
የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ነሃሴ 17 እና 18 ቀን 2010 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በብአዴን 12ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ረቂቅ ሪፖርትና ለጉባዔው በሚቀርቡ ሌሎች ወቅታዊና መደበኛ ጉዳዮች ላይ ተወያቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ባለቤትነት በሀገር ደረጃና ብአዴን በሚመራው የአማራ ክልል የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል ወሳኝና ታሪካዊ ጊዜ ላይ የሚካሄድ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ድርጅቱ የመሪነት ሚናውን ከምንጊዜውም በላይ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ለጉባኤው እንዲቀርቡ ጥልቀት ያለው ውይይት ካካሄደ በኋላ በጉባዔ አጀንዳዎችና በሌሎች ጉዳዮች ስምምነት ላይ በመድረስ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
- በመቀጣጠል ላይ ያለውን ክልላዊና ሃገራዊ ለውጥ ለመጠበቅ፣ መሰረቱን ለማስፋትና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ እንዲቻል ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሕጋዊ የለውጥ እርምጃዎች በተከታታይ ይወሰዳሉ፡፡ በዚህ ሂደት ብአዴን የደረስንበት መድረክ የሚጠይቀውን ደረጃ ያሟላ ተመራጭ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ በመገኘት የክልሉን፤ ብሎም የሃገራችንን ህዝብ የዲሞክራሲና የልማት ጥያቄዎች ከፍ ባለ ደረጃና በዘላቂነት እየመለሰ ግንባር ቀደም አታጋይ ድርጅት ለመሆን ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ለመላው የአማራ ህዝብ፣ ለድርጅቱ አባላትና አመራሩ በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ያበስራል፡፡
- የአማራን ህዝብ ታሪክ፣ ትግል፣ ባህል እና ስነ ልቦና በአግባቡ የተገነዘበና የተረዳ፣ እንዲሁም አሁን ከተፈጠረው አዳጊ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታ ጋር አብሮ የሚራመድ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ድርጅቱ ቀደም ሲል ሲመራበት የነበረው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ የህዝቡንና የአባላቱን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ግለጽ በሆነ ተሳትፎ እንዲሻሻል ይደረጋል፡፡ በዚህ ረገድ የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት የድርጅታችን አባላት ጥያቄ እስከሆነ ድረስ የድርጅቱን ስያሜ ጨምሮ ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮችም በአግባቡ እየተፈተሹ ሥርዓቱን በጠበቀ መንገድ ማሻሻያ ሊደረግባቸው እንደሚችል ማዕከላዊ ኮሚቴው ያምናል፡፡
- የአማራ ብሄርተኝነት በህብረ-ብሄራዊነትና በዲሞክራሲያዊ የኢትዮጵያ አንድነት መርህ ለይ ተመስርቶ እንዲገነባ ብአዴን በጽናት ይታገላል፡፡ በፌዴራል ሥርዓቱ ውስጥ የህዝቦች እራስን በራስ የማስተዳደር፣ የእኩልነትና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ በነጻነት የመስራትና የመኖር መብቶች ሁሉ በትክክለኛው ገጽታና በተሟላ መንገድ እንዲከበሩና ኢትዮጵያ ለሁላችንም የተመቸች ሃገር እንድትሆን ብአዴን ከሌሎች እህት ድርጅቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን ይሰራል፡፡ ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስት አባላት የሆኑ ክልሎች አከላለል በህዝቦች እውነተኛ ፍላጎትና ንቁ ተሳትፎ፣ ብዝሃነትንና ሃገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ ሕገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ እንዲከለል እንታገላለን፡፡ ባለፉት የትግል ዓመታት ክልላችንን ጨምሮ በመላ ኢትዮጵያ ለህዝቦች መፈናቀልና መሰደድ፣ ለህይወት መጥፋትና ንበረት መውደም ምክንያት የሆኑ የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው በህዝብ ነጻ ተሳትፎ እንዲፈቱ ብአዴን በምክንያት ለይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ትግል ያካሂዳል፡፡
- የሃገሪቱም ሆነ የክልሉ ሕግጋተ መንግሥታት ዘመናዊ፣ ዓለም ዓቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችንና መሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶችን አሟልተው የያዙ፣ የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ እንደመሆናቸው መጠን ለህገ መንግሰታዊ መብቶች መከበር ብአዴን በጽናት ይታገላል፡፡ ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ ማሻሻያ ሳይደረግበቸው የዘለቁት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎቻችን ውስጥ አንዳንዶቹ አገራችን ዛሬ ከደረሰችበት የዲሞክራሲ እድገት ደረጃ ጋር ተጣጥመው መሄድ አለባቸው የሚለውን የህዝብ አስተያየትና ጥያቄ ብአዴን በበጎ ጎኑ ይመለከተዋል፡፡ ስለሆነም እንዲህ አይነት ጥያቄወች ሕገ መንግስቱ ራሱ ያስቀመጠውን ሥርዐት ጠብቀው እስከቀረቡ ድረስ የሚነቀፉበት ምክንያት የለምና ሕጋዊና ትክክለኛ ምላሽ አግኝተው በሃገራችን የተጀመረው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበለጠ እንዲጠናከር ብአዴን በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡
- የህግ የበላይነት መከበር ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ እንደሆነ ብአዴን በጽናት ያምናል፡፡ እስካሁን በተካሄደው ትግል በዜጎች ለይ የተፈጸመን ማንኛውንም ሓላፊነት የጎደለው ኢ-ሕገ መንግስታዊ ተግባር እያወገዝን በእንዲህ አይነት ድርጊት ውስጥ ገብቶ የተገኘ ማንኛውም ቡድን፣ የመንግስት ባለስልጣንና ግለሰብ የሃገሪቱ ህግ በሚፈቅደው አኳኋን ለህግ ቀርቦ ተጠያቂ እንዲሆን በጽናት እንታገላለን፡፡ ከዚህም በኋላ በሃገራችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በተሟላ መንገድ እንዲከበሩ፣ ዜጎች በገዛ ሃገራቸው ተዋርደው ሊኖሩ እንደማይገባ፣ በዚህ ረገድ የሚፈጸምን ማንኛውንም ኢ-ሕገ መንግስታዊ ድርጊትም ውጉዝ እንደሆነ ብአዴን አጥብቆ ያምናል፡፡ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ፈር ለማሳት የሚፈጸም ማንኛውንም ሕገ ወጥ ተግባር በመታገል በሃገራችንና በክልላችን ዋስትና ያለው ዲሞክረሲ እንዲገነባ ይደረጋል፡፡
- የግለሰብና የቡድን መብቶች ተጣጥመው መከበር እንዳለበቸው እናምናለን፡፡ የግለሰብ መብት ባልተከበረበት የቡድን መብት ቦታ እንደማይኖረው፣ የቡድን መብት ባልተከበረበትም የተሟላ ዲሞክራሲ እንደማይኖር የታወቀ ነው፡፡ ሁለቱን መብቶች አጣጥሞ በመሄድ ረገድ ሕገ መንግስታችን ብዙ እርቀት ተጉዟል፡፡ በመሆኑም በሃገራችን ትክከለኛ ዲሞክራሲ እንዲገነባ ትልቅ መሰረት ተጥሏል፡፡ ይሁን እንጅ ባለፉት ዓመታት በሁሉም መስክ በቂ ሥራ ካለመሠራቱም በላይ በተለይ ደግሞ ለቡድን መብት መከበር የተሰጠውን ትኩረት ያክል ለግለሰብ መብትም ስላልተሰጠ የተጀመረው የቡድን መብት የማስከበር ሥራ ወደፊት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ትኩረት ተነፍጎት የቆየው የግለሰብ መብት በሚዛናዊነት የሚከበርበት ሥረዐት እውን እንዲሆን ይደረጋል፡፡
- ብአዴን በውስጡ ጤናማ የሆነ የአመራር ቅብብሎሽ ሥርዐት ይኖር ዘንድ ለአመራር ግንባታ ሥራ በቂ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ በተለይም አሁን እየታየ ያለውን ከፍተኛ የፖለቲካ ንቃትና ምርጥ ህዝባዊ መዕበል በእድልነት በመጠቀም በድርጅቱ ውስጥ በብቃት የተገነባ ብልህ፣ አርቆ አሳቢና አስተዋይ ተኪ አመራር እንዲኖር የተማረውን ወጣት መዕከል ያደረገ የአመራር ምልመላና ግንባታ ስራ ያካሂዳል፡፡ በአነጻሩም አሁን ከተደረሰበት የትግል መድረክና ከለውጡ እንቅስቃሴ ጋር አብረው መጓዝ በተሳናቸውና ህዝባዊ ሃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት ባልቻሉ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ለይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ድርጅቱ ራሱን የማጥራት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ የብአዴን 12ኛ ድረጅታዊ ጉበኤም ይህንኑ ግምት ውስጥ ያስገባ ውሳኔ የሚተላለፍበት እንዲሆን በዚህ አጋጣሚ ለመላ አባላችንና አመራራችን ጥሪ እናቀርባለን፡፡
- ሁለተኛው የእድገትና ትራንሰፎርሜሽን እቅድ በብቃት እንዲመራና በቀሪ ጊዚያት በሚሰራ ስራ ያለፈውንም ማካካስ በሚችልበት ደረጃ ለይ እንዲደርስ ህዝቡን፣ ወጣቶችን፣ ባለሃብቱንና ምሁራንን በማረባረብ ክልላዊና ሃገራዊ እድገት እንዲረጋገጥ ይደረጋል፡፡
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች የክልሉ ህዝብ ያሉበትን ተጨባጭ የልማት ችግሮች እየፈቱና ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ስርዓት መመራት እንዳለባቸው እናምናለን፡፡ በመሆኑም የጥረት ኮርፖሬት እና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የተባሉት የልማት ድርጅቶች የክልሉ ህዝብ ሃብት እንደመሆናቸው መጠን የላቀ ልማት ማረጋገጥ በሚችሉበት አኳኋን መመራት ስላለባቸው ተጠሪነታቸውም ለክልሉ መንግስት እንዲሆን የፖለቲካ ውሳኔ ተወስኗል፡፡ አፈጻጸሙም ሕጉን ተከትሎ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- በአሁኑ ሰአት የተፈጠረውን ምቹ ሃገራዊና ክልላዊ ሁኔታ በመጠቀምና የዲሞክራሲ ምህዳሩን መስፋት እድል በማድረግ ሃገር ውሰጥ ከሚንቀሳቀሱም ሆነ ውጭ ሃገር በስደት ቆይተው ከተመለሱ ተፎካካሪ ፓርቲወች ጋር በሚያለያዩን ጉዳዮች ተከባብረን አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች አብረን ለመስራትና ዲሞክራሲን ለማስፋት ጽኑ ፍላጎት እንዳለንና በዚሁ መሰረት ለመራመድ ወስነናል፡፡
- በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለው የድንበር ማካለል ጉዳይ በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስ የሁለቱም ወገን አርሶ አደሮች የያዙትን የእርሻና የደን መሬት እንደያዙ እየተጠቀሙ እንዲቆዩ በሁለቱ ሃገራት መንግስታት መካከል ስምምነት ተፈርሞ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጅ በተለይ በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ ደለሎ በተባለው አካባቢ ታሪካዊ ዳራውንና ነባር የይዞታ መብታችንን ያላስጠበቀ፣ የሚመለከታቸውን አካላት ያላሳተፈና የጋራ አቋምም ያልተያዘበት ውሳኔ ተሰጥቶ እንደነበር አውቀናል፡፡ ይህ ውሳኔ ብአዴንና አመራሮቹ ለረጅም ጊዜ በህዝብ ዘንድ ባልተገባ መልኩ ሲታሙና ሲጠረጠሩ እንዲቆዩ አድርጓል፡፡ በመሆኑም ውሳኔው በፌደራል መንግስት በኩል አስቸኳይ ማስተካከያ እንዲደረግበት እንጠይቃለን፡፡ ለጋራ የጸጥታ ማሰከበር ስራ ይጠቅማል የሚለውን ስምምነት ምክንያት በማድረግ በቋራ ወረዳ ልዩ ስሙ ነፍስ ገበያ በተባለው አካባቢ ለጊዜው ሰፍሮ የነበረው የሱዳን ወታደርም ይዞታ እያሰፋፋና ቋሚ ካምፕ እየገነባ ከያዘው ጊዚያዊ ይዞታ ሳይለቅ መቆየቱ ተገቢ እንዳልሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡ የካመፑም መኖር የድንበሩን ጉዳይ የበለጠ እያወሳሰበውና የክልሉ አርሶ አደሮችም የእርሻ ስራቸውን በሰላም እንዳያከናውኑ እንቅፋት እየሆነ ይገኛል፡፡ ከዚህ አኳያ የሱዳን ወታደር እስካሁን ድረስ ከያዘው ይዞታ ለቆ አለመውጣቱ ተገቢ ባለመሆኑ በፍጥነት ከይዞታችን ለቆ እንዲወጣና የፌደራል መንግሥትም ይህንኑ እንዲያሰፈጽምልን እንጠይቃለን፡፡ ብአዴን በክልላችን የሚገኘው ይህ የኢትዮ ሱዳን የድነበር ጥያቄ የነዋሪወችንና የአርሶ አደሮቻችንን ይዞታ መሰረት አድርጎ፣ ታሪካዊ ዳራውን ሳይለቅና የሃገርን ሉዓላዊ ጥቅም ባስከበረ መንገድ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድበት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
- ምሁራን የአማራ ክልልን የልማትና የመልካም አስተዳር ችግሮች ለመፍታት በሚደረገው ርብርብ የድርሻቸውን ለመወጣት እያሳዩ ያሉትን የጋለ ተሳትፎና ጥቁር መጋረጃውን የቀደደ ሞያዊ ግዴታን የመወጣት ታሪካዊ ዘመቻ ከልብ እናደንቃለን፡፡ በዚህም አጋጣሚ የአማራ ህዝብ በመላ፣ ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶችና የድርጅታችን አባላት ከብአዴን ጎን ቆማችሁ ክልላችንና ሀገራችንን የመገንባት ጉዞ እንድትደግፉ ጥሪ እናቀርብላችኋለን፡፡
ለውጡን በመጠበቅ፣ በማጥለቅና ቀጣይነቱን በማረጋገጥ የእድገትና ትራንሰፎርሜሽን ዕቅዱን እናሳካለን!!
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ፡፡
ነሃሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም
ባ/ዳር
(ምንጭ፤ ኢቢሲ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
ብአዴን…”በመቀጣጠል ላይ ያለውን ክልላዊና ሃገራዊ ለውጥ ለመጠበቅ፣ መሰረቱን ለማስፋትና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ እንዲቻል ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሕጋዊ የለውጥ እርምጃዎች በተከታታይ ይወሰዳሉ፡፡”
** በረከት ስሞዖን :- መሰረተቢስ እርምጃ ነው። ይሄ የሚጠበቅ ነገር ነበር። ይሄ ገና የመጀመርያቸው ነው (just a tip of the iceberg)። ወደፊት ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ይመጣሉ ብዬ እገምታለሁ።እንደ እኔ አስተሳሰብ ይሄ እርምጃ የመጣው አንደኛ ምክትል ጠ/ሚሩን በቅርቡ በተካሄደው የመተካካት ወቅት አለመደገፌ፣ በአቋሜ የማልደራደር ስለሆነ እና ፊት ለፊት ስለምናገር እንዲሁም የማጥራት አካሄድ (cleansing move) ነው። ምክንያቱም በረከት ከተለየ አካባቢ የመጣ ነው ስለሚባል ነው። እርግጥ ቤተሰቦቼ የኤርትራ ስር መሰረት ቢኖራቸውም እኔ ተወልጄ ያደግኩት ጎንደር ነው።”
… ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል! አማራ በሄደበት ይታረዳል! ይፈናቀላል!ይቃጠላል!ይበለታል! ፱ሚሊየን አማራ ተወልዶ ባደገበት ተጋብቶ ወልዶ በከበደበት ክልል(ጋጣ) እንኳን የማዕከላዊ ኮሚቴ አመራርነት ቀርቶ ወካይ የሌለው መጤ ሰፋሪ ይባላል.. ኤርትራዊ በትውልድ አማራዊ !?
— መለስ ዜናዊ ” በሽግግሩ ውስጥ አማራ የተወከለው “አመለካከቱን በሚያንፀባርቁ” የግድ የዚያ ብሔር ያልሆኑ እንደሆኑ አውቀን ነው”
ብአዴን…”ቀደም ሲል ሲመራበት የነበረው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ የህዝቡንና የአባላቱን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ግለጽ በሆነ ተሳትፎ እንዲሻሻል ይደረጋል፡፡ በዚህ ረገድ የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት የድርጅታችን አባላት ጥያቄ እስከሆነ ድረስ የድርጅቱን ስያሜ ጨምሮ ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮችም በአግባቡ እየተፈተሹ ሥርዓቱን በጠበቀ መንገድ ማሻሻያ ሊደረግባቸው ይችላል።”
***በረከት.. አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ከእኔ ግለ- አስተሳሰብ ጋር አብሮ ስላማይሄድ አልቀጥልም። I’m thinking of coping with it Lidetu’s style (የልደቱን ስታይል ለመከተል እያሰብኩ ነው)።አሁን ያለው ሁናቴ ፖለቲካን fair በሆነ መልኩ ለማካሄድ ያመቻል ብዬ አላምንም።”
ብአዴን..”ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ ማሻሻያ ሳይደረግበቸው የዘለቁት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎቻችን ውስጥ አንዳንዶቹ አገራችን ዛሬ ከደረሰችበት የዲሞክራሲ እድገት ደረጃ ጋር ተጣጥመው መሄድ አለባቸው የሚለውን የህዝብ አስተያየትና ጥያቄ ብአዴን በበጎ ጎኑ ይመለከተዋል፡፡
ጠ/ሚሩ ሹመት ሊሰጥዎ አስበዋል እንበል። ሹመቱን ይቀበላሉ ወይስ በተቃራኒው?
አቶ በረከት:- በፍፁም! የእስካሁኑ ይበቃኛል።
— የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች “(የልደቱን ስታይል ለመከተል እያሰብኩ ነው)። ልደቱ በተጣደበት ሁሉ ሲያማስል አንድ ነገር አላበሰለም!። ጭራሽም ፓርቲ ሰርቶ ከማፍረስ ወደ ⶃተኛ አማራጭ ‘እያመሰገኑ እያወደሱ’ መለጠፍንም ቢሆን አብይ አህመድ ጩኸታቸውን ቀምቶ ማስጮህ ጀምሯል…ተቃዋሚና ተቋቋሚወን ሁሉ ሥራ ፈት አደረገው ልበል!፧ እንግዲህ በእየድግሱ እየቀረቡ የፖለቲካ ተንታኝና በታኝ ልደቱ፡ በረከትና ጀዋር የአየር በአይር ፓርቲ ሊያቋቁሙ ይሆን? ከውጭ ገባን ያሉትም ቤተ ኢህአዴግ ቢሮ ሶፋ ላይ ተደርድሮ ባንዲራ ለበሶ ፎቶ ከመነሳት ውጭ ምን አተረፉ?
ብአዴን “በዜጎች ላይ የተፈጸመን ማንኛውንም ኀላፊነት የጎደለው ኢ-ሕገ መንግስታዊ ተግባር እያወገዝን በእንዲህ አይነት ድርጊት ውስጥ ገብቶ የተገኘ ማንኛውም ቡድን፣ የመንግስት ባለስልጣንና ግለሰብ የሃገሪቱ ህግ በሚፈቅደው አኳኋን ለህግ ቀርቦ ተጠያቂ እንዲሆን በጽናት እንታገላለን፡፡”
— የቀድሞው ጠ/ሚር ታምራት ላይኔ ባለቤት እርስዎ ላይ ወቀሳ ሰንዝረዋል። እርሳቸው በመታሰራቸው በእርግጥ ደስተኛ ነበሩ? ከሆነስ ለምን?
አቶ በረከት:- የታምራት ላይኔ ጉዳይ በፍርድ ቤት ተወስኖ ከዛ ደሞ በህግ መሰረት ተፈቷል። ፲፪ ዓመት ትምህርት ካላስተማረው እኔ ምንም ማረግ አልችልም። እስር ላይ የቆየው ባላደረገው ነገር አይደለም። ማንም ጣቱን ወደ እኔ አሁን ላይ ቢቀስር ለእኔ ምንም ማለት አይደለም።
ጠ/ሚ አብይ አህመድን ይህ የይቅርታ እና ምህረት ግዜ ወደፊትም መቀጠል አለበት። ዋናው ግን ይህ ሀገር sensitive ስለሆነ የ balance ስራ ሁሌ መሰራት አለበት።”
— በእርግጥ አቶ በረከት ስሞዖን የለውጥ ደጋፊ ናቸው? ወይስ ያለፈ ጥፋታቸው በይቅርታ በመታለፉ ደግፊ/ተለጣፊ? በእርግጥ ፖለቲካ/ሥልጣን ካልፈለጉ አማራ ካልፈለጋቸው በእርቅ ምሕረትና መደመር ማሳለጫ በኤርትራ ማሊያ ሊሰለፉ ይሆን?
ብአዴን ” አሁን ከተደረሰበት የትግል መድረክና ከለውጡ እንቅስቃሴ ጋር አብረው መጓዝ በተሳናቸውና ህዝባዊ ሃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት ባልቻሉ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ለይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ድርጅቱ ራሱን የማጥራት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡”
በረከት “ይሄ ገና የመጀመርያቸው ነው (just a tip of the iceberg)።” ሲሉ አማራ ክልልና ብአዴን ውስጥ አርቀው የቀበሩት መርዝ ሰንኮፉ ይመነገላል ብለው አውቀውታል!? ወይስ መኖሩን መጠቆማቸው ነው?
ብአዴን “የጥረት ኮርፖሬት እና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የተባሉት የልማት ድርጅቶች የክልሉ ህዝብ ሃብት እነደመሆናቸው መጠን የላቀ ልማት ማረጋገጥ በሚችሉበት አኳኋን መመራት ስላለባቸው ተጠሪነታቸውም ለክልሉ መንግስት እንዲሆን የፖለቲካ ውሳኔ ተወስኗል፡፡
[በረከት በመወለድ ያገኘው አማራነትና ተስፋዬ ግብረእባብ በሞጋሳ ያገኘው ኦሮሞነት ገዳ አሳዘነኝ]….አልተግባብቶም
“ብአዴን ራሱን የማጥራት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል!”
” አካባቢያችን አትገኝ! እና እገዳው መሰረተ ቢስ ሳይሆን ጥልቅ መሠረት ያለው ሥርተከል ለውጥ ነው በለው!
አሁንስ ጅብ በሚያውቁት አገር . .. ሆነ እንዴ?
ታሪኩ ዝ፟ ቀኜ መንዝ ላሎ ማማ ምደር
በረከት ስምኦን የሚዲያ ዘመቻ ምንን ግብ አድረጎ የተነሳ ነው? በመጀመሪያ የጠፋ ስሙን ለማደስ ይሆን ብዬ አሰብኩ፡፡ ምን የሚታደስ ስም አለውና ነው ይህ ጭራቅ ብዬ ሃስቡን ጣልኩት፡፡ መጽሃፉን ሊያሻሽጥ? ምናልባት፡፡ የፊት በሩን የዘጋብትን ህዝብ በጓሮ በር ገብቶ ለመከፋፍል መጽሃፉ አማራጭ መንገድ ነው፡፡ የገንዘብ ችግር ባይኖርበትም አስተሳሰቡን ለማስርጽ ሊጠቀምበት ይቸላል፡፡ መናልባት ለአማራ ህዝብ አዝኖ ይሆን? ህምምምም .. ከደቡብ እስከ ሰሜን፤ ከምስራቅ እስከ ምራብ፤ አማራ ሲፈናቅል ሲገድል እና ስልታዊ ጥቃት ሲፍጸምበት ተደራቢ ሆኖ “ትምከህትኛ ስልሆነ ነው” ያለ ግለሰብ ለምን ዛሬ የነጻነት ብርሃን ሲያይ ቆረቆረው? ይህ ሊሆን አይችልም፡፡ ታዲያ ለምን? የኔ ግምገማ የመቀሌ ጌ ቶቹ ባስቅምጡለት የፕሮፐጋንዳ እቅድ መሰርት የተካነበትን “ የብትና ማዳከምና መልሶ መዋጥ ” እቅድ እዬተገበረ ነው ፡፡ ይህንም እንደሚከተለው ላስረዳ፡፡
የበአዴንና ኦህዴድ ጥምርት፤ ያማራ ህዝብ፡ መሪ ድርጅቱ በአዴን፡ በስደት በበርሃና በከተማ ያሉ ተቀዋሚዎች ባጥቃላይ ሁሉም አማራ ባማራ ጉዳይ ወጥ አቋም መያዛቼውና በአንድ መሰለፋቼው ለፋሺስት ዎያኔ እንቅልፍ ነስቷል፡፡ ይህ “መርህ አልባ ጥምርት” መበተን አለበት፡፡ ሲበተን ይዳከማል፡፡ ሲዳከም ተራ በተራ ይሰለቀጣል፡፡ ታዲያ በዎያኔ ስልት ጠላትን ተራ በተራ እንጅ አንድ ላይ መግጠም ኪሳራው በዙ ስልሆነ አይደገፍም፡፡ ስለሆነም ስልታዊና በተጠና መልኩ አንዱን ጠላት አንዱን ወዳጅ ማድረግና ሁለቱንም ተራ በተራ መሰልቅጥ ተመራጩ መንገድ ነው፡፡ በረከትም እየሞከረ ያለው ይህን ነው፡፡
ኦህዴድና አብይን መደገፍ፤ በተጻራሪ በአዴንን ደመቀን ጠላት ማደረግ፤ የአማራ ህዝብን ጸድቅ አደርጎ መሪ ድርጅቱን ማጠልሼት፤ “ለአማራ ወጣት ተቆርቋሪ” የሆነው በረከት ያዘጋጀውን የስራ ፈጠራ እቅድ ገዱ የተባለ ያማራ ወጣት “ጠላት” ማደናቅፍ፤ ያማራ ክልል ባልሰልጣናት በኤርትራ ፕረዘዳንት ተመክረው በረከትን የመሰለ ያማራ ተሟጋች ማባረራቼው፤ እና ሌሎቹም የዘረዘራቼው በሙሉ የለውጥ ሃይሉን ለመበተን ያልሙ ካለቆቹ የወርዱለት ትርክቶች ናቼው፡፡በረከት ትወናውን እየትወነና እኛም “ወይ አለማፈር” እያልን ያለብት ሁኔታ ተፍጥሯል፡፡ ከሁሉም ምስኪን ሃይለማርያምን በረክት ለዘመናት ላጠፋው ጥፋት እንደ “ማምልጫ” መጠቀሙ በሰማይ ቤት መግቢያውንም ሳያሳጣው አይቀርም፡፡ በምድር የትም መሂጃ ያልው አይመስልም፡፡
በረከት በቃለመጠይቁ ማጠቃልያ ላይ ውግንናው ከማን ጋራ እንደሆነ ሳያውቀው አሳብቋል፡፡ የአማራ ደመኛ ጠላት የሆነው ወያኔ አማራን በሌሎች ክልሎች/ቢሄርሰቦች/ ለማሰጠላት ለ 30 አመት የሚረጨውን መርዝ ደግሞልናል፡፡”ያማራ ክልል አደገኛ አቅጣጫ ይዟል፡፡ ሃገሪቱን ሊበትናት ይችላል” ክልሎች ሆይ! አማራ ሊያጠፋችሁ ነው፡፡ ሃገሪቱ ልትፈርስ ነው፡፡ መብታችሁን ሊደፍጠጥ ነው፡፡ ከነጻአውጭ ዎያኔ ጎን ቁሙና አማራን እናጥፋ ማለቱ ነው፡፡ በወያኔ ያልተዘረፈ፡ ያልተጨፈጨፈ፡ ፍዳውን ያላዬ ክልል ቢኖር ሰሚ ሊኖር ይችል ነበር፡፡ ማን ይሰማሃል?
በረክት አንተ ዛሬ ለዲሞክራሲ፡ ለነጻ ምርጫ፡ ለሰላም፡ ላማራ ወጣት፡ ፤ለአማራ ህዘብ፡ ለለውጥ፡ ወዘተ ጠበቃ ሆነህ ቀርብሃል፡፡ እኛ የምናውቀው አንተ የዚህ ሁሉ ተቃራኔ መሆንህን ነው፡፡ በዚህ ድርጊትህ የአሜሪካ መንግስት ግዛቱ እንዳትገባ የከለከልህ፡ ሃና ጎበዜ በጭራቅ የመሰልችህ፡ የባዴን ካደሬ እንደ መላከ ሞት የሚፈራህ፡ ህዝብን እቅድ አውጥተህ ያስጨፈጭፍክ፤ ምርጫና ዲሞክራሲን ባፍጢሙ የደፋህ፤ አማራን አስረህ ለውርደት ያበቃህ፡ ወጣቶቻችንን አንገት ያስደፋህ፡ የወጣህበትን ማህበረሰብ ክደህ ከዘረኛው የአጋዚያን ነቅናቄ የወገንክ ከሃዲ መሆንክን ነው፡፡ አምባሳደም የማትሆነው ሃገሮች ባለህ ሪኮርድ እንደማይቀበሉህ ስልምታውቅ ነው (እውንት አብይ ጠይቆህ ከሆነ)፡፡
የማያውቁህ ሃገር ሂደህ ይህን ሁሉ ብትል (ለምሳሌ ሰሜን ኮርያ) አንድ ነገር ነው፡፡ እዚሁ ሌት ተቀን ልታፈርሳት ከምትደክምው ኢትዮፕያ ላይ እንዲህ ያለ ደፍረት?
ዲያቢሎስ እባክህ ከአማራ ምድር ራቅ!
በረከት በኤርትራዊነቴ ምክንያት ነው የተገለልሑት እያለ የሚዘላብደው በእውነት የሚያዝንለት ሰው የሚያገኝ እየመሰለው ይሆን? ኣሁን እንግዲህ ይህ ጭራቅ በማህል ሀገር መላወሻ ስለሚያጣ፣ ወደ መቀለ ሄዶ ከብጤዎቹ ዎያኔዎች ጋር ኣብሮ ይደበቅ!!!!!