• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ታሪክን ምርኮኛ የማድረግ ዘመቻ

February 9, 2017 02:32 am by Editor Leave a Comment

ከሰሞኑ የፖለቲካችን የስበት ማእከል ታሪክ እና የታሪክ ባለሙያዎች ሆነዋል። ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ የተባሉ የታሪክ ምሁር ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በሶሻል ሚዲያው ከፍተኛ አዋራ ማስነሳቱ ሳያንስ፣ የተዳፈኑ የመሰሉ ጉዳዮችንም በመቀስቀስ ላይ ይገኛል።

በመጀመሪያ የዶክተሩን ቃለምልልስ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በጽሞና ለመከታተል ሞክሬአለሁ። በዚህም ተጠያቂውን ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ከሙያም  ሆነ ስነምግባር አንጻር የበቃ ችሎታቸውን ለመታዘብ ችያለሁ። ውዝግቡ ከተቀሰቀሰም በኋላ የኦሮሞ አክቲቪስት ነን ከሚሉ ሰዎች በተሰነዘረውን ክስ ላይ ተመስርቼ ቃለ-ምልልሱን በሂሳዊ አይን ለማየት ሞክሬአሁ። ህዝብ የተሰደበበት እና ወደ አንድ ሚዛን ያጋደለ አቀራረብ ፈልጌ ማግኘት ተቸግሬአለሁ። እንዳውም ዶ/ር ሃይሌ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አወዛጋቢ ቦታ ስለሚይዘው ግራኝ አህመድ በጎ የሆነ እይታ እንዳላቸው መታዘብ ይቻላል። ግራኝ አህመድን  በሚመለከት ያላቸው እይታ በአዲስ አበባ ዩኒቪርሲቲ የታርክ ትምህርት ክፍል እውቅ የታሪክ ተመራማሪ ከነበሩት ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደ አረጋይ ጋር ተመሳሳይ እይታ እንዳላቸው ማወቅ ይቻላል። በዚህ መሰረት አክቲቪስቶች ነን የሚሉት ክስ መነሻ ሌላ መሆን አለበት በሚል አዲስ መላምት ጥረቴን ሌላ ምክንያት ቢኖርስ ወደሚል አቅጣጫ ለወጥሁት።

በዚህ ሂደት ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ የኦሮሞ አክቲቪሰት ነን የሚሉት አክራሪ ብሄረተኞች በዶ/ር ሃይሌ ላይ  ዛቻ እና ማስፈራሪያን ጨምሮ፣ አጓጉል ስሞችን እስከ መስጠት የደረሰ ዘመቻ ውስጥ እንደነበሩ መረዳት ይቻላል። ከዛም አልፎ በተማሩበት የታሪክ ጥናት መስክ ያላቸውን ችሎታ በማጣጣል፣ የዶክትሬት ደረጃቸውን ሃሰተኝነት በመናኘት፣ ማንኛውም መድረክ እንዳይጋበዙ፣ ተደማጭነት እንዳያገኙ እንዲሁም ከሚያስተምሩበት ስራ እንዲባረሩ ያላደረጉት ጥረት የለም ማለት ይቻላል። የነፍጠኞች ተላላኪ ወኪል፣ የኦሮሞ ደመኛ ጠላት ተደርገው በአደባባይ እንዲሳሉም ተደርጎዋል። ይህ አልበቃ ብሎ በተለያዩ መድረኮች ቀርበው ጥናታዊ ጽሁፍ እንዳያቀርቡ ቅስቀሳ ሲደረግ እንደነበረ በቅርብ ግዜ የምናስታውሰው ነው። ለዚህ አንድ ምሳሌ ብንጠቅስ ባለፈው ዓመት ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ጋር ባዘጋጁት ኮንፍረንስ ዶክተሩ እንዳይጋበዙ በአዘጋጆቹ ላይ ጫና ሲደረግ ነበር። ሌላው ዶ/ር ሃይሌን የተመለከቱ ተለያዩ መዛግብትን በድረ-ገጽ በመበተን የማስተማር ችግር እንዳለባቸው እንዳውም ዶክትርነታቸው የሃሰት እንደሆነ ሲነዛ ነበር። ጉዳዩን በቅርብ የምንከታተል ዶ/ር ሃይሌ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ያሳተሙትን ጥናታዊ የሆነ መፅሃፍ ይፋ ሲደረግ የሚቀርብባቸው ክሶች መሰረተቢስ፣ በጥላቻ የተነሳሱ እንደሆኑ ለመታዘብ ችለናል። ይህ አልበቃ ብሎ፣ ዶክተሩ በሚያስተምሩበት ዩኒቨርሲቲ ላይ ጫና በማሳደር ከስራ እንዲባረሩ ለማድረግ ዘመቻ ተደርጎ እንደነበረ እናስታውሳለን። ሰሞኑንም ይህን አይነቱ ዘመቻ በድጋሚ ተጀምሮ ፊርማ የማሰባሰቡ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። እዚህ ጋር ሁላችንም መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ግን ለምን ዶክተር ሃይሌ ላሬቦ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጥቃትና የጥላቻ ኢላማ ተደረጉ የሚለው ጥያቄ ነው።

ዶክተር ሃይሌ ላሬቦ ተመርጠው የዚህ ሁሉ የስም ማጥፋት እና ማሸማቀቅ የውርጅብኝ ዘመቻ የተከፈተባቸው በሶስት ምክንያቶች እንደሆነ ነው።

አንደኛው በዚህ ወቅት የፖለቲከኞች ቁማር መጫወቻ በመሆን እየተበላሸ ያለውን የሃገራችን ታሪክ ሳይፈሩ እውነቱን ከሃሰቱ በመለየት የመናገር ድፍረት በማሳየታቸው ሲሆን፣

ሁለተኛው የዶክተሩ የት መጣነት (የዘውግ ማንነት) ከደቡብ በመሆኑ ነው።

ሶስተኛው ምሁሩ ከዚህ ቀደም የጎሳ ፖለቲካ ዝንባሌ ባላቸው የታሪክ ጸሃፊዎች የተደረሰውን የታሪክ ልብ ወለድ እርቃኑን በማስቀረት ያሳዩት ቆራጥነት ነው።

በአሁኑ ወቅት ጎሰኞች የልብ ልብ አግኝተው ታሪካችንን በማጣመም ብቻ ሳይወሰኑ፣ ትክክለኛ የሆነው የሃገራችን ታሪክ እንዳይነገር የተለያዩ ማሸማቀቂያዎችን በመጠቀም የታሪክ ባለሙያዎች የዳር ቆመው ተመልካች የሆኑበት ሁኔታ ተፈጥሮአል። የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም የፖለቲካ አጀንዳ ያነገቡ ግለሰቦች በታሪክ ላይ የለየለት ውንብድና በመፈጸም የተወላገደ ታሪክ ሲጻፍና ሲነገር እያየን ነው። በዚህም የተነሳ ብዙዎቹ  የታሪክ አዋቂዎች ስድብን፣ ነቀፋን በመፍራት ብሎም በፖለቲካዊ ተአርሞ (political correctness) ተሸብበው እንዳላዩ ሆነው ማለፍን በመረጡበት ወቅት ነው እንግዲህ ዶ/ር ሃይሌ ወዳደባባይ በመውጣት ሙያቸው የሚጠብቅባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት እየሞከሩ ያሉት።

ሳይንሳዊ የጥናት ዘዴን በሚከተል አካዳሚያዊ  ምርምር ምንም ነገር ቢሆን ከመፈተሽ፣ ከመመርመር፣ ከመተችት እና  ነጻ (immune ) አይደለም። በታሪክ ጥናት ዘርፍ ውስጥም ባለሙያው የምርምር ህግን ተከትሎ፣ በአመክንዮ ላይ ተመስርቶ ማንኛውንም ነገር ማጠየቅና እውነተኝነቱን ማረጋገጥ መሰረታዊ ግዴታው ነው። ከዚህ ውጭ የታሪክ ባለሙያው በማህበራዊ መገናኛ ላይ በሚፈጠሩ የጫጫታ ማእበሎች በመርበትበት እና ሙያዊ ግዴታውን ከመወጣት ወደኋላ ማለት የለበትም።

በዚህ በኩል በዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ቃለመጠይቅ ላይ የተነሳውን የሰሞኑ እሰጥ-አገባ ስንመለከት፤ የታሪክን በማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ጩህት በማንበርከክ ሃቁን ለማዳፈን የሚደረግ መውተርተር እንደሆነ መረዳት እንችላለን። በዶ/ር ሃይሌ በኩል የተያዘውም አቋም ይበል የሚያሰኝና አሁንም ሳይንሳዊ የሆነውን የታሪክ ጥናት ዘርፍ ፈለግ እስከተተለ ድረስ መቀጠል ያለበት ጥረት እንደሆነ ነው። በነገራችን ላይ በአካዳሚክ  እና  ሃሳብን በነጻነት ጸር የሆኑት፤ የዘመናችን አክራሪዎቹ ተግባት ያስገነዘበን ሌላ ነገር ቢኖር ከዚህ የበለጠ እርምጃ የመውሰድ አቅም ቢሆኖራቸው አሁን በስልጣን ላይ ካለው የህወሓት ቡድን የበለጠ ነገር ሊከሰት እንደሚችል አመላካች ነው።

ሁለተኛውና አክራሪ የኦሮሞ ብሄረተኞችን ከማስቆጣት አልፎ ወደ መረረ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከተታችው ምክንያት የዶክተሩ የመጡበት አካባቢ ከደቡብ ኢትዮጵያ መሆኑ ነው። በእነዚህ አክራሪ ብሄረተኞች አመዳደብ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰሜንና ደቡብ በሚባሉ ሁለት ዘውጎች (dichotomies) የተከፈለ ሲሆን፣ ሰሜነኛው  የአቢሲኒያ ዘውግ የለየለት ጠላት፣ ጨቋኝ እና የቀድሞ ስርዓት ናፋቂ በሚል መለያ ሲጠሩት ኖረዋል። ከዚህ ውጪ ያለው የኦሮሞና ደቡብ ዘውግ ከሰሜነኞቹ አንጻር በተቃራኒ የቆሙ ብቻ ሳይሆኑ የጨቆና እና የብዝበዛ ሰለባ በመሆናቸው አጋር አድርገው ይመለከቷቸዋል። የዶክተር ኃይሌ ታሪክ ትንተና የበለጠ ቁጣን የጨመረው ይህን የሁለት ዘውግ አከፋፈል ዋጋ ቢስ ስለሚያደርገው ነው። እዚህ ላይ ክርክሩ ያለው በአመክንዮ ወይንም ሳይንሳዊ ፈለግን ተከትሎ የሚደረስበት አካዳሚያዊ ድምዳሜ ሳይሆን በአክራሪ ኦሮሞ ብሄረተኞች አይን ይሄኛው ምሁር ከዚህኛው ዘውግ ከመጣ ወገንተኝነት ማሳየት ያለበት ለእውነት ወይንም ሙያዊ ግዴታው ሳይሆን ለመጣበት ጎሳ ወይንም አካባቢ መሆን አለበት የሚለው የጠባብነት መነሻ ነው። ይህ አይነት ጠባብ አክራሪነት በአካዳሚው ዓለም ገብቶ የሚያደርሰው ጉዳት ለጠቅላላው የሃገራችን ታሪክ ብቻ ሳይሆን በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ላይ የሚደረጉ የወደፊት ምርምሮች/ጥናቶችን የተዓማኒነት ጥርጣሬ ላይ የሚጥል ነው።

አክራሪ የሆኑት የኦሮሞ ልሂቃን በዶክተር ሃይሌ ላሬቦ ላይ የመረረ አቋም እንዲይዙ ካደረጉ ምክንያቶች ሶስተኛው፣ ምሁሩ ከዚህ ቀደም የጎሳ ፖለቲካ ዝንባሌ ባላቸው የታሪክ ጸሃፊያን የተደረሰውን ልብ-ወለዳዊ ታሪካ ገላልጠው እርቃኑን በማስቀረታቸው ነው። እኒህ አክራሪዎች ዶክተሩን ጠምደው የያዙበት ምክንያት ሌላ ሳይሆን ለምን እኛ የምንፈልገውን ታሪክ አልነገረንም ነው።

በኦሮሞ ጥናት ዘርፍ ውስጥ አዘውትረው ከሚጠቅሷቸው ጸሃፊያን መካከል ሲሳይ ኢብሳ፣ መኩሪያ ቡልቻ፣ አሰፋ ጃለታ፣ እና ቦኒ ሆለኮምብ (ብቸኛዋ የውጭ ሰው) ስራዎች ብንመረምር የአካዳሚክሱን ዓለም ምርምር ስርዓትን ያልተከተለ፣ የፖለቲካ ዓላማን ለማሳካት ተብሎ ብጭቅጫቂ እውነቶችን ከበዙ ውሸት ጋር በማዳበል የተደረሱ መሆናቸውን መረዳት ይቻላል። እንዲውም በታሪክ እና ስነ-ሰብ ጥናት አንቱ የተባሉ ምሁራን ከላይ በተዘረዘሩት ጸሃፊዎች ስራዎች ላይ ካቀረቡት ሂስ አንዱ ‘በምንም አይነት መለኪያ አካዳሚያዊ ደረጃን የማይመጥኑ’ እንደሆኑ ነው።

እነዚህ ከታሪክነት ይልቅ ለፕሮፓጋንዳ ፋይዳ ታልመው የተጻፉ ድርሳናት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ፣ በቂም በቀል እና የቁጭት ትረካዎች ላይ በማተኮር ታሪክ ሊኖራት የሚገባትን የመዳኘት ስልጣን እንዲንጋደድ በማድረግ የፖለቲካ መገልገያ እንድትሆን አድርገዋል። የዶክተር ሃይሌ ላሬቦ አደባባይ ወጥቶ የእነዚህን ሃሳውያን የታሪክ ትርከት ገልብጥቡን ያወጡት። የአክራሪ ብሄረተኞቹን ትርከት በተጨበጠ በታሪክ ማስረጃ ሲፈተን ለእውነት ሚዛን ላይ መቀመጥ እንደማይበቃ ዶ/ር ሃይሌ በትንተናቸው አረጋግጠዋል። አክራሪዎቹ የቆሙበትን የሃሰት ትርክት ከስር መሰረቱ በማናጋታቸው ነው የወከባ እና ማሸማቀቅ ሰለባ የሆኑት።

እንደ ሃገር በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ምህረት የለሽ ትችቶችን እንዲሁም ማጣጣሎችን እንደ ቋሚ ተግባራቸው  ይዘው የነበሩ እኒህ አክራሪ ብሄረተኞች አለን የሚሉትን የታሪክ ትርከት የሚያጠይቅ ባለሙያ ወደ አደባባይ ሲመጣ ዝም የማሰኘት በዘመቻ ሲጠመዱ ማየትን የመሰለ አሳሳቢ ነገር የለም። ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር የለችም፣ ታሪኳን ደብታራዎች የጻፉት ነው፣ ምኒሊክ ጥቁር አፍሪካዊ አይደለሁም ብሎአል፣ አቢሲኒያ በ19ኛው ክፍለዘመን ባደረገችው ወረራ 9 ሚልዮን ኦሮሞዎች አልቀዋልን የመሳሰሉ የታሪክ ፍብረካዎችን እንድንቀበል ያልተደረገ ሙከራ አልነበረም። ይባሱኑ ባለሙያው ታሪክን በተለየ ዓይን እንድናይ በማድረጉ ሃገር ይያዝልን ማለት፣ አንድ ጸሃፊ እንዳለው አለን በሚሉት የታሪክ መሰረት የራስ መተማመን ችግር (cultural insecurity) እንደሚጎላቸው ያሳያል።

እንደ ወጉ ከሆነ በዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ትንታኔ ወይንም የታሪክ አቀራረብ አለመስማማኝነት ተገቢ ሲሆን፣ ነገር ግን ከጭብጡ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ክሶች በመደርደር አቅጣጫ ለማስቀየር መሞከር እውቀትም ብልጠትም አይደለም። የቀረበውን የታሪክ ትርክት የሚቃወም ወገን አለኝ ከሚለው ማስረጃ እና የታሪክ አተናተን ጋር መቅረብ ሲቻል፣ ጉዳዩን ህዝባችን ተሰደበ ተንቋሸሸ በሚሉ አጓጉል ምክንያቶች ወደሌላ መውሰድ አክራሪ ብሄረተኞቻችን ምን ያህል ሃገራችንን እና ህዝብን ወደ አደገኛ  መንገድ እየወሰዱአት እንዳለ ያመላክታል። ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ በሃገራችን የአካዳሚክ ምርምር ነጻነት እና ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት የባሰ አደጋ ውስጥ እየገቡ እንዳለ ጠቋሚ ነው። ይህ ድርጊት ታሪክን ከማጣመም የከፋ ወንጀል ባሻገር፤ የሚፈጥራቸው ሌሎች አስከፊ መዘዞችም አሉ። እነዚህ አክራሪ ብሄረተኞች የደረሱበት ነገርን የማደፍረስ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃም ጭምር ሌላ አይነት የኢትዮጵያ ታሪክ ትርከት ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ  ፋታ የለሽ  የተቀናጀ ዘመቻ መሰረታዊው ምክንያት የኢትዮጵያ ምሁራን – በተለይ ወጣቶች ቸልተኝነት እና በበቂ ሁኔታ የተቀናጀ እና ተከታታይነት ያለው ምላሽ የመስጠት ጥረት ባለመኖሩ ነው።

(ዶ/ር ነብዩ ጋቢሳ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule