የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አቅዶ ሲነሳ፣ የግቡ መረማመጃ ያደረገው የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆኑ ተቋሞችን፣ ኃይማኖቶችን፣ ዕሴቶችን እና በተለይም «ዐማራ» የተሰኘውን ነገድ ተወላጆች ነጥሎ ማጥፋት የሚል ሥልት በመከተል እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም መሠረት የጥፋቱ ቅድሚያ ዒላማ ያደረገው ለትግራይ ሕዝብ በችግሩ ጊዜ ደራሽ እና የተራበ አንጀታቸውን ዳሳሽ በሆነው የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምትና የሠቲት ወረዳዎች ሕዝብ ላይ ነው። ወያኔ በእነዚህ የትግሬ አዋሣኝ ወረዳዎች ሕዝብ ላይ የጥፋት ክንዱን የዘረጋው በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው።
የመጀመሪያውና ታላቁ ምክንያት የእነዚህ ወረዳዎች ሕዝብ ዐማራ በመሆኑ እና የትግራይ አዋሳኝ ስለሆነ የትግራይን ታሪክ ክፉውንም ሆነ ደጉን ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት የዚያ አካባቢ ሕዝብ የትግሬ-ወያኔ ለተነሳለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ዐማራ እንቅስቃሴ የማይተኛ እንደሆነ ስለሚረዳ ይህን ሕዝብ ብቻውን አቁሞ ማጥፋት ለወደፊቱ ግሥጋሴው ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው በማመን የችግር ጊዜ ደራሻቸውን ሕዝብ ያለርኅራኄ ጨፍጭፈውታል።
ሁለተኛው ምክንያት «ታላቋን ትግራይ» ለመመሥረት ባላቸው ዕቅድ ለውጭ ግንኙነታቸው መውጫ መግቢያ እንዲሆናቸው ከሱዳን ጋር የሚዋሰኑትን እነዚህን ወረዳዎች ወደ ትግራይ ማጠቃለል ስለነበረባቸው ነው። ሆኖም የአካባቢው ሕዝብ «ነገዳችን ዐማራ፣ ጠቅላይ ግዛታችን ጎንደር ነው።» እያለ እንዳያስቸግራቸው በቅድሚያ ነባር ነዋሪውን ጎንደሬ አጥፍቶ በሠፋሪ ትግሬ ማስያዝ ለዓላማቸው ሥምረት ያገለግላል ብለው በማመናቸው ነው።
ሦስተኛው ምክንያት የሠቲት፣ የወልቃይት፣ የጠገዴ፤ እና የጠለምት ወረዳዎች ለሠፋፊ የእርሻ በተለይም ለጥጥ፣ ለሰሊጥ፣ ለማሽላ፤ ለዱር ሙጫ፣ ወዘተርፈ ምርት የሚያመች የለም እና ሠፊ መሬት ባለቤት በመሆኑ ነው። ስለዚህ የእነዚህ የሚያጓጉ የተፈጥሮ ኃብቶች ተጠቃሚ ለመሆን ተቀናቃኙን የጥንት ነዋሪውን ሕዝብ የግድ ማጥፋት አለብን ብለው በማመናቸው ነው።
ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በዐማራ ነገድ አባሎች ላይ የተቀነባበረ የዘር ማጽዳት ወንጀል መፈጸም የጀመረው ድርጅቱ ገና «ተጋድሎ ሓርነት ሕዝቢ ትግራይ (ተሓሕት)» ተብሎ ይጠራበት ከነበረበረበት የጨቅላነቱ ዘመን ጀምሮ እንደሆነ የድርጅቱ ታሪክ ያስረዳል። በተለይም የትግራይ አዋሣኝ በሆኑት የሰሜን ጎንደር ታሪካዊ አካሎች በነበሩት ወረዳዎች ነዋሪ የሆኑ ዐማራዎችን ለማጥፋት ተሓሕት-ሕወሓት ፕሮግራም ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረው ከ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ የድርጅቱ ነባር አባሎች ያስረዳሉ። የሰሜን ጎንደር ለም እና ድንግል ወረዳዎች የሚባሉት፦ ወልቃይት፣ ሠቲት፣ ላይ እና ታች አርማጭሆ፣ ጠገዴ እና ጠለምት ናቸው። በሕወሓት ታሪክ ውስጥ «የዲማ ኮንፈረንስ» በመባል የሚታወቀው እና ከ፻፶ (አንድ መቶ ሃምሣ) ያላነሱ አባላቱ ተካፋይ በሆኑበት በየካቲት ወር ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. «ጸደቀ» የተባለው ፕሮግራም ወልቃይትን፣ ሠቲት፣ ጠገዴን እና ጠለምትን ከዐማራ በማጽዳት ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ መጠቃለል እንዳለባቸው ያስገነዝባል።
ይህ ፕሮግራም ዐማራውን ከማውገዝ አልፎ፣ በትግሬ ደመኛ ጠላትነት በመፈረጅ በግልፅ ቋንቋ «የትግላችን ዓላማ ፀረ-የዐማራ ብሔራዊ ጭቆና ነው» ይላል። ከዚህ በተጨማሪም ፕሮግራሙ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅም እና የሕዝቧን አንድነት በእጅጉ የሚጎዳ ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱ እንደአገር እንዳትቀጥል የሚያደርግ ዓላማ ያለው መሆኑ በፕሮግራሙ መሠረት ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በመፈጸም ላይ ያሉት ተግባሮች ሁነኛ እማኖኞችና ነቃሾች ናቸው።
በ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. የጸደቀውን የድርጅቱን ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ አርከበ ዕቁባይ «ወደ ታላቋ ትግራይ ረፐብሊክ ሊካተቱ ይገባል» የተባሉትን ከጎንደር ወልቃይትን፣ ጠገዴን፣ ጠለምትን፣ ሠቲት፤ እንዲሁም ከወሎ ክፍለሀገር ደግሞ ራያና ቆቦን፣ አላማጣን፣ ወልድያን፣ ጨምሮ እስከ አሸንጌ ኃይቅ ድረስ ያሉትን ሥፍራዎች የሚያካትት ካርታ አዘጋጀ (ተያያዥ ካርታዎችን ከ፩-፬ ይመልከቱ)። በዚህ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ የምትመሠረተው «የትግራይ ረፐብሊክ» ከሱዳን ጋር የሚያገናኛት የመሬት አካል እንድታገኝ ሆነ። በዚህም መሠረት በ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. ተሓሕት-ሕውሓት ያለ የሌለ ኃይሉን ከጎንደር ክፍለ ሀገር ነጥቆ ወደ ትግራይ ባካለላቸው ጥንተ-ነዋሪ የዐማራ ሕዝብ ላይ የጥፋት ክንዱን አነሳ።
ከሁሉ አስቀድሞ መታወቅ ያለበት ጉዳይ የትግሬ-ወያኔ ዐማራን ማጥፋት የጀመረው ኢትዮጵያዊነትን በሁለንተናዊ መልኩ ከትግራይ ሕዝብ አዕምሮ እንዲጠፋ ካደረገ እና የዓላማው ተቃዋሚ የሆኑ የራሱን ነገድ አባሎች ከትግራይ ምድር ካጸዳ በኋላ ነው። ይህ በዚህ እንዳለ በ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. የተሓሕት-ሕወሓት አመራር አባላት የሆኑት ስብሐት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ዐባይ ፀሐዬ፣ ሥዩም መሥፍን፣ ስዬ አብርሃ እና አውአሎም ወልዱ «በትግራይ ክፍለሀገር ውስጥ የሚኖሩ ዐማሮች፣ ኦሮሞዎች እና የሌሎችም የኢትዮጵያ ነገዶች ተወላጆች ከትግራይ መሬት ለቀው ይውጡ፤ ትግራይ የትግሬዎች ብቻ ናት!» ብለው ሲወስኑ በወቅቱ ይህን ውሣኔ ተቃውመው የቆሙት ግደይ ዘርዓፅዮን እና ዶክተር አታክልቲ ቀጸላ ብቻ እንደነበሩ ስለሁኔታው የሚያውቁት አቶ ገብረመድህን አርአያ በተለያዩ አጋጣሚዎች አሣውቀዋል። ያ ውሳኔ ተግባራዊ ሆኖ፣ ዛሬ ትግሬዎች ትግራይን በብቸኝነት፣ ቀሪዋን ኢትዮጵያ ደግሞ በገዥነት ተቆጣጥረው ይገኛሉ።
ተሓሕት-ሕወሓት የሰሜን ጎንደር አካል በሆኑ ወረዳዎች ነዋሪ በሆኑ ዐማሮች ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመፈጸም እንዲሁ ዘሎ ወደ አካባቢው አልገባም። ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነበረበት። ለዚህም ሁኔታዎች እስኪመቻቸቹ ድረስ ጊዜ መግዛት ነበረበት። አንደኛ፥ ጠለምት፣ ወልቃይት እና ጠገዴ በኢሕአፓ ተዋጊዎች የተያዘ ስለነበር፣ አቅሙ እስኪጎለብት እና ኢሕአፓን መጓባት እስኪችል መጠበቅ ግድ በማለቱ፤ ሁለተኛ፥ በወቅቱ የአካባቢው ሕዝብ እንደማይቀበለው ያውቅ ስለነበር፣ ሕዝቡን አሸማቆ እና ረግጦ መቆጣጠር የሚችልበት አቅም መፍጠር ስለነበረበት፤ እንዲሁም ከሁሉም በላይ የአካባቢውን ሕዝብ ማንነት የሚያውቅ ባንዳ መልምሎ ማሰልጠን ጊዜ የሚጠይቁ በመሆናቸው ነበር። ይኽም ሆኖ፣ ተሓሕት-ሕወሓት በተጠቀሱት ወረዳዎች በመሽሎክሎክ አሻራውን ከማስቀመጥ አልቦዘነም።
በ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ላይ ለተሓሕት-ሕወሓት ዓላማ መሳካት የሚያመች አጋጣሚ ተፈጠረ። ይኸውም በሻዕቢያ እና በጀበሓ፣ እንዲሁም በኢሕአፓ እና በተሓሕት መካከል የተደረጉት የጦፉ ውጊያዎች ነበሩ። በጦርነቱም ሻዕቢያ እና ተሓሕት-ሕወሓት የድሉ ባለቤቶች ሆኑ። ጀብሓ እና ኢሕአፓ ተበታትነው የትጥቅ ወረዳቸውን ለቀው በቡድን እና በተናጠል ወዳፈተታቸው አካባቢ አመሩ። ወረዳዎቹን ሁለቱ አጥቂ ኃይሎች ተቆጣጠሯቸው። ከሁሉም በላይ የኢሕአፓ ተዋጊ የነበሩት፦ ያሬድ ጥበቡ፣ ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሠ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ታደሰ ጥንቅሹ፣ ሕላዌ ዮሴፍ፣ ካሣ ተክለብርሃን እና በአጠቃላይ በቁጥር ፴፯ (ሠላሣ ሰባት) የሚሆኑት ለተሓሕት-ሕወሓት በሎሌነት አደሩ። እኒህ ቀደም ሲል ከተሓሕት-ሕወሓት ጋር ግንኙነት መሥርተው ስለነበር፣ የኢሕአፓን ተዋጊ ኃይል እንዲጠቃ የባንዳነት ሥራ ሠሩ። በዚህም የተነሳ የኢሕአፓ ተዋጊ ኃይል በተሓሕት ተገደለ፣ ተማረከ፣ ዕድለኛ የሆነውም በስደት ሱዳን ገባ። ይህ ሁኔታ ለተሓሕት-ሕወሓት ዐማራን የማጥፋት ተልዕኮው ሠፊ በር ከፈተለት።
በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሠቲት እና ጠለምት ዐማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም አመራር የሰጡ የተሓሕት-ሕዋሓት መሪዎች፦
(1) ስብሐት ነጋ (በወቅቱ የተሓሕት-ሕወሓት ሊቀመንበር የነበረ)፣
(2) መለስ ዜናዊ (የቀድሞው የትግሬ-ወያኔ መሪ፣ በ፪ሺህ፭ ዓ.ም. በሞት የተለየ)፣
(3) አረጋዊ በርሄ (ዶክተር፣ በስደት ሆላንድ የሚኖር)፣
(4) ዐባይ ፀሐዬ፣
(5) ሥዩም መሥፍን፣
(6) ግደይ ዘርዓጽዮን (በስደት ኖርዌይ የሚኖር) ናቸው።
መመሪያውን በማስፈጸም ጥቃቱን በአካል ያስፈጸሙት ደግሞ ሥዬ አብርሃ (በአሜሪካን አገር ይኖራል)፣ አርከበ ዕቁባይ፣ ፃድቃን ገብረተንሣይ፣ ዘርዓይ አስገዶም እና አውአሎም ወልዱ መሆናቸውን የድርጊቱን ሂደት በተጨባጭ የሚያውቁት አቶ ገብረመድኅን አርአያ ያረጋግጣሉ። ሁሉንም የሰሜን ጎንደር ዐማራዎች የጭፍጨፋ ዘመቻ በበላይነት ይመራው እና ያስተባብረው የነበረው ስብሐት ነጋ እንደነበር የዐይን እማኞች የነበሩ በተለያየ ጊዜ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
ሕወሓት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት እና በአርማጨሆ የዐማራ ተወላጆች ላይ የጥቃት ዒላማውን ሲያነጣጥር፣ መንገድ መሪ እና መረጃ አቀባይ በመሆን የጥፋቱን ከፍተኛ ድርሻ የሚወስደው በአባቱ የወልቃይት-ጠገዴ፣ በእናቱ ደግሞ የሽሬ ተወላጅ የሆነው የ«ሪጅን አንድ» የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው በዓለም ስሙ «ዮሴፍ ዘለለው» (በበረሃ ስሙ ደግሞ «መኮንን ዘለለው») በመባል የሚታወቀው ግለሰብ ነው። መኮንን ዘለለው በአሁኑ ሰዓት በስደት በአሜሪካን አገር ይኖራል። ለመኮንን ዘለለው ከሕወሓት የተሰጠው ተልዕኮ፦ በሕዝቡ መሃል እየተዘዋወረ ሠቲት፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት እና አጎራባች ወረዳዎች የትግሬ ግዛት አካል መሆናቸውን፣ ሕዝቡም ትግሬ መሆኑን በመስበክ ማሣመን፣ የሚያምኑትን መመልመል፤ «ትግሬ አይደለንም» ያሉትን እና አጥብቀው የተከራከሩትን እየመዘገበ ለፈዳያን (ገዳይ ቡድኖች) ስማቸውን በማስረከብ ማስገደል ነበር። በዚህም መሠረት መኮንን ዘለለው ከላይ በተጠቀሱት ወረዳዎች እየተዘዋወረ፦ «ይህ መሬት የትግራይ መሬት ነው። እናንተም ከእንግዲህ ወዲያ የሰሜን ጎንደር ዐማራ ተወላጆች አይደላችሁም። በመሬቱ እንኖራለን ካላችሁ ትግሬዎች መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ። እኛ ትግሬ አይደለንም፣ መሬቱም የትግራይ አይደለም የምትሉ ካላችሁ ደግሞ፣ የሕወሓትን ውሳኔ ጠብቁ።» የሚል ማስጠንቀቂያ ይሰጥ ነበር። ሆኖም ሕዝቡ ያላዳች ማመንታት የሰጠው መልስ «እኛ ዐማራዎች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም። የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት፣ እና የሠቲት ወረዳዎችም የትግራይ አካል ሆነው አያውቁም።» የሚል ነበር። «የሁለቱ ክፍለ ሀገሮች ማለትም፦ የትግራይ እና የጎንደር (ቤጌምድርና ሰሜን) የተፈጥሮ ወሰናቸው ተከዜ ነው። የትግራይ ግዛት ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም።» በማለት ታሪክ እያጣቀሱ ሞገቱት።
መኮንን ዘለለው ከሕዝቡ ያገኘውን ምላሽ ለአለቆቹ ሪፖርት አቀረበ። ሪፖርቱ ተልዕኮው ያልሰመረለት መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ፣ በወቅቱ የሕዋሓት ሊቀመንበር የነበረው ስብሐት ነጋ በብስጭት በመኮንን ላይ የስድብ ናዳውን በማውረድ ከሪጅን አንድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊነቱ እንዲነሳ አደረገው። ሕወሓቶች መኮንን ዘለለውን ባያስሩትም የተለያዩ ሥቃዮችን እንዲቀበል አደረጉት። ሕወሓትም በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ቂም ቋጠረ። ዕውነትን ጋሻ፣ ታሪክን ማጣቀሻ አድርገው የሞገቱትን ሰዎች እየለቀሙ አድነው ጨፈጨፏቸው። በዚህም መሠረት የትግሬ-ወያኔ ከ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ጀምሮ ተከዜን ተሻግሮ በቅድሚያ ከጨፈጨፋቸው የአገር ዘብ የነበሩ የወልቃይት-ጠገዴ የዐማራ ተወላጆች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
1) ግራዝማች ወልዴ የኔሁን፣
2) ቄስ በለጠው ተስፋይ፣
3) ቄስ ትዕዛዙ ቀለመወርቅ፣
4) ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣
5) አቶ ማሞ ዘውዴ፣
6) አቶ እንደሻው ታፈረ፣
7) አቶ አያሌው ሰሙ፣
8) አቶ በርሄ ጎይቶም፣
9) አቶ ሐጎስ ኃይሉ፣
10) አቶ ልጃለም ታዬ፣
11) ወጣት ግዛቸው ዳኜው፣
12) ወጣት አዲስይ ልጃለም፣
13) ወጣት ደረጀ አንጋው፣
14) ወጣት ዋኘው መንበሩ፣
15) ወጣት ሕይዎት አብርሃ፣
16) ወጣት ታደለ አዛናው፣ እና
17) ወጣት ማሞ አጀበ ናቸው።
ከዚያን ወቅት ወዲህ የትግሬ-ወያኔ በአካባቢው ይኖሩ በነበሩ የዐማራ ተወላጆች ላይ በተከታታይ ከፈፀማቸው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መካከል ለአብነት ለመጥቀስ ያህል፦
1) በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. «ርዋሳ» የተባለውን እና ከ፭፻ (አምሥት መቶ) በላይ ቤቶች የነበሩበትን የገበሬ መንደር አቃጥለው የትግሬ ተወላጆችን አሠፈሩበት። በዚህ ቀበሌ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ለከፍተኛ ችግር ከተጋለጡት መካከል አቶ ጫቅሉ አብርሃ፣ አቶ አብርሃ ሣህሉ፣ ወይዘሮ ስንዱ ተስፋይ፣ አቶ ዋኜው ይገኙበታል።
2) ከ፲፱፻፹፰ እስከ በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. በነበረው ጊዜ ከ፫ (ሦሥት) ሺህ በላይ ጥማድ በሬዎች ባለቤቶች የነበሩ ገበሬዎችን ገድለው እና አሰድደው የትግሬን ገበሬ አስፍረውበታል።
3) ከ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. ጀምሮ በማይ ኅርገጽ፣ በቤት ሞሎ፣ በማይ ጋባ፣ በማይ ደሌ፣ በአንድ አይቀዳሽ፣ በእምባ ጋላይ፣ በትርካን፣ በቃሌማ፣ በእጣኖ፣ በመጉዕ፣ ወዘተርፈ ይኖሩ የነበሩ ነባር የዐማራ ነገድ ተወላጆችን አባርረው የትግሬ ተወላጆችን አስፍረዋል። በአጠቃላይ የትግሬ-ወያኔዎች ሰሜን ጎንደርን ከወረሩበት ከ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ጀምሮ በነበሩት ፴፬ (ሠላሣ አራት) ዓመቶች በአካባቢው ለም መሬቶች ከ፫፻(ሦሥት መቶ) ሺህ በላይ የሚሆኑ የትግሬ ተወላጆችን አስፍረዋል።
ኃብት እና ንብረቶቻቸውን የተነጠቁ፣ እንዲሁም እንዲወድምባቸው የተደረጉ የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የሠቲት፣ እና የአካባቢው የዐማራ ተወላጆች መካከል ለመጥቀስ ያህል፦
1) የአቶ ዘነበ ሐጎስን ፬፻፶(አራት መቶ ሃምሣ) ያህል የቀንድ ከብቶች ዘርፈዋል፤
2) የአቶ አባየው ቢያድግልኝን ከ፮፻(ስድስት መቶ) የማያንሱ የቀንድ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈው በመጨረሻም ሰውዬውን ገድለዋቸዋል፤
3) የአቶ ገብረሕይዎት ኃይሌን ከ፹(ሰማንያ) በላይ የቀንድ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈዋል፤
4) በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. የአቶ አለባ ሕደጎን ከ፭፻ (አምሥት መቶ) በላይ የቀንድ ከብቶች እና በርካታ ኩንታል እህል ዘርፈዋል፤
5) የቀኛዝማች ገብሩ ገብረመስቀልን ፳፬(ሃያ አራት) በሬዎቹ አርደው ከ፱፻ (ዘጠኝ መቶ) መቶ በላይ ማድጋ እህል ወርሰዋል።
ከዚህ በታች የቀረበው ሠንጠረዥ ደግሞ ከሰሜን ጎንደር የዐማራ ተወላጆች መካከል በትግሬ-ወያኔ አማካይነት ከ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ጀምሮ የተገደሉ፣ የታፈኑ እና የደረሱበት ያልታወቁ ዜጎችን ዝርዝር በጥቂቱ መለክታል።
ተራ ቁጥር |
ስም ከነአባት |
ተራ ቁጥር |
ስም ከነአባት |
ተራ ቁጥር |
ስም ከነአባት |
1) |
አበበ ይርጋ |
2) |
አበራ ኃይሌ |
3) |
አበራ ዓለማየሁ |
4) |
አበራ ገብረመስቀል |
5) |
አበራ አስረስ |
6) |
አበራ ሐጎስ |
7) |
አበጀ ክፍሌ |
8) |
አባተ እሸቴ |
9) |
አባው ጠጅነህ |
10) |
አብርሃ አዳነ |
11) |
አብርሃ አርጉ |
12) |
አብርሃ ነጋ |
13) |
አብርሃ በላይ |
14) |
አቻምየለህ ሽታዬ |
15) |
አቸናፊ ጽጌ |
16) |
አደበ ዓለም |
17) |
አደራጀው ገብሬ |
18) |
አዲሱ አበበ |
19) |
አዲስ አብተው |
20) |
አዲሰይ ልጃለም |
21) |
አዳነ ደረሰ |
22) |
አዳነው ርስቴ |
23) |
አለባቸው ደፈርሻ |
24) |
አለበል ይርጋ |
25) |
አለኸኝ መሥፍን |
26) |
አለማው ታረቀ |
27) |
አለማይ ካሣ |
28) |
ዓለሙ ጌታቸው |
29) |
ዓለሙ ለገሠ |
30) |
ዓለሙ ፈንታይ |
31) |
ዓለማየሁ አበጠለው |
32) |
አለነ ክንዲሽ |
33) |
አላቸው ልጃለም |
34) |
አላቸው ገብረመድኅን |
35) |
አማረ ፈንቴ |
36) |
አንገረብ ተሰማ |
37) |
አንዶም ካሣ |
38) |
አረጋ ወልዴ |
39) |
አረጋው አየነው |
40) |
አረፈዓይኔ መኮንን |
41) |
አረፈ በለጠ |
42) |
አረፈ ግደይ |
43) |
አስገዶም ጥሩነህ |
44) |
አስመላሽ ይገዙ |
45) |
አስማረው ግደይ |
46) |
አስመራው ወልዴ |
47) |
አስማረው አስረሴ |
48) |
አስማረው መለሰ |
49) |
አስረስ ታከለ |
50) |
አስፋው መንግሥቴ |
51) |
አስፋው ወርቁ |
52) |
አሸናፊ ወንዱ |
53) |
አታላይ አበራ |
54) |
አታላይ አማረ |
55) |
አታላይ ዘነበ |
56) |
አጥናፈይ ዓለማየሁ |
57) |
ዐወቀ ዘውዱ |
58) |
አየነው ሙሉ |
59) |
አየነው ርስቴ |
60) |
አየነው በየነ |
61) |
አያሁነኝ ወንዶሻል |
62) |
አያሌው ሰሙ |
63) |
አያና ገብሬ |
64) |
አዘነህ ልጃለም |
65) |
አዛናው ቸሬ |
66) |
አዛናው ይደግ |
67) |
አዛናው ጽጌ |
68) |
እንዳልካቸው ጠጆ |
69) |
እንደሻው ታፈረ |
70) |
እንግተይ አየልኝ |
71) |
እሪበይ ገብሩ |
72) |
እሸቴ አያልነህ |
73) |
እሸቱ መስፍን |
74) |
በየነ ፍሬይ |
75) |
በየነ አየልኝ |
76) |
በሪሁን ደስታ |
77) |
በዕዱ ወንድም አገኝ |
78) |
በላይ ሙሉ |
79) |
በላይ ታደሰ |
80) |
በላይ መኮንን |
81) |
በለጠ ዓለም መብራት |
82) |
በለጠው ተስፋዬ |
83) |
በልጤ ወንድም-አገኝ |
84) |
በራ የማነ |
85) |
በራ ወልደሥላሴ |
86) |
በርሄ ሐጎስ |
87) |
በሪሁን ይግዛው |
88) |
ቢያድግልኝ ዘውዴ |
89) |
ባሕታ ፈንታይ |
90) |
ባሕታ መኩሪያ |
91) |
ባሕታ ወንድምአገኝ |
92) |
ባሕታ ረዳ |
93) |
ባሕታ እርትብ |
94) |
ባሕታ መንግሥቱ |
95) |
ባየው ባሕታ |
96) |
ባየው ቢያረግልኝ |
97) |
ባየው ልጃለም |
98) |
ብሪሁን ይርጋ |
99) |
ብላታ አብርሃ |
100) |
ብርሃኔ ማሞ |
101) |
ብርሃኑ ዳኛቸው |
102) |
ብርሃኑ ሽታዬ |
103) |
ገብረሕይዎት ኃይሌ |
104) |
ገብረመድኅን የኋላ |
105) |
ገብረመድኅን ዘርፉ |
106) |
ገብረመስቀል ጥርፊነህ |
107) |
ገብረሥላሴ ረዳ |
108) |
ገብረሕይዎት ባሕታ |
109) |
ገብረሕይዎት ገዛኸኝ |
110) |
ገብረማርያም አረፈዓይኔ |
111) |
ገብሬ ሐጎስ |
112) |
ገረመው ዳኜው |
113) |
ገሪማ ተኽላይ |
114) |
ጉበን ፊያሃጸን |
115) |
ጉዎይ መብርሃቱ |
116) |
ጉዎይ አዳነ |
117) |
ጊፍታቸው ዳኘው |
118) |
ጌቱ ጠለለው |
119) |
ጌታቸው አብርሃ |
120) |
ጌታቸው ብዙነህ |
121) |
ጌታቸው ተገኜ |
122) |
ጌቴው ታምሬ |
123) |
ግደይ ካሣ |
124) |
ግደይ ማሙ |
125) |
ግንባይ ጌታሁን |
126) |
ግርማ ይደግ |
127) |
ግርማይ ትኩስ |
128) |
ግርማይ ጥቄ |
129) |
ጎይቶም ምኅረት |
130) |
ጎይቶም ሐድጎ |
131) |
ጎርፉ ገብሩ |
132) |
ጎሹ አሰፋ |
133) |
ጎሹ ትርፍነህ |
134) |
ደቢል ዘነበ |
135) |
ደቢል ተክለሃይማኖት |
136) |
ደገፋ ጎይቶም |
137) |
ደሣለኝ ዋርካው |
138) |
ደስታ ሰርጸ |
139) |
ዳኜው ሢሣይ |
140) |
ድራር ገሠሠው |
141) |
ሀብቱ ይርጋ |
142) |
ሀፍቴ ዘነበ |
143) |
ወግሃታይ መንበሩ |
144) |
ወረታ ገብሩ |
145) |
ወልዴ ኢዮብ |
146) |
ወልዴ የኔሁን |
147) |
ወንድም ፍስሃ |
148) |
ወንድም ጠለለ |
149) |
ወንድም ጠጋ |
150) |
ወንድምአገኘሁ ታረቀ |
151) |
ወርቅዬ ገብረመድኅን |
152) |
ወርቅነህ አታላይ |
153) |
ዋኘው መንበሩ |
154) |
ዘውዱ ሽባባው |
155) |
ዘውዴ ሢሣይ |
156) |
ዘለቀ ግርማይ |
157) |
ዘራይ መርሻ |
158) |
ዘሩ በላይ |
159) |
ሐጎስ ገብራይ |
160) |
ሐጎስ መንግሥቱ |
161) |
ሐጎስ ይስፋ |
162) |
ጣሌ ገብሬ |
163) |
ጣሰው አሰፋ |
164) |
ጤላ ኃይሌ |
165) |
ጥጋቡ መኳንንት |
166) |
ጥላሁን ተወልደ |
167) |
ጥላሁን ታደሰ |
168) |
ጥሩነህ መብራቱ |
169) |
ጫኔ ይርጋ |
170) |
ጫቅሌ ገበየሁ |
171) |
ጫሉ ይዘዘው |
172) |
የኋላሸት ዘለቀ |
173) |
የሻለም በሪሁን |
174) |
የሽዓለም ጽጌ |
175) |
ይበይን ገብረእግዚአብሔር |
176) |
ይደግ አየነው |
177) |
ይደግ አያሌው |
178) |
ይዘዘው ገብረመስቀል |
179) |
ይላቅ ተዘራ |
180) |
ይርጋ ደምሰው |
181) |
ይስፋ ፋንታይ |
182) |
ከሰተ ይርጋ |
183) |
ካሱ ንጉሤ |
184) |
ካሂሱ ንጉሡ |
185) |
ካሣሁን ሲሣይ |
186) |
ካሣ መብራት |
187) |
ካህሱ ጌታው |
188) |
ክንፈ ከበደ |
189) |
ክንፈ ናሁ |
190) |
ለማ ታደሰ |
191) |
ሉሌ መሥፍን |
192) |
ሊላይ ሐድጉ |
193) |
ልዑል ገብረመስቀል |
194) |
ልዕልቲ ወንድምአገኝ |
195) |
ልጃለም በላይ |
196) |
ልጃለም ታዬ |
197) |
መብርሃቱ ይግዛው |
198) |
መብርሃቱ ገብረእግዚአብሔር |
199) |
መሓሪ አዱኛ |
200) |
መኮንን ለውጤ |
201) |
መኮንን አበራ |
202) |
መኳንንት ዋርካው |
203) |
መኩሪያ ገብረማርያም |
204) |
መንገሻ ሙሉጌታ |
205) |
መርዕድ ገብረሚካኤል |
206) |
መሣፍንት ዳኜው |
207) |
ሙኮጠይ ታደሰ |
208) |
ሙሉዓለም ዋርካው |
209) |
ሙላው ዞፌ |
210) |
ሙሉ አታላይ |
211) |
ሙሉ አማረ |
212) |
ሙሉ በርሄ |
213) |
ሙሉ ገብረኪዳን |
214) |
ሙሉነህ ደሞዜ |
215) |
ማለፊያ ጉዎይ |
216) |
ማሌ ዘነበ |
217) |
ማሙ ዋርካው |
218) |
ማሙ ቸሬ |
219) |
ማሙ ታደሰ |
220) |
ማሙነህ ይደግ |
221) |
ማማይ አብርሃ |
222) |
ማማይ አየልኝ |
223) |
ማማይ አለዩ |
224) |
ማማይ በላይ |
225) |
ማማይ ሙሉ |
226) |
ማማይ ረዳቴ |
227) |
ማማይ ፈረደ |
228) |
ማማይ በላይነህ |
229) |
ማሞ ደስታ |
230) |
ማሞ ዘውዴ |
231) |
ምራጭ ተሰማ |
232) |
ሞላ ጠለለ |
233) |
ነጋ አስረስ |
234) |
ነጋ አለበል |
235) |
ነጋ ጌታሁን |
236) |
ነጋ ሐጎስ |
237) |
ነጋ ምትኩ |
238) |
ነጋ ተበጀ |
239) |
ንጉሡ አብርሃ |
240) |
ንጉሤ ቀለመወርቅ |
241) |
ንግሸት ሐድጉ |
242) |
ሰጠኝ እንዳለው |
243) |
ሰጠኝ ሽታዬ |
244) |
ሰረበ ረዳ |
245) |
ሲሣይ አበራ |
246) |
ሲሣይ ተስፋሁነኝ |
247) |
ስማቸው ማሙ |
248) |
ስማቸው ዓለሙ |
249) |
ሺሙዬ ደምሰው |
250) |
ሺሙዬ ማሙ |
251) |
ሺሙዬ አለሜይ |
252) |
ሻንቆ በለጠ |
253) |
ሽፈራው ውብነህ |
254) |
ሽፈራው ንጉሤ |
255) |
ሽፈራው ተስፋይ |
256) |
ሽሁን ኪዳኔ |
257) |
ፈለቀ ግርማይ |
258) |
ፈረደ ዘርዓይ |
259) |
ፈረደ ፍሉይ |
260) |
ፈንቴ ገብራይ |
261) |
ፈንቴ ዘነበ |
262) |
ፋንቱ ሲሣይ |
263) |
ፋንታዬ አየልኝ |
264) |
ፍሬይ ተወልደ |
265) |
ፍታለው ታፈረ |
266) |
ጽይተይ አብርሃ |
267) |
ቁዊ ተዘራ |
268) |
ረዳኢ ለማ |
269) |
ርስከይ መለሰ |
270) |
ርስከይ ምንተስኖት |
271) |
ርስከይ ይልማ |
272) |
ርስከይ ኃይሌ |
273) |
ሮስኬ ማንጆስ |
274) |
ተበጀ መለሰ |
275) |
ተበጀ በቀለ |
276) |
ተገኘ ነጋ |
277) |
ተገኘ ደምሴ |
278) |
ተካልኝ አበበ |
279) |
ተካልኝ መንግሥቱ |
280) |
ተሰማ አብቅህለው |
281) |
ተሰማ ፍሬይ |
282) |
ተስፋ ፀጋዬ |
283) |
ተስፋይ አብርሃ |
284) |
ተስፋይ አጽብሃ |
285) |
ተስፋይ መኮንን |
286) |
ተስፋይ ኃይሉ |
287) |
ተሻገር ገብረመድኅን |
288) |
ተሾመ ፈረደ |
289) |
ተሾመ ጠለለ |
290) |
ታደለ አባተ |
291) |
ታደሰ ከሺ |
292) |
ታፈረ ሊላይ |
293) |
ታገል ተድላ |
294) |
ቶጋ ተገኘ |
295) |
ቻላቸው አበረ |
296) |
ቻላቸው ታደለ |
297) |
ቻላቸው ታደሰ |
298) |
ኃየሎም ይርጋ |
299) |
ኃይሉ ልዩነህ |
300) |
ፀጉ ዘነበ |
301) |
ፀጋዬ አበበ |
302) |
ፀጋዬ የኔሁን |
303) |
ፓስተር በለጠ ተስፋይ |
ይህ እንግዲህ በግልጽ መረጃ የተገኘላቸው ናቸው። በአጠቃላይ ከ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ጀምሮ በሰሜን ጎንደር የትግሬ-ወያኔ በጅምላ የጨፈጨፋቸው ዐማራዎች ቁጥር ከ፳(ሃያ) ሺህ የማያንስ እንደሆነ የአካባቢው ተወላጆች ይመሠክራሉ። ከዚህ በተጨማሪም በሰሜን ጎንደር አካልነት ከሚታወቁት የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የሠቲት እና አጎራባች ወረዳዎች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማራዎች ከአፅመ-ርስታቸው ተፈናቅለው በገዛ አገራቸው ስደተኞች ሆነዋል፣ አካባቢውም በሠፋሪ ትግሬዎች ተወርሯል።
በአሁኑ ወቅት የእነዚህ በግፍ በትግሬ-ወያኔዎች ደማቸው የፈሰሰው ወገኖቻችን ደም ይጣራል፣ በገዛ አገራቸው ሥደተኛ የሆኑት ወገኖቻችንም የድረሱልን ጥሪያቸውን ያሰማሉ። ዐማራው ዘሩ እየጠፋ ነው። ይህ ሁሉ ሲፈፀም እጅን አጣምሮ በመቀመጥ የሚመጣ መፍትሔም የለም። ስለሆነም ችግሩ መኖሩን አምኖ ተቀብሎ ወገብን ጠበቅ አድርጎ ለኅልውና መታገል ይገባል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
የዐማራው ደም የውሻ ደም ሆኖ አይቀርም!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!
gebeyehu says
the information is better if it include the source for the whole information.No one knows this info. include other things behind.
ahmed says
this history new for me i have no idea when it happened or not happened so all ethiopians are my family & if you ethiopian like zat as i understod you meant you declaring civil war you are saying let to kill each other like a terrorist im disagree wz ur idea
Tsegaye Sisay says
This is totally a crap. Yes there are people who will benefit from this. A garbage story added on some truthful facts to fuel up and fire a hate and killing between us. Ethiopians always watch such kind of stupid craps. Try and fight the other way, but do not bring it to a machete kind of philosophy like Rwanda.
Raichard says
i need a source to believe
Selam says
First, you need to differentiate the TIGRAI people and TPLF. Second, let the “Program” you post is TPLF’s , if they hate AMHARA and wanted independent TIGRAI,why they wrote it in AMHARIC? Third, among the names you mentioned here there are people whose full names are TIGRIGNA. And finally, why now after all these years?! The intention of the article seems creating hate,mistrust and revenge among the people for some political purposes.
Aychew says
Yes it is the principlr of tplf & ertreas to desyroy the identity of the smhara peaple because it is the only nation that has proud of ethiopia and has resourcres for the benefit to tigray as eell as has been powerful in the ethiopian era. wayane never afrade you. where have you been to defend your self at thay time? we gevern you long and long years only this nation id our enemy, to live long this nation musy be destroy and we do
Ibsaa sabaa says
Betam yasazenal……woynne tigra they are genociding our poeple but we are still sleeping those who are residing in Diasporas we should support our people togethers …..Death to wyanne tigra …Death to meles koshasha
Lisane Hizb says
ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል የምርጫ ታዛቢ ሊሆኑ የነበሩት ለስደት ተዳረጉ።
ከወ/ሮ መንበረ ተክለማርያም ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ—ክፍል ፩
ከልሳነ ህዝብ
ወ/ሮ መንበረ ተክለማርያም ይባላሉ። ተወልደው ያደጉት በአዲስ አበባ ከተማ ነው። ባለትዳርና የሶስት ሴት ልጆች እናት ናቸው። ሰማያዊ ፓርቲ ከምስረታው ጀምሮ በአባልነት ያገለገሉና በማንኛውም ሁኔታ እውነትን ለመናገር የማይፈሩት ጠንካራ ተቃዋሚ ሰሞኑን ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ወደ ካናዳ በመጓዝ የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ስንሰማ ካለንበት በስልክ ቃለ ምልልስ እንዲሰጡን ጠየቅናቸው።
ወይዘሮ መንበረ ካለምንም ማቅማማት ከኛ ጋር ቃለ ምልልስ ለማድረግ ፈቃደኛ በመሆናቸው በዝግጅት ክፍላችንና በመፅሄታችን አንባበዎች ስም ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርብላቸዋለን።
ል/ህ፡ ወ/ሮ መንበረ ከተለመደው አጠያየቅ ወጣ ባለ መልኩ ጥያቄ ላቀርብልዎት ነው የፈለግኩት ምን አስተያየት አለዎት?
ወ/ሮ መንበረ፡ እኔ ምን ቸገረኝ? ጠያቂው አንተተ ነህ፡ መላሿ ደግሞ እኔ። የማውቀው ነገር ከጠየቅከኝ እመልስልሃለሁ፡ ከከበደኝ ደግሞ ይለፈኝ እልሃለሁ።
ል/ህ፡ መልካም። እርስዎ እራስዎትን አንዴት ነው የሚገልፁት? ማለትም ከፖለቲካ ህይወትዎ ጋር በተያያዘ መልኩ እራስዎትን ሲገልፁት እንዴት ያስቀምጡታል?
ወ/ሮ መንበረ፡ በመጀመሪያ እራሴን እንደ ፖለቲከኛ አይቼም አስቤም አላውቅም። መጀመሪያ የፍትህና የዲሞክራሲ መጓደል በሽታ ለዘመናት በተጠናወታት አገር ሰለተፈጠርኩ ለህዝብ የሚገባ መብት መነፈግ የለበትም ብዬ እምርሬ መታገል በመጀመሬ እንደ ፖለቲከኛ ታየሁ እንጂ እኔ እራሴ የፖለቲካ ሰው ለመሆን ብዬ የተራመድኩት አንድ እርምጃም የለም።
ል/ህ፡ ዞሮ ዞሮ ግን እርስዎ በመንግስት ላይ በቀጥታና በግልፅ ትችት በመሰንዘር አዲስ አበባ ከተማ በወረዳዎ ታዋቂ ነዎትና ፖለቲከኛ ሆኑ ማለት አይደለም እንዴ?
ወ/ሮ መንበረ፡ እንተ እንደፈለግክ ግለፀው፡ እኔ ግን ሁሉም ሰው የሌላውን ሰው መብት እስካልነካ ድረስ የመሰለውን ሃሳብ ካለምንም ፍርሃትና መሸማቀቅ መግለፅ የእግዚአብሄር ስጦታ የሆነ መብቱ ነው። ፍትህን የማግኘት የተፈጥሮ መብት በሰዎች አማካኝነት መከልከል የለበትም በማለት ይህንን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም ማድረግ ያለብኝ ከዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር በመወገን ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ስለነበረ ነው ሰማያዊ ፓርቲን ከመጀመሪያው ጀምሬ የተቀላቀልኩት።
ል/ህ፡ ከሰማያዊ ፓርቲ በፊት ለምን በሌላ ፖለቲካ ፓርቲ አልታቀፉም ነበር?
ወ/ሮ መንበረ፡ መጀመሪያ ወያኔ የሚባለው መንግስት የተሳሳተ የጎሳ ፖለቲካ ይዞ ሲመጣ በየስብሰባው ልክ እንዳልሆነ ተነስቼ ህዝብ ፊት እናገር ነበር። በሁዋላ በርካታ ሰዎች ሰለባ እየሆኑ ሲመጡ በወያኔ ጠሪነት በሚከናወኑ የህዝብ ስብሰባዎች መገኘቴን ቀነስኩ። በህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል ግን ከቀን ወደ ቀን እየከፋ ሄደ። ቀደም ባሉት ጊዜያት ቀርቦ ስለ ሰላማዊ ትግል ያወያየኝ ሰው አልነበረም፡ ምናልባትም እስካሁን አባል ሳትሆን አትቀርም ከሚል አመለካከትም ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ።
ል/ህ፡ ስለፖለቲካው ወደኋላ እናቆየውና እርስዎ የቤተሰብ ሃላፊና የሶስት ሴቶች ልጆች እናት ሆነው ጎን ለጎንም ደግሞ የንግድ ስራ ያከናውናሉ፡ እንደሚወራው ከብዙ አባላት በተለየመልኩም አንዳንድ ሃይማኖተኞች ቤት ለቤት እየዞሩ እምነታቸውን እንደሚሰብኩት ስለ ሰማያዊ ፓርቲ ለሰዎች ይመሰክሩ ነበር ይባላል። እነዚህን ተግባራት ለማከናወን ደግሞ ጊዜ ያስፈልጋል። ወ/ሮ መንበረ 25 ሰዓት ያለው ቀን ነው ያላቸው የሚለው የሚያውቋቸው ሰዎች ትችትን እንዴት ነው የሚያዩት?
ወ/ሮ መንበረ፡ ያን ያክል ባይጋነንም time management ላይ ጥሩ ተሰጥኦ ሳይኖረኝ አይቀርም። ምናልባት በርካታ ስራዎች በአንድ ቀን ስለማከናውንና አንዳንዴም ስለሚሳካልኝ ይሆናል። ለዛሬ ያሰብኩት ዛሬውኑ ለማከናወን እጥራለሁ። ምክንያቱም ነገ የራሱ የሆነ ሌላ task ይዞ ነው የሚመጣው። እነዛ የተባሉት ሃላፊነቶች እርግጥ ነው በተቻለኝ አቅም አጣጥሜ ለማከናወን እሞክራለሁ። ብዙ ሰው አንድ ከበድ ያለ ስራ ካከናወነ ቀኑን በሙሉ ሊያሰራው የሚችለውን energy አልቋል ብሎ ያምንና ለዛሬ ያከናወንኩት ብዙ ነው ብሎ ለሌላ ቀን ቀጠሮ ይይዛል፡፡ እንደዚያ ማድረግ በራሱ የሰው አስተሳሰብ የወለደው ድክመት ነው። እኔ እንግዲህ በጣም የተለየና ብርቅ የሆነ ችሎታ ባይኖረኝም እንደነገርኩህ ጊዜዬን በደንብ ነው የምጠቀምበት።
ል/ህ፡ ከአሜሪካ ጉዞዎ መልስ አዲስ አበባ ላይ ታስረው እንደነበር ሰማን፡ ይህ የሆነው ለምንድነው?
ወ/ሮ መንበረ፡ እንዲህ ዓይነቱ ነገር እንኳ በግላችን ብናወራው ነበር መልካም፡ ንገሪኝ ካልክ ግን ያው መንግስት ማንንም ስለማያምን በራሴ ማለትም በቤተሰብ ጉዳይ ሄጄ ስመለስ በአሜሪካ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመገናኘትና ለሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው የሄድሽው በማለት ነበር ችግር የፈጠሩብኝ።
ል/ህ፡ ስለ መታሰርዎ ህዝብ ቢያውቀው ምን ገዳት አለው?
ወ/ሮ መንበረ፡ አየህ የኔ መታሰር በአገራችን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ሲታይ በጣም የሚያስደነግጥና የሚያስገርም ክስተት ስላልሆነ ነው። በርካታ ሺዎች ኢትዮጵያውያን አሁን በዚች ደቂቃም ጭምር በየእስር ቤቱ በሚሰቃዩበት ሰዓት ስለራሴ ባወራ ግብዝ የሆንኩ ስለሚመስለኝ እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም። ስለራሴ ሳወራ መናገር ለማይችሉት ፍትህ ፈላጊ ወገኖቼ ሳልናገር እንዳልቀር እንጂ ስለራሴ ለመናገር ካለመፈለግ አይደለም። እናንተ እንግዲህ ልሳነ ህዝብ ነን የምንባለው ብለኸኝ የለ ስለሳራችሁ ሳይሆን ስለሌሎች ነው የምትናገሩት። እኔም የመናገር መብት ለተነፈጉት ወገኖቼ ብናገር ነው በጣም ደስ የሚለኝ።
ል/ህ፡ ገባኝ። አሁን በካናዳ የፖለቲካ ጥገኝነትቶ ጥያቄ እንዳቀረቡ ነው የሰማሁትና ወደፊትስ በምን ዓይነት መንገድ ነው የጀመሩትን ሰላማዊ ትግል ማስቀጠል የሚፈልጉት?
ወ/ሮ መንበረ፡ እኔ አሁን ባለሁበት የሰለጠነ ማህበረሰብ ስለወገኖቼ በደልና ጥቃት ከመናገርና ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን
ከሚያካሄዱት ሰላማዊ ትግል በመቀላቀል በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ዓለም አቀፍ ጫና የሚካሄድበትን መላ አፈላልጋለሁ። እዚሁ ከመጣሁ ጀምሮ እንኳ ላገኘሁዋቸው ኢትዮጵያውያና ካናዳውያን ስለሃገሬ ተጨባጭ ሁኔታ በመንገር ድጋፍ እንዲሰጡ ስነግራቸው ነው የሰነበትኩት። አቅሜ ሲፈቅድ ደግሞ ከዚያ በላይ ለማድረግ ሃሳብ አለኝ።
ል/ህ፡ በወረዳዎ ለምርጫ ተወዳዳሪነት ሃሳብ ቀርቦልዎት እምቢ ማለትዎ ስሰማ በጣም ነበር የተገረምኩት። ለምንድነው ለመመረጥ ፈቃደኛ ያልሆኑት?
ወ/ሮ መንበረ፡ እኔ በወረዳዬ እንድወዳደር የመጀመሪያው criteria ሆኖ የቀረበው ፖለቲካዊ ብቃቴ ሳይሆን በምኖርበት አከባቢ በህዝብ ዘንዳ ያለኝ ተቀባይነት ብቻ ግምት ውስጥ ያስገባ አካሄድ ነበር። ያ አደገኛና ለምወክለውም ሆነ ለራሴ ጠቀሜታ የሌለው አስተሳሰብ ስለነበር ነው እኔ አልመጥንም በማለት ዕጩ የመሆን ጥያቄውን ያልተቀበልኩት። እራሴን ለማታለል ካልሆነ በስተቀር እኔ ጥልቀት ያለው የፖለቲካ ዕውቀትና በህዝብ ፊት የተቀነባበረ ንግግር የማድረግ ችሎታ የለኝም። አቅምህን ማወቅ በራሱ እኮ ትልቅ ነገር ነው።
ል/ህ፡ ብዙ ሰው ፓርላማ መግባት እንደ ሹመት ስለሚያየው ደስተኛ ሆኖ ነው ዕጩነቱን የሚቀበለው፡ እንደውም አንዳንድ ቦታ ላይ እኔን ይገባኛል በማለት ሌላ ሰው ሲታጭ የሚያኮርፉ ሰዎችም አሉ። የርስዎ ስሳኔ ደግሞ ከዚሁ ከተለመደው አካሄድ የተለየ ነውና እንዴት ይገልፁታል?
ወ/ሮ መንበረ፡ አኔ እራሴን ነው የማስበው፡፡ ምናልባት ፖለቲካዊ ብቃቱ እንዲሁም የስነ ልቦና ዝግጅቱ ቢኖረኝ ኖሮ እኔም ይገባኛል የማልልበት ምክንያት አይታየኝም። እኔ የራሴን ጥንካሬዎችና ድክመቶችን በደንብ ነው የማውቃቸው። በዚሁም መሰረት የማይመጥነኝ ክብደት ልሸከም በማለት እራሴን መጉዳት አልፈልግም። ባገራችን የዲሞክራሲ ባህል ባይኖርም ባደጉት አገሮች የሚደረጉ የፖለቲካ ስልጣን ውድድሮችን አልፎ አልፎ በቴሌቪዥን አያለሁ። እነዛ አገሮች የደረሱበት ደረጃ ላይ ስላልደረስን መወዳደር ማለት አብዛውን ጊዜ በአደገኛ ፍፃሜ ላይ የተመሰረቱም ስለሆኑ እንዲሁ ጥልቅ የሚባልበት አይሆንም።
ል/ህ፡ ወደ አገራቸችን ኢኮኖሚ ልውሰድዎትና፡ የኢትዮጵያ መንግስት ያገሪቱ ኢኮኖሚ በያመቱ በሁለት ዲጂት እያደገ ነው፡ በማለት ሲለፍፍ ይሰማል። እርስዎ ይህንን አባባል እንዴት ያዩታል?
ወ/ሮ መንበረ፡ በመሰረቱ እኔ አካውንቲንግ እንጂ ኢኮኖሚክስ ሰላላጠናሁ ስለ ኢኮኖሚ ማደግም ሆነ አለማደግ የአሃዝ መረጃ በማቅረብ ላስረዳ አልችልም። እንደዛ ባደርግም አላስፈላጊ ድፍረት ስለሆነ። እኔ ጥያቄህን መመለስ የምችለው እንደ ሁሉም ተራ ዜጋ common sense ላይ ተመስርቼ ነው። በህገ ልቦና የተገነዘብኩት ነገር በአጭሩ ልንገርህ። ባገራችን በርካታ ኮንስትራክሽኖች ሲከናወኑና በጣም ጥቂት ሰዎች ከምንም በመነሳት በእጭር ጊዜ ውስጥ ባልታወቀ ምከንያት ሚሊዬነር ሲሆኑ ማየት የተለመደ ነው። ሰፊው ህዝብ ብለን የምንጠራው በሚሊዮኖች የሚቆጠረው ህዝብ ግን እጅግ በከፋ ድህነት ሲሰቃይና ድህነቱ ከጊዜ ወደ
ጊዜ እየከፋ ሲሄድ እንዲሁም በችጋር ምክንያት ብዙ ቤተሰቦች ሲበተኑ ታያለህ። የኑሮ ውድነቱ እጅግ አሰቃቂ ነው ቢባል ማጋነን አይደለም። እጅግ ሃብታሞችና በሚዘገንን ድህነት ወስጥ የሚኖሩ ዜጎች በአንድ ባንዴራ ስር መፈጠራቸው ኢኮኖሚ የማደግ ምልክት ከሆነ ፍርዱ ለአንባቢያን እተወዋለሁ። ከጥቂቱ እድለኞች በስተቀር ሁሉም ዜጎች ማለት ትችላለህ እያንዳንዷን ቀን በሰቀቀንና በፍርሃት የሚኖሩበት የኢኮኖሚ መዋቅር መዘርጋት የኢኮኖሚ ማደግ ነው ለማለት ያስቸግራል። ያገሪቱ ወጣት ባብዛኛው በስራ አጥነትና በአደንዛዥ ዕፅ የዘፈቀ ኢኮኖሚ የመልካም ኢኮኖሚ መገለጫ ነው ማለት እርስ በርሱ የሚጣረስ አስተሳሰብ ለማስታረቅ መሞከር ነው። ከዚህ ሌላ ምንም ያልነበረው ካዝና ውስጥ መቶ ብርም ከታየ ቁጥሩ ለውጥ ነውና በዚህ ዓይነት ስሌት ከሆነ ምናልባት መንግስት የራሱን ሰዎች ደስ ለማሰኘት ያዘጋጀው መላ ሊሆን ይችላል።
ል/ህ፡ ለህዝቡ ኑሮ አለመሻሻል ተጠያቂው ማን ነው ብለው ያምናሉ?
ወ/ሮ መንበረ፡ አሁንሞ እንደ ባለሙያ ሳይሆን እንደዜግነቴ የሚሰማኝን እነግርሃለሁ። መጀመሪያ አንዲት ሃገር እንድታድግ መልካም አስተዳደር ያስፈልጋታል። ለህዝብ የሚጠራ መንግስትና ህዘቡ የሚቆጣጠረውና የሚያርመው ቢሮክራሲ ሳይኖር እንዴት አድርጎ ነው የኢኮኖሚ ዕድገትና የኑሮ መሻሻል የሚመጣው? በዚህ ላይ ሙስናው ጣራ የነካ ነው። ማንም ሰው ወደ መንግስት መስሪያ ቤት ሄዶ ካለጉቦና መጉላላት መብቱ የሆነውን ነገር ማስፈፀም አይቸልም። ቀደም ሲል እንደነገርኩህ በጣም በአጭር ጊዜ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር እየተመሳጠሩ ሚሊዬነር የሚሆኑ ሰዎች ከየት አመጣችሁት? ይሄ ሁሉ ሃብት ታክስ ከፍላችሁ ካገኛችሁት ገቢ የተገኘ ነው? ብሎ የሚጠይቃቸው አካል የለም። በአንፃሩ ደግሞ በጣም አነስተኛ ቢዝነስ ያላቸው ሰዎች ሊከፍሉም ሆነ ሊያስቡት የማይችሉትን ግብር በማምጣት ከስራ ውጭ ይሆናሉ፡ አቤት የሚሉበት ቦታም የለም። መንግስት የህዝብ አስተዳደር ስራን ትቶ አእራሱ በፓርቲዎቹ በኩል የሸቀጣሸቀጥ ንግድ ውስጥ በገባበት ኢኮኖሚ ፍትሃዊ ወድድር የለም። ፍትሃዊ ውድደር በሌለበት ሲስተም ደግሞ ኢኮኖሚ ሊያድግ አይችልም።
ል/ህ፡ በርስዎ ግምት አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከስልጣኑ በቀላሉ ይለቃል ብለው ያምናሉ?
ወ/ሮ መንበረ፡ ካለኝ ልምድ የማምንበት አንድ ጉዳይ ካለ ከእግዚአብሄር መንግስት በስተቀር የማይወድቅ መንግስትና ስርወ መንግስት በዚህ ምድር ላይ ታይቶ አይታወቅም። ይህ መንግስት ከአፄ ሃይለስላሴ ወይም ከደርግ የበለጠ ተቀባይነትና ድጋፍ የለውም። እነርሱ እንኳ ወድቀዋል። የሚወድቁ የማይመስሉህ እንደ ሳዳም ሁሴን፣ ጋዳፊና ሙባረክ ያሉት መንግስታትና መሪዎች እንኳ ቀናቸው ሲደርስ ወድቀዋል። ይህ የጊዜ ጉዳይ ነው። ጊዜ የማያሳየን ተዓምር የለም።
ል/ህ፡ ውድ አንባቢያን ቀሪውን ቃለ ምልልስ በክፍል ፪ ዝግጅታችን ይዘን እንቀርባለን። ቸር እንሰንብት።