በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ስሞኑን ህመሙ ጠንቶባቸው ከሁለት ወር በፊት በሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕልና ተጭነው በድብቅ ለህክምና ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ የሚገኝ አንድ «ቡግሻን» እየተባለ የሚጠራ ሪፈራል ሆስፒታል የልብ ቧንቧ ማስፋት ህክምና ቢደረግላቸውም የባለስልጣኑ የጤነነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለወጥ ባለማሳየቱ ለዳግም ህክምና ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ከሳምታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬም የአቶ በረከት ጤንነት መልካም ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ምንጮች የሆስፒታሉን የምርመራ ውጤት አብነት ጠቅሰው ይናገራሉ። አቶ በረከት በጤንነታቸው መታወክ ፍጹም መረጋጋት እንደማይታይባቸው የሚገልጹት እነዚህ ውስጥ አዋቂዎች ቀደም ሲል ባለስልጣኑ ህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት ወደ ሳውዲ አረቢያ በሚስጥር ለህክምና መግባታቸውን ተከትሎ በተለያዩ ድህረገጾች ዜናው በስፋት መናፈሱ በውስጣቸው በተፈጠረው አለመረጋጋት በልባቸው ምት አለመስተካከል በወቅቱ በቂ ህክምና መውሰድ እናዳልቻሉ ታውቋል። የአቶ በረከት የጤነንት ሁኔታ ዛሬም አስተማማኝ እንዳልሆነ የሚያውሱ እነዚህ የአይን እማኞች ከእለት ተዕለት የባለስልጣኑ የአካል መጠን በማይጠበቅ ሁኔታ መቀነስ እና የፊታቸው ገጽታ መለዋወጥ በውስጣቸው መልካም ነገር እንደማይታይ ያሳብቃል ብለዋል።
የአቶ በረከት ስሞኦን ህይወት ለመታደግ የአቅማቸውን ያህል ጥረት እያደረጉ የሚገኙ «ቡግሻን» የሳውዲ አረቢያ ሆስፒታል ዶክተሮች ስለበሽታው አደገኝነት ግንዘቤ በማስጨበጥ አቶ በረከት ከተለያዩ መጠጦች እና አእምሮ አደንዛዥ እጾች መራቅ እንዳለባቸው እና የጤነንታቸው ሁኔታ አስተማማኝ ሁኔታ እስኪደርስ እረፍት መውሰድ እንደሚገባቸው ሙያዊ ምክሮቻቸውን ለገሰዋቸዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ አቶ በረከት ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲያቀኑ የህክምና ውጪያቸውን እየሸፈኑ ከሚገኙት ሼክ አላሙዲን ባሻገር ለኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት ሚስጥር መሆኑ አያሌ ወገኖችን በስፋት እያነጋገር ነው። ከሁለት ወር በፊት አቶ በረከት እኩለ ለሊት ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ ሳውዲ አረቢያ በሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕላን በድብቅ ለህክምና መግባታቸው ለኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወሬው የደረሰው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዘ-ሃበሻ እና ጎልጉል ድህረገጾች በተለቅቁ መረጃዎች መሆኑን የሚናገሩ ምንጩች ለሁለተኛ ጊዜ ዳግም ህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲመለሱ በሼክ አልሙዲን በኩል በክብር «በፕሮቶኮል» ሊገቡ እንደሚችል በወቅቱ ከጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የወጡ መረጃዎች ቢያረጋግጡም የአቶ በረከት ስሞኦን እንደተለመደው በድብቅ ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባት ባለስለስልጣኑ በውስጥም በውጨም ጥሩ ወዳጅ እንደሌላቸው የሚነገረውን ሃቅ ያጠናክረዋል ብለዋል።
አቶ በረከት ትላንት በተደረገላቸው ምርመራ የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው የሚገልጹ የሆስፒታል መረጃዎች ባለስልጣኑ የተሰጣቸውን ምክር እና የተለያዩ መድሃኒቶቻቸውን ይዘው ከሆስፒታሉ ውጭ ወደሚገኘው ምስጢራዊ ማረፊያቸው ማቅናታቸው ተገልጾዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና መስረት አቶ በረከት ስሞኦን ዛሬ ማምሻውን ለአስቸኳይ ጉዳይ ህክምናቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመልሱ ምስጢራዊ መረጃዎቻችን አክለው አረጋግጠዋል። Ethiopian Hagere Jed Bewadi
(Ethiopian Hagere ዜናውን የላኩልን በOct 31፣ 2014 ነበር በሥራ መጣበብ ሳናቀርበው በመዘግየታችን ይቅርታ እየጠየቅን ይህንን ዜና ከዚህ አንጻር አንባቢያን እንዲያነቡት ለማሳሰብ እንወዳለን)
Leave a Reply