት ሃገር፣
(ሐ) ህወሃት/ትህነግ ጫካ ሳሉ በ1968 ዓ.ም ባፀደቁት ማኒፌስቷቸው ላይ በግልጽ የአማራን ህዝብ ማህበራዊ ሰላም እናሳጠዋለን በማለት በዛቱት መሰረት በለስ ቀንቷቸው የሃገሪቱን ስልጣን ከተቆጣጠሩበት ካለፋት 27 ዓመታት ጀምሮ የአማራ ህዝብ ላይ ተቋማዊ በሆነ ሁኔታ ግፍና መከራ እያዘነቡበት ይገኛሉ፣ ከፓለቲካው በማግለል፣ በኢኮኖሚው በማድቀቅ፣ ት/ት ቤቶች እንዳይስፋፉ መንገድና ጤና ጣቢያዎች እንዳይገነቡ Sabotage በመስራት፣ የአማራው ህዝብ ከድህነት ወለል በታች አድርገውታል፣ በጤና ችግር እንዲጎዳና ተደርጓል፣
(መ) ወያኔ፣ ኦነግ፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ እና የመሳሰሉት አማራ ጠል ሆነው በወያኔ ተጠፍጥፈው የተፈጠሩ ድርጅቶች እንዴት የአማራን ህዝብ እንደሚጎዱት እቅድና ፓሊሲ ነድፈው፣ ስልጠና ሰተው፣ በሰው ሃይል አደራጅተው፣ በጀት ተመድቦላቸው በት/ት ቤት፣ በመንግስት መ/ቤት፣ በቀበሌውና በገበሬ ማህበሩ በአማራ ህዝብ፣ ባህል፣ እምነትና ታሪክ ላይ ዘመቻ በመክፈት በህዝቡ ላይ ጥላቻንና በቀልን በመቀስቀሳቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራዎችን አጥፍተዋል፣ አፈነናቅለዋል፣ ገለዋል፣ አስረው አንገላተዋል፣ አማራ ይጠቀምበታል ያሉትን ሁሉ አጥፍተዋል፣ ቤተክርስቲያኑንና መስኪዱን እንኳን ሳይቀር አቃጥለው ካህናቱን ቤተ መቅደስ ውስጥ በሜጫ/በገጀራ አርደዋል።
(ሠ) ስለዚህ በሃገርና በዜጎቾ ላይ ይህንን ሁሉ መከራና ግፍ የፈፀመ፣ በዘረፋና በንፁሃን ደም ላይ የቆመ፣ ከመነሻው ችግር ያለበት ይህን ፋሺስታዊና የአፓርታይድ ስርዓት በጥገናዊ ለውጥ ደጋግፎ ማቆም ማለት በንፁሃን ደም መነገድ፣ በሃገራችን ላይ ጊዜ ጠብቆ የሚነሳ በሽታ (ቫይረስ) መሸከም እንደ ማለት ነው፣ ከችግሩ ለመላቀቅ ቁርጠኝነቱ ካለ ችግሩን የፈጠረውን ስርዓት ከስር መሰረቱ ከፓሊሲዎቹና ከመዋቅሩ ጋር አንድ ላይ ጠራርጎ መጣል ነው። ነገር ግን Risk መውሰድ ካልተቻለ ወይም ወኔው ከሌለ – በሻይረሱ ያልተበከለውንና ታክሞ የሚድነውን በጥንቃቄ በመለየት – ዋናውን ካንሰር ተሸካሚውን ቆርጦ በመጣል የቀረውን አካል ከስቃይ ማዳን ተገቢ ነው።
2) ክልሎችና የመሬት ቅርምት በኢትዮጵያ (Scramble for Ethiopia)
እንደሚታወቀው በ1885 (እኤአ) የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን ለመቀራመት ጀርመን በርሊን ላይ ስብሰባ አድርገው የአፍሪካ ካርታን እንደ ምግብ በመካከላቸው ጠረጴዛ ላይ ዘርግተው አፍሪካን እንደ ቅርጫ ስጋ ያለከልካይ ተከፋፈሏት። ይህም የበርሊኑ አፍሪካን የመቀራመት ጉባኤ «Scramble for Africa» ተብሎ ይታወቃል። በተመሳሳይ ሁኔታ በ1983 ዓ.ም ደርግ ወድቆ ወያኔና ኦነግ የሽግግር መንግስት በጋራ እንደመሰረቱ። ባለው የህዝብ ብዛትም ይሁን ለሃገር አንድነትና ስልጣኔ ዋጋ የከፈለውን የአማራን ህዝብ አግልለው ይህንን ወሳኝ የህልውና እና የሃገር ባለቤትነት ጉዳይ ብቻቸውን በራቸውን ዘግተው እንዳሻቸው ኢትዮጵያን በክልል በመሸንሸን ተቀራመቷት። የኢትዮጵያን ካርታ ጠረጴዛ ላይ ዘርግተው ሽንሸናውን ሲያከናውኑ ሳይንሳዊና በተጠና መንገድ ማለትም የወቅቱን የኢትዮጵያን ህዝብ ብዛት፣ የህዝቡን ፍላጎትና ስብጥር፣ አሰፋፈር፣ የተፈጥሮ ወይም ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ ስነልቦና፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ዝምድናን እና የመሳሰሉትን ግምት ውስጥ ያስገባ አልነበረም።
በጣም የሚገርመው በወቅቱ እራሳቸው ወረቀት ላይ ባስቀመጡት የቋንቋና የጎሳ መስፈርት መሰረት እንኳን ያልተከናወነ ነበር። እንደነሱ የቋንቋና የጎሳ መስፈርት መሰረት በትክክል ቢሰራ ኖሮ ትግራይ ቢያንስ 5 ወይም 6 ክልሎች ማለትም የትግሬ፣ የኩነማ፣ የአገው፣ የይሮብና የሳሆ (የጠልጠል፣ አፋር) ክልል ይወጣት ነበር። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋም ሆነ ብሔረሰብ በሃገሩ ላይ እኩል መብት አለው፣ አንዱ ከሌላው አያንስም፣ አይበልጥም እስከተባለ ድረስ የህዝቡ ብዛት 10 ሺህም ሆነ 10 ሚሊዮን የሁሉም መብት እኩል ተከብሮ እራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ ሊረጋገጥለት ይገባል። ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ አጠቃላይ በጎሳዎቻ ቁጥር ወይም ቋንቋዎች ብዛት ስንሄድ በኢትዮጵያ ከ85 ክልል በላይ በተፈጠረ ነበር። ነገር ግን ወያኔና ኦነግ በወቅቱ የነበራቸው ዋና ዓላማ ሁሉኑም የሃገር ባለቤት ማድረግ ሳይሆን ወደፊት ለመመስረት ላቀዱት ለትግሬ ወይም ለኦሮሞ ነፃ መንግስት ኢኮኖሚ ምንጭነት ይጠቅመናል ብለው ያሰቡትን ለምለም አካባቢዎችንና የተፈጥሮ ሃብቶችን (Natural Resources) በህግ ሽፋን ወደ እነሱ ክልል ማከማቸት (ማግበስበስ) ነበር።
በኤርትራ ተሰኔ በሚባል ቦታ ወያኔ፣ ኦነግና ሻዕቢያ ከደርግ ወድቀት በኋላ ስለሚፈፅሙት ነገር ጉባኤ ተቀመጡ። 1ኛ. በተለይ ወያኔና ኦነግ ኢትዮጵያን በቋንቋና በጎሳ ከፋፍለው ተስማሙ፣ 2ኛ የኤርትራን ነፃ መንግስትነት እንደሚቀበሉና አስፈላጊውንም እገዛ እንደሚያደርጉ በድርጅቶቻቸው መሪዎች በሆኑት በመለስ ዜናዊ፣ በሌንጮ ለታና በኢሳያስ አፈወርቄ አማካኝነት ተፈራረሙ። በተለይም ወያኔና ኦነግ ባደረጉት የሁለትዮሽ ስምምነት ስልጣን እንደያዙ መጀመሪያ ለማድረግ የተስማሙት ኢትዮጵያን ለዘጠኝ ክልሎች መከፋፈል ነበር። ስለዚህ አሁን በኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች የተፈጠሩትም ሆነ ድንበራቸው የተወሰነው የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠይቆ፣ ተወያይቶበትና ድምጽ ሰጥቶበት ሳይሆን በወያኔና በኦነግ አመራሮች መሃል በተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት ነው። እውነተኛ ከሆኑ ለምን ይህ ተንኮልና ድብብቆሽ አስፈለገ? ለምንስ የኢትዮጵያን ህዝብ በይፋ አላወያዩም? ይህ የሚያሳየን ወያኔና ኦነግ በኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ የተፈጥሮ ሃብት ላይ የውንብድናና የማፍያ ስራ መስራታቸውን ነው።
በመሆኑም ኦነግና ወያኔና እንደ ኦህዴድ ዓይነት ተለጣፊ የጎሳ ድርጅቶች የህዝቡ ፍላጎት ሳይጠይቁና ድምጽ ሳይሰጥበት በፈጠሩት አዲስ ክልሎች የተቀራመቱትን መሬት ለህዝባቸው – ታግለን ያስገኘንልህ የክልልህና ካርታህ ይህ ነው በማለት አስተዋወቁ፣ ባዘጋጁት በክልላዊ ህገ መንግስታቸው ላይ ድንበራችን ከዚህ እስከዚህ ነው በማለት አሰፈሩ፣ ካርታም ሰርተውና አትመው ለህዝቡ አሰራጩ፣ በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ በማስገባት የክልሉ ተማሪዎች እንዲማሩትና ካርታውን እንዲለምዱት አደረጉ።
በዚህ የተነሳ በኢትዮጵያ የብሔር ጭቆና ነበር ይሉት ከነበረው በላይ እጅግ አስፈሪ የሆኑና ሃገሪቷን ሊበታትኑ የሚችሉ የማንነትና የድንበር ጥያቄዎች መነሳት ጀመሩ። እኔ ሌላ ሳልሆን አማራ ነኝ የሚሉ የማንነት ጥያቄዎች በወልቃይት፣ በራያ፣ በመተከልና በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተነሱ፣ ይህ መሬት የኦሮሞ ሳይሆን የጉጂ፣ የሶማሌ፣ የደቡብ፣ የአማራ … ነው የሚሉ ጥያቄዎች በየቦታው ተቀጣጠሉ። በደቡብ ኢትዮጵያ ብቻ በንጉሱም ሆነ በደርግ ጊዜ ያልነበሩ በርካታ ችግሮች ተፈጠሩ። ባጠቃላይ ይህ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ የጎሳ ፌዴራሊዝም ገና ከመነሻው ችግር የነበረበት፣ ህዝቡን እርስ በርሱ መቋጫ ወደሌለው ጦርነት ውስጥ የሚከት፣ በሃገሪቷ ውስጥ ቀድሞ ያልነበረ አዲስ የድንበርና ማንነቴ ይይከበርልኝ፣ የኔ ጎሳ እናንተ የሰጣችሁኝ አይደለም ማንነቴን ተነጠኩኝ፣ ተዋጥኩ፣ ተጨፈለኩ የሚሉ ጥያቄዎች ተነሱ። የወያኔና የኦነግ ቅንነት የጎደለው፣ በተንኮል የታጀለ የጎሳ ፌዴራሊዝምና የኢትዮጵያን ህዝብ መሬት መቀራመት ግጭቶችን እዚህም እዛም በማስነሳት ሃገሪቷን መቋጫ ወደሌለው ውዝግብ ውስጥ ከተታት።
የኢትዮጵያን ህዝብ ባልመከረበትና ባልተወያየበት፣ የህዝቡን ይሁኝታ ባላገኘ ኢፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ የተፈጠረን የክልል አደረጃጀትን በተመለከተ በአሁኑ ሰዓት ስለ ትክክለኛነቱ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ የሚሰሙት የፈጠሩት ወያናኔ ኦነግ ብቻ ናቸው። በተለይ ኦነግና ሌሎች የኦሮሞ ብሔር የጎሳ የፓለቲካ ድርጅቶች ለእነሱ ጥቅም ስለሰጣቸው ብቻ ችግሩ የፌዴራሉ ስርዓት ሳይሆን ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ስላልሆነ ነው በማለት ጉዳዩን ለመሸፋፈን ይከጅላሉ። መጀመሪያውኑ ወያኔና ኦነግ ኢትዮጵያን ህዝብ ሃብት የሆነውን የጋራ መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ለዘጠኝ ክልል ሲከፋፍሉ ማን ውክልና ሰቷችሁ ነው?
ይህንን ወሳኝ የሆነ ነገር ያደረጋችሁት ለሚለውና ለምን የኢትዮጵያን ህዝብ አላወያያችሁም? ህዝቡ ተጠይቆና ድምጽ ሰጥቶበት የክልል ሽንሸናው በህዝቡ ፍላጎት መሰረት አልተደረገም ለሚለው ጥያቄ መልስ የላቸውም። ከዚህ ተራራና ወንዝና መለስ ትግራይ ይባላል፣ ይህንና ያንን አጠቃሎ እስከዚያ ድረስ ደግሞ ኦሮሚያ ነው፣ እገሌና እገሌ የሚባሉ ጎሳዎች የዚህ ክልል ባለቤት ሲሆኑ የቀሩት ደግሞ ባለመብት አይደሉም እያሉ በማን አህሎኝነትና በዘፈቀደ እንዳሻቸው ያደረጉት ድልድል ስለሆነ አሁን በህዝቡ ለሚነሱ የማንነትና የድንበር ጥያቄዎች በህገ መንግስታችን መሰረት ይፈታል በማለት በተለይ የአማራ ህዝብ በማያውቀውና ባልተወየያበት በወያኔና በኦነግ ህገ መንግስት መሰረት ለድንብር ጥያቄዎቹ መልስ እንሰጥበታለን ማለት ከማፌዝ በላይ የኢትዮጵያን ህዝብ መናቅም ጭምር ነው።
3) የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ፓሊሲ፣ (የኢብሳ ጉተማና የገነት ዘውዴ የት/ት ፓሊሲ)
ወያኔና ኦነግ የመሬት ነጠቃና ቅርምቱን እንደጨረሱ በመቀጠል በአዲስ የትምህርት ፓሊሲ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ መማሪያ አወጡ። ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማራቸው መልካም ሆኖ ሳለ በማር እንደተለወሰ መርዝ አዋጁ ብዙ ችግር ይዞ መጣ። በነገራችን ላይ የአፍ መፍቻ እና የክልሉ የስራ ቋንቋ ሊለያይ ይችላል፣ በአንድ በዘፈቀደ ወያኔና ኦነግ በከለሉት ክልል ውስጥ ከአንድ በላይ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ሊኖሩ ይችላሉ። በመሆኑም ልጆች በአፍ መፍቻ ወይም በእናታቸው ቋንቋ ይማሩ የሚለው የተባበሩት መንግስታት ህግ እና በክልሉ የስራ ቋንቋ ማስተማር ይለያያል። ስለዚህ ይህ ህግ በኦሮሚያም ሆነ በትግራይ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ደረጃ ተግባራዊ ሆኗል ማለት አይቻልም። ለማንኛውም በየአካባቢው የክልሉ የስራ ቋንቋ ይህ ነው ተብሎ በፓለቲከኞቹ በተወሰነው መሰረት የተማሪዎች መማሪያ መፃህፍት በክልሉ የስራ ቋንቋ መዘጋጀት ተጀመረ።
እዚህ ላይ አንድ ነገር ግልጽ ማድረግ የሚገባ ነገር ያለ ይመስለኛል እሱም ከገነት ዘውዴ በፊት ማለትም በሽግግሩ መንግስት ወቅት የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር የነበረው የኦነጉ ኢብሳ ጉተማ ሲሆን ምክትሉ ደግሞ የደቡቡ የሃዲያው ተወካይ አማራ ጠሉ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ነበር። ኢብሳ ጉተማ በተማሪው እንቅስቃሴ ወቅት ማነው ኢትዮጵያዊ የሚል ከፋፋ የሆነ መርዘኛ ግጥም ያቀረበ ነው። ለማንኛውም ኦነግ በሽግግሩ ጊዜ አማራ የጋራ ጠላታችን ነው በማለት ከወያኔ ጋር በፈጠረው ወዳጅነት ፓለቲካውን ወደ ህዝቡ ለማስረጽና የኦሮሞን ወጣቶችን በዘረኝነትና በአማራ ጥላቻ ለመበከል ተጠቅሞበታል። ኦነግ፣ ወያኔ እና በአካል የወያኔ – በመንፈስ ደግሞ የኦነግ ፍጥረት የሆነው ኦህዴድ በቅንጅት የመንግስት መገናኛ ራዲዮ፣ ቴሌቪዥንና ጋዜጦችን በመጠቀም እንዲሁም በአካል ካድሬዎቻቸውን በየቀበሌው፣ ገበሬ ማህበሩና ትምህርት ቤቶች በመላክ ከጎረቤቶቻቸው የነጠቁትን መሬት ለህዝባቸው ታግለን ያስገኝንልህ የክልልህ ካርታ ይህ ነው በማለት አስተዋወቁ፣ “በክልላዊ ህገ መንግስት” ላይ ድንበራችን ከዚህ እስከዚህ ነው በማለት አሰፈሩ፣ ካርታም ሰርተው ለህዝቡ አሰራጩ፣ በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ በማስገባት የክልሉ ተማሪ እንዲማረውና ካርታውን እንዲለምደው አደረጉ።
ወደ ጀመርነው የሽግግር መንግስቱ የት/ት ፓሊሲና አተገባበሩ ስንመለስ በወቅቱ በኢብሳ ጉተማ ይመራ የነበረው የትምህርት ሚኒስቴር የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ የተማሪዎችን መማሪያ መፃህፍትና የመምህራንን መመሪያ (Students Text Book and Teachers Guide) እንዲያዘጋጁ ውክልና ለክልሎች ሰጣቸው። በዚሁ መሰረት የክልል የትምህርት ቢሮዎች ካድሬ መምህራንን በመመልመልና ስልጠና በመስጠት በየክልላቸው ለሚማሩ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያገለግል የሙከራ (Trail Edition) መማሪያ መፃህፍት በክልሉ የስራ ቋንቋ ማዘጋጀት ጀመሩ። ባዘጋጁትም የታሪክ፣ የቋንቋና የጂኦግራፊ (የህብረተሰብ) መፃህፍት ውስጥ በፊት በደርግ መንግስት ታትሞ በነበረው መጻህፍት ውስጥ እንደ አብዲሳ አጋ፣ ዘርዓይ ደረስ፣ አበበ ቢቂላ፣ የኢትዮጵያ አርበኞች የተጋድሎ ታሪኮች፣ ስለ አድዋና ስለ አቡነ ጴጥሮስ ይቀርቡ የነበሩ ግጥሞች፣ ስለ አጼ ቴዎድሮስ፣ ስለ አጼ ምኒልክ እና ስለመሳሰሉት የሃገር ባለውለታ ጀኞች፣ ስለ ጀግንነታቸውና ለሃገራቸው ስልጣኔ ስላበረከቱት እስተዋዕፆ፣ ስለ ሃገር ግንባታና ድለ ወንድማማችነት የሚያስተምሩ ጽሁፎች ከታሪክ፣ ከቋንቋና ከህብረተሰብ ማስተማሪያ መጻህፍት ጽሁፎች (Passages) ውስጥ ለቅመው በማውጣት ነፍጠኛ ይህንን ያንን አደረገ በሚሉ ተራ ትርክቶች ተኳቸው።
ካድሬዎች የፈጠሩት የተዛባ ትርክቶች፣ የቦታ ስያሜዎች፣ በህዝቦች መሃል ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሴረኛ አመለካከቶችን፣ አንዳንዴም አንድ ተራራ ወይም አካባቢንና ወንዝን የኔነው በሚል ስሜት በሁለት ክልሎች መማሪያ መጽሐፍት ውስጥ ይካተቱ ነበር። የተማሪውን አዕምሮ በጥላቻና በቂም የሚያጭቅ እንጂ በእውቀትና በፍቅር በማያጎለብት ሁኔታ አጨማልቀው መጽሐፍቶቹን አዘጋጁ። ይህ ታሪክን ማዛባትና በህዝቦች መሃል ጠላትነትን የሚያስፋፋ፣ የድንበር (የወሰን) ግጭት የሚፈጥር መማሪያ መጽሃፍትን የየክልሎቹ ካድሬዎች ሆን ብለው የሚፈጽሙት ቢሆንም ችግሩን ት/ት ሚኒስቴር የሚያጣራበትም ሆነ የሚከታተልበትና የሚያርምበት አሰራር አልዘርጋም ነበር።
በተለይ ኦሮሚያን፣ ደቡብን፣ ሶማሌና ትግራይ አንድ የሚያደርጋቸው አማራውን ለክልላቸው ህዝብ ጠላት አድርገው በየተማሪው መፃህፍት ውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ማካተታቸው ነበር። አማራ ነፍጠኛ ጠላታቸው እንደሆነ፣ ኦርቶዶክስ የነፍጠኛ ሃይማኖት መሆኑ፣ የምኒልክ ይህንን ያንን አድርጓል፣ እገሌ የሚባል ከአማራ አገር የመጣ ራስ ወይም የጦር አለቃ እዚህ አካባቢ ጦርነት ከፍቶ ይህንን ጉዳት አድርሷል የሚሉ የፈጠራና የውሸት ትርክቶች በተማሪው መፃህፍት ውስጥ ተካተቱ። በተቃራኒው ደግሞ እገሌ የሚባል የኦሮሞ፣ የሲዳማ ወይም የ… ተዋጊ ወይም አባ ገዳ ነፍጠኛን ተዋግቶ እዚህ ቦታ አሸንፎታል በማለት እራስን የማጀገንና ታሪክን የማዛባት፣ ጥላቻን የያይስፋፉና ጦርነትን የሚቀሰቅሱ ፁሁፎች በተማሪው መፅሐፍት ውስጥ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ተካተቱ።
ኦነግ በወያኔ ስልጣኑን ተቀምቶ ከሽግግር መንግስቱ ከተባረረ በኋላ በኦነጉ በኦቦ ኢብሳ ጉተማ ተይዞ የነበረውን የት/ት ሚኒስቴርን የተካችው የህወሃት ታማኝ አገልጋይ (House Negro) የምትባለው የብአዴኗ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ነበረች። ገነት ዘውዴ ኦነግ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች በሙከራ (Trail Edition) ስም ጀምሮት የነበረውን ትውልድ አምካኝና ሃገር አፍራሽ የንሆነውን የትምህርት ስርዓት እስከ ዩኒቨርስቲርስቲ ድረስ በመቀጠል አጠናቃ አፀደቀችው።
ባጠቃላይ በዚህ ቋንቋን መሰረት ባደረገ በጎሳ ፌዴራል ስርዓት በተለይም በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በትግራይና በሶማሌ … በወጣቱ ላይ ጥላቻንና በቀልን ዘርተዋል። ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን አስተምረዋል። ኢትዮጵያም ከሰው ልጅ መፈጠር ጀምሮ በሂደት የተገኘች የሰው ልጅ መገኛ የአለም እምብርት ሳትሆን በድንገት የተከሰተች፣ ታሪኳ ከአንድ እድሜ ጠገብ ከሆነ ሰው ከመቶ አመት እንኳን የማይበልጥ ታሪክ የሌላት፣ ባዶ የህዝቦች ጥርቅምቅሞሽ የሆነች፣ ህዝቦቿም ዝምድና፣ የጋራ ታሪክና እሴት የሌላቸው፣ ባንዲራዋም ጨርቅ እንደሆነ በአደባባይ ሰብከዋል።
ላለፋት 27 ዓመታት ፍቅርንና አንድነትን ሳይሆን ጥላቻንና በቀልን ተሰብኮ ያደገው ወጣት ትውልድ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ጥቂት የማይባሉት በመንግስት ሥራና ሃላፊነት ላይ ተመድበው በመስራት ላይ ይገኛሉ። ዛሬ በሃላፊነት ላይ የተቀመጠው በኢብሳ ጉተማና በገነት ዘውዴ የትምህርት ፓሊሲ የተማረ ቄሮ ትናንት በትምህርት ቤቱ ጠዋት የሚሰቅለውና ማታ የሚያወርደው ባንዲራም ሆነ የሚዘምረው የህዝብ መዝሙር የክልሉን እንጂ የኢትዮጵያን አይደለም። እድለኛ ሆኖ ቤተሰቡ ወይም ታላላቆች ካላስተማሩት በስተቀር ከክልሉና ከጎጡ የዘለለ እውቀት የሌለው፣ አስፍቶ ማየት የማይችል፣ ነፍጠኛ ይህንን ባንዲራ ይዞ ነው የወጋህ፣ የገደለህ እየተባለ ያደገና፣ አድጎ ለመበቀል ሲዝት የኖረ ትውልድ ነው።
በኢብሳ ጉተማና በገነት ዘውዴ የትምህርት ፓሊሲ ዘረኝነትንና ጥላቻን ሲጋት ያደገው የቁቤ ትውልድ ጀግኖች አባቶቻችን ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት፣ ክብርና ለሃገራችን ሉአላዊነት ሲሉ ደማቸውን ያፈሰሱላትን፣ ህይወታቸውን የገበሩላትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማዋን በማውረድ ረግጦና አቃጥሎ የኦነግን ባንዲራ የሰቀለ ብቻ ሳይሆን በደቦ (በመንጋ) እየተነዳ በበርካታ ንብረት ላይ ውድመት ያደረሰ፣ እንዳልሰለጠነ ኋላ ቀር (Primitive) ማህበረሰብ የሰውን ልጅ በድንጋይ ቀጥቅጠው፣ ዘቅዝቀው የሰቀሉ ሰብአዊነት የማይሰማቸው ዘረኝነትንና ጥላቻን ሲማሩ ያደጉ ናቸው።
ስለዚህ በአሮጌ አቁማዳ አዲስ ወይን ጠጅ አይጠመቅምና ይህንን በኢትዮጵያ ምድር ስቃይና መከራ ያመጣ ለሰላማችንና እፕብሮነታችን ጠብቅ የሆነ የጎሳ ፌዴራል ስርዓትን እስከ ግሳንግሱ አስወግዶ በአዲስ ከዘመኑ ስልጣኔ ጋር በሚሄድ ስርዓት መተካት ነው ለኢትዮጵያና ለህዝቧ የሚበጀው።
derejepol@gmail.com
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
kirubel says
Dear Derje
The article written to pin point root cause of current social, economic, and political problem. And also the author mentioned role of TPLF/OLF education policy for the current crisis in Ethiopia. I think Dr. Abyi started to reform/CHANGE education and military to tackle future crisis. The article written with good Amharic grammar . F
Delta Tango says
በ Golgul ጋዜጣ<>;በምለዉ ርእስ ስር አቶ ደረጄ ተፈራ በAugest,26/2018/ያስነበበን ሀቅ በተለይ አዲሱ ትዉልድ ማወቅ ያለበት ነዉ::
Solomon Bek says
woow
Gi Haile says
ወንድም ደረጀ፡ ፅሁፍህ የኢትዮጵያዊነት መመዘኛዎችን ያረቀቀ ማነው? የኢትዮጵያን ኣንድነትና መለያቸው ምንድነው? አንድ ሊያደርጋቸዉ የሚችል ነገር ምንድነው? ምን ቢደረግ መፍትሔ ሊኖር ይችላል? ለአሁኑ ችግሮች ተጠያቂነትን የሚወስዱ መቶ በመቶ ኦነግን ማድረግ ለምን ኣስፈለገ? 27 ኣመት በሃይል፡ በጉልበት፡ በኢኮኖሚ፡ በሁሉም ተጠቃሚ የነበረው ወያኔ ሆኖ ሳለ፡ ኦነግ በሽግግሩ መንግስት ወያኔ ኣባረራቸው ከሚለው አገላለፅ ጋር አይጋጭም? አንተም ግራ ገብቶህ ፃፃፍክ እንጂ መፍትሔው ይህ ነዉ አለማለትህ ደግሞ በሌላ መልኩ የኣማራን እንባ ከማንባት በቀር እንባቸውን ለማበስ የመፍትሔ ሃሳብ ለምን ኣታቀርብም? ወያኔና ኦነግን በተለይም አንድ ቀን ሥልጣን ለይ ያልነበረውን ኦነግን አፈርድሜ አገበህ ታዲያ የኢሳያስ ነገር ምንም ሳታነሳ ወያኔና ኦነግ ኤርትራን አስገነጠሉ ብለህ ፃፍክ? ተዲያ ምን ይደረግ ነዉ የምትለው ያንተ ፅሁፍ ከሰማይ የነሱ ሥራ ደግሞ ከምድር ሆነ መፍትሔ ከለህ ለህዝቡ አቅርብ። ወያኔ፡ ኦነግ ብኣዴን አና ኢሳያስ አብረው ሰለተወያዩ ገዢ በልነበረበት ደርግ በወደቀበት ወቅት ልንበታተን ባልን ጊዜ ያቆዩልንን ሃገር ኣንተ ሁሉንም ጥፋተኛ አደረግህ? አረ ደረጃ አንተ ምን ሰራህ እነሱስ ይህን አደረጉ ኣልክ፡ እባክህ መፍትሔ ካለህ አንድ እንድንሆን ጀባ በለንና ታሪክ ሥራ አለበለዚያ ግን አታለዝንብን። በፅሁፍህ መፍትሔ ሃሳብ ስለሌለ ለወደፊቱ የመፍትሄ ሃሳብ አፍልቅ።
ጆ says
@ Gi Haile አስተያየትሂን አነበብኩት አቶ ደረጀ የታያችሀውን የነበረውን ደባ ለማሳየት ሞክረዋል ካመንኪበት መፍቲውን አብሮ መመካከር ነው ካላመንክበት ይሃ አይደላም ችግሩ ብለህ ማኪረብ ነው ሁሉንም ነገር ከአንድ ሰው መጠበቅ ኝ ግ ን ከተሳዳቢ አእምሮ ተስሸክሞ መንገላወድ ሚንም አይጠቅምም