ከኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ፓርቲ ለጦር ሃይሎች የቀረበ ጥሪ ዘረኛው የወያኔ/ኢሕአዴግ ቡድን ላለፉት 25አመት ሀገር በመከፋፈልና ሕዝብን በመግደል የፈፀመው እልእቂት አነሰ ብሎ አሁን ከሰሜን ሸዋ እስከ ጎንደር ክፍለ ሃገር ባለው ወገናችን ላይ የፈፀመው የዘር ማጥፋት አላማውን እያፋጠነ ነው። ለዚህም እውን ማስረጃው በየጊዜው ከሚያወጣው መግለጯወችና አዋጆች መገንዘብ ይቻላል። ይህ አልሞት ባይ ድርጊት የመጨረሻ ውእሳኔአቸው በመሆኑ ለአጋዚ ወታደሮቻቸው ለሰው ልጆች ሕሊና የሚቀፍና የሚሰቀጥጥ ትእዛዝ በተግባር እንዲፈፀም አስተላልፏል። ከዚህ አዋጅ በመነሳት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በሰሜን ክፍለ ሃገራትና በአዲስ አበባ ውስጥ አሮጊት ሽማግሌ ወጣትና ሕፃናት በተገኙበት አካባቢ እሳት በማጋየትና በእስር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችንን እንዲሁም የከተማ ነዋሪዎችን የጥይት መለማመጃ አድርገዋቸዋል። (የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply