• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከአሜን ባሻገር በበዕውቀቱ ስዩም

February 21, 2016 10:54 pm by Editor 6 Comments

ከአሜን ባሻገር በ19 ምዕራፎች የተቀነበበች246 ገጽ የሆነች ተነባቢ መፅሃፍ ነች። የዞን ዘጠኙ በፍቃዱ እንደነገረን ከሆነ አብዛኛዎቹ ምእራፎች በመጽሄትም በጋዜጣም የወጡ ስለነበሩ አዲስ አይደሉም ብሏል። በመጽሄትና በጋዜጣ የሚወጡ መጣጥፎች ማጣቀሻ ዋቢ ስለማያክሉ ከጊዜ ብዛትም ጸሀፊውም ስለሚረሳቸው የይድረስ ይድረስ ነገር ሻጥ ሻጥ ይደረጋሉ። የበዕውቀቱ ከአሜን ባሻገር በዚህ ረገድ ጉልህ ጎደሎነት አሳይቷል። ከቤተ አማራ ፖለቲካ አቀንቃኞችንም ጋር እሰጥ አገባ ያስገባው ይሄ የመጽሃፉ ደካማ ጎን ለምንጭ ለዋቢ የሚሰጠው ግምትና ቦታ። በሁለተኛው እትም ይስተካከላሉ የሚል ግምት አለኝ።

ስለ 19ኞቹ መጣጥፎች በዕውቀቱ በ13 ቃላት በሁለት አረፍተ ነገር ሲገልጽ “መጣጥፎቼ የእንጉርጉሮና የልግጫ ድብልቅ ናቸው። የሐሳብ አርአያዎቼ አንጎራጓሪ ሴቶች እንጂ ፕሮፌሽናል ፖለቲከኞች አይደሉም።”

ከአሜን ባሻገር ተስፋ መቁረጥና ንዴት ይታይበታል። ለዚህ ተስፋ መቁረጥና ንዴት የመፅሃፉ ጀርባ ጽሁፍ ጥሩ ገላጭ ይመስለኛል። ከአሜን ባሻገር በዚህ ስሜት ቢነበብ ለመረዳት አያስቸግርም።

በዕውቀቱ ሲጀምር እንዲህ ይላል። “የዘመኔ ጀግና እንዲህ የሚል ይመስለኛል”

“በኔ ዘመንና በጥንት አቴናውያን የቸነፈር ዘመን መካከል መሰረታዊ መመሳሰል አለ።”

“በሁለቱም ዘመኖች ውስጥ ለነገ ተስፋ ማድረግ የሚባል ነገር የለም።”

“ለፍቼ የሰራሁት ቤቴን ባቡር ይሁን ሰርጓጅ መርከብ በውል ያልታወቀ ነገር ጥሶት የሚያልፍ ከሆነ ቤት ለመስራት እንዴት ላቅድ እችላለሁ?

“ሰባት መቶ ሺህ ብር የገዛሁትን ቤቴን በክረምት አፍርሶ ደርዘን ጃንጥላ የማይገዛ ፍራንክ ሸጎጥ አድርጎ፣ ቤተ መቅደስ እንደገባች ውሻ አካልቦ የሚያባርረኝ ባለስልጣን ባለበት ሀገር ውስጥ ጎጆ ለምን እቀልሳለሁ።”

“ጌቶች ለችግር ቀኔ ያጠራቀምኩትን ብር በጥጋብ ዘመናቸው የሚወርሱብኝ ከሆነ የባንክ ደብተር የማወጣው ለምንድነው?”

“ልጄ በሕይወት እያለሁ እጓለማውታ ሊሆን እንደሚችል እያወቅሁ፣ “የዛሬ ዓመት የማሙሽ ልደት” እያልሁ የምዘፍንበት ምክንያት ምንድነው?”

“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” ከሚለው መፈክር በስተቀር ኢትዮጵያን ለዘላለም የሚያኖራት መሰረት መፍረሱን እያወቅሁ ለሚቀጥለው አመት እንዴት ላቅድ እችላለሁ?”

“ተው ባክህ! እኔም እንደጥንቱ አቴናውያን የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት ሰው እኖራለሁ። የመሰቀያው ገመድ አንገቴ ውስጥ እንደተፈረደበት ሰው እኖራለሁ። የመሰቀያው ገመድ አንገቴ ውሰጥ እስቲገባ ድረስ የጥንቱ ባላገር ግጥም በቃሌ እወጣለሁ።”

ይህን ይመስላል የበዕውቀቱ ስዩም ከአሜን ባሻገር የተጻፈበት መንፈስ። አብዛኞቹ የመፅሃፉ ምእራፋት ባንድም ሆነ በሌላው በኩል የኦሮሞዎችን ላገር ግንባታ ያደረጉት አስተዋፆ ተንታኝ ነው። የኦሮሞ ታሪክ ሲነሳ ምኒልክም መነሳታቸው ስለማይቀር አንድ ሁለት ምእራፍ ምኒልክም ተችሯቸዋል። ዳያስፖራውም አንድ ምዕራፍ ደርሶታል። የኦሮሞ ታሪክ ሲነሳ ራስ ጎበናም ስለተነሱ አንድ ማስተካከያና አንድ ሀሳብ ልጨምር።

1) “ይታመሳል አሉ ከፋና ቦረና

አማን አይደሉም ወይ እነ ራስ ጎበና” (ገፅ 70)

በዕውቀቱ ይህንን ግጥም አንተርሶ ጎበና አማን (ሰሜን ሸዋ) በተባለ ቦታ ተወልዷል ይለናል። የግጥሙ አማን ሚዛን ቴጲ የሚገኘው ሲሆን ጎበና ደቡብ ሄደው የጎበና መልክተኛ ድምፅ በመጥፋቱ የተገጠመ ነው።

2) በዕውቀቱ “የጎበናን ቅኝት” ምዕራፍ የጀመረው በዮፍታሄ ግጥም ነው

አጥንቱን ልልቀመው መቃብር ቆፍሬ

ጎበናን ተሸዋ፤ አሉላን ተትግሬ

አሉላን ለጥይት፤ ጎበናን ለጭሬ

አሉላ ሴት ልጁን፤ ጥይት ሲያስተኩስ

ጎበና ሴት ልጁን፤ ሲያስተምር ፈረስ

አገሬ ተባብራ፤ ካረገጠች እርካብ

ነገራችን ሁሉ፤ የእምቧይ ካብ የእምቧይ ካብ…

መነሳት የነበረበት ግን በዕውቀቱ ያላነሳው የጎበና ሴት ልጅ ማናት ነው (በዕውቀቱ ያነሳው የጎበናን ወንድ ልጅ ወዳጆን ስለሆነ) ግን ደግሞ በዕውቀቱ ላነሳው ትርክት አጋዥ እሷ ትሆነው ነበር። አስካለ ማርያም ትባላለች የራስ አበበ አረጋይ እናትም ነች። እንዲህም ተብሎላቸዋል።

“በለው በዱባይ በለው በዱባይ

የአስካለ ማርያም ልጅ አበበ አረጋይ”

በዕውቀቱ ስለ ውጫሌው ውል በሌላው ምዕራፉ ሲያትት ገብርኤል ጎበና የተባለ አስተርጓሚ እንደነበር ያትታል። በዚህ ትርክቱ ግራዝማች ዮሴፍ ሲካተቱ አፅመ ጊዮርጊስ ተዘለዋል። በሁለተኛው ከአሜን ባሻገር እትም የሶስቱን ሚና ይልይልናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

በዕውቀቱ ስለ ሀሰን አንጃሞ ሲፅፍ ሀሰን ወንጃቦ ብሎታል አስተካክላችሁ አንብቡለት።

በሌላው ገፅ (224) እንዲሁ የኦሮሞዎችን ላገር ግንባታ አስተዋፅኦ ሲያጎላ በስህተት የዳውሮውን ተወላጅ የኦሮሞ ተወላጅ ብሎታል።

እራሮት ቢበዛበትም ከአሜን ባሻገር ተነባቢ ፅሁፍ ነው። እንድታነቡት እጋብዛለሁ።

መልካም ንባብ

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mus'ab says

    February 24, 2016 05:23 pm at 5:23 pm

    ውድ ወንድሜ: በውቀቱ ማለት ለእኔ በዘመኔ እንድኮራ በስነ-ፅሁፍ በታሪክ እንዲሁም በቁም ነገር ጭውውቱ አንቱ ከምላቸውና ልክ እንደ ስሙ የተፈጠረ መሆኑን እወቀው::

    Reply
  2. Alex says

    February 24, 2016 05:53 pm at 5:53 pm

    Dear Daniel,

    I didn’t get you at all.

    Reply
  3. አማረ መኮን ን says

    February 28, 2016 05:06 am at 5:06 am

    የበዕውቀቱ መጽሐፍ፤አሁን ለምንገኝበት የፖለቲካ ምስቅልቅል አንድ አግጣጫ ሊያሲዘን ይችላል የሚል እምነት አለኝ።
    ኢትዮጲያችንን ያጋጠማት ችግር ምንድነው መፍትሔው ወደ ሚል መንገድ ይወስደና።

    አማረ

    Reply
  4. bufta says

    March 1, 2016 03:26 pm at 3:26 pm

    losers are always blaming and criticizing genius peoples and preachers of peace and love for their greedy short period benefit as well, to defame others for their good will. i have seen this critics as a loser!

    Reply
  5. satenaw says

    April 27, 2016 08:27 pm at 8:27 pm

    ከአሜን ባሻገር ተስፋ መቁረጥና ንዴት ይታይበታል። ለዚህ ተስፋ መቁረጥና ንዴት የመፅሃፉ ጀርባ ጽሁፍ ጥሩ ገላጭ ይመስለኛል። ከአሜን ባሻገር በዚህ ስሜት ቢነበብ ለመረዳት አያስቸግርም።በዕውቀቱ ሲጀምር እንዲህ ይላል። “የዘመኔ ጀግና እንዲህ የሚል ይመስለኛል”“በኔ ዘመንና በጥንት አቴናውያን የቸነፈር ዘመን መካከል መሰረታዊ መመሳሰል አለ።”“በሁለቱም ዘመኖች ውስጥ ለነገ ተስፋ ማድረግ የሚባል ነገር የለም።”“ለፍቼ የሰራሁት ቤቴን ባቡር ይሁን ሰርጓጅ መርከብ በውል ያልታወቀ ነገር ጥሶት የሚያልፍ ከሆነ ቤት ለመስራት እንዴት ላቅድ እችላለሁ?“ሰባት መቶ ሺህ ብር የገዛሁትን ቤቴን በክረምት አፍርሶ ደርዘን ጃንጥላ የማይገዛ ፍራንክ ሸጎጥ አድርጎ፣ ቤተ መቅደስ እንደገባች ውሻ አካልቦ የሚያባርረኝ ባለስልጣን ባለበት ሀገር ውስጥ ጎጆ ለምን እቀልሳለሁ።”“ጌቶች ለችግር ቀኔ ያጠራቀምኩትን ብር በጥጋብ ዘመናቸው የሚወርሱብኝ ከሆነ የባንክ ደብተር የማወጣው ለምንድነው?”“ልጄ በሕይወት እያለሁ እጓለማውታ ሊሆን እንደሚችል እያወቅሁ፣ “የዛሬ ዓመት የማሙሽ ልደት” እያልሁ የምዘፍንበት ምክንያት ምንድነው?”“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” ከሚለው መፈክር በስተቀር ኢትዮጵያን ለዘላለም የሚያኖራት መሰረት መፍረሱን እያወቅሁ ለሚቀጥለው አመት እንዴት ላቅድ እችላለሁ?”“ተው ባክህ! እኔም እንደጥንቱ አቴናውያን የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት ሰው እኖራለሁ። የመሰቀያው ገመድ አንገቴ ውስጥ እንደተፈረደበት ሰው እኖራለሁ። የመሰቀያው ገመድ አንገቴ ውሰጥ እስቲገባ ድረስ የጥንቱ ባላገር ግጥም በቃሌ እወጣለሁ።”ይህን ይመስላል የበዕውቀቱ ስዩም ከአሜን ባሻገር የተጻፈበት መንፈስ። አብዛኞቹ የመፅሃፉ ምእራፋት ባንድም ሆነ በሌላው በኩል የኦሮሞዎችን ላገር ግንባታ ያደረጉት አስተዋፆ ተንታኝ ነው። የኦሮሞ ታሪክ ሲነሳ ምኒልክም መነሳታቸው ስለማይቀር አንድ ሁለት ምእራፍ ምኒልክም ተችሯቸዋል። ዳያስፖራውም አንድ ምዕራፍ ደርሶታል

    Reply
  6. Yared says

    June 11, 2016 11:51 pm at 11:51 pm

    Golgul, wanted to share article i came across. Thanks.
    http://ethiopianchurch.org/en/books_reviews/268-%E2%80%9C%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B4%E1%89%B5-%E1%89%A5%E1%88%B5%E1%8A%AD%E1%88%8C%E1%89%B3%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%B0%E1%89%A5%E1%8A%A8%E1%8B%8D%E2%80%9D.html

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule