• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወፌ ቆመች በሉና!!

September 13, 2012 02:06 pm by Editor 5 Comments

መረጃ ለአንድ ማህበረሰብ ከምንም በላይ አስፈላጊና አንገብጋቢ አጀንዳው ነው። ይህ የሚሆነው በአግባቡ ሚዛኑን ጠብቆ ሲራመድ ብቻ ነው። ስርዓት ጠብቆና በተቻለ መጠን ሙያዊ ስነምግባሩን ተከትሎ መራመድ የሚችል ሚዲያ የወደፊቱን በማየት ህብረተሰብን ያነቃል፣ ያሳስባል፣ ያዘጋጃል፣ የተለያዩ ሃሳቦችን ገደብ ሳያደርግ ያስተናግዳል። በዚህ እሳቤ ላይ ተመስርቶ ለመስራት የተስማማው የጎልጉል ኤዲቶሪያል ቦርድ በአገራችን አዲስ ዓመት ዋዜማ ለንባብ ሲውል ቀዳሚ ጥሪው ያደረገው ለመቆም የሚውተረተር ህጻን የሚበረታታበትን “ወፌ ቆመች” የሚለውን ባህላዊ ቃል ነው። ወፌ ቆመች!!

ሚዲያ እንደ ንፋስ ከነፈሰና በስማ በለው ከነጎደ ስቶ ከማሳቱ በላይ ማህበረሰብን ሚዛን በሌለውና በተራ አሉባልታ በማዥጎርጎር ቀላል የማይባል የስሜት ግሽበት ያስከትላል ብለው ከሚያምኑት ክፍሎች ተርታ ራሳችንን እንመድባለን። በተራ ዘለፋና ስድብ አዘል መልዕክቶች የትኛውንም ዓይነት አስተሳሰብና የትኛውም ዓይነት አቋም ያላቸውን ክፍሎች ማስተማር፣ ማረምና መገሰጽ አስቸጋሪ ነው ብለን ስለምናምን ለመቆም የምንውተረተረው ከዚህ የጸና ዓላማችን ዝንፍ ሳንል እንደሆነ ለምታቋቁሙን አስቀድመን ለማሳወቅ እንወዳለን።

ሁላችንም እንደምንረዳው በአሁኑ ወቅት በስፋት የሚስተዋለው የመሞጋገስ አካሄድ ብቻውን ወደሚፈለገው ግብ ያደርሳል ብለን ከቶውንም አናምንም። ኢትዮጵያን “አውራ ፓርቲ ነኝ” በማለት ያለ ህዝብ ይሁንታ እየመራ ያለው ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን የተቃዋሚው ጎራም  ሲሳሳት – ተስተካከል፣ ባለበት ሲረግጥ – ተንቀሳቀስ፣ ሲረጋና ሲጋገር – ሩጥ፣ ከህዝብ ሲርቅ – ወደ ህዝብ ተጠጋ፣ ውስጣዊ ዴሞክራሲ ሲጎድለው – ተመለስ፣ በስሜት ሲነዳ – አስተውል፣ ራዕይ አልባ ሲሆን ራዕይ ሰንቅ፣ ቅርብ አዳሪ ሲሆን ሩቅ ተጓዥ ሁን… አልሰማ ሲልና ወደ በረዶ አለትነት ተቀይሮ የለውጥ ጠረን ካጣ በቃህ፣ ለተተኪ አስረክብ… የሚል ከወተት እስከ አጥንት የጠጠረ ሂስ ሊቀርብበት ይገባል ብለን እናምናለን።

አገራችንና ህዝቧ የተቆፈረላቸው የጎሳና የዘር ጉድጓድ አፉ ሰፊ፣ ጥልቀቱ የራቀ፣ መጠኑ ትልቅ በመሆኑ ይህንን ገደል የመድፈን ስራ ከቶውንም ዕረፍት የሚሰጥ ባለመሆኑ ዜጎች ከጎሳ ይልቅ ለመፈቃቀርና ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንዲሰጡ ማስተማር ከየትኛውም አገር ወዳድ ዜጋ የሚጠበቅ እንደሆነ ይሰማናል። በአንድ ሰው ነፍስና የሞት ወለል ላይ የተቸነከረችው አገራችን ከሙት መንፈስ አመራርና ራዕይ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በተደጋጋሚ በሃዘን ድባብ ውስጥ የሰነበቱት የኢህአዴግ አመራሮች ነግረውናል። አገሪቱ በሙት መንፈስ እንደምትመራም አረጋግጠውልናል። አገር መሸጥና የአገርን ታሪክ ማጉደል፤ ከሌላው ህዝብ ላይ እየዘረፉ የራስን ቆዳ ማስዋብ፣ አገርን በዘርና በጎሳ በልቶ ማባላት፣ የባህር በሯንና መሬቷን መሸጥ፣ የሚበሉና የበይ ተመልካች የሆነ ህዝብ መፍጠር፣ የፕሬስ ነጻነትን ማሸግ፣ የመናገርና የመሰብሰብን ተፈጥሯዊ መብት መዝጋት፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ማሳደድ፣ ጋዜጠኞችንና ንጹሃን ዜጎችን ማሰር፣ አገር ወዳዶችን መግረፍና ማሰቃየት፣ አፈናና የአፈና ተቋማትን በማደራጀት ስልጣንን በአንድ ብሄረሰብ ዙሪያና በቤተሰብ በማካለል ዜጎችን ባይተዋር ማድረግ… እንደ ታላቅ ጀብድና ዝና ተቆጥሮ “አጽምህ ይምራን” ሲባል መስማት እጅግ አስነዋሪና ከባድ አገራዊ ውድቀት ነው።

ኢህአዴግ የሚያሰራጨው ፕሮፖጋንዳ ሰለባ ያደረገው ህዝብ፣ ሰለባ ካደረገው የፕሮፖጋንዳ ባህር ይላቀቅ ዘንድ አበክሮ መስራት ካልተቻለ ሁሉንም ነገር አዳጋች ያደርገዋልና “ወፌ ቆመች” በሉን ስንል እንዲሁ ተረት ለማስታወስ አይደለም። ኢህአዴግ አማራጭ መገናኛዎች እንዳያብቡ በውስጥም ሆነ በውጭ አገር ከፍተኛ ሃብት እያፈሰሰ የሚዋጋው የሚዲያን ኃይል ስለሚረዳው ነውና ይህ እልህ እኛም ዘንድ ሊፈጠር ግድ ይላል። በተረትና በፉከራ የሚፈጠር አንድም ነገር የለምና ከወዲሁ መድረሻውንና መነሻውን ያስቀመጠ የሚዲያ አብዮት ሊቀጣጠል ይገባል። ህዝባችንን በባርነት ከያዘው የኢህአዴግ ፕሮፖጋንዳ ለማላቀቅ አስተውሎ መስራት ከወፌ ቆመች ያለፈ ታላቅ ተግባር ነውና ጎልጉልን እነሆ። ጎልጉል የዘመቻችን የመጀመሪያዋ መሳሪያ ናት። አሁንም ወፌ ቆመች!!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Ewnetu says

    September 11, 2012 12:32 pm at 12:32 pm

    Dear brothers and sisters of Golgul,
    we wish you a successful start and wish you strength in the bumpy road to democracy and freedom. We hope that you do not remain a site which only “copies and pastes” every cram which appeared on the internet. Ethiopians now above all need true and meaningful information that leads to a more strategic struggle.
    We also hope that you do not fall in the trap of woyanes which dissiminate misinformation labled as “sources from within”.
    We expect that the disinformed, brainwashed and blinded woyane supporters are not going to prolong the agony of ethiopian people.
    Dear Golguls Welcome to the ethiopian struggle for freedom!!

    Reply
  2. Girmu says

    September 12, 2012 10:12 am at 10:12 am

    Dear Golgul editor,I like your effort,but you are one of those guys who prolonged Melese Zenawi`s regime and still you are doing it by rejecting the oppositions unity.I do not know for how long you are going to make sweet words reiteration.Rethorics and gossple words by themselves won`t bring any change.Think about what you are doing,question yourselve what you are doing,your preach with sweet words tactic is over,now you need to practical shift or paradiam.Do not think this advise is from the enemies camp,it is from one of the Ethiopian nationalists

    Reply
  3. Kebena says

    September 12, 2012 10:38 am at 10:38 am

    Hi there,
    It is a good begining and hope you will be different from other in providing ture information that cover all parts of Ethiopia. Pls try not to concetrate on the news from capital city but try to cover the real situation of people who are living in country side as well.
    Wish you all the best.

    Reply
  4. tesfaye says

    September 13, 2012 06:50 pm at 6:50 pm

    is good place send any articles to my email address

    Reply
  5. Dereje Mengesha says

    September 19, 2012 12:35 pm at 12:35 pm

    It is a good begning and we must break the information monopoly of TPLF/EPRDF. g o go go

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule