• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እኛ ያልነው ለፉገራ…

June 2, 2013 04:24 am by Editor Leave a Comment

በሰሞኑ ቀልድ ልጀምር። የአፈሪካ ህብረት ድርጅት 50ኛ አመቱን በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ ሲያከብር በነበረው የሻምፓኝ ስነ-ስርዓት ላይ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ብቻ ከመሪዎቹ ተነጥለው ያለ ብርጭቆ  ቆመዋል። ለፕሮቶኮል እንዲመሳሰሉ ቢጠየቁ አሻፈረኝ አሉ። የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ስለነበሩ ለይሰሙላ እንኳን ብርጭቆዋን ጨብጡ ቢባሉ አይሆንም፣ ሃይማኖቴ አይፈቅድም አሉ።  በመጨረሻ ግን በረከት ስምዖን በጆሯቸው አንዳች ነገር ነገራቸውና የያዘውን ብርጭቆ ሲሰጣቸው ተቀብለው በደስታ ጨለጡት።

በረከት ለጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በጆሯቸው እንዲህ ነበር ያላቸው። “ብርጭቆ ውስጥ ያለው መለስ የጀመረው ወይን ነው።”

አሁን አሁን መቀለጃ እየሆኑ የመጡት ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ መለስ የጀመረውን ሁሉ፤ ፉገራም ቢሆን – ያንን ለመጨረስ ነው የተቀመጥኩት ይሉናል። እየደጋገሙ!

ብርኖ  በምትባል የቼክ ሪፐብሊክ ትንሽ ከተማ ከነበርኩበት ሆቴል ውሰጥ የተሰቀለ ቲቪ ካለወትሮው የ’ሕዳሴውን’ ግድብ የሚያሳይ ምስል ይዞ ብቅ አለ። የምሽት ዜና ትንተና መሆኑ ነው። በቼክ ቋንቋ ይተላለፍ የነበረው የዜና ትንተና ባይገባኝም ከምስሉ የመልእክቱን ይዘት ለመረዳት አላስቸገርኝም።

ግን ምን አዲስ ነገር ተገኘ?

የቲቪውን ጣቢያ መቀያየር ጀመርኩ። ሲ.ኤን.ኤን፣ ቢ.ቢ.ሲ.፣ አል ጃዚራ…ቪ.ኦ.ኤ.። የኳታሩ አል ጃዚራ ጉዳዩን በስፋት ይዞታል። Death on the Nile (በአባይ ላይ ግድያ) በሚለው አምዱ ምሁራንን እና ባለስልጣናትን እያቀረበ ስለ ‘ሕዳሴው’ ግድብ ያወያያል። በአሜሪካን መንግስት በሽብርተኝነት የተፈረጀው  የግብጹ ሱኒ ‘አል ጋማ አል ኢስላሚያ’ ድርጅት ደግሞ ኢትዮጵያን በጦር ለመውጋት ዝግጁ መሆኑን ባለፈው ረቡዕ አውጇል።

ሂደቱ እንደገና ሌላ ጥያቄ አጫረብኝ።  የግድቡ ወሬም ሆነ ስራ ከተጀመረ ሁለት አመት ሊሞላው ነው። ዓለም አቀፉ ሜዲያና ዘራፍ ማለት የጀመሩት ቡድኖች ዛሬ ያባነናቸው ምስጢር ምንድነው? አመቱን ሙሉ የት ነበሩ? መልሱን የምናውቀው እኛ ባለቤቶቹ ብቻ ነን። በእርግጥ አቶ መለስ የአባይ ካርድን ይዘው ይጫወቱት የነበረውን ጨዋታ ግብጾች ጠንቅቀው ያውቁት ኖሮ የ’ሕዳሴው’ን ሽርጉድ ከቁብ አልቆጠሩትም ነበር።

ከሁሉም ነገር እንግዳ የሚሆነው፣ በየመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ አስተየት የሚሰጡ የፈረንጅ ‘ምሁራን’ ጉዳይ ብቻ ነው። እነዚህ ተመራማሪዎች ስለ አባይ፣ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ…ወዘተ ሊቅ ሆነው የተሳሳተ ግምታቸውን እያቀረቡ ሌላውንም ግራ ያጋቡታል።  ስለ ግድቡ በአልጃዚራ አስተያየት ትሰጥ የነበረችዋ ኤክስፐርትም ሂደቱን ‘ብቀላ’ እንደሆነ ገልጻዋለች። ሌላውም እንዲሁ ‘የሕዳሴው ግድብ’ ጦርነት እንደሆነ ገልጿል። የአካባቢ ጥበቃ፣ ኤኮሎጂ… ወዘተ ችግር ያስከትላል የሚሉም አሉ።  ሁሉም አስተያየቶች ግን ከኛ ከሃገሬው አመለካከት የራቁና ከመላምት ያለፉ አይደሉም። እውነታው ሌላ ነው። ፉገራ እና ፉከራ!

በደርግ ጊዜ ነው። መንገድ ላይ ቆሞ አላፊ አግዳሚውን ‘የሚቀፍል’ አንድ ወጣት ነበር። በዚህ ሰው የፖለቲካ ‘ፉገራ’ ፈገግ የሚሉም ሳንቲም ጣል ያደርጉለታል።  አነድ ቀን ‘ኢሰፓኮ፣ ባዶ ባኮ! ‘ እያለ ሲቀልድ ካድሬዎች አይን ውስጥ እንደገባ ነቃና ማምለጫ ዘዴ ፈጠረ።  መንጌን ማወደስ። ‘የሰው ጥራቱ፣ እንደ መንግስቱ!…’ እያለ ከተማውን አቀለጠው። ይህ ዘዴው ከተደገሰለት ሞት ቢያስተርፈውም፣  ከእስር ግን አላስመለጠውም። የማታ ማታ በሚሊሽያዎች ተይዞ ታሰረ። እዚያው ሆኖ እነዲህ አለ። ‘እኛ ያልነው ለፉገራ እነሱ ግን ለመግደል ሙከራ።’

የነጻ ትግል ስፖርት የሚሰሩ አትሌቶች ተመልካቾቻቸውን አልፎ አልፎ ‘Be smart. Don’t try this at home’ ሲሉ ይመክራሉ። ‘አስተውሉ! ይህንን ነገር እቤታችሁ አትሞክሩ።’ እንደማለት ነው።  በቦክስ ሪንግ ውስጥ የሚያደረገው መዝለል፣ መውደቅ እና መነሳት ሁሉ ቀድመው ተለማምደው የሰሩት አክሽን መሆኑን ነው የሚናገሩት። እነዚህ አትሌቶች ለመኖር ሲሉ የሚሰሩት ድራማ እንጂ፣ የሚታየው ድብድብ ሁሉ የ’ፉገራ’ መሆኑን ነው በማስታወቂያቸው የሚናገሩት። በግልጽ ባይሉትም። እንዲህ አይነቱ ጨዋታ ጥበብን ስለሚጠይቅ ማየት እንጂ መሞከሩ አደጋ ያመጣል።

አቶ መለስ ‘Be smart. Don’t try this at home.’ ሳይሉ ማለፋቸው ይመስላል እነ ሃይለማርያም ዛሬ ማኖ እየነኩ ያሉት። ‘መለስ የጀመረውን ለመጨረስ ቃል ገብቻለሁ።’ አይደል እያሉን ያሉት?

ባለፈው ማክሰኞ የአባይ ወንዝ አቅጣጫ መቀልበስ ስራ በኢቲቪ የቀጥታ ስርጭት መታየት ሲጀምር ነው ጫጫታው በዓለም አቀፍ ሜዲያ  የተከተለው። እስከዚህች ቀን ድረስ ግን ኢቲቪ ይቀርበው የነበረው ፕሮፓጋንዳ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማሰልቸት ያለፈ የሜዲያ ትኩረት አልሳበም ነበር። ዜጎችን በፕሮፓጋንዳ በማሰልቸት ኢቲቪ በእውነቱ የሂትለሩን ጆሴፍ ጎብልስ ሚና በደንብ ነው የተጫወተው። ጆሴፍ ጎብልስ እንዲህ ብሎ ነበር። “ውሸትን እየደጋገምክ ተናገር። በመጨረሻ ሕዝቡ እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል።”

የቅልበሳው ትእይንት ማክሰኞ እስከታየበት ቀን ድረስ የ’ሕዳሴው’ ግድብ ተረት-ተረት እንደሆነ ነበር እነ ግብጽ የሚያውቁት ለማለት የሚያሰቸል ክስተት ነው ያየነው። የግበጽና ሱዳን ጩኸት፣ የሌሎች ቡድኖች ማስፈራሪያ ዛቻና የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ማግኘት የጀመረውም ከዚያ በሗላ ነው። “እኛ የመሰለን ፉገራ …።” እንደማለት ነው።

ነብሳቸውን ይማረውና አቶ መለስም በህይወት ቢኖሩ ኖሮ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ጠርተው፡ “እኛ ያልነው ለፉገራ፤ እናንተ ለመገደብ ሙከራ!” ይሏቸው ነበር።

ኢትዮጵያ ከአባይ ወንዝ ከ80 እጅ በላይ ድርሻ አላት። ይህንን ያህል ለአባይ እየገበርን እሰካሁን በአባይ ወንዝ ተጠቃሚ ያለመሆናችን የሚያንገበግብ ጉዳይ ነው። አባይ ተገድቦ ለኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ቢውል የማይደሰት ሰው ቢኖር የኢትዮጵያ ጠላት በቻ ነው።

አሁን በተያዘው መልኩ አባይ ተገድቦ ስራ ላይ ይውላል ብሎ የሚያስብ ካለ ግን ልጅ ውይንም ጅል መሆን አለበት።  ‘አባይ ይገደባል’ ብለው የሚከራከሩኝ ወዳጆቼ ለሃገራችን እድገት ካላቸው በጎ ምኞት ያለፈ ሌላ እውነታ እንደሌለው ነው ማስረዳቸው።

የ’ሕዳሴው’ ግድብ፤  የቱኒዥያውን ቤን አሊ፣ የግብጹን ሆስኒ ሙባረክ፣ እንዲሁም የሊቢያውን ጋዳፊ የጠራረገው የሰሜን አፍሪካው ህዝባዊ ማእበል የወለደው ሃሳብ ነው። ለችግር ጊዜ ተቀምጦ የነበረ ጆከር ነው የሳቡት። ይህ ደግሞ የወጣቱን አንደበት ከያዘው የኮብል ስቶን ፕሮጀከት ጋር በመታገዝ እነ መለስን ከማዕበሉ ጠብቋቸዋል።

የ ‘ሕዳሴው ግድብ’ ፕሮጀክት በአምስት አመቱ የ’እድገትና ትራንስፎርሜሽን’ እቅድ ውስጥም አልነበረም። እንደ እንጉዳይ ተክል ከመቅጽበት ብቅ ያለ ነገርም አይደለም። ለዘላቂ ሳይሆን ይልቁንም ላጭር ጊዜ እንደሚወሰድ የእድሜ ማራዘሚያ መድሃኒት አይነት ነው።  አቶ መለስ ዜናዊ የግድቡን መሰረት ሲጥሉ 6ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨቱ ጉዳይ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችልም ጠንቅቀው ያውቁታል።

ለዚህም አንደኛው ምክንያት በ1993 (እ.ኤ.አ.) አቶ መለስ ዜናዊ ከግብጹ ሆስኒ ሙባረክ ጋር ያደረጉት  ስምምነት ነው። (የሁለቱን መሪዎች ፊርማ የያዘውን ይህንን ሚስጥራዊ ስምምነት በወቅቱ ለህትመት በማብቃቴ ለማእከላዊ እስር ተዳርጌ ነበር።) በዚህ ሁለትዮሽ ውል በአንቀጽ አምስት ላይ ‘አንዱ ሃገር ሌላውን ሃገር በሚጎዳ መልኩ ውሃውን መጠቀም አይችልም።’  በማለት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የተፈጥሮ መብት የሚገፍ ሃረግ ተቀምጧል። ይህ ዲፕሎማሲዊ አንቀጽ በህግ ቋንቋ ሲገለጽ ‘ኢትዮጵያ አነዲት ማንኪያ ውሃ ከአባይ ላይ ብትቀዳ፡ የግብጽን ተፋሰስ ሰለሚቀንስ ከዚህ ድርጊት መቆጠብ አለባት።’ እንደማለት ነው። ከኛ አልፎ ግብፅ ምድር ላይ የሚንፏለለውን ውሃ ካይሮ ተጠቀመች አልተጠቀመች እኛ ምን አገባን?

በአለም አቀፍ ህግ፣ ሁለት ሃገሮች ተስማመተው የሚያጸድቁት ሰነድ ደግሞ ሁለቱ ተስማምተው እስካላፈረሱት ድረስ ሀጋዊ ሰነድ ሆኖ ይቆያል።

አቶ በረከት ስምዖን አልጃዚራ ላይ ባለፈው አርብ ቀርበው፤  በቅኝ ግዛት ወቅት የነበረውን ሰነድ ሲያነሱ፤ የራሳቸው ስርዓት በ1993 ያፀደቀውን ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ያላትን የተፈጥሮ እና ሀጋዊ መብት አሳልፎ የሰጠውን ውል እንደዋዛ አልፈውታል። ይህ ሰነድ በቅኝ ግዛት ዘመን ከነበሩ ስምምነቶች ሁሉ የከፋና ለክርክር እንኳን የማያመች ነው።

በአባይ ወንዝ 84 በመቶ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያን ያላሳተፉ እነዚያን የቅኝ ግዛት ውሎች ሁሉ ውድቅ ለማድረግ የህግም ሆነ የሞራል የበላይነት አለን ብዬ አምናለሁ።  ግና የ1993ቱ ምስጢራዊ ሰነድ እንዴት ነው ሊፈርስ የሚችለው? ይህ ውል ሳይፈርስ እንዴትስ ነው አባይ ሊገደብ የሚችለው? ለዚህ ጥያቄ እነበረከት በእርግጠኝነት መልስ ሊስጡን አይችሉም።

በሁለተኛ ደረጃ ማየት ያለብን አባይ ዓለም አቀፍ ወንዝ መሆኑን ነው። ዓለም አቀፍ ወንዝ ደግሞ በአንድ ሃገር አዋጅ ሳይሆን፤ በዓለም አቀፍ ህግ ነው የሚመራው። የአባይ ወንዝ ለመጠቀም  የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች ሁሉ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ህጉ ያስገድዳል።

በሶስተኛ ደረጃ አባይን ከምር መገደብ ካስፈለገ፤ አባይን መገደቢያ ገንዘብ አይጠፋም። የህወሃቱ ኢፈረት ብቻውን አንድ አይደለም፤ አራት አባይን መገደብ የሚያስችል ገንዘብ አለው።  ገዢው ፓርቲ እርግጥ ለኢትዮጵያ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ስኬት ካሰበ በፓርቲው ስም ያከማቸውን ገንዘብ አውጥቶ ለግድቡ ተግባር ማዋል ይችላል። የኢፈርት ህለቀመሳፍርት ገንዘብ ቢያጓጓው እንኳ በአክሲዎን ሽያጭ ገንዝብ መሰብሰብ ይችል ነበር። ለግድቡ ያስፈልጋል የሚሉን 80 ቢሊየን ብር ነው። እስካሁን ከህዝብ በውዴታም ሆነ በግዴታ ተገኘ የተባለው ደግሞ 7 ቢሊየን ብር። 73 ቢሊየኑን ታዲያ ማን ሊሞላው ይሆን? ወይንስ እንዳሁኑ አይነት ያልተጠበቁ ችግሮች ሲገጥሙ ስራውን ለማቆም እንደምክንያት ሊቀርብ?

ከውስጥ ሰዎች እንደምንሰማው ከሆነ ደግሞ እነ መሶበ ሲሚንቶ እንዲሁም  የህወሃት ኮንስትራክሽን ድርጅቶች የግድቡን መሰረት በመጣል ስም ከህዝብ የተሰበሰበውን 7 ቢሊየን እየተቋደሷት ይገኛሉ። በአንድ ወንጭፍ ሁለት ወፍ .. እንዲሉ። 7 ቢሊየን  ቀላል ገንዘብ አይደለም።  በቅጡ ቢያዝ ኢትዮጵያን ጸብ ውስጥ የማይጨምራት እጅግ ብዙ የሚተገበር የልማት ስራ ላይ ሊውል ይችል ነበር። ኢትዮጵያ ሃይል ሊያመነጩ የሚችሉ በርካታ ትናንሽ ወንዞችም አሏት።

የ’ሕዳሴው ግድብ’ በዚህ ሂደት ተግባራዊ ይሆናል ወይ?  የሚለውን ጥያቄ ምላሽ በቅርብ የምናየው ይሆናል።  ለገዢው ፓርቲ ግዜ መግዣነት ስለማገልገሉ ግን ቅጥ ያጣው የፕሮፓጋንዳ ስራ ብቻ ምስክር ነው። ጫወታው ሳይገባቸው በሃገር ፍቅር ስሜት ብቻ የተሸውዱ እንዳሉ ሁሉ ሕዝቡን ባልተጨበጠ ነገር የሚያሞኙት ልማታዊ ጋዜጠኞች እና ልማታዊ አርቲስቶች ነገ ትዝብት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

በአንድ ጽሁፌ ለመዳሰስ እንደሞከርኩት በኡጋንዳ – ጂንጃ የነጭ አባይ ምንጭ የሆነው የቡጃጋሊ ግድብ ስራ ተጠናቋል። ኡጋንዳ የነጭ አባይ ምንጭ ነች። ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ  የሃገሪቱን የሃይል አቅርቦት ችግር ለማቃለል የሚያስችል የነጭ አባይ ፕሮጀክት ዘርግተው ተግባራዊም አድርገዋል። ለዚያውም በአለም ባንክ እና በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ እርዳታ! ነጭ አባይ የሃገሪቱን የሃይል ምንጭ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይገመታል።

ይህ ግድብ ሲታቀድም ሆነ ሲሰራ ታዲያ በጩኸት እና በመፈክር አልነበረም። የሃገሪቱ አርቲስቶች አልዘፈኑለትም። ሕዝቡ ስለፕሮጀክቱ እንዲጮህለትም ሆነ እንዲጮህበት አልተደረገም። እነደ”ህዳሴ”ው መዋጮ ሁሉ የዜጎች ኪስ አልተበረበረም፤ ከወር ደመወዙ የተቆረጠ ነገር የለም። ቡጋጃሊ ሲገደብ ቦንድ አልተሸጠም፤ ወታደራዊ ማርሽም አልተሰማም።  ሙሴቬኒ አንባገነን ቢሆኑም ለሃገራቸው እድገት ብልሃት በተሞላበት መንገድ ሄደዋል።  ‘Think global, act local’ ነው ጫወታቸው። ‘ሞያ በልብ ነው’ ብለን ልንተረጉመው እንችላለን።

አባይን በፕሮፓጋንዳና በጩኸት ለመገደብ የተነሱት የኢትዮጵያ ገዢዎች ታዲያ ይህንን እያዩ እንኳን አልተማሩም።  አባይ ሲቀለበስ በላይቭ ቲቪ ማሳየት ከፕሮፓጋንዳነቱ ባሻገር ምንድነው ጥቅሙ?  ድርጊቱ ህልውናው በአባይ ወንዝ ላይ የሆነ ሕዝብን ለጦርነት መጋበዝ ይመስላል። ውግዘቱና ጫናው ሲበዛ ጉዳዩን ለማቆም ምክንያት ለመፍጠርም ያመቻል።

አለም አቀፉ ህብረተሰብ በ’ሕዳሴው ግድብ’ ጉዳይ ላይ ዝምታን ነው የመረጠው። ለዚህም ምክንያት አለው። ኢትዮጵያ ጨለማ ውስጥ ሆና ሌሎች ሃብትዋን ያላግባብ ሲጠቀሙ፤ ድልድሉ ትክክል እነዳልሆነ አለም ሳይረዳው ቀርቶ አይደለም። የመለስና ሙባረክ ፊርማ ሳይቀደድ የተጀመረው የአንድዮሽ ውሳኔም የት ተጀምሮ የት ላይ እንደሚያልቅ ያውቁታል። ለዚህም ይመስላል ለግድቡ የገንዘብም ሆነ የሞራል ድጋፋቸውን ሊነፍጉ የቻሉት።  የግድቡ ጅማሮ አንደኛ አመት ሲከበር የመንግስት ባለስልጣናት እና የውጭ ዲፕሎማቶች የእግር ኳስ ግጥሚያ እንደሚያደርጉ ፕሮግራም ወጥቶ ነበር። ዲፕሎማቶቹ ግን በስፍራው ሳይገኙ ቀሩ። ለ’ሕዳሴው’ ግድብ እውቅና በመስጠት የፖለቲካ ስህተት ላለመስራት የመከሩ ይመስላል።

ፕራግ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፡ ግንቦት 24፣ 2005 ዓ.ም.

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule