“የአካኪ ዘራፍ ፖለቲካና ከስሜት ያልጸዳ የፖለቲካ ትግል መሪውንም ሆነ አምኖ የሚመራውን ህዝብ ለድል” እንደማያበቃ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ። ከኤርትራ ጋር ስምምነት ቢደረግ መልካም መሆኑን፣ ነገር ግን ስምምነቱ የመሪዎችና የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብን ስሜት የጠበቀ ሊሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል።
ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጋር በተለይ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕ/ር በየነ “አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስተዋይነት የሚፈልግ፣ ዘመናዊ የትግል ስልት የሚጠይቅ ነው” በማለት ተናግረዋል። በቃለ ምልልሳቸው ደጋግመው “አሁን በተያዘው የአካኪ ዘራፍ መንገድ የትም አይደረስም” በማለት ምክንያታቸውን ዘርዝረዋል።
ትንንሽ ጠርዝ በመያዝ የትም የማይደርስ ትግል ከየአቅጣጫው እንደሚፈለፈል ፕ/ር በየነ አመልክተዋል። በዚሁ የተነሳ ስትራቴጂካልና ታክቲካል ጉዳይ የመለየት አቅም አናሳ በመሆኑ የፖለቲካው መንደር የርስ በርስ ንትርክና ውግዘት ሊሆን እንደቻለ ገልጸዋል። ለዚህም ተጠያቂዎችና ቅድሚያ ተወቃሾች ህዝብና አገር የምትፈልጋቸው የዘመናዊ ለውጥ መሪዎች መሆን ሲገባቸው የዳር ተመልካች የሆኑት የአገሪቱ ልሂቃን እንደሆኑም በግልጽ ተናግረዋል።
“ችግሩ በአገር ውስጥ ባሉት ልሂቃን ላይ ጎልቶ ቢታይም፣ በውጪው ዓለም ባሉት ምሁራኖችም ላይ ተመሳሳይ ችግር አለ” የሚሉት ፕ/ር በየነ “እነዚሁ ክፍሎች ትግሉን ከመቀላቀል ይልቅ እኛን በመውቀስ አገራዊ ሃላፊነታቸውን የተወጡ መስለው ይታያሉ” ሲሉ ስሜታቸውን ገልጸዋል።
“የፖለቲካው መስመር ክፍተትን አይወድም” በማለት የሰከነ አመለካከት ላላቸውና ከስሜት ፖለቲካ ነጻ ለሆኑት ዜጎች መልዕክት ያስተላለፉት ዶ/ር በየነ፣ ሰዓትና በጀት በመመደብ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ክፍሎች ሰድቦ የማሰደብ ተግባር ሲከናወን ማየታቸው በጅጉ እንደሚያሳዝናቸው ተናግረዋል። በጦር መሳሪያና በሃብት ብዛት መፎካከር ባይቻልም፣ በሰብአዊ ብቃት ኢህአዴግን መፎካከር እንደሚቻል የጠቆሙት ዶክተሩ የተቃዋሚው ሰፈር በተቃራኒው የተፈረካከሰ፣ እርስበርስ ለመባላት ቅድሚያ የሚሰጥ፣ የትግል ስልቱም ሆነ አቅሙ ስትራቴጂካዊና ታክቲካል ጉዳዮችን መለየት በማያስችል ደረጃ የተዋቀረ መሆኑ ትግሉን ፍሬ አልባ እንዳደረገው ተናግረዋል።
“ለአውራነት/ኮርማነት የታሰበ በሬ ተመልሶ ላሚቱን ጠባ” በሚል በሃድያ የሚነገር ተረት በማስታወስ ሃሳባቸውን ያጠናከሩት ዶ/ር በየነ፣ የዚህ ሁሉ ችግር መንስዔው የልሂቃኑ ዝምታ እንደሆነ አመልክተዋል። አገራቸውን ወደ ተሻለ መንገድ ለማሸጋገር የሚችሉ ሁሉ ዝምታቸውንና ዳር ቆመው የሚመለከቱትን የአገራቸውን ውድቀት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል። ዶ/ር ነጋሶ የወሰዱትን ርምጃ በማንተራስ ስለ ፖለቲካ ጡረታም ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል።
“እናንተ አርጅተሃል ካላችሁ እንጂ እኔ አላረጀሁም። ጤነኛ ነኝ። የነጋሶን ያህል እድሜም የለኝም” በማለት መልሳቸውን ይጀምራሉ። በማያያዝም “ልተውስ ብል እንዴት ብዬ?” ሲሉ ይጠይቃሉ። “ልሂቃኑ ዳር ቆመው ተመልካች ሆነዋል። በዚህ ላይ የምመራቸውና ውህደት የፈጠሩት የደቡብ ህብረትና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ አደራውን ከኔ አላወረዱም። አሁን በቃኝ ማለት ሰራዊት በትኖ እንደሚፈረጥጥ መሪ የመሆን ያህል ነው።”
ኸርማን ኮህን በቅርቡ ይፋ ያደረጉትን የእርቅ ሃሳብ አስመልከቶ ማብራሪያ ሰጡት ዶ/ር በየነ “በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት የሚደረግ ስምምነት ከቶውንም ቢሆን ተቀባይነት የለውም። ከኤርትራ ጋር እርቅ መልካም ቢሆንም በፖለቲከኞችና በውስን ሃይሎች ፍላጎት ተከናውኖ ሰዶ ማሳደድ እንዳይሆን እፈራለሁ” ብለዋል። ከዚሁ ጋር በማያያዝ አሜሪካ በኢህአዴግና በወያኔ የፖለቲካ እምነት ደስተኛ እንዳልሆነች ተናግረዋል። ድጋፍ የምትሰጠው ከፍቅር ብዛት እንዳልሆነ በማመልከት የተቃዋሚው ክፍል ይህንኑ ቀዳዳ ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል። “ታዲያ” አሉ ፕ/ር በየነ “ታዲያ በማንጓጠጥና በዘለፋ ሳይሆን በሰከነ መንፈስና ስሜትን በገደለ አስተዋይነት” ሊሆን ይገባል። በመጪው ምርጫ የ1997 ምርጫ ዓይነት ሁኔታ እንዲፈጠር ዘመቻ መጀመሩንና የድጋፍ ፍንጭ መታየቱን የገለጹት ዶ/ር በየነ ስለ ሃይል አማራጭና ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት ውስጥ አለ ስለሚባለው የመፈረካከስ ችግር ተጠይቀው “ጦርነት የሁለት የጎበዝ አለቆች ጸብና ድብድብ ነው። ከአሁን በኋላ እኔ ላገሬ ጦርነት አልመኝም” በማለት ከምክንያታቸው ጋር አስቀምጠዋል። ህወሃትና ኢህአዴግ ውስጥ አለ ስለተባለ የመፈረካከስ ችግር “የዋህነት አይጠቅምም፣ በስሜትና በአካኪ ዘራፍ ፖለቲካ የሚመጣ ለውጥ ይኖራል ብዬ አላስብም” ብለዋል። ስለ ስጋታቸውም ተናግረዋል።
“ወያኔ የሚባለውና ተዘጋጅቶ አገሪቱን የተቆጣጠረ ሃይል ለሰበሰበው ሃብትና ንብረት ሲል ፖለቲካውን በበላይነት ለመምራት ከቀን ወደ ቀን የሚፈጽመው ጥፋት ህዝብ እያማረረ መጨረሻው አገሪቱን ወደ ጥፋት እንዳይወስድ ነው። የከፋቸው በጨመሩ ቁጥር ችግሩ መከሰቱ አይቀርምና በጥበብ ታግሎ ካሰቡት ለመድረስ እነሱ ከሚያስቡት በተለየ በልጦ ማሰብና መታግል አስፈላጊ ነው። ለዚህም የልሂቃኑ ዳር ቆሞ መመልከት መቆም አለበት” ብለዋል። በማያያዝም ዲያስፖራው አገር ውስጥ ለሚታገሉ ድርጅቶች ልዩነት ሳያደርግ ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። ድጋፉም ሆነ እገዛው ሰክኖ ለማሰብ እንደሚመነጭም ገልጸዋል። ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ በተለይ ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ያደረጉትን ሙሉ ቃለ ምልልስ በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Abegaz says
Prof. Beyene is right. He should not resign from his leadership position. There is a difference when you are a leader of a party in opposition and a leader of a governing party in countries like Ethiopia where there is no freedom and rule of law. If an opposition leader resigns it will kill the party’s strength. An opposition party is not corrupt and gets no payment. He/she does not have power as such to oppress others. If he/she tries, the party will be weakened. This principle of leadership change should only apply to a governing party leader. He/she has power and oppresses anyone on his way using the government brute force. After all old leadership is there because the young are not ready to task. Dr. Negaso was on power because there was no better and responsible youth leadership in place. I do not agree on blaming old leadership. Today’s youth is not as dedicated as those of yesterdays. Compare the youth dedication under EPRP to the current youth. When I see a 6 ft young adult running like a rat just by looking a 100 pound and 5 ft police in front of Saudi Arabian embassy, I said to myself why in the first place he went to there. When the old Kiniji leaders went to Kaliti jail, I have not seen the prison surrounded by dedicated youth. This is part of peaceful struggle. When a leader is arrested people should come out to the streets in mass. Only then peaceful struggle succeeds. Do we have a youth leadership that does that? No. That is why the old are still in the struggle.
aradaw says
he has a very long resume in Ethiopian politics as a diaspora and as opposition in the country. I doubt about his contribution to date. I also doubt how much he contributes in his old age.
በለው! says
>>>“የአካኪ ዘራፍ ፖለቲካና ከስሜት ያልጸዳ የፖለቲካ ትግል መሪውንም ሆነ አምኖ የሚመራውን ህዝብ ለድል” እንደማያበቃ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ።
___ማነው አካኪ ዘራፍ የሚለው? አውራው ፓርቲ ፩ተኛ ? አጋር ፓርቲ ፪ተኛ ?(ጠላጣፊና ተደራቢ ፓርቲ) እናደናግር ፓርቲ (፫ተኛ አማራጭ) የልደቱ አያሌው የኢህአዴግ ክንፍ? የአቶ ሌንጮ ለታ (፬ተኛ አማራጭ) ለኢህአዴግ (፫ተኛ አማራጭ )ለኦሮሞ?
**ከኤርትራ ጋር ስምምነት ቢደረግ መልካም መሆኑን፣ ነገር ግን ስምምነቱ የመሪዎችና የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብን ስሜት የጠበቀ ሊሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል።
___ኤርትራ ጋር ሲባል ከሕዝቡ ነው? ከባለሥልጣናቱ ነው? ከሥልጣን ተረካቢው ነው? በአዲስ አባባ ቢራ ከሚጠጣውና ከሚነግደው ተተፎካካሪ ፓርቲ ነው? አሁኢን ኢትዮጳያን ከሚመሯት ኤርትራውያንና ትውልደ ኤርትራውያን ነው? ስብሃት ነጋን ጨምሮ ” ስልጣንና ትምህርት ሳይኖራቸው ስለሁሉም የኢትዮጳያና ኤርትራ ፖለቲካል ኢኮኖሚ መከላከያውን ጨምሮ የሚያውቁና መልስ ያላቸው ብቸኛው ህወአት ታጋይና አታጋይ ታዋቂ!?
**“ለአውራነት/ኮርማነት የታሰበ በሬ ተመልሶ ላሚቱን ጠባ” ከሃዲያ ቋንቋ ወደ ብሀየር ብሄረሰብ ሲለወጥ እንግዲህ… ሰው ሳይሞት ትቁር መነፅርና ጥቁር ልብስ (ከል) ያሰፉትን፣ሆዳቸው ባበጠ ቁጥር ሀገር አደገች የሚመስላቸው፣ በአዛባ በተለቀለቀ መደብ ላይ ተወልደው የመደብ ትግል ያማራቸው፣ አድር-ባይ፣ ሆድ-አደር፣ በቲቪና ሬዲዮ ቃለመጠይቅ ወሬ ለመሰንጠቅ የሚሯሯጡ፣ ሀገራዊ እርቅ ሲባል ዕጥአቸው ዱብ የሚል፣ለሕዝብ የሚበላ ሳይሆን ሕዝብን የሚያባላ ሲፈጥሩ ሲሸርቡ የሚያድሩ፣ እርስ በእርስ መጨፋጨፍን ሽብር አመፅን ፅንፈኝነትን የሚነዙ፣ በሃኢቡ ተደራጅተው የኪራይ ሰብሳቢነታቸው ያየር በአየር ንግዳቸው እነዳይሰተጋጎል አለውን መንገስት በመካብ ሀገር በማፍረስ ትውልድ በማምከን ንበረት በማባከን የተደራጁ ብሄር ተኮር አጋጭና አባጣባጭ ፣ ከህወአት በፊት ለቦንብ መሞከሪያ ቀድመው የሚደፉትን ባንዳ ሙሰኞች ልሂቃን፣ ሱምባሽ ካድሬ፣ ኢንቨስተር፣ ፵/፷ ዲያስፓራና ሌሎችም ሥማቸውን ያልዘረዘርኳቸውን በአንድ የሻቢያህወአት ጥላ ሥር የታቀፉትን ማለታቸው ነው።
**አገሪቱን የተቆጣጠው የሻቢያህወአት ወሮ በላ ቡድን ለሰበሰበው ሃብትና ንብረት ሲል ፖለቲካውን በበላይነት ለመምራት ከቀን ወደ ቀን የሚፈጽመው ጥፋት ህዝብ እያማረረ መጨረሻው አገሪቱን ወደ ጥፋት የሚወስድ ነው። ______” እኛ ከሌለን ትበታተናላችሁ” ማለት የፈጠርናችሁ ማንነታችሁ የተረጋገጠው በእኛ ለእኛ ከትውልድ ትውልድ ይሆናል!። አራት ነጥብ። ብሉ፣ አብሉን፣ አባሉ፣ እኛ የምንሰራውን እንዳትጠይቁ፣ በራሳችሁ ቋንቋ ተናገሩ፣ እኛ አናውቀውም ለማወቅም አንፈልግም፣ በገቢያችን አትድረሱ እናንተ እረስ በእርሳችሁ የራሳችሁ ጉዳይ ነው። ጠንክራችሁ ከመጣችሁ ግን የሀገሪቱ ውስጠ ሚስትር ቀልፍ በእጃችን ነውና ያልበላነውን ችረን መድፋታችን አይቀርም! ስለዚህ ሀ)ዝም ትላላችሁ ለ)ዝም እናሰኛችሁ ሐ) ትበጠብጣላችሁ አማራን አንጥራባችሁ መ) ምናባታችሁ ይሻላችኋል!?። መሐል ገባችሁም ከጎን ያጀባችሁም ከፊት ቀድማችሁ እና አንሙት የማትሉ ከኋላ እየተገረፋችሁ ምትነዱም ብትሆኑ ወይም ካዳር ቆማችሁ የምታዩ ቡካታም ልሂቃን ሆይ ኢትዮጵያ ከሁሉም ሕዝቧ ጋር ታፍራና ተከብራ የኖረችው በቆራጥ ልጆቿ በደም በአጥንት መስዋዕትነት እንጂ በተፃፈ ህገመንግስት አልተፈጠረችም!በሕዝብ ለሀገር ሉዓላዊነት በማይሆን በማናቸውም ነገር ላይ አትደራደር! አትፍራ! “ሞት አንድ ናት ወይ ጠኔ ወይ ቁንጣንም ሊገልህ ይችላል።” እንቢኝ ባለ ነው መይሳው! እንቢኝ ባለ ነው ምንይልክ! ተከብረን የኖርነው እንቢኝ በል በለው!
Abegaz says
Ardaw,
The current youth in Ethiopia is not responsible. Look, it is still the old guard that carries the burden of this country. For example see the Ethiopian boarder committee in the USA confronting Sudan and TPLF/EPRDF. Have you heard anything from the youth in the USA. The use is about pleasure, dance, good food and dating. So I do not believe people like Prof. Beyene retire from politics.
Ere Tew says
Abegaz,
እውነትን መደፍጠጥ አግባብ አይመስለኝም። ምነው ሰማያዊ ፓርቲን ዘነጋሀው? የጅምላ ወቀሳ አግባብ አይደለም።
jarso says
i have never witnessed so far a confrontational youth in Ethiopia after the 2007 Ethiopian election. The Semyawi party seem to me in a dwindling mood following the harsh tretment the woyane served for number of its members. Such shock treatment scared and retreat them from staging continous anti-woyane demonstration. Not only Semayawi party but also the Muslims (demsatchin Yesma) Friday rallies no more heard for the last three months. I think the abscence of confrontational situations ,embolden the woyane to intensify its action of quelling and supressing opposing forces with brute force .Because all oppositions parties have failed miserably to connect the dots so as to lead the struggle to its logical conclusion. In my opinion the opposition have historical obligation and have vowed to pay sacrfice for the cause pledged to defend .So to realize their pleadge have to go hard or else have to go home.