
ኢትዮጵያን እየመራ የሚገኘው ኢህአዲግ/ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን እርስ በርሱ እንዳይተማመን፣ እንዲነቃቀፍ፣ እንዲጠራጠር ከእዚህ ባለፈ ደግሞ ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ 22 ዓመታትን ዘለቀ። ህዝቡ እለት ከእለት በገዢው መንግስት የሚወጠኑለትን የእርስ በርስ ማጋጫ ተንኮሎች እየተመለከተ ልቦናው በእጅጉ እየደማ ነው።
አንድ ወራሪ የውጭ ጠላት ሊሰራ የሚችለውን ያህል ህዝብን ከሕዝብ ጋር የማጋጨት ሥራ ኢህአዲግ/ወያኔ በትክክል ሰርቶበታል። የሃገሪቱን ፌድራል አስተዳደር በየትኛውም ዓለም ያልታየ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ደገሰላት። ፌድራላዊ አስተዳደር በዘመናዊው ዓለም አንዱ እና አማራጭ የአስተዳደር ዘይቤ ይሁን እንጂ በየትኛውም ሀገር መሰረት የሚያደርገው የመልክዓ ምድርን አቀማመጥ እና ታሪካዊ አሰፋፈርን ነው። እርግጥ ነው ጣልያን ሀገራችንን በወረረ ዘመን አሁን ወያኔ የሚጠቀምበትን የክልል አስተዳደር የመሰለ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የአስተዳደር መዋቅር ዘርግቶ ነበር።
አንዳንዶች የአሁኑ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር የብሔር ብሄረሰቦችን መብት ከማስከበር አንፃር የሚመስላቸው የዋሃን አይጠፉም። ግን ፈፅሞ አላማው ይህ ላለመሆኑ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል።እርግጥ ነው የህዝብ ባህል ማለትም ቋንቋው፣ አለባበሱ፣ ታሪኩ ወዘተ ሊጠበቅለት እና ከለላ ማግኘት አለበት። ይህ ከለላ በማግኘት መብት ስም ወንጀል ሲሰራ፣ ቁርሾ በባትሪ እየተፈለገ ሲራገብ እና ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ሲውል ነው ወንጀሉ።
ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ እርስ በርሱ በጎሳ ሲጋጭ መፍትሄ ለመፈለግ ከመነሳት ይልቅ ጉዳዩን ሲያባብስ እና ቤንዚን ስያርከፈክፍ ማየት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዕለት ከዕለት የሚመለከተው ድራማ ሆኗል። ለእዚህም ብዙ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል። ለእዚህ ፅሁፍ ግን ሁለት ምሳሌዎችን እንጥቀስ –
- በዩንቨርስቲዎች ውስጥ ወጣቶች ‘አንተ የእገሌ ነህ አንተ የእንቶኔ ነህ’ ተባብለው ፀብ ሲነሳ ጉዳዩ የመጪው ትውልድ እና የአሁኑ ትውልድ አደገኛ አቅጣጫ ነው ብሎ የችግሩን ስር ለመፍታት ከመጣር እና የጉዳዩን አስከፊነት በመገናኛ ብዙሃን ከመግለፅ እና ከማስተማር ይልቅ ፖሊስ ይልቁን ከአንድኛው ወገን ቆሞ ሌላውን ሲያስር እና ሲቀጣ መመልከት ዘግናኝ ተግባር ነው።
- ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት የእርሻ ቦታ ”የእገሌ ዘር ነህ” ተብሎ በክልል መስተዳድሮች ጭምር ሲባረር ለጉዳዩ እንደ መንግስትነት ለመዳኘት ሳይሆን የሚሞከረው እንደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ አባባል ”ቀድመው ባልተወለዱበት ሀገር መስፈር የለባቸውም” እንደ አቶ አለምነህ የብአዴን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደግሞ ”የትዕቢት ልጋግ” ነው የሚሉ መልሶችን መስማት እራስ ያማል። መሪዎቻችን እንዲህ እያሉ ከጉርዳፈርዳ እስከ አሶሳ፣ ከአሶሳ እስከ ሐረር፣ ከሐረር እስከ ጅጅጋ፣ ከጅጅጋ እስከ ቦረና ጉጂ፣ ድረስ በብዙ አስር ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ተሰደዱ፣ ተገደሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን መንግስት ጉዳዩን እንደ ትልቅ ችግር ሳይሆን እንደ አንድ የማስተዳደርያ ዘዴ እንደቆጠረው በ እርግጠኝነት መረዳት ይቻላል።
በያዝነው ሳምንት በሃያ ሚልዮን ብር ወጪ የሚመረቀው የመርዝ ብልቃጥ
የእርስ በርስ ግጭቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሻገሩ የሚጥረው ኢህአዲግ/ ወያኔ ለእርስ በርስ ጦርነቶች እየመረጠ ሃውልት ሲሰራ ከርሞ በእዚህ ሳምንት ደግሞ ለየት ያለ የጥፋት ድግስ የሚሆን ከመቶ አመታት በፊት ለመፈፀሙ ምንም አይነት የታሪክ ማስረጃ የሌለው በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን በአርሲ ዞን በሂቶሳ ወረዳ ተፈፅሟል ያለውን የታሪክ ምሁራን ያላረጋገጡትን የፈጠራ ታሪክ ከሃያ ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያሰራውን ”አኖሌ ሐውልት” እና ሙዝዬም በእዚህ በያዝነው ሳምንት እንደሚመረቅ ኢቲቪ ዛሬ መጋቢት 22/2006 ዓም የዜና እወጃው ላይ አስታወቀ። የፈጠራው ታሪክ ከመቶ ዓመታት በፊት የአፄ ምኒልክ ሰራዊት የኦሮሞ ሴቶችን ጡት ቆርጦ ነበር እና ማስታወሻነቱ ለተቆረጡት ጡት እና እጅ ይሁን” ይላል የሃውልቱ የመሰራት ምክንያትን ኦህዴድ /ኢህአዲግ/ወያኔ ሲናገር። አሳዛኝ የደረስንበት የዝቅጠት ዘመን። በየትኛውም ሀገር ውስጥ በቀደሙ መሪዎች ያውም ከመቶ አመታት በላይ ለሆነው ታሪክ ቀርቶ የቅርቦቹም ቢሆን ለተሰሩ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች ለመጪው ትውልድ የሚያቆይ የእልቂት ድግስ ከፋች ሃውልት አይሰራም። የሚጠጣ ውሃ፣ የምበላው ምግብ ለሌለው ሕዝብከ 20 ሚልዮን ብር በላይ አውጥቶ መበተን ምን የሚሉት ፈልጥ ነው?
አንድ መንግስት ሕዝብ ከህዝብ ጋር አብሮ የሚኖርበትን ዘዴ ሲቀይስ ልዩነትን እያጎላ ሳይሆን አንድነትን እያሳየ እና እያጎላ ሕዝብ በፍቅር እና በስምምነት እንዲኖር ይጥራል እንጂ እንዴት ከአሁኑ ትውልድ አልፎ ለመጪው ትውልድ ቂም ለማውረስ ተግቶ ይሰራል? ይህ ተግባር ማንን ይጠቅማል? ለመሆኑ ያለፉ ነገስታት በወቅቱ በነበረው የቅጣት መንገዳቸው ሁሉ የቀጡትን የቅጣት አይነት እየዘረዘርን ሃውልት ብንሰራ የቱን ከየቱ እንመርጣለን?
የሃውልቱ ምርቃት እንደ ትልቅ የሀገር ልማት ዛሬ ኢቲቪ ቀድሞ ዛሬ ይናገረው እንጂ ወቅቱ የሩዋንዳው እልቂት የተጀመረበት 20ኛ አመት ጋር ገጥሟል። በሚያዝያ 7/1994 ዓም እስከ ሐምሌ/1994 ዓም እ ኤ አቆጣጠር የቆየው በቱትሲዎች እና በሁቶዎች መካከል የተደረገው እልቂት ከአምስት መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ሕይወት ቀጥፏል። የሩዋንዳው እልቂት በአንድ ሌሊት ድንገት የደረሰ ጉዳይ አይደለም። በሂደት አልፎ አልፎ በተነሱ ቁርሾዎች ጥርቅም ሳብያ መሆኑን መዘንጋት አይገባም። የዛሬ የባለ ሃያ ሚልዮን ሃውልት ገንቢዎችም ሆኑ አስገንቢዎች መዘንጋት የሌለባቸው በሰሩት ሥራ ሁሉ የሚጠየቁበት ቀን እንደሚመጣ መጠራጠር አይገባም። የመርዝ ብልቃጡም ይሰበራል የፍርድ ቀኑም ይቆረጣል።
(ምንጭ: ጌታቸው በቀለ ጉዳያችን)
poor idea from poor mind., if this is called “yemerz bilqax” what about the those erected in Bahirdar Hawasa and Mekelle?
ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ ለማፋጀት የገነባውን “የመርዝ ብልቃጥ”የሚለውን ፅሁፍ ያነበቡ በተለያዩ ድረ-ገፆች ላይ ሃሳባቸውን ለሰጡ አመሰግናለሁ።
እዚህ ላይ በተለይ በ”ዘሐበሻ” እና ”ጎላጉል” ድረ-ገፅ ላይ ሃሳብ ከሰጡት ውስጥ የፅሁፉን ይዘት ያልወደዱ (ከቋንቋ እና ጎሳዊ ስሜት ይቅርታ ይህን ቃል በመጠቀሜ) በማየት ብቻ የሰጡትን አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የሚወክል የአንድ ወንድሜን ጥያቄ ላንሳ እና ሃሳቤን ላብራራ።
አብዛኛው የፅሁፉ ነቃፊዎች ጥያቄ የሚወክለው ብዬ ያሰብኩት ጥያቄ እንዲህ የሚለው ነው – ”የ አኖሌን ሃውልት ትቃወማለህ ግን ለምን የምኒልክ ሃውልት በመሰራቱ ምንም አልተሰማህም? የምኒልክ ሃውልት እንደተሰራ ሁሉ ይህ ሃውልት መሰራቱ ምን ያስገርማል?” ይላል።
በመሰረቱ የዳግማዊ ምኒሊክ ሐውልት የተሰራው በኢትዮጵያ ቀጣይ ታሪክ ላይ ጠባሳ ጥሎ ሊሄድ የነበረውን የአድዋ ጦርነትን በማሸነፋቸው ነው።ኢትዮጵያ በእርስ በርስ ጦርነት የተሞላ ታሪኮች ችግር የለባትም።ግን እኔ እስከማውቀው ድረስ በብሔራዊ ደረጃ እውቅና የተሰጠው የእርስ በርስ ግጭት ማስታወሻ ወይንም ሰሜኑ ደቡቡን ደቡቡ ምሥራቁን አልያም አንዱ ደጃዝማች ንጉስ እገሌን ለማሸነፉ የሚል ሐውልት አልተሰራም።ለእርስ በርስ ግጭት የተሰራ ሃውልት ኢትዮጵያ በታሪክ ያየችው የኢህአዲግ መንግስት የሰማዕታት ሃውልት እያለ በመቀሌ፣ባህርዳር ወዘተ በብዙ ሚልዮን ብር እያወጣ የገነባቸው ሃውልት ነው።ከእዝያ ቀደም ብሎ የነበሩን ሐውልቶች ሁሉ ከውጭ ጋር ለነበሩን ውግያዎች ማስታወሻ ናቸው።ከእዚህ ባለፈ የነገስታት እና የታሪክ ሰዎች ሃውልት ይህም በእርስ በርስ ጦርነት እና ግጭቶች ”ጀግኖች” ተብለው ሳይሆን ለሀገራቸው ባደረጉት ሥራ ብቻ ሐውልት ቆሞላቸዋል።
የ አኖሌን ሃውልት በተመለከተ ተከትሎ የሚመጣ ብዙ ጥያቄዎች ይኖራሉ።አንዱ ከላይ እንደጠቀስኩት ለእርስ በርስ ግጭቶች በተጠቂም ሆነ በአጥቂ ወገን ማንም ጀግና ስለማይባል ሃውልት መስራቱ አይረባንም።እንስራ ብንል ደግሞ ብዙ የሚሰሩ ስንደረድር ሳንስማማ ዓለም ማለፉ አይቀርም።በግራኝ መሐመድ ዘመን ያለቁትን ይዘን፣በኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ በ 16ኛው ክ/ዘመን ተገፋን የሚሉትን ሕዝብ ይዘን እስከ 19ኛው ክ/ዘመን የአፄ ምንሊክ የደቡብ እና ምዕራብ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ድረስ የደረሱ ብዙ ክስተቶች ይኖራሉ።ታድያ ለእነኝህ ሁሉ ሃውልት እየሰራን ለልጆቻችን ማስቀመጥ ፋይዳው ምንድን ነው? ደግሞስ አሁን ያለነው ትውልዶች ባለፈው ለተደረገው በጎም ሆነ ክፉ ታሪክ የእኛ ሚና ምን ነበር? መልሱ ምንም ነው።ስለዚህ ባለፈው ላይ ሚና ከሌለን እኛ የምንናቆርበት ምክንያት ምን ሊሆን ይቻላል? አሁንም መልሱ ምንም የሚል ነው። የእዚህ አይነቶቹን ክስተቶች ህዝብን አስተዳድራለሁ የሚለው እና የመገናኛ ብዙሃኑን ጨምድዶ የያዘው መንግስት አንድ አይነት ማስተካከያ ከማድረግ ወይንም ለወደፊቱ ትውልድ የሚበጅ አቅጣጫ ከማመላከት ይልቅ ይባስ ቤንዚን አርከፍካፊ መሆኑ የወቅቱ እውነታ ነው።እንዲህ ባይሆን ኖሮማ 20 ሚልዮን ብር አውጥቶ ለቂም መያዣ ባልደከመ ነበር።እንዲህ ባይሆን ኖሮማ ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ለብዙ ተከታታይ ክፍል ምሁራንን ጠርቶ በወቅቱ ተያያዥ ውዝግቦች ላይ ሲያወያይ እና መፍትሄ ሲያፈላልግ ሀገር ቤት ያሉ ሚድያዎችን ያፈነው መንግስት በዝምታ ባላለፈው ነበር።እዚህ ላይ ለ”አኖሌ” ሃውልት ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው ታሪክ በታሪካዊ ማረጋገጫ የተደገፈ ላለመሆኑ ብዙዎች እንደሚስማሙት እኔም መስማማቴን ለመግለፅ እፈልጋለሁ።
ባጠቃላይ የእዚህ አይነት ቁርሾን ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚደረጉ ተግባራት በሙሉ ሌላ ምንም ስም አይሰጣቸውም ”ከብልቃጥ መርዝ” ሌላ። ለጊዚያዊ የፖለቲካ ፍጆታ እና ስሜታዊነት ተገዢ መሆን እና የዛሬውን ትውልድ ከመጪው ጋር ሳይጎረባበጡ እንዲገናኙ የማድረግ ክህሎት የተለያዩ ናቸው።እርግጠኛ ነኝ ከአመታት በኃላ ዛሬ ሐውልቱን የሰሩት እና ያሰሩት ወገኖች እንዲሁም በሐውልቱ ንዴታቸውን የተወጡ የሚመስላቸው ሁሉ በሰከነ አእምሮ የሚመለከቱበት ዘመን ይመጣል።ይህ የግድ ነው።ይህ የሚሆነው ደግሞ ከሁለቱ በአንዱ መንገድ ነው። አንዱ የእዚህ አይነቱ ሥራ ‘የብልቃጥ መርዙን’ ለማዛመት ውሎ የፀፀት መከራ አምጥቶ ወይንም ሁለተኛው ደግሞ ብስለት እና ማስተዋል ወደ ልቦና መጥቶ።ሁለተኛው እንዲሆን እንመኝ።
ጉዳያችን http://gudayachn.blogspot.no
መጋቢት 24/2006
‘ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ ለማፋጀት የገነባውን ‘የመርዝ ብልቃጥ’ ” የሚለውን ፅሁፍ ያነበቡ በተለያዩ ድረ-ገፆች ላይ ሃሳባቸውን ለሰጡ ተጨማሪ ማብራርያ ”ከጉዳያችን ብሎግ ” click the link https://www.facebook.com/notes/ጉዳያችን-ጡመራ/ኢህአዲግወያኔ-ሕዝብ-ለማፋጀት-የገነባውን-የመርዝ-ብልቃጥ-የሚለውን-ፅሁፍ-ያነበቡ-በተለያዩ-ድረ-ገፆች-ላይ-ሃሳባቸውን-ለሰጡ-ጥቂ/434604930017346
seenna dhugaa dhoskuuf dhigaa ilmaan oromoo akka bishaanii dhangala’ee goocha suukaneessa(Annoolee) minlik raawate soba ragaan qabataman hin jiru yeroo jetan xiqoo siinitti hin ulfaatu? kun kan mulisuu ummata oromoo miliyoonaa10 olii ta’u dhumaniif kabaja siin qabdaniif hammasii oromoon yoo du’ee omma mitti jechuu ta’uu keessan nibeekitu——isaa darbeefuu garaan nuugubata