
ማን ነው እሱ አንበሳ ፤ ክህደትን ከሀዲ
በመላ ምርኮ ጣይ ፤ የሐበሻ ጋንዲ
ታሪክ ሠሪ አርበኛ ፤ ልበ ሙሉ ጀግና
ምርጥ ብርቅ ዜጋ ፤ ኮስታራ ቆፍጣና
በንስር ክንፎቹ ፤ አየር ላየር ሔዶ
ሽው ባይ እንደ ነፋስ ፤ ዱብ እንደ በረዶ
ምርኮን በዓይነት ይዞ ፤ ጠፍንጎ ቀፍድዶ
መቸ ይህ ብቻ ነው ፤ ቆራጡ ሳተና
ከእኛ ጋር የሆኑ ፤ አሉን ብዙ ገና
እውነት መሰላቹህ? ፤ ቢመስል ደናና
ምንም እንዳልከፋው ፤ ቢታይ ብሎ ዘና
ልክ እንደተመቸው ፤ ቢስቅ በገናና
ሀገር ሕዝብ የጠላ ፤ ከጦር ማን አለና
ለማን ሲል ገባና ፤ አይደል ለጅል ዝና
ለእናት ሀገሩ እንጅ ፤ ላለበት አደራ
ለወገኑ እንጅ ፤ ሊያድን ከመከራ
አይደለም ለቡድን ፤ ለጎጥ ለደንባራ
ለጠባብ ጥርቅም ፤ ለቅጥረኛ ጎራ
ከነ አካይስት በቀር ፤ ከነ ሕልመ መና
ከነ የጥፋት ልጅ ፤ ከነ ዓይኑ ገና
ከቡድኑ ግብረ አበር ፤ ከነ ቅስም ሰናና
ታንከኛው የኛ ነው ፤ መድፈኛውም የኛ
እግረኛው የኛ ነው ፤ የሀገር ምርኮኛ
ሁሉም ነው ዘብ ቋሚ ፤ ለሀገሩ አርበኛ
አይደለም የማንም ፤ ምንትስ ቅጥረኛ
ባንዳ የባንዳ ልጅ ፤ የወገን ደመኛ
የገዛ ሀገሩን ፤ ገሎ ሟች አድመኛ
አይደለም ጦራችን ፤ ከንቱ ሽብርተኛ
ቀን ነው የሚጠብቀው ፤ ያችን ምቹ ሰዓት
ያገሩን ጠላቶች ፤ ጉድ የሚያደርግበት፡፡
ታሕሳስ 13 2007ዓ.ም.
Dear Argaw Bedhaso,
I am surprised not to see the word Oromo or Oromiya in your poem. When do you think you would stop using your offensive languages and calm down, accept the reality and start discussing positively any issues you have with any person, party or ethnic group?
May God give you that chance.
Even the picture you used speaks a thousand words about your fixation to the past. Mekabr yalewun neftegna yastawusal.