• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አልመች አለው ጎኔ!”

May 3, 2015 08:59 pm by Editor Leave a Comment

ጥበብ የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ስሜት የሚገለጽባቸው ቀዳሚው እያዝናና የሚያስተምር ዘርፍ ቢሆንም አሁን አሁን ግን ያ እየሆነ አይታይም። የማፍር፣ የምኮራባቸው ጥበበኞች ጉዳይ  አሁን አሁን ያሳስበኝ ይዟል … እናም የጎልማሳው አቀንቃኝ  የጃኪ “አልመች አለው ጎኔ!” ጣዕመ ዜማ ውስጥ ስሜቴን ቢነካካው፣ የማፍር የምኮራባቸው፣ ጥበበኞች … ብየ ጀመርኩት!

የጥበብ ሰዎች በግል እንደ ተራ ዜጋ የፈቀዱትን ፖለቲካ አቋም  የመያዝ መብታቸውን የማከብር ቢሆንም ታዋቂነታቸውን ተጠቅመው ከእውነተኛ የህዝብ መብት ጥያቄና ስሜት ሳይሆን ለሆዳቸው ሲያድሩ ማስተዋል ስሜትን ይጎዳል። በተለይም ደግሞ የጥበብ ሰዎች ለሆዳቸው አድረው ከገዥ አንባገነኖች ጋር ወግነው የህዝብ ድምጽ ሳይሆን የፖለቲካ ፖርቲዎች ቱልቱላ ሲሆኑ ማየት ያማል።

ያለመታደል ሆኖ በእኛ ኢትዮጵያ ከጥቂት የጥበብ ሰዎች በስተቀር አብዛኛው የጥበብ ሰዎች ከህዝብ እውነት የራቁ  አዎዛጋቢ ሰብዕና ያላቸው እየሆኑ ነው። የሀገሬውን መከራ፣ ስቅየትና የኑሮ ውጣ ውረድ ገባ ብለው መግለጹ ቀርቶ ሲገፋና ሲበደል እንኳ አጋርህ ነህ የማይሉት አሳፋሪዎችም እየሆኑ ለመምጣታቸው ብዙ ያየነው በሊቢያ በሰሞነኛውን የISIS ጥቃትን ተከትሎ የታዘብነው አቋም ነው። ሀገር ሲያዝን፣ የሀገሬውን መከራ፣ ስቅየትና የኑሮ ውጣ ውረድ ከፍቶ መጠን ሲለቅ፣ ህዝብ ከአድማስ አድማስ ሲጨነቅ በሀዘን በመከራው ወቅት ትክክለኛውን የህዝብ ስሜት የተጋሩና የገለጹት ምንኛ የታደሉ ናቸው? በአንጻሩ ጥበብ አጓጉል ክብርን፣ ገንዘብ ለማግበስበሻነትና ለፖለቲካ ወገንተኝነት አድርገውትና አግድመው ለፖለቲካው አድልተው የህዘብን ጉዳት ያልተሰማቸው፣  ድምጻቸውን ያላሰሙት ምንኛ ያልታደሉ ናቸው?

ብቻ ጥበብ የህዝብ ስሜት መገለጫ ጭምር ናትና የህዝብ ጥበበኛ መሆን መቻል መታደልም ጭምር ይመስለኛል። ይህ እውን ሲሆን ማየትም ደስ ይለኛል ፣ ደስ ይለናል …

“አልመች አለው ጎኔ!” ይለናል ጃኪ … የውስጥ ህመማችን በሚማርክ  የድምጽ ቅላጼው አልመች፣ አልደላን ማለቱን  ሲገልጸው … ለማለዳ ወጌ መነሻ መድረሻ የሆነኝም ይህው ነጠላ ዜማ ነው፣  እኔ ወድጀለታለሁ …!

አልመች አለው ጎኔ
============
እዳክራለሁ እኔ
እዳስሳለሁ እኔ፣
ወጥቸም አልተሳካ፣
በቤቴም ሆዳ አይሞላ፣
ይሄ ሲሄድ ያ ይመጣል
ጊዜ ሽሮ ቃል ያነባል፣
አልመች አለው ጎኔን!

አንዱ ጊዜ አልፎ ጸና
ነገ እንደ ዛሬ ገና
ምድር ከሰማይ ርቃ
አንዱ ሲሄድ አንዱ ይመጣል
ጊዜ ሽሮ ቃል ያነባል፣

እዚህም ሲያልቅ ወገኔ
ማየት ተሳነው አይኔ
በቁሙ ነፍሱን ሲያጣ
እንዴት ደራሽ እንጣ?
አረ ጉድ ነው አቤት ቁጣ!
ሀሰት  እውነት  ሁኖ  እየኖረ
ስንቱ ኑሯል  እያማረረ

ተስፋው፣ ሲጨልምበት
ነፍሱን ሰጠ፣ ለስደት

አይነጋም ወይ? ያ ጨለማ
አለው በይን  አንች  እማማ!
አልመች አለው ጎኔን!

ደርሶ የሞላ እለቱ
በዘመድ በጥረቱ
ተረሳ የትናንቱ
ከፍ ስላለ ቤቱ

ጉርሻ አምጣ
አለው ጣጣ
በዚህ ቁጣ
ለውጥ የት ይምጣ?

ጣፋሽ  ስኳር ስትልስ
ኑረሃል አንተ ምላስ
ይበቃሃል ሀቁ ይውጣ
የላዩም አይቆጣ
ፍርድ የላይ ነው ምድር ከንቱ
ይበጀናል እንደ ጥንቱ

ሳቅ ሳቅ ሲለኝ
ዝም አንች አያፍርም
ስቅ ሲለኝ
ውሃ ዘግ የለም

ብዙ ሚሊዮን ቆጥሮናል
መስማማት አቅቶናል

ማን በቤቱ አርፎ ይተኛ
ሰው በሰው ቤት ሆኖ አድመኛ

አልመች አለው ጎኔን
ርቆ እንደሰማይ ከኔ
አልመች አለው ጎኔን …

****  ****** ******
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 22 ቀን 2007 ዓም

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule