• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ነጻነት ሰው ከመሆን የሚገኝ መብት ነው”

November 15, 2016 02:13 am by Editor 3 Comments

ግዛው ለገሰ በጣም መሠረታዊና አንገብጋቢ፣ ጊዜያዊም ጉዳዮችን አንሥቷል፤ በበኩሌ ጉዳዮቹን በማንሣቱ በጣም እያመሰገንሁት አስተያየቴን በአጭሩ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

‹‹ህወሓት የተቋቋመው በአማራ ጥላቻ ነው፡፡ ይህን ሀቅ ሳይቀበሉ ስለነፃነት ማታገል አይቻልም፡፡ ነፃነት ደግሞ የዜግነት መበት እንጂ የወል መብት አይደለም፡፡ ነፃነት በማንነት ትግል አይገኝም፡፡›› ግዛው በጣም መሠረታዊ ነጥብና ሀሳብ አቅርበሃል፤ ነገር ግን ድብልቅልቁ ወጣብኝ!

መነሻ፡–‹‹ሕወሀት የተቋቋመው በአማራ ጥላቻ (ላይ?) ነው፤›› ከዚህ ትነሣና፡–

‹‹ይህንን ሀቅ ሳይቀበሉ ስለነጻነት ማታገል (መታገል?) አይቻልም፤›› ትላለህ፡፡

እንደምረዳው ግልጽ ያልሆነልኝ ግዛው ሁለቱን ዓረፍተ ነገሮች እርስበርሳቸውና እያንዳንዳቸውን ከነጻነት ጋር ያቆራኛቸው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ በእኔ አስተሳሰብ ምንም ግንኙነት የላቸውም፤ የአማራን (በአንተው ቃል ለመጠቀም) ጥላቻም ሆነ በአማራ ላይ ያለውን ጥላቻ ይዞ ለነጻነት መታገልም ሆነ ማታገል የማይቻልበት ምክንያት አይታየኝም፤ ነጻነትን ‹‹አማራ›› ከምትለው ጋር አቆራኝተኸዋል! እንዴት ብሎ?

ሁለተኛው ዓረፍተ ነገርህ ለእኔ በጣም ፈር የለቀቀ ነው፤ ለእኔ ነጻነት ሰው ከመሆን የሚገኝ መብት ነው፤ ስለዚህም የሰው ልጆች ሁሉ መሠረታዊ የጋራ (የወል) መብት ነው፤ ከዜግነት ጋር ማያያዝህ በመሠረቱ ትክክል ቢሆንም ነጻነት የሌላቸው ዜጎች በያለበት ይገኛሉ፤ ከዚሁ ጋር አያይዘህ ‹‹ነጻነት በማንነት ትግል አይገኝም፤›› ስትልም በዝቅተኛ ደረጃ ያሉ ማንነቶችን (ለምሳሌ ባል/ሚስት መሆን፣ ክርስቲያን/እስላም መሆን፤ የዚህ/የዚያ ጎሣ አባል መሆን፣ …) ከሆነ ትክክል ትመስለኛለህ፤ በሰውነትና በዜግነት ደረጃ ካየኸው ግን እንለያያለን፤ ለእኔ መሠረታዊው ነጻነት የሚፈልቀው ማንነትን አንደኛ በሰውነት ደረጃ ሁለተኛ በዜግነት ደረጃ እያዩ በመታገል ነው፤ እኩልነት የነጻነት አካል ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፡፡

እኩልነትን ከነጻነት ጋር አቆራኝተህ ለመታገል የምትችለው በሰውነትና በዜግነት ደረጃ ብቻ ነው የምትል ከሆነ አብረን እንቆማለን፤ ሌሎች ዝቅተኞች ማንነቶች ለእኩልነት ቦታ የላቸውም፤ እንዲያውም አብዛኛውን ጊዜ ጸረ-እኩልነት ናቸው! የአንዳንድ ጎሣዎች አቀንቃኞች የጎሣቸው ሥርዓት ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› ነው፤ ነጻነት አለበት ይላሉ፤ (በሴቶች ላይ የሚያሳድሩትን ክፉ ጭቆና ይረሱታል!) ይህ ወይ የማያውቁትን ለማሞኘት ነው፤ ወይም ስለዴሞክራሲና ስለእኩልነት፣ ስለነጻነት አለማወቅ ነው፡፡

ግዛው ያነሳኸው ዋና ነጥብ ሁሌም የሚረሳና በጎሠኛነት አረም የተሸፈነ ነው፤ ዜግነት! የአንድ አገርን ሰዎች በሕግ በነጻነትና በእኩልነት አዋኅዶና አዛምዶ የሚይዛቸው ዜግነት ነው፤ በጎሠኛነት ያለው መንገድ የወያኔ ብቻ ነው፤ የወያኔን መንገድ ተከትሎ ወደዜግነት መድረስ የሚቻል አይመስለኝም!

በመጨረሻ አንድ ያነሣኸው ነጥብ አለ፤ ጥላቻ በመሠረቱ ክፉ የአእምሮና የመንፈስ በሽታ ነው፤ በዚህም በሽታ ይበልጥ የሚጎዳው ማኅደሩ ነው፤ ስለዚህም ‹‹አማራን›› መውደድም ሆነ መጥላት፣ ‹‹በአማራ›› መወደድም ሆነ በጥላቻ መታየት ለዜግነት፣ ለአኩልነት፣ ለነጻነትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግዴታ አይደሉም! በተግባር ፍቅርና አብሮ የመኖር ልምዱ መኖሩን ከተለያዩ ጎሣዎች የወጡት ወጣቶች ተጨባጭ ማስረጃዎች ናቸው፡፡

እንኳን ሰው ነግሯቸውና አይተውም መረዳት የማይችሉ በሥልጣንና በሀብት በተለወሰ ጎሠኛነት የሰከሩትን ለማሳመን አይቻልም፤ በማየት መረዳት የሚቻል ቢሆንማ ኤርትራን አይቶ ልብ መግዛት ቀላል ነበር፤ በፖሊቲካ ጉዳይ ገና በሕጻንነት ደረጃ መሆናችን የሚረጋገጠው ጎሠኛነት በሃያ አምስት ዓመታት ውስጥ እያደገና እየሰፋ፤ ተምረናል የሚሉ ሰዎች የተሰለፉበት የእንጀራ እናት ሆኖ ማደጉና መስፋፋቱ ነው፡፡

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ኅዳር/2009

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. ገብረየሱስ says

    November 23, 2016 07:20 pm at 7:20 pm

    ህወሓት የተቋቋመው “በአማራ ጥላቻ ነው” ይህ ስህተት ነው መስተካከል ኣለበት ያንተውና የሌላውን ለመለየት። ልክ እንደ መኢሶን፣ ኢህኣፓ፣ ኢድዩ፣ ደርግ፣ እጨዓት፣ ሌሎችም ህወሓት ተመሰረተ። በሂደት ግን ሌሎች ኣንድነቶች ሲሰው እነ ስብሃት ነጋ፣ ኣባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ ታዳጊው መለስ ዜናዊ እድል ኣግኝተው የኣማራ ጥላቻ ካርታ ተጫወቱበት። ስለዚህ እነኝህን ለይተን ካስቀመጥናቸው ከኣንድነቶች ጋር ለመስራት ይቀላል። ካልሆነ በትግራዮች በኣማራ በኦሮሞ በዓፋሮች ስም እንደ ወያነ በጅምላ መወንጀል እውነተኞች ይራራቃሉ መልካም ስራ ሊሰራም ኣይችልም።

    Reply
  2. Gebito says

    November 25, 2016 04:53 pm at 4:53 pm

    Goitay Golgul,

    Yet again there is an image in the article but no mention of who is who and indication of the source or credit to it. Still you claim to be credited – funny that, especially news mixed with opinions of the author. Last time you said that it was intentional a hand written note was scanned reverse side. Come on guys grow up stop this militancy in your replies to readers. All these recycled cut-and-paste news sites pride yourselves as journalists you don’t even have a single reporter or correspondent anywhere so I suggest take it easy and grow slowly. Don’s chase your tails in attempting to be reliable sources. Gebito!

    Reply
    • Editor says

      November 26, 2016 12:17 am at 12:17 am

      Gebito,

      If, with evidence, you are able to provide us the source of the picture, we will give credit for that. The rest is garbage.

      Editor

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule