• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የኦህዴዱ መሪ” ወርቅነህ ገበየሁ ትግሬ ነው፤ ምስጢሩ እነሆ…

September 21, 2016 09:51 pm by Editor 2 Comments

ከምርጫው ጥቂት አስቀድሞ የወርቅነህ ገበየሁ አያት ስም ገብረኪዳን ነበር። የቀድሞ ወዳጄ ወርቅነህ የአያቱን ስም ከገብረ-ኪዳን ወደ ኩምሳ ለመቀየር የወሰደበት ግዜ እና ምክንያቱ አላስደነቀኝም። ይህንን የዘር ፖለቲካ ጨዋታ ጠንቅቆ የሚያውቀው ዶ/ር መረራ ጉዲናም የተቃዋሚ እጩ ተመራጭ ነበር። ጉዳዩን ጠንቅቆ ያውቀዋል። በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካ ሳይንስ ፋካልቲ ስንማር ሁለታችንንም በአንድ ክፍል አስተምሮናል። የወርቅነህ ትክክለኛ አያት ስም ያለበት ሰነድም በእጁ አለ። ግን ጉዳዩን አላጋለጠውም። ምናልባት የሙያው ስነ-ምግባር ይህንን ለማድረግ አይፈቅድ ይሆናል።

ወርቅነህ ገበየሁ ሻሸመኔ ነው ተወልዶ ያደገው። እዚያ መኖሩ ደግሞ ኦሮምኛን አቀላጥፎ እንዲናገር ረድቶታል። ዘር መቁጠር ጸያፍ ቢሆንም ይህ ግን መታወቅ ያለበት ጉዳይ ነውና የወርቅነህ ገበየሁ ወላጆች ኦሮሞዎች አይደሉም። ከትግራዩ አቶ ገበየሁ ገብረኪዳን ይወለዳል።

ወርቅነህ ገበየሁ ውሎውም ቢሆን ከጆሌ ኦሮሞ ጋር አይደለም። ከነ ጌታቸው ረዳ፣ ከትግራይ  ተወላጆች ጋር በብዛት ያዘወትራል። ለዚህም ምክንያት አለው። ይህ ሰው አሁን የኦሮሞውን ድርጅት እንዲመራ መመረጡ አንደኛው ምክንያት ነው። በህወሃት የፖለቲካ ጨዋታ ምክትል ሆነው የሚቀመጡት በዘር መስፈርት ተለክተው አልያም ታማኝ አገልጋይ ሲሆኑ ብቻ ነው። ዋናውን ስራ የሚሰሩትም በምክትል ስም ያሉት ናቸው። ከስር ሆነው ዋናዎቹን እንደ ሮቦት ያንቀሳቅሷቸዋል። ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ምክትሉ ደብረጽዮንን ያስተውሏል!

ለመሆኑ ወርቅነህ ገበየሁ ማን ነው? ለምንስ ታስሮ ተፈታ? የወንጀል እስረኛ የነበረ ይህ ሰው እንዴትስ በጥቂት ጊዜ እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርስ ቻለ? ከዚህ ቀደም በማስታወሻዬ ላይ ያሰፈርኳትን ቁም ነገር ላካፍላችሁ። መልካም ንባብ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጭር ብሏል። ኢህአዴግ ወደ አዲስ አበባ ሲጠጋ፤ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ደግሞ ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ብላቴ ማሰልጠኛ ካምፕ ገብተው የተኩስ ልምምድ በማድረግ ላይ ነበሩ። በግንቦት ወር ኢህአዴግ ከተማውን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ ተማሪዎች እንደወትሮው ጥቁር ጋዋናቸውን ለብሰው፤ የአበባ እቅፍ አልተበረከተላቸውም – 1983 ዓ.ም.።

ከወራት በኋላ በዩኒቨርሲቲው አካባቢ ይመላለሱ የነበሩ ተማሪዎች ተስፋ የሚያስቆርጥ ዜና ሰሙ። አዲሱ የሽግግር መንግስት እንደከዚህ ቀደሙ ተማሪዎችን በየመስሪያ ቤቱ የማይመድብ መሆኑ ተገለጸ። ከዜናው ጋር የብዙ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ተስፋ አብሮ ጨለመ። በተለይ በወቅቱ በፖለቲካ ሳይንስ ለተመረቅነው ተማሪዎች፤ ምንም ክፍት የስራ ቦታ እንደሌለ በግልፅ ተነገረን።

በዚህ አይነት ያለ ስራ ብዙ ቆየን። በወቅቱ በፖለቲካ ሳይንስ ከተመረቅነው መካከል በከፍተኛ ነጥብ የተመረቀው ወርቅነህ ገበየሁ ጭምር ምንም አይነት የስራ እድል ለማግኘት አልቻለም።

ህወሃት ካመጣብን የዘር ፖለቲካ በፊት በትምህርት ቤትም ሆነ በዩኒቨርሲቲ ከቶውንም የትውልድ ዘራችንን ተጠያይቀን አናውቅም። ማን ምን እንደሆነ፣ ለማወቅ ፍላጎቱም አልነበረንም። የኋላ ኋላ ግን ነገሮች እየተቀየሩ መጡ። በጓደኛሞች መካከል የሚፈጠር ጥርጣሬና፣ የዘር ግንድ ማጥናቱ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ እንደተስቦ ያመጣብን በሽታ ነበር እና የቅርብ ወዳጅን ማወቁ የግድ ሆነብን። ወርቅነህ ገበየሁም የሻሸመኔ ልጅ ከመሆኑ ባሻገር፤ ከትግራይ ሰው መሆኑን ያወቅነው ከዩኒቨርስቲ ከወጣን በኋላ ነበር። በወቅቱ ነበረው የሽግግር መንግስት ባወጣው የዘር መስፈርት መሰረት፤ ወርቅነህ በትግራይነትና በደቡብ ህዝብነት መካከል የቆመ፤ ምርጥ የትግራይ ልጅ አለመሆኑ፤ በዚህም ምክንያት ሊያገኝ ይችል የነበረው ጥቅማ ጥቅም በመቅረቱ የጓደኛችን ጉዳይ ያሳዝን ነበር።

ከብዙ ጊዜ አንዴ ስንገናኝ፤ አንዳንድ ጓደኞቻችን ፀጉራቸው አድጎ፤ ንፅህናቸው ተጓድሎ፤ ከስተውና ተኮሳምነው ይታዩ ነበር። ከነዚያ ከሰውነት ውጪ ከሆኑት ተማሪዎች መካከል አንዱ ወርቅነህ ገበየሁ ይጠቀሳል።

የ1980ዎች አጋማሽ የፕሬስ ነጻነት የታወጀበት ወቅት በመሆኑ በርካታ መጽሄቶችና ጋዜጦች በገበያ ላይ ይውሉ ነበር። ሞገድ ጋዜጣም በወቅቱ ከነበሩት ከመጀመሪያዎቹ የነጻ ፕሬስ ጋዜጦች ረድፍ ላይ ይሰለፋል። ወርቅነህ ገበየሁም በነበረው አቋም ምክንያት የሞገድ ጋዜጣ ተባባሪ አዘጋጅ ሆኖ የመስራት እድሉን አገኘ። ወርቅነህ የጋዜጣው አዘጋጅ እንደመሆኑ መጠን በእለት ተለት የጋዜጣው ህትመት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም። ሆኖም ሳምንታዊ ደሞዙን ለመቀበል ወደ ቢሮ ሲመጣ በወጡት ዜናዎችና ጽሁፎች ላይ አልፎ አልፎ እንነጋገራለን። አንዳንዴም በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ስናገኝ፤ ከማንም በፊት ከወርቅነህ ጋር በመመካከር መስራታችንን ቀጠልን።

አንድ ቀን የሃሙስ እትማችንን የውስጥ ገጽ ስራዎች አጠናቀን በፊት ለፊት ሊቀርቡ የሚገቡ ዜናዎችን እየመረጥን ሳለ፤ ስልክ ተደወለ። ግርማቸው ነበር።

“ሰላም ግርማቸው? ምን ዜና አለ?”

“ብቻህን ነህ?”

“አዎ”

“ጥብቅ የሆነ ሚስጥር ነው። ተጠንቀቅ።”

“ምንም ችግር የለም፤ ንገረኝ።” አልኩና እስክሪብቶና ወረቀት አዘጋጀሁ።

ግርማቸው ጉዳዩን ሙሉ ለሙሉ በስልክ ሊነግረኝ የፈራ ይመስላል። ፈራ ተባ እያለ፤ “ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የኢህአፓ አባላት ናቸው…”

“እና ምን ሆኑ?”

ግርማቸው አሁንም በስጋት ስሜት፤ “ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። ለማንኛውም ለምን አንገናኝም?” አለኝ።

“ፖስት ራንዴቩ እንገናኝ?” ስለው ከጭንቀቱ የገላገልኩት ያህል፤ “አዎ እዚያ እንገናኝ።”

ረቡዕ ቀን ረፋዱ ላይ ፖስት ራንዴቩ ወደ ግርማቸው ጋ ስሄድ ብቻዬን አልነበርኩም። ወርቅነህ ገበየሁ አብሮኝ ነበር። በቀጠሮው ቦታ በሰዓቱ ተገናኘን።

ግርማቸውን ፖስት ራንዴቩ ስናገኘው ዘና ብሎ ያጫውተን ጀመር። “እንግዲህ ሰዎቹ የኢህአፓ አባላት ናቸው። ጉዳያቸው በሚስጥር መያዝ አለበት። ወደ አገር ቤት የመጡት ልዩ ሚሽን ተሰጥቷቸው ነው። ጉዳዩን ስትገናኙ በዝርዝር ትነጋገራላችሁ።” አለንና ስለሰዎቹ ማንነት አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮችን ሲገልጽልን እስክሪብቶና ወረቀት አውጥቼ መጻፍ ጀመርኩ።

“በምታገኛቸው ጊዜ ይህንን የሚስጥር ኮድ መናገር አለብህ” አለና የድብቅ ስማቸውን ነገረኝ።

“የድብቅ መጠሪያ ስማቸው ‘ቤሬክ’ ይባላል” ሲለኝ ወረቀት ላይ ይህንኑ አሰፈርኩት። ወርቅነህም እስክሪብቶውን ከኪሱ አውጣ።

“በዚህ ስልክ ደውሉና የእኔን ስም ጥሩላቸው። ለጋዜጣችሁ በርካታ መረጃዎችን ሊሰጧችሁ ይችላሉ።” አለን ግርማቸው።

ስልክ ቁጥራቸውን እየነገረን ወረቀት ላይ መጻፍ ስጀምር፤ ወርቅነህም ስልክ ቁጥሩን በእጁ መዳፍ ላይ ሲጽፍ አይቼ ሁኔታው አስገርመኝ። ነገር ግን በይሉኝታ ዝም አልኩት።

በወቅቱ በርካታ ጋዜጦች የፈሉበት ጊዜ በመሆኑ፤ ወርቅነህ ይህንን ዜና ከሞገድ ጋዜጣ ውጪ ለሚታተሙ ፕሬሶች አሳልፎ ሊሰጥ ነው በሚል ጥርጣሬ ብቻ ድርጊቱ አስገረመኝ። ከአንድ የትምህርት ቤት ጓደኛ፣ ከዛ በላይ ላስብ አልችልም። ልጠይቀውም አሰብኩና ጠይቆ ከመቀያየም ዝም ማለቱን መረጥኩ። በወቅቱ በውስጤ ቅሬታ አሳደረብኝ።

በሚቀጥለው ቀን … ግርማቸው በሰጠኝ ስልክ በተደጋጋሚ ብደውል እነ ቤሬክን ላገኛቸው አልቻልኩም። ቀን ላይ፣ በምሽት እና በሌሊት፣ ስልኩን መቀጥቀት ያዝኩ። ስልኩ ይጠራል። የሚመልስ ግን አልነበረም።

ከቀናት በኋላ ግርማቸውን ለመፈለግ ዘወትር ወደምንገናኝበት ወደ ፖስት ራንዴቩ ለብቻዬ አመራሁ። ሌሎች ጓደኞቼ እንደወትሮው ክብ ሰርተው ይጫወታሉ። ግርማቸው ግን አልነበረም።

“ግርማቸውስ?” አልኳቸው ወድያው እንደተቀላቀልኩ። ሞቅ ያለ ጨዋታቸውን እንዳቋረጥኳቸው ይሰማኛል።

“ሰላምታ አይቀድምም?” አለ አንዱ፣ ከፊቴ የሚነበበውን የድንጋጤ ስሜት በማስተዋል።

“ቀን ላይ ተደዋውለን ነበር። በሆነ ጉዳይ ትንሽ ተረብሿል። ለማንኛውም ዛሬ እንደምንገናኝ ነግሮኝ ነበር።” ሲል ሌላኛው መለሰ።

ግርማቸው አረፋፍዶ ብቅ አለ። ፊቱ ላይ አንዳች የብስጭት ስሜት ይነበባል። በውስጡ የታመቀውን ንዴት ያወጣው ገና ወንበሩ ላይ ሳይቀመጥ ነበር።

“ሰዎቹን አሳሰራችኋቸው አይደል?” ሲል ፍጹም ሃዘን በተሞላበት አንደበት ጠየቀ፣ ወደ እኔ እየተመለከተ።

“ወርቅነህ!” አልኩ ሳላስበው በመጮህ።

በመካከላችን ለአፍታ ጸጥታ ሰፈነ። ለተልካሻ ነገር የጠረጠርኩት ሰው ከጀርባዬ ሆኖ ከባድ ወንጀል እየሰራ ኖሯል!

የነ ቤሬክ መሰወር በውስጤ ጥርጣሬ፣ ፍርሃት እና ቅያሜ ፈጥሮብኝ ኖሮ ወርቅነህን እርቀው ጀመር፣ ከዛ ስልክ ከተቀበልንበት እለት በኋላም አልተገናኘንም። ከሞገድ ጋዜጣም ቀስ በቀስ እየራቀ መጣ።

አንድ ቀን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ የሃይድሮ ፖለቲክስ ምሁር የሆኑትን ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ ስለአባይ ጉዳይ ቃለመጠይቅ ለማድረግ ሄጄ ወርቅነህን ከሩቅ አየሁት። ከዚያ ደግሞ ተሰወረ።

ስራዬን ጨርሼም ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ለመውጣት ስሯሯጥ ከኋላዬ አንድ ሰው ያዘኝ።

እኔን ያላየኝ መስሎኝ ነበር። ከእነማን ጋር እንደምንገናኝና ምን እንደምሰራ በአይነ ቁራኛው ይከታተለኝ ኖሯል ወርቅነህ።

“ለምንድነው የምትሸሸኝ?” አለኝ፣ እንደመቆጣት እያደረገው።

ትንሽ እንደመደንገጥ ብዬ ስለነበር ለሰኮንዶች ጸጥ ካልኩ በኋላ “አንተስ ለምንድ ነው የምትከታተለኝ?” አልኩት በቁጣ።

“እውነቱን እንድነግርህ ነው የምትፈልገው?… ተረጋጋና አድምጠኝ፣ ሁሉንም ጉዳይ እነግርሃለው።” አለኝ መልሶ ረጋ ባለ አንደበት። ቁጣዬን ለማብረድ ሲል ያደረገው ይመስላል። በድንጋጤ የተነሳ የምናገረውም ጠፋብኝ እና ጸጥ ብዬ ከአንደበቱ የሚወጡትን ቃለት መተባበቅ ጀመርኩ።

“በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥሬ እየሰራሁ ነው።” ሲለኝ ያልጠበኩትን ሚስጥር ድንገት ስለነገረኝ ሁኔታው አስደነገጠኝ።

“በደህንነት ውስጥ በመስራቴ ደግሞ እናንተን ከስንት አደጋ ጠብቅያችኋለሁ። በአጭሩ ‘I am protecting you’ ስለዚህ አትሽሸኝ።” አለኝ። ከእግር ጥፍሬ እስከራስ ጸጉሬ አንዳች ነገር ወረረኝ። ልቤ በፍጥነት ሲመታ፣ ደምስሮቼ ሲገታተሩ ተሰማኝ።

“እና ሰዎቹን…” መናገር አልቻልኩም።

“የምን ሰዎች?”

“እነቤሬክን ያሳፈንካቸው?” አልኩትና መልስ ሳልጠብቅ እዛው የቆመበት ጥዬው ሄድኩ።

***

ከወራት በኋላ ወርቅነህ የደህንነት ሃላፊ ሆኖ ሻሸመኔ ስራ መጀመሩን ሰማሁ። ይህንን ዜና ሰምተን ብዙ ሳንቆይ “ወርቅነህ በጦር መሳሪያ ሽያጭ ተያዘ” ተብሎ ወደ እስር ቤት ተወረወረ።

ከሰባት ወራት በኋላ ወርቅነህ ገበየሁ ከእስራት መፈታቱን ሰማሁ። ከእስራት ሲፈታ ግን የምናውቀው የወርቅነህ ገበየሁ የዘር ሃረግ ተቀይሮ፤ የ‘ኦሮሞ’ ብሄር ተወላጅ ተብሎ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ከፍተኛ አመራር ሆኖ፤ ሹመት አግኝቶ የኢህአዴግን ካምፕ በግላጭ ተቀላቀለ … ወጣት ወርቅነህ ገበየሁ።

የእድሜ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የስራ ልምድ፣ በተለይ በፖሊስ ሰራዊት ስራ የሚጠይቀው የስራው ስነ-ስርዓት እና በሙያው ስነምግባር ላልተካነ ግለሰብ ያንን ትልቅ ስፍራ እንዲመራ ነው፤ አቶ መለስ ዜናዊ ሹመት የሰጡት።

አንዳንዴ ወርቅነህ ገበየሁ በቴሌቭዥን ሲቀርብ የድሮውን መልካም ሆነ ክፉ ነገር እያሰብኩ፤ “ወይ ጊዜ” ማለቴ አልቀረም። ወርቅነህ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ በባችለር ዲግሪ በጥሩ ውጤት የተመረቀ ወጣት ስለሆነ ከሌሎቹ ፊደል ካልቆጠሩ የህወሃት ባለስልጣናት የተሻለ ነው። ሆኖም በማናቸውም ጊዜ የግል ፋይላቸው ታይቶ ወደ እስር ቤት ሊወረወሩ ከሚችሉት፤ በ“ቀይ መስመር” ከቆሙት ባለስልጣኖች አንደኛው መሆኑ እርግጥ ነው። ግና ለጌቶቹ ታማኝ መሆኑን በዘሩ ብቻ ሳይሆን በስራውም አረጋግጦላቸዋል። ዛሬ ኦህዴድን የሚመራው የኦሮሞ ተወላጅ ሳይሆን የኦሮሞ ተናጋሪ ትግሬ እንዲሆን የተፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ትክክለኛዎቹ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ህወሃት እምነት ስላጣ ይመስላል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Ayu says

    September 22, 2016 06:21 am at 6:21 am

    Ato Kuma Demeksa also not Oromo – he is Tigray.
    Can you dig out his profile.

    Thank you

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    September 25, 2016 03:14 am at 3:14 am

    ጔዶች! ውሸት ነጭም ጥቁርም ነው ይባላል! ጎልጉል ነጭ ውሸት እየዋሸ ነው!!

    Reply

Leave a Reply to Ayu Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule