• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወገንን በመርዳት ለኢትዮጵያ ያለን ፍቅር ይገለጻል!

January 25, 2014 05:39 am by Editor Leave a Comment

የዶክተር ካትሪን ሃምሊን እና የባለቤታቸው በዶ/ር ሬጅ ሃምሊን ግማሽ ክፍለ ዘመን የተጠጋው በጎ ምግባር የሚያሳዩ ድርሳናትን ስፈታትሽ አድሬ አረፋፈድኩበት ። “የፊስቱላ ተጠቂዎች የተስፋ ታሪክ ” በሚል በአንድ ወቅት በፊሱትላ በሽታና በዶክተር ካትሪን እና በቤተሰባቸው በስራ ባልደረቦቻቸው ተጋድሎ ዙሪያ የቀረበ በእጀ ነበረ  ከሲድኒ አውስትራልያ መስፍን ማሞ ተሰማ ያቀረበልንን ድንቅ በበቂ መረጃ ደጋግሜ አነበብኩት። “ዶ/ር ካትሪን ሀምለን በአሁን ሰአት በአውስትርሊያ ግዛት በአንድ የባህር ዳርቻ በሚገኘው ምቾታማና የናጠጠ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ቀሪውን የህይወት ዘመናቸውን እንኳ ለማሳለፍ አልፈለጉም።

hamlinዛሬም በዚህ እድሜያቸው ከሃገር ሃገር እየዞሩና እየተንከራተቱ ዕርዳታ በመጠየቅ የፊስቱላን በሽታ ከምድረ ኢትዮጵያ ለማስወገድ እንዲቻል የፋይናንስ፤ የማቴሪያልና የባለሙያ ኃይልን እያደራጁ ይገኛሉ።!”  ይላል የመስፍን ነጋሽ መረጃ!  እውነት ነው!  ስለ ዶር ካትሪን ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ታዋቂዋን ቶክ ሾው አቅራቢ ኦፕራን ጨምሮ ከተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር ያደረጓቸውን ቃለ መጠይቆች ዙሪያ ዳሰሳ አደረግኩ  ። ጥናታዊ ፍልሞችንም ተመለከትኩ  ! የእኛዎቹ ምንዱባን  ልብን ይነካሉ … የነጯ እምቤት ስራ ነፍስን በተስፋ ያድሳል!  የእኛ ኑሮ ውሎ አዳር ያሳስባል እና አሰብኩት! እናም የእኒህ እመቤት ውለታ ቢከብደኝ የእኛ ነገር ቢያሳስበኝ እኔው ራሴ ለራሴን መላልሸ ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት ነው ?  ብየ ጠየቅኩት!

ሩቅ ተጉዠ ሃገር ቤት ያሉ የእኛ ሃኪሞችና በሰብአዊ እርዳታ መስሪያ ቤቶች በከባድ ሃላፊነት ተቀምጠው ለወገን በተለመነው እርዳታ የበለጸጉ የማውቃቸው የምናውቃቸውን ወገኖች በአይነ ህሊናየ አስታወስኩ ። በዙሪያየ ካለው የቅርብ ወራት ትዝታ አዝግሜም በሳውዲ የኮንትራት ስራ መጥተው የተለያዩ ጥቃቶች ደርሰውባቸው የጅዳና የሪያድ መጠለያዎች ተሞልተው የከረሙትን ተፈናቃይ ወገኖችና ከቅርብ ርቀት በባንዴራና በመፈክር አሸብርቀው ስብሰባ ድግስ ሲፈራረቅባቸው የከረሙትን አዳራሾች አስታወስኩ! ጉራጌ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ፣ኦሮሞ ሁሉንም የሃገሬ ብሔር መወከል የሚችሉ ግፉአን የከፋ በደል ደርሶባቸው ቅስማቸው ተሰብሮ ውለው በሚያደረሩበት ግቢ ጉራጌ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ፣ኦሮሞ እና በቀረው ብሔር ብሔረሰብ የቋቋሙት የልማት ማህበራትና ድርጅቶች ዲል ያለ ድግስ ደግሰው የተወለዱ፣ የተቋቋሙበትን፣ የአመት ሪፖርት ገንዘብ ማሰባሰቢያ ድግስ ዲል አድርገው ሲደግሱ የብሔር ብሔረሰብ ልጆችን እንባ መጥረጉ ቀርቶ ችግሩን አንስተው መወያየት የተሳናቸውን አጋጣሚ በንጽጽር አስታወስኩት።

እንዲህ እንዲህ እያልኩ ብዙን አስታወስኩ ።  ” አይ የእኛ ነገር !” አልኩ ከትንነት በስቲያ ወዳጃችን አርአያ ተስፋ ማርያም አንድ መጣጥፍ እንደገና ታውሶኝ … የአርአያ ተስፋ ማርያም ከዋሽንግተን ሆኖ እንደ ሸረሪት ድር በሚያገናኘን የኢንተርኔት መረብ አማካኝነት በፊስቡክ ገጹ የለቀቀው ገጠመኝ  እንዲህ የሚል አለበት “በዲሲ 13ኛው መንገድ አመሻሽ ላይ በእግሬ ሳዘግም በስተግራ በኩል ካለ የተንጣለለ አዳራሽ አንድ ድምፅ ከጆሮዬ ጥልቅ አለ። በአማርኛ የሃይማኖት ስብከት ሲሆን ሰባኪው፥ «ኢየሱስ የተቸገሩ፣ የተራቡ፣ የታመሙ..እርዱ ይላል..» እያለ በአዳራሹ ለተሰበሰበው ህዝብ (ሃበሻ) ይሰብካል። በአዳራሹ ሁለተኛ መግቢያ በኩል ሁለት ሰዎች ጥግ – ጥግ ይዘው በዛ ቁር ኩርምት ብለዋል። … ተጠግቼ አናገርኳቸው። «ለምን እዚህ እንዲያስጠጓችሁ አትጠይቋቸውም?.» ስል ጠየኳቸው። ሙላቱ « ወንድሜ መኖራችንን ካወቁ ፖሊስ ጠርተው ያባርሩናል። ከሰው አይቆጥሩንም።fistula1 እያንቋሸሹ፣ ሊደበድቡን ይቃጣቸዋል። ህይወት ፊቷን ስታዞርብህ ምንም ያልበደልከው ወገንህ ተደርቦ ለምን አሳርህን እንደሚያሳይህ ይገርመኛል!» አለኝ። ንግግሩ አንጀት ይበላል። … እምነት በተግባር ካልታጀበ ምን ዋጋ አለው?…ሰባኪው ስለየትኞቹ ችግረኞች ነው የሚናገረው?..አፍንጫው ስር የወደቁ ወገኖችን ካለመርዳቱ ባሻገር ጭራሽ ለአይን መጠየፍን ምን ይሉታል?..የሃይማኖቱ ተከታዮችስ ይህን እያዩ ማለፋቸው ምን ይባላል?.. ” ይለናል አርአያ በሃብታሟ ሃገር በአሜሪካ የብዙሃን መናህሪያ በዋሽንግተኗ በእኛ መንደር የሚታየውን ምስቅልቅል ህይዎት ሲያስቃኘን ።  …ይህም ያማል!

ይህንና ያንን አውስቸ በራሳችን እየሆነ ባለው አፍሬ ተሸማቀቅኩ ፣ አዛውንቷ የሰው ሃገር ሰው ዶር ካትሪን ባከበሩት 90ኛ አመት የልደት መታሰቢያ ግን መልካም ስራቸውን አውስቸ ደምቅኩ ። ዶ/ር ካትሪን ከልጅነት እስከ እውቀት ለእኛ በኖሩባቸውን ረጅም አመታት የደገፉዋቸውን ወደ 40 ሽህ የሚጠጉ ኢትዮጵያን የማህጸን (የፊስቱላ) ህሙማንን የሰመረ ህይዎት መልሸ መላልሸ አሰብኩት ። ማነጻጸር የማይመቸውን እያነጻጸርኩ ለምን እያልኩ ራሴን ወዘወዝኩት!   “ኢትዮጵያን እንወዳለን!” ለማለት ሰንደቅ ባንዴራ አረንጓዴ ቢጫ ቀለሙን በመላብስ ጌጣ ጌጦች የምንደምቀውን የእኛን ስራ አስታውሸ ውስጤን አንዳች ክፉ ሰሜት ሸነቁጠው … እናም ኢትዮጵያ ማለት ምን ማለት ነው? ብየ ራሴ ላጠየቅኩት ራሴው በመመለስ ቢያንስ ለእኛ ሲሉ የሚሰሩትን በመደገፉ እንበርታ ለማለት ስንደረደር ኢትዮጵያ በሚለው መልስ ይሆናል ያልኩትን የሆዴን ለመናገር መሞነጫጨር ጀመርኩ…

ኢትዮጵያ ማለት ስም ነው ፣ የማይበጥ የማይቧጠጥ ! ምሳሌ ነው ፣ መለያ ነው  ! ኢትዮጵያ ማለት ስም ነው መለያ ፣ በምድሯ የታጨቀው ወገን መታወቂያ ! ኢትዮጵያ ማለት ሰው ነው በቀየዋ የሚኖረው ፣  መሬቷን አርሶ ግሮ ጥሮ የሚኖረው ፣ ኢትዮጵያ ማለት ተምሮ ፣ አስተምሮ ፣ ተመራምሮ ተስፋን ሰንቆ የሚኖረው !  “ኢትዮጵያን እወዳለሁ!” የሚለው ወገኑን ለመታደግ አለፋ ስቅየት የሚከፍለው !  ለክብር ነጻነቷ ቀናኢው ኢትዮጵያ ማለት እሱ ነው በምድሯ የበቀለው ! “ኢትዮጵያን እወዳለሁ!” በሚል ደስኳሪው  ፣ ሃገሩን አሳልፎ ሰጭው ፣ ወገኑን በመታደግ ፋንታ ዘራፊው፣ በራሱ ወገን የሚጨቆን የሚረገጠው  ፣ የሚጨቁነው!  ወገኑን መደገፍ ያቃተው …  ኢትዮጵያዊ እሱ ነው ደጉም ክፉውም ሰው…  !

ኢትዮጵያ ማለት ተራራ ምድር ሸንተረሩ፣ ቆላው፣ ደጋው፣ ወይና ደጋው፣ ለገዛው የሚገዛው መሬት፣ አለያም በተቀደደለት የሚፈሰው ውሃ ማለት አይደለም ኢትዮጵያዊነት ! ኢትዮጵያዊነት ክብሩ ስሙ ነው የሰው ፣ የህዝብ የወገኑ … !  ኢትዮጵያን መውደድ ፣ ባንዴራን ማፍቀር ማለት ህዝብ ወገንን መውደድ፣ መደገፍ ፣ማበልጸግ ማለት ካልሆነ ፍቅር መውደዱ ከንቱ ነው … !

እናማ “ኢትዮጵያ ሃገራችን እንዎዳለን? ”  ካልን በተግባር እናሳየው ! ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ወገንን በመርዳት ፍቅራችን በድጋፍ እንግለጸው ! የዶር ካትሪንን እና የቀሩትን ፈና ወጊ የሰው ሃገር ሰው ስራዎች ተመልከቱ ! ዛሬ ያነሳሳናቸውን እመቤት በጎ ምግባር ብንመረምረው ሰብዕና አስገድዷቸው ከሃገረ አውስትራልያ በለጋ የልጅነት እድሜ ጀምሮ ዛሬ እስከሚከበረው የ90ኛ እድሜያቸው ፊስቱላን ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም ! … ባላቻ ጋብቻና በአስገድዶ መድፈር እኛው ባጠፋነው ጥፋት ፣ በማህጸን በሽታ fistula2በለጋ እድሜ ለሚሰቃዩ እህቶች እና እናቶች ህይዎት ትንሳኤን እያበሰሩ ግማሽ ክፍለ ዘመን የተጓዙ ሃኪም ናቸው! ዶር ካትሪን ፊስቱላን ከእኛ ሃገር ለማጥፋት የጀመሩት ጉዙ በእኛ ካልታገዘ የትም አይደርስም ” ባይባልም ቢያንስ የመልካሙ ዘመቻቸው አካል በመሆን ሰብዕናችን እናሳይ ዘንድ ግድ ይለናል!

“አብዛኛውን እድሜዬን ያሣለፍኩት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ሌላ ሃገር ኖሬ አላውቃም። ከእንግዲህ ምን አልባት አንድ አመት ወይም አምስት አመት ልኖር እችል ይሆናል። እኔ ካለፍኩ በኋላ የጀመርነውን ሥራ ግቡን ሳይመታ እንዳታቆሙ አደራ!ፊስቱላን ከኢትዮጵያ ገጽ ማጥፋት አለብን።” በማለት የተናገሩት ዶር ካትሪን በኦክቶበር 2009 በአውስትራሊያ ርዕሠ ከተማ ካንቤራ ውስጥ የሳቸውን የኢትዮጵያ ቆይታ ተመርኩዞ በተሰራውን ዶክመተሪ ፊልም የምረቃ ዝግጅት የተናገሩት ቢሆንም ካትሪን በቀረቡባቸው መድረኮች ሁሉ ፊስቱላን በታዳጊ ሃገሮች ለማጥፋት ያላቸውን ቁርጠኝነት አመላክተዋል።

አዎ እውነት ብለው ፣ ስለእውነት እየሰሩ ያሉት እናት የዶ/ር ካትሪንን ፊስቱላ ከሃገረ ኢትዮጵያ ለማጥፋት እንቅስቃሴ እደግፋለሁ!

ዶ/ር ካትሪን እርስዎስ ለኢትዮጵያ እንኳንም ተወለዱ!

እናታችን  ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን! እርስዎስ ለኢትዮጵያ እናቶች እንኳንም ተወለዱ!

አክባሪዎ

ነቢዩ ሲራክ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Social Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule