ማንን እንመን ?
ኢህአዴግ ሶማሌ፣ ትህዴን “ኢትዮጵያዊያን ናቸው” ይላል
በቦሌ ክፍለ ከተማ በቤት ውስጥ ፈነዳ በተባለው ፈንጂ ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸው ሁለት የሶማሌ ዜጎች እንዳልሆኑ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ አስታወቀ። በፈንጂው የሞቱት ሁለት ሰዎች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ስማቸውም “ምክትል ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባሉ የፖሊስ አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባሉ ሲቪል ናቸው” ሲል የገለጸው ትህዴን የሟቾቹ ስም በመታወቂያ መረጋገጡን አመልክቷል። የመታወቂያውን ቅጂ ግን በገጹ አላተመም። ከአደጋው ጋር በተያያዘ በስፍራው ታይታችሁዋል በሚል በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን ያመለከተው ዜና የሶስት ሰዎችን ስም ይፋ ያደረገው ኦክቶበር 19 ቀን 2013 ነው።
በሌላ በኩል ኦክቶበር 16 ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ማዞሪያና ቦሌ ሚካኤል መግቢያ አካባቢ በቦምብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈው ሁለት ሶማሊያውያን ሽብርተኞች መሆናቸውን ማረጋገጡን፣ የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡
የአንድ ግለሰብ ሰርቪስ ቤት ተከራይተው ከነበሩት ሶማሊያውያኑ መካከል፣ አንደኛው ከ20 ቀናት በላይ የቆየ ሲሆን፣ ሌላኛው ፍንዳታው ከመድረሱ ከሁለት ሰዓታት በፊት የደረሰ መሆኑን ግብረ ኃይሉ ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡ ሽብርተኛ የተባሉት ሶማሊያውያኑ ካፈነዱት ቦምብ በተጨማሪ መጠናቸው ያልተገለጸ ቦምቦችና አንድ ሽጉጥ ከሁለት ካርታ ጥይት ጋር መገኘቱን፣ የፈንጂ ማቀጣጠያና የአደጋ መከላከያ ጃኬቶች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሊያና ቀበቶዎች መገኘታቸውም ተገልጿል፡፡ከሶማሊያውያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎችና የቤቱ አከራይ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄባቸው መሆኑንም ግብረ ኃይሉ አክሏል በማለት ዘግቧል። አዲስ አድማስ በበኩሉ ከዚህ በታች ያለውን ዜና አስነብቧል
የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጐቹ ራሳቸውን ከጥቃት እንዲከላከሉ አስጠነቀቀ
ባለፈው እሁድ በቦሌ ሚካኤል አካባቢ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ሁለት ተጨማሪ የፍንዳታ ጥቃት ለማድረስ አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ቡድን እንደዛተ የገለፀው የአሜሪካ ኤምባሲ፤ የዛቻው ተአማኒነት ባይረጋገጥም በኢትዮጵያ የሚገኙ አሜሪካዊያን ጥንቃቄ እንዳይለያቸው አሳሰበ፡፡
የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ቡድኖች ግጥሚያ በሚካሄድበት ሰዓት ጥቃት ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ሁለት ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት በማወጅና ሽብር ለመፈፀም በመዛት የሚታወቀው አልሸባብ “ድርጊቱ በኔ አባላት የተፈፀመ ነው” ብሏል፡፡
አልሸባብ በቦሌ ሚካኤል ለተከሰተው ፍንዳታ ሃላፊነት እንደሚወስድ በትዊተር እንዳስታወቀ ኤምባሲው ጠቅሶ ባሰራጨው ማሳሰቢያ፤ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አካባቢ የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እንደዛተም ገልጿል፡፡
በቦሌ ሚካኤል በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተከሰተው ፍንዳታ ሁለት የሶማሊያ ተወላጆች መሞታቸውን የገለፀው ፖሊስ፤ ከሟቾቹ አንዱ የኢትዮጵያ ማሊያ በመልበስ ከኳስ ተመልካቾች መሃል የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደነበር ጠቁሟል፡፡
ለጥቃት የታሰበው ፈንጂ እዚያው ፈንድቶ ሁለቱ አሸባሪዎች መሞታቸውን ፖሊስ ተናግሯል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፤ የፍንዳታው ፈፃሚዎች አልሸባብ መሆናቸውን ተጠይቀው ገና አልተረጋገጠም ብለዋል፡፡ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ጉዳዩን እየመረመረ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ሽመልስ፣ ግብረ ሃይሉ የደረሰበት ውጤት ጊዜውን ጠብቆ ይፋ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡
40/60 ቤት ክፍያ ያጠናቀቁ የህብረት ስራ ማህበር ሊሆኑ ነው
የቤት ባለቤት ለመሆን ሙሉ ክፍያ ያጠናቀቁ የ40/60 ተመዝጋቢዎች በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር ወደ ተነደፈው ፕሮግራም እንዲዛወሩ የአዲስ አበባ አስተዳደር ማግባባት ጀመረ፡፡ በ40/60 ፕሮግራም የተመዘገቡ የተሻለ ገቢ ካላቸው ነዋሪዎች መካከል ክፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሚጠበቅባቸውን ሒሳብ መቶ በመቶ መክፈላቸው ይታወቃል፡፡ ይህንን ያጤነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እነዚህን መቶ በመቶ የከፈሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማግባባት ወደ መኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፕሮግራም እንዲዛወሩ ለማድረግ ጥረት መጀመሩን ሪፖርተር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሥር የሚገኘው የኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጃ ጽሕፈት ቤት ምንጮች ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።
በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም 81,257 ነዋሪዎች መመዝገባቸውና በሦስቱም የመኖርያ ቤቶች (10/90 እና 20/80) ፕሮግራሞች የተመዘገቡ ነዋሪዎች 2.5 ቢሊዮን ብር መቆጠባቸው ይታወቃል፡፡ የእነዚህን ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር መንግሥት ተጨማሪ 7.5 ቢሊዮን ብር እንደመደበ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሐሙስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጸዋል::
አንደበት
“በኤርትራ ጉዳይ፣ በሻዕቢያ አላማዎችና አሰራሮች፣ እንዲሁም ኢሳያስን በተመለከተ ያለኝ በጣም ግልጽ ነው። ከነሙሉ ችግራችን ኤርትራ በትክክለኛው ሃዲድ ላይ እየተጓዘች ነው ብዬ አምናለሁ። የሚታረሙ ነገሮች ካሉ ዋናው ጉዞአችን ሳይነካ እየተስተካከለ ሊሄድ ይችላል ብዬ አምናለሁ። የምጽፈውም ሆነ የምሠራው ይህን መሠረት ያደረገ ነው።” …
“አሻግሬ ስመለከት በርቀት ሰማያዊ ተራሮች ይታየኛል። ከተራሮቹ ስር ያለው ለጥ ያለ የእርሻ ሜዳ የአባቴ አገር ነው።” …
“ይህን ታሪክ እጽፈዋለሁ: 3 ተከታታይ መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል። ባህረነጋስያን በመጀመር የኤርትራን ታሪክ እጽፈዋለሁ። የሻቢያን የትግል ታሪክ እጽፈዋለሁ። ይህም ኢትዮጵያዊያን ስለኤርትራ ተገቢውን ሃቅ እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። በዚህ መጽሐፍ ጠላት አፈራለሁ። ቢሆንም ግን እጽፈዋለሁ። ስለዚህ ከአሁኑ ፍንጭ መስጠቱ ጠቃሚ ነው። በተቃውሞ የምጽፍ የሚመስላቸው ስለሚኖሩ እስከዚያው ድረስ ይዝናኑበት። ኤርትራ ለመመለሴ ምክንያት ይሰጥልኛል።”
በኦጋዴን የነዳጅ ጉድጉድ ቁፋሮ ተጀመረ
ኒው ኤጅ የተሰኘው የእንግሊዝ ኩባንያ በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኦጋዴን ቤዚን፣ ኤልኩራን በተባለ ሥፍራ የነዳጅ ጉድጓድ ቁፋሮ ጀመረ፡፡ ኒው ኤጅ በኦጋዴን ብሎክ ሰባት፣ ስምንትና አዲጋላ በተባለ ድሬዳዋ አቅራቢያ በሚገኙ የነዳጅ ፍለጋ ቦታዎች አፍሪካ ኦይል ከተሰኘ የካናዳ ኩባንያ ጋር በነዳጅ ፍለጋ ሥራ የተሰማራ ኩባንያ ነው፡፡
ኩባንያው ኤልኩራን በተባለ በሶማሊያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ አካባቢ የነዳጅ ጉድጓድ ቁፋሮ ጀምሯል፡፡
ታማኝ የዜና ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኩባንያው የመቆፈሪያ ማሽኑን ተክሎ የቁፋሮ ሥራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ሳለ የቁፋሮ ባለሙያዎች በማሽኑ ላይ የቴክኒክ ችግር በማግኘታቸው የቁፋሮ ሥራውን ሳይጀምሩ አዘግይተውታል፡፡ ባለሙያዎቹ በማሽኑ ላይ ያገኙትን የቴክኒክ ችግር አስወግደው የቁፋሮ ሥራውን ባለፈው ሳምንት መጀመራቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የሚቆፈረው ጉድጓዱ ጥልቀት 2,800 ሜትር እንደሆነና የቁፋሮውን ሥራ ለማጠናቀቅ ሦስት ወራት ያህል እንደሚፈጅ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከሦስት ወራት በኋላ በጉድጓዱ ውስጥ ነዳጅ መኖርና አለመኖሩን የሚጠቁም የሙከራ ሥራ እንደሚሠራ ታውቋል፡፡
አፍሪካ ኦይል በቅርቡ በድረ ገጹ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ከኒው ኤጅ ጋር በመተባበር በኦጋዴን ላይ አተኩሮ እንደሚሠራ ገልጿል፡፡
አፍሪካ ኦይል በኤልኩራን የነዳጅ ክምችት እ.ኤ.አ. በ1970ዎቹ መገኘቱን ጠቅሶ፣ አሁን በሚቆፈረው ጉድጓድ በአካባቢው የሚገኘውን የነዳጅ ክምችት መጠን ለማወቅ እንደሚቻል አስታውቋል፡፡
‹‹በኤልኩራን ነዳጅ መኖሩ ይታወቃል፡፡ አሁን ዋናው ሥራ የሚሆነው በሚቆፈረው ጉድጉድ ውስጥ የነዳጅ ፍሰት እንዲከሰት በማድረግ በአካባቢው የሚገኘውን የነዳጅ ክምችት መጠን ማወቅ ነው፤›› ምንጮች ተናግረዋል።
ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፔትሮሊየም ባለሙያዎች በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ቴኔኮ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ በኤልኩራን በቆፈረው የመጀመሪያ የነዳጅ ፍለጋ ጉድጓድ የተፈጥሮ ዘይት ፍሰት ማግኘቱን አስታውሰው፣ በወቅቱ ኩባንያው ክምችቱ በቂ አይደለም በሚል ትቶት ሄዷል ብለዋል፡፡ አክለውም አሁን ባለው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው አፍሪካ ኦይልና ኒው ኤጅ በኤልኩራን ከፍተኛ መጠን ያለው የነዳጅ ክምችት ሊያገኙ እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ ዜናው የሪፖርተር ነው።
በናይጀሪያ ድጋፍ ሰበብ አፈ-ጉባኤና ወታደሮች ሞቱ
በኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ የእግር ኳስ ጨዋታ በጋምቤላ ክልል ኚኝኛግ ወረዳ በደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የወረዳው አፈጉባኤ እና ወታደሮች እንደሞቱ ምንጮቼ ነገሩኝ ሲል አዲስ አድማስ ጋዜጣ በቅዳሜ እትሙ አስታውቋል። ጋዜጣው የአደጋውን መጠንና የጉዳቱን ስፋት ለማረጋገጥ ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት በመጠቆም ባተመው ዜና ችግሩ የተከሰተው ጋምቤላ ክልል መሆኑን አመልክቷል።
የደቡብ ሱዳን አዋሳኝ በሆነችው የኚኝኛግ ወረዳ ባለፈው እሁድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከናይጄሪያ አቻው ጋር በአዲስ አበባ ስቴዲየም ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ባደረጉት ወቅት፣ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በማሸነፉ ደስታቸውን በጭፈራ በመግለጽ ላይ በነበሩ እና በድርጊቱ በተቆጡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ የኚኝኛግ ወረዳ አፈጉባኤና ከሁለት በላይ ወታደሮች እንደሞቱ ታውቋል።
ችግሩ እንደተፈጠረ ከፌደራልና ከክልል የተውጣጡ ባለስልጣናት ቦታው ድረስ በመሄድ የማረጋጋት ስራ መሥራታቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሁኔታው ለማየት ወደ ስፍራው የሄዱ ሲሆን ስለ ጉዳዩ ፕሬዝዳንቱን በስልክ ለመጠየቅ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡
መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በጨንጫ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤት መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን ተከትሎ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ኢሳት ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ ም ባሰራጨው ዜና አመለከተ።
የጨንጫ ፣ ጭነቶ፣ ጦሎላ፣ ጨፌ፣ ጺዳ እና ቱክሻ ትምህርት ቤቶች መምህራን በአድማ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ተማሪዎች ቤታቸው ለመቀመጥ ተገደዋል። የወረዳው እና የዞን መምህራን ማህበር ከመምህራኑ ጋር በመሆን አድማውን እያስተባበሩ ሲሆን፣ አድማው ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች እና አካባቢዎች ሊዛመት እንደሚችል መምህራኑ ተናግረዋል።
መምህራን “ደሞዛችን በግድ መቆረጡ አንሶ፣ እኛ በጠየቅነው ቀርቶ ባልጠየቅነው ወር ለምን ይቆረጥብናል ” በማለት አድማውን እንደ ጀመሩ አንድ መምህር እንደገለጹለት ያመለከተው ኢሳት መምህራን የአንድ አመት ደሞዛቸውን ከተቆረጠ በሁዋላ፣ ከመስከረም ጀምሮ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር ማስቆረጥ ጀምረዋል ያለው ኢሳት የኢትዮጵያ መንግስት መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በፈቃዳቸው ከደሞዛቸው እንዳስቆረጡ በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱንም አስታውሷል።
ዓለምአቀፍ ጠበቆች የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ለፍርድ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመሩ
በወጣት አብዱላሂ ሁሴን አማካኝነት በኢትዮጵያ የኦጋዴን ክፍል የተፈጸመውን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፊልም የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በስዊድን ቁጥር አንድ ቴሌቪዥን በትናንትናው እለት መቅረቡን ተከትሎ አለማቀፉ ጠበቆች ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ኢሳት በጥቅምት 5 ቀን 2005 ዜናው አስታወቀ።
ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጸው ፊልሙ ከተላለፈ በሁዋላ ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን የሰጡት ሲሆን፣ ስቴላም የተባሉ የ አይ ሲ ጄ ጠበቃ ጉዳዩን ፍርድ ቤት እንደሚያቀርብ በሬዲዮ ይፋ አድርገዋል። የስዊድን የጦር ወንጀል ኮሚሽን ፍርድ ቤትም ማስረጃዎችን በመመርመር ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ከወጣት አብዲ ጋራ ቀጠሮ ይዟል። ጠበቆቹ ጄኔቫ ካለው አይሲጄ እና ከሌሎችም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንደሚሞክሩ ኢሳት አመልክቷል።
ቀደም ሲል ይፋ ከተደረገው በተጨማሪ አዳዲስ መረጃ የያዘው አዲሱ ፊልም “ልዩ ፖሊስ” እየተባለ በሚጠራው ሀይል የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ወንጀልና የክልሉን ፕሬዚዳንት የተቸች አንዲት ሴት በኦበነግ አባልነት ስትፈረጅ የሚያሳይ መረጃ ተካቶበታል ። የክልሉ ፖሊስ ሀላፊ በእስር ላይ የሚገኙትን ሴቶች በመድፈር ብዙ ህጻናት በእስር ቤት ውስጥ መወለዳቸውን በፖሊሶች በራሳቸው ሲነገር የሚያሳይ ፊልም መካተቱትን ወጣት አብዱላሂ ገልጿል። ፊልሙ ” የዲክታተሮች እስረኞች” የሚል ርእስ ተሰጥቶታል።
ጉዳዩን በማስመልከት የአለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ኮሚሽን በእንግሊዝኛ ኢንተርናሽናል ኮሚሽን ኦፍ ጁሪስትስ ኮሚሽነር የሆኑት ስቴላ ጋርደ ለኢሳት እንደገለጹት የወንጀሉን ፈጻሚዎች ወደ ፍርድ ለማቅርብ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የአለማቀፍ ወንጀል (ICC) ፈራሚ አገር ባለመሆኑዋ ማስረጃውን በቀጥታ ለፍርድ ቤቱ መላክ እንደማይቻል የገለጹት ኪሚሽነር ጋርደ፣ ይሁን እንጅ ሰቆቃን ለመከላከል የተቋቋመው ኮሚቴ (Committee Against Torture) ፈራሚ አገር በመሆኑ ጉዳዩን በዚሁ በኩል ለመከታተል እና የስዊድን ፖሊስ ምርመራ ጀምሮ እርምጃ ለመውሰድ እንዲችሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ከኢሳት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንደገና በአዋጅ ሊቋቋም ነው
በሀገሪቱ በኮምፒውተር የሚሰሩ ማንኛውም የመሰረተ ልማት ተቋማትና የመረጃ አገልግሎት የኔትወርክ አውታሮች ላይ ከውጪና ከሀገር ውስጥ የኮምፒውተር ቫይረስን ጨምሮ በተለያየ መንገዶች የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲቻል ታስቦ የተቋቋመው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንደገና በአዋጅ እንደሚቋቋም ኢሬቴድ ገለጸ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀነራል ተክለብርሀን ወ/ዓረጋይ ረቂቅ አዋጁ ህግ ሆኖ ሲፀድቅም የሀገሪቱን የመረጃ ደህንነት ከማስጠበቅ ባሻገር የመንግስትና የግል የልማት ድርጅቶች ከሳይበር ወይም ከኮምፒውተር ጥቃት በመከላከል የሀገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል ያስችላልም ማለታቸውን ዜናው አመልክቷል። ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም አዋጁ ኤጀንሲው የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነትን ቀድሞ በማወቅ እና በመከላከል እርምጃ እንዲወሰድ የመረጃ ማምረትና ተደራሽ የማድረግ ተግባራትን በአግባቡ እንዲወጣ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡
በተለይም ደግሞ አዋጁ ምስጢራዊ የሀገር ደህንነት መረጃዎችን እና የኢንዱስትሪዎችን ፣የባንኮችን ፣የቴሌኮሚኒኬሽን ፣የኤሌክትሪክ ሀይል ፣የመገናኛ ብዙሀንን ተቋማት እንዲሁም የግዙፍ ፕሮጀክቶች የኮምፒውተር ኔትወርክ አውታሮች ከሳይበር ጥቃት እንዲጠበቁ እንደሚያስችልም በውይይቱ ተብራርቷል፡፡ ድንበር የለሹ ይህ የኮምፒውተር ወንጀል አዲስ የሀገር ልዋላዊነት የጥቃት ምንጭ እንደሆነ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይህንንም ተግባር የሚፈጽሙ ግለሰቦች የሽብር ፣የፖለቲካ ፣የወንጀል ምክንያቶችን ጨምሮ የተለያዩ ዓላማዎች ይዘው የሚንቀሳቀሱ እንደሆኑ ኢሬቴድ አመልክቷል።
ኢንሳ ዜጎችን በማፈንና ኢህአዴግ ለስለላ የሚጠቀምበት ዋንኛ ማሽኑ እንደሆነ በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል።
በለው! says
ቲሪ. .ቲሪ ..ጡሩ ሩሩ ባባባ…”የሙስሊም ኦሮሞ ፈረስትና ጆሌ ቢሸፍቱ ትውልዲ ኤርትራ የጋራ መጋለጫ አወጡ” በለው!
“እንዳዋረዳችሁኝ፣ እንዳጋለጣችሁኝ፣ ኢትዮጵያን ይዤ ወደ መቃብር እሄዳለሁ!ከኢህአዴግ ጋር አብረን ልንሠራ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ጋር ተነስተናል መከላከያውንና ኢኮኖሚውን ልንረከብ ነው።
እያንገዋለለ!…የአባባ ተስፋዬ ልጆች ተንጫጩ ፣አባባ ተስፋዬም ተሰፋ አልቆርጥም አሉ; ታዋቂው ደራሲ፤ የተደረሰበት፤ የማይደረሰው ሲደረሰበት ምን ይላሉ? ?”ቸብ ቸብ አድርጉለት ይታይ እስክስታው መድረኩን ልቀቁ ይታይ…አለ። በቀጥታ ወደ ጭፈራው እናመራለን፡-
፩) አርዕስቱ ይስተካከል”ኢትዮጵያን ይዤያት ወደ መቃብር እሄዳለሁ!” የብሸፍቱ ሊቅ አቶ ተስፋዬ ገብረአብ የት ተናገረው እዚያው እቤቱ ደጃፍ ላይ…ማን አየው? ገና ሳይናገር አቶ ጌታቸው ረዳ ‘ኢትዮጵያ ሰማይ’ አዘጋጅ።
አቶ መለስ ዜናዊ ሰንደቁን ጨርቅ ነው ሲሉ ፮ ጫማ ወደታች ሳልገባ ሐሳቤን አለውጥም እንዳሉ ችሩ አምላክ ቃላቸውን ሰማቸው ፮ጫማ ወደታች በዚያችው አመለኛ ሰንደቅ ተጠቅልለው በብሔር ብሔረሰቦች ትብብር ባህላዊ ደማቅ አቀባባር በዘጠኙም ክልል !።ተስፍሽ “የዘሬን ብተው ይዘርዝረኝ አለ!እንዲህ እንዳዋረዳችሁኝ አፍርሻችሁ እሞታለሁ አለ ይመችህ አንደቃልህ ብለናል።ጭረሽ በኣማራና ኦሮሞ ክልል በ፪ባንዲራ በኢትዮጵያ፣በኤርትራና በሆላንድ ፫ሰንደቅም የመጠቅለል ዕደሉ ሰፊ ነው ።!
*ብቻውን አደለም ! “ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቼ ሚሊዮኖች አሉ።በተለያዩ ምክንያቶች አገር ቤት መግባት አይችሉም። ከጥቂት ጊዜያት በሁዋላ ግን እንደጎርፍ ነው ወደ አገራችን የምንገባው።ይህንን ነው ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው። እሰይ በይ ህወአት! አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ም/ል ፕሬዘዳንት ሊሆኑ ነው?።ቦንብ አፈንዱ ብሎ የላካቸው አቀጣጥለው እሳት ሲሞቁ ፈነዳባቸው አሁን በንዴት እራሱ ገብቶ ሊያፈነዳ ነው?።የልብ ስሜቴን መንጠቅ የሚችል አንድም ሰው የለም!ማንም ሊከለክለኝ አይችልም!። ማንም ሊሰጠኝ አይችልም!። ጌታዋን የታመነች ቀበሮ ሆላንድ ሆና ትጮሓለች።
፪)” / አበባ ይበተንለታል/ ለከለከሉኝ ክፍሎች ማን ነው ያ… ከልካይ በመሰረቱ?
“ማነው ተው የሚለኝ ማነው? አለ። በአቶ አብርሃ ደስታ ከመቐለ “ትንሽ ስለተስፋዬ” እንድናገር ተልኬ መጥቻለሁ ዘራፍ !በሚል ድጋፋቸው ላይ ምላሽ ስሰጣቸው ይህ ቃል ሠፍሯል” **”በጎ ምክር ለጓዶች” ለታጋዮች ለጓደኞቼ ሲልም ከውጭ የቃረማትን ሁሉ ለኢህአድጎች ይነፋላቸዋል!። “ደርዘን ጥያቄዎች ከተስፋዬ ገብረአብ ሲልም ዲያስፖራውንና ሌሎችንም አስተያየት ለቃቅሞ ለኢህአዴግ ጥንካሬ የሌላውን ድክመት በራሳቸው ድረ-ገፅ ጥናታዊ ስለላውን ይፅፋል፤ በፓል-ቶክ ያደንቁታል፣ ያጨበጭባሉ አባባ ይበትናሉ፣ ይሳለቅባቸዋል፣ ያስቅባቸዋል፣ ይስቅባቸዋልም፣ ቆይቶም ይበትናቸዋል። በለው!” ይህ ቃል እውነታው ሲያንገሸግሸው !ተቆጣቸው አስፈራራቸው አምጡት አለ”እሱ ማነው ?ይላል በአንድ ፅሁፌ ላይ እነዲህ አስነብቧል “በቅርቡ ግን አንድ ወሬ ሰምቻለሁ። ይላል ዲያስፖራውን የሚያስተዳድረው ተስፋዬ…
በብእር ስም ተሸሽገው የተሳሳተ መረጃ የሚፅፉና የሚሳደቡ ሰላቢ ብእረኞችን ላለማስተናገድ የድረገፅ ዋና አዘጋጆች በመነጋገር ላይ ናቸው። በቅርቡ ኢትዮሜዲያ በብእር ስም የፃፈ ሰላቢ ካስተናገደ በሁዋላ መልሶ ፅሁፉን አስወግዶታል። ይህ አንድ ትልቅ እርምጃ ነው።” ከዚህ በላይ ሰላይ አለን ተስፋዬ እራሱ ነው ያጋለጣቸው። አብረው ነው ሀገር የሚያደሙት የቁራ ጩኽት የአዞ ዕንባ የሚያነቡት።
፫) ያ… ሰው ምን አደረገ ለአገሪቱ?እኔ የቢሾፍቱ ልጅ ነኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ።
ተስፋዬ ሃይማኖት ስለሌለው በቃለመሐላ አይታመንም ግን እንደ አቶ መለስ ።አራት ነጥብ ። አባዛበት… የማይተማመን አብዮተኛ “በእየ ድረገጹ ይፎጋገራል” ማለት ነው። ““ተስፋዬ ስለ ፃፈው ጥሩ ወይ መጥፎ ነገር መነጋገር እንችላለን። የተስፋዬ ሁኔታ በማጋለጥ የተስፋዬን ፅሑፍና ሓሳብ ማጥቃት ግን አይቻልም!። እንዳውም ህፀፅ ነው (Ad hominem Circumstantial Fallacy) ” ብለው ካስፈራሩን ሌላ..ሌሎችም አሉ በሚል” **ግን እኮ ካለበት የተጋባበት አደለምን!በዚሁ ላይ የሚከተሉትንም አስፍሬ ነበር(ኢካድኤፍን)ይጎብኙ!
****”ይህንን በነካ እጅህ እያሉ ኦሮሞ ያልተናገረው ግን ኤርትራዊው የሚፅፍልን ሚስጥር እያሉ ከኋላ የሚቀውጡት እነጃዋር መሐመድ፣ የቢሸፍቱ ፈረስት እነ ጁነዲን ሳዶም ተዋናይ ነበሩን? ሌሎችስ አነማናቸው? ለመሆኑ አብርሃ ደስታ ከመቐለ ዳንኤል ገዛኸኝ ከጅጅጋ (ከአትላንታ)..ክፍሉ አሰፋ ለምን ይንጣጣሉ?በመፅሐፋቸው፣ ትችትና አጫጨር ፅሑፎች ላይ የተስፋዬን ሀሳቦች ተብራርተው ስለሚፃፉና እንደወረደ ልብወለዱን እንደእውንት ማስረጃ ስለሚደግሙትና ስለሚያጅቡት በአነስተኛና ጥቃቅን ውሸታሞች ማህበር የታቀፉ ‘የጋዜጠኖች አዟሪ ማህበር አቋቁመዋል ።(… ) *በተራ ቁጥር
፫) ይህ አጋጣሚ ‘አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ለራሱ ብሔር ከሚናገረውና ‘አንድ አማራ ለኦሮሞ ብሔረተኛ ከሚቆረቆረው በላይ ለኤርትራዊው ሰላይ እነደ ውጭ ዜጋ ለማሽቃበጥ ተመቸው!
፬) ኦሮሞዎች የሚቆረቆርላቸው አስመሳይ ኤርትራዊ ታሪክ ፀሀፊ በማግኘታቸው ፈንጥዘዋል!መጽሐፉን ተሻምተው ይገዛሉ!
source Awra Amba web site:Jaware Mohamed Defending
“…On one hand he attempts to justify receiving aid from Eritrea, on the other hand he accuses Oromos as fools for appreciating an Eritrean author who tells our story”….
Jawar Mohammed, Political Analyst and Oromo Activist
Responding to Judge Woldemichael Meshasha’s recent interview with Hiber radio. Judge Woldemichael said that Tesfaye Gebreab is deceiving our Oromo brothers with “falsehood sympathy”…. ለመሆኑ ኢትዮጵያዊነት በግድ የተጫነበት ኦሮሞ ፈረስት ፖለቲካ በታኝና ኤርትራዊው የብሸፍቱ ልጅ የኦሮሞ ማደጎ እንዴት ተቧደኑ? አሃ! አብረው ነው ሀገር የሚገቡት? ለመሆኑ ከህወአት አጃቢነት በኤርትራውያን አማራር የሙስሊም ኦሮሞ ፈረስት በቅርብ ቀን መንግስት ሊያቋቁሙ ወይንስ መንግስት ሊቆጣጠሩ? ጠርጥር በሽንብራውም ትል አለበት ! ሸዋ ተበላህ በለው!።ሊበቀልህ ነው!!
*ስለእራሳቸው ሙሉ ዜግነትና የፀፃፍ ችሎታ ያሽቃበቱት ተስፍሽ አፈታሪክና ቀልድ ቧልት(ጆክ)ከጠጅ ቤት ከጠላና አረቄ ቤት፤ ከድራፍት ቤት፤አንዳንድ የሠፈር ልጆች የሚሰጡት ማሽሟጠጥ፣ ፉገራ(ጥገራ)ለቅሶ ቤት ንፍሮ እየተቃመ ጫት እየተጋጠ፣ ካርታ እየቆመሩ ድንኳን ውስጥ ፍራሽ ዘርግቶ አርባ ቀን ድረስ የሚነፋ ቱልቱላ ተስፋዬ ተክኖበታል። ጫልቱ ሄለን ሆነች አቤት በአፍ መቆላት ለመሆኑ ዛሬ በእየወሩ ፲ሺህ ወደ ኣረብ ሀገር የሚሔዱት አብዛኛው የኦሮሞ ሴት ልጆች…ሊሊ፣ሔለን፣ ቡቡ ፣ጫልቱ፣ ቡርቃ፣እየተባሉ ነው ወይንስ ፋጡማ፣ ከድቻ፣ አሚና፣ሃዋ፤ እየተባሉ በግድ እየሰለሙ ነው። የሚሸጣቸው ሻቢያ ለመሆኑ አቶ ስብሃት ነጋን ጠይቅ !!ኦሮሞ ፈረስት ፓርቲ አጋርህን አማክር !አተላ ለትውልድ ስደት፣ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ሽብርና እልቂት ተጠያቂ ናችሁ።
የተስፋዬ ገብረአብን በኦሮሞ ላይ ማላገጥ ካነበቡት ቤልጂግ አሊ…”እስኪጣራስ” በሚል ከፃፉት..
ሰለ አንድ ማሊክ ሰለሚባል ሶማሌያዊ ሕጻን ፦
ገጽ 25 ፡ –
“ማሊክ በእናቱ እንደታቀፈ አንገቱን ወዲያ ወዲህ ሲያሽከረክር እኔ ከሁዋላ ነበርኩና አይን ለአይን ተጋጨን። ልክ እኔን ሲያይ እንደገና ማልቀስ ጀመረ። እናቱ ልጇ ያለቀሰበትን ምክንያት ለማወቅ ነው መሰል ዘወር ስትል እኔን አየችኝ። ሰይጣዊ ክፉ መንፈስ እንዳየች ሁሉ እሷም ፊቷን ጭምድድ አድርጋ ዘወር አለች። እኔም ምንም እንዳልተፈጠረ መንገዴን በመቀጠሌ እናትና ልጅ ከሁዋላዬ ሆኑ። ማሊክ ማልቀሱን አቆመ።” (ለልጅ ይታየዋል…)
***እኔም እላለሁ…**”በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ‘ለማሊክ የተገለጥክና እባብን ከፊቱ አብረህ ሰላም የሰጠህ አምላክ ሆይ፣-በሶማሌም ይሁን በኢትዮጵያ በእስራኤልም ይሁን በኤርትራ..አንድ ሆናችሁም ከዚያም በላይ ሥሜን በጠራችሁበት ቦታ ሁሉ እገኛለሁ እንዳልከን ኀይልና ሞገስህን ቢዚህ ስላሳየኽን ቃልህ ይክበር። “ለማሊክ ደርስህ ከለቅሶ አድነኸዋልና ክብር ምስጋና ለአንተ ይገባሃል። አሁንም ለእኛ ድሃና የዋህ ኩሩ ኢትዮጵያኖችና ሀገረ ኢትዮጵያ የሰተኸውን ቃል አትሻርብን ከትቢያ ከተነሱ ትሎች፣ምቀኖችና ሰው በላ፣ አድነን ስለት(ሜንጫ) እያቀረቡ ፍጥሩህን ሠላም የሚነሱትን ቅሰፍልን አሜን! አሜን! ይቀጥላል በለው!
ezra says
ምነው ጃል ! ኢሳት ዘወትር አጠራጣሪና በአብዛኛው “ቀደዳ” በሚያሰኝ መልክ የሚለቀዉን ዜና እየታዘብንም ቢሆን መሠማታችን አልቀረም። በአንፃሩ ተጨበጭ እንዲሁም የታየና የሚዳሠሥን ነገር በቅርቡ በወንድማችን በሳዲቅ መሐመድ በአሜሪካ ከተማ ጀግንነትን ተመልክተናል። ይሁነና (በአሜሪካ Star Back ውስጥ) በሳዲቅ መሐመድ አፋጣጭ ድንገተኛ ጥያቄ አነገቱን ያደፋዉ የማፊያው ህወሃት ቁጥር 1 ነብሰ ገዳይ ሰው ስብሃት ነጋን የኢሣቱ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ደረጀ ደስታ (የቆሎ ጓደኛው) እስኪመሰል ጋሸ ስብሃት እያለ ለስላሳ ጥያቄ ሲያቀረብ ደረጀን ትዝበት ውስጥ ከቶታል። ነገር ግን በመረጃ ተደግፎ ማንነቱ የተጋለጠው ተስፋዬ ገብረአብን ጉዳይ በተመለከት ኢሳት ላለመዘገብ ዝምታን መረጠ። ኢሳት ታዲያ ይሄንን የመሰለ ጮማ መረጃ ይዞ የወጣን የ ተስፋዬ ገበረአብን ጉዳይ አፍኖ እንዳይስተጋባ እያደረገ ያለው ኢሳት ደጋግሞ ለጆሮአችን የሚያንቆረቁረው መፈከሩ “ኢሣት የሕዝብ ዓይነና ጆሮ ወይስ የዝንብ ማጠራቀሚያ ገንዳ” … ጎልጉሎች እባካችሁ ይሄንን የቆሻሻ ዝንብ ማራቢያ የሆነዉን ኢሳት ጎልጉላችሁ ታፀዱት ዘንድ አደራ እንላለን።