• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ስሉሱ” ዞረ እንዴ?!

March 14, 2015 03:52 am by Editor 2 Comments

ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ባልተለመደ ሁኔታ ኢህአዴግ ላይ ታዋቂ የዓለማችን ጋዜጦች የጀመሩት ተከታታይ ትችት፣ ማሳሰቢያና መፍትሔ ጠቋሚ ዘገባዎች መነጋገሪያ አጀንዳ ሆነዋል፡፡ ሚዲያዎቹ በዘገባቸው ኢህአዴግን ከቻይና አምባገነናዊና አክራሪ አገዛዝ ጋር አመሳስለዋል፡፡ ኢህአዴግ እከተለዋለሁ የሚለውን የኢኮኖሚ መርህ ከቻይና የተኮረጀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ውጤቱም ሆነ መድረሻው ግራ የሚያጋባና የማይታወቅ እንደሆነ ዘግበዋል፡፡ ጋዜጦቹ ኢህአዴግን በሚንከባከቡት መንግሥቶቻቸው እና በራሱ ኢህአዴግ ላይ የሰላ ሒስ መሰዘንዘር መጀመራቸው የፖሊሲ አውጭዎችን አስተሳሰብ የሚያስቀይር ከመሆን አልፎ ኢህአዴግ ላይ “ስሉሱ” ዞሯል የሚያስብል እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

“ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” በሚል ርዕስ የሰብዓዊ መብት ተመልካች የሆነው ድርጅት (ሂዩማን ራይትስ ዎች) ኢህአዴግ በሚያደርስባቸው ስልታዊ አፈና፣ ማስፈራሪያ፣ ህይወት የማጥፋት ዛቻ፣ … ምክንያት ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች ላይ አፈና በማድረግ የቀዳሚነቱን ስፍራ መያዟን ባለ 76 ገጽ ዘገባ ካወጣ በኋላ በምዕራቡ ዓለም ያሉ ሚዲያዎች በኢህአዴግ አፋኝነት ላይ ጠንከር ያሉ ዘገባዎችን ማውጣታቸውን ይፋ እየሆነ መጥቷል፡፡

በዚህ ረገድ ቀዳሚውን ቦታ የወሰደው በዋሽንግቶን ዲሲ የአሜሪካ ፖሊሲና ሕግ አውጪዎችን አቅጣጫ በማመላከት የሚታወቀው “ዋሽንግቶን ፖስት” የዛሬ ወር አካባቢ የሰብዓዊ መብት ድርጅቱን ዘገባ ተተርሶ (የታፈነው የኢትዮጵያ ፕሬስ) “Ethiopia’s stifled press” በሚል ርዕስ አቋም የያዘበት ርዕሰ አንቀጽ ነው፡፡ ጋዜጣው እንዳለው በሟቹ መለስ የተጀመረው አፈና በቀጣዩ ሃይለማርያም አገዛዝም በይበልጥ እየከረረ መሄዱን ጠቁሟል፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ከባላንጣዋ ኤርትራ እየባሰች መምጣቷን እንዲያው በተሻለ ሁኔታ ኤርትራ በጥር ወር ውስጥ በርካታ ጋዜጠኞችን ከእስር መፍታቷን ጨምሮ ገልጾዋል፡፡ ጋዜጣው ግልጽና የጠነከረ አቋም በወሰደበት በዚህ ርዕሰ አንቀጽ ማብቂያ ላይ አሜሪካ ለኢህአዴግ ዋንኛ ድጋፍ ሰጪ መሆኗን በመናገር በ2014 ለልማት ዕርዳታ በሚል 373 ሚሊዮን ዶላር መስጠቷን አስረድቷል፡፡ በአንጻሩ አሜሪካ ለዴሞክራሲና ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ ማስፋፊያ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ዕርዳታ በ2012ዓም 3.4ሚሊዮን ዶላር የነበረው በ2014ዓም ወደ 163ሺህ ዶላር ማሽቆልቆሉን ተናግሯል፡፡ ይህ የሆነበት ዋንኛ ምክንያት ኢህአዴግ ያወጣው የመያዶች ሕግ እንደሆነ ጋዜጣው ጨምሮ ገልጾዋል፡፡

ዋሽንግቶን ፖስት ርዕሰ አንቀጹን ሲጠቃልል ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ዕርዳታ በማግኘት ቀዳሚ እንደመሆኗ በዴሞክራሲ ዕድገት እየሄደችበት ያለው ጎዳና አጠያያቂ እንደሆነ እንደምታ ያለው ሃሳብ ከሰነዘረ በኋላ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) እና የኦባማ አስተዳደር እንዲሁም ባጠቃላይ ምዕራባውያን ማድረግ የሚገባቸውን በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ስቴት ዲፓርትመንት በኢትዮጵያ እየተደረገ ባለው የሚዲያ አፈና ላይ ተቃውሞውን ማሰማት አለበት፤ ይህም ግን ከቃላት ማለፍ አለበት፤ የኦባማ አስተዳደር የሚሰጠውን ዕርዳታ ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች እንዲፈቱ ከመጠየቅ ጋር ማቆራኘት አለበት (የማይፈቱ ከሆነ ዕርዳታ እስከመከልከል)፤ ሌሎች ምዕራባዊ ለጋስ አገራትም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ማድረግ አለበት፤ ምዕራባዊ አገራት በአጠቃላይ ጋዜጠኞችን በማሰር በዓለም ታዋቂ ለሆነ አገዛዝ የሚያደርጉትን ዕገዛ ማቆም አለባቸው የሚል በዓይነቱ ተጠቃሽ የሆነና የምዕራቡ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ የፖሊሲ ለውጥ እንዲያደርግ ግፊት የሚያደርግ ርዕሰ አንቀጽ ነበር፡፡

anuak woman aboboበቀጣይ የእንግሊዙ “ዘ ጋርዲያን” ኢህአዴግ በምዕራባውያን ዕርዳታ ከዓለም ባንክ የሚያገኘው 98ቢሊዮን ብር እንደነጠፈበት በመዘገብ “በመብት ረገጣ ምክንያት ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው ዕርዳታ አፈገፈገች” (British support for Ethiopia scheme withdrawn amid abuse allegations) በሚል ርዕስ ያወጣው ነው፡፡ ኢህአዴግን ከማንገስ ጀምራ በሥልጣን እንዲቆይ እንዲሁም በርካታ ድጋፍ ስትሰጥ የቆየችው እንግሊዝ እንዲህ ዓይነቱን እርምጃ ለመውሰድ መቻሏን ጋዜጣው በሰበር ዜና መልክ ማተሙ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ከተወሰኑ ጊዜያት በስተቀር በኢህአዴግ አገዛዝ ላይ የሰላ ሒስ ከመሰንዘር ከሚቆጠቡት የእንግሊዝ ሚዲያዎች አንጻር ዘጋርዲያን የወሰደው አቋም ለየት ያለ ነው፡፡ የእንግሊዙ የልማት ተራድዖ መ/ቤት “ኢትዮጵያ አድጋለች” በማለት ዕርዳታውን ከማቆም በማይተናነስ መልኩ ወደ 5በመቶ ማውረዱን ጋዜጣው ቢጠቅስም “ለዕድገቷ ማስረጃ” እንዲሆን ዜናውን ሲያትም በገዢነት ያወጣው የፎቶ ምስል በድንግዝግዝ ጸሃይ በአቧራ የተሰራ ቤት አቅራቢያ አቧራ ሲጠርጉ የሚታዩ ደካማ የአኙዋክ ሴትን ነው፡፡ የእርዳታው ገንዘብ ይሰጥ የነበረው መሠረታዊ አገልግሎቶችን ማለትም ትምህርት፣ ጤና፣ ንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ መንገድ ሥራ፣ ወዘተ ለመሳሰሉ የዜጎችን ኑሮ ለሚያሻሽሉ አስፈላጊ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያነት ነበር፡፡

ያለፈው ሳምንት አጋማሽ ኒው ዮርክ ታይምስ “በድህነት ተዳክማ የነበረችው ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ፍንዳታ እየጋለበች ነው” (Ethiopia, Long Mired in Poverty, Rides an Economic Boom) በሚል ርዕስ በርካታ ጉዳዮችን በመዳሰስ ያወጣው የዜና ዘገባ ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡ ለኢኮኖሚ ዕድገቱ አብነት እንዲሆኑ የዘመኑን ሰዎች እና ባለሃብቶች ጋዜጣው ቃለመጠይቅ በማድረግ በቂ ሽፋን ሰጥቷል፡፡ በአዲስ አበባ ውስጥ ጎልተው የሚታዩ እና “ከዕድገቱ” ጋር በንጽጽር ሊቀርቡ የሚገባቸውን ጉዳዮችንም ዳስሷል፡፡ በከተማዋ የተንሰራፋው ድህነት፣ የመገናኛ ዕጥረት፣ የኤሌክትሪክ መቋረጥ፣ የኢንተርኔት ኤሊነት፣ የቴሌኮሙኒኬሸን ኢተዓማኒነት፣ ወዘተ ላይ ጋዜጣው የሰላ ሒስ ሳያነሳ አላለፈም፡፡ ኢህአዴግ የሚታመንበትን የዓለም ባንክ ኃላፊንም አነጋግሯል፡፡ በኢትዮጵያ የባንኩ ዳይሬክተር የሆኑት ጉዋንግ ቼን አሁን አጠቃላይ ያለው አሠራር ተጠቃሽ መሆኑ ከገለጹ በኋላ ሲቀጥሉ “እንዲህ ያለው የኢኮኖሚ ሞዴል ለኢትዮጵያ ሰርቷል፤ ጥያቄው ቀጣይነት አለው? የሚለው ነው፤ ባንኩም ይህንኑ በመጠየቅ የኢኮኖሚው ሞዴል ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት መቀጠል ይችላል ወይ? በማለት ይጠይቃል፤ በእኛ አመለካከት መልሱ አይችልም ነው” ማለታቸውን ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል፡፡

ለማመዛዘን የተቃዋሚዎችን ሃሳብ ያቀረበው ጋዜጣ በፖለቲካው ረገድ ቀልብ የሚስቡ ሃሳቦችን አስፍሯል፡፡ ተቺዎች ያሉት ነው በማለት የመንግሥት አስተዳደር በትግሬዎች የበላይነት ቁጥጥር ሥር መውደቁን፣ ህወሃት ምንም ዓይነት ተቃውሞ መስማት የተሳነው መሆኑን፣ የተቃዋሚው እንቅስቃሴ (በትግሬዎች) የቁጥጥር መረብ ውስጥ የወደቀ መሆኑን፤ ፓርላማው በኢህአዴግ የበላይነት “የሚነዳ” መሆኑን፤ ማንኛውም የተቃውሞ ድምጽ የታፈነ መሆኑን፤ ጋዜጣው ማስረጃዎችን በማጣቀስ ሃተታውን ሰጥቷል፡፡ ሲያጠቃልልም የዞን 9 ጠበቃ የሆኑትን አቶ አመሃ መኮንን የሰጡትን አስተያየት ጠቅሷል፡፡ “በመንግሥትና በሕዝብ መካከል መተማመን መኖሩ ለዕድገት ጠቃሚ ነው፤ ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ መተማመን አለ ብዬ ለማመን አልችልም” በማለት የሕግ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ “ዎል ስትሪት ጆርናል” ኢህአዴግ የሚከተለው የልማት ፕሮግራም የተቃዋሚውን ድምጽ እንዲታፈን ያደረገ መሆኑን በመጥቀስ “Ethiopia’s Growth Program Cuts Out Dissent” በሚል ርዕስ  ዘገባ አስነብቧል፡፡ በኢህአዴግ ፓርላማ ፓርቲ አልባ ብቸኛ “የተቃዋሚ ፓርቲ አባል” በሆኑትን አቶ ግርማ ሰይፉ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ “ገዢው ፓርቲ ምርጫውን ያጠናቀቀው” መሆኑን በመግለጽ መጪው ምርጫ አስቀድሞ የተወሰነ መሆኑን ዘግቧል፡፡ በቻይና ስልት ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ኢህአዴግ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ በሚፈልገው መልኩ ጸጥ ያሰኘ መሆኑን ያተተው ጋዜጣ ስልቱን ሲተነትን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከጋዜጠኛ ጋር በፖለቲካ ጉዳዮች ለመነጋገር እንደሚፈሩ፤ የስልክ ጥሪዎች ክትትል እንደሚደረግባቸው፤ አገዛዙን የሚተቹ ድረገጾች ውታፍ የተደረገባቸው እንደሆነ፤ የኢህአዴግን አገዛዝ የሚተች ማንኛውም ሰው ሥራ ለማግኘት፣ ንግድ ለማከናወን፣ ጨረታ ለማሸነፍ፣ ወዘተ የሚቸገር መሆኑን፤ ከነዋሪዎች ቃርሞ ባገኘው መረጃ አስረድቷል፡፡girma seifu maru

ከኢህአዴግ ሹሞች ስለታሰሩት ጋዜጠኞች ጉዳይ የአጸፋ ምላሽ ያሰፈረው ዎል ስትሪት አፈቀላጤው ሽመልስ ከማል የታሰሩት “ጋዜጠኞች አለመሆናቸውን” የታሰሩትም ሃሳባቸውን በመግለጻቸው አለመሆኑን ጋዜጣው ለንጽጽር አቅርቧል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሰብዓዊ መብት ተመልካቹ መ/ቤት በሚዲያ እና ጋዜጠኞች ላይ ያወጣውን ዘገባ በማጣቀስ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የሰብዓዊ መብት ረገጣና በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸመውን እንግልት ለአብነት አስፍሯል፡፡ በመልካም አስተዳደር እና በሌሎች ጉዳዮች አገሪቱ ወደታች እያሽቆለቆለች እንደሆነ የተናገረው ዎል ስትሪት ጆርናል በቅርቡ በተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች የአገዛዙ ጥበቃ ኃይላት በሰልፈኞች ላይ ጥይቶች መተኮሳቸውን ዘግቧል፡፡

መጪው ምርጫ ብዙም ተስፋ የሚጣልበት እንዳልሆነ በሃተታው እንደምታ የገለጸው ጋዜጣ የምዕራባውያንን ዝምታ ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡ አሜሪካ ከኢህአዴግ ጋር ባላት የአካባቢው ጸጥታና የሰላም ጥበቃ ውል ምክንያት የራሷን ጥቅም የምታይ ብቻ መሆኗን ጋዜጣው ያስረዳል፡፡ በመሆኑም አቶ ግርማ እንዳሉት ምርጫው አስቀድሞ የተጠናቀቀ መሆኑን ጋዜጣው በመጥቀስ የምዕራብ ፖሊሲ አውጪዎች እንዲህ ዓይነቱን ዝምታ በመምረጥ ከኢህአዴግ አፋኝ አገዛዝ ጋር መሞዳሞድ መቀጠላቸው የራሳቸውን አገር ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ እየጣሉት እንደሆነ ሊገባቸው በሚችል ቋንቋ አስረድቷል፡፡

የምዕራቡ ዓለም ሚዲያ ውጤቶች በኢህአዴግ ላይ ይህንን መሰሉ ትችት ሲያቀርቡ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ እንዲህ ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ ታዋቂ የሆኑ ጋዜጦች በተደጋጋሚ ኢህአዴግን ሲተቹ ግን በዓይነቱ የመጀመሪያው ነው ሊባል ይችላል፡፡ ከዚህ ቀደም አንድ የምዕራብ ሚዲያ በኢህአዴግ ላይ የሰላ ትችት ሲደርስ ኢህአዴግ “በእጅም በእግርም” በማለት በሌላ ተመጣጣኝ ሚዲያ የአጸፋ ምላሽ ሲሰጥ በተደጋጋሚ የተከሰተ እውነታ ነው፡፡ አሁን ግን ከአንድ ጊዜ በላይ ይህንን ዓይነት ተደራራቢ ትችት ሲቀርብበት ሊያስተባብልለት የሚችል ተመጣጣኝ ሚዲያ አለማግኘቱ ወይም ሞክሮ እምቢ መባሉ “የስሉሱን” መዞር እውነተኛነት የሚያጠናክር እንደሆነ አብሮ የሚጠቀስ ነው፡፡

በጥቂት ሳምንታት ውስጥ አራት የምዕራብ አገራት ታዋቂ ጋዜጦች ይህንን ዓይነት ዘገባ ማቅረባቸው የምዕራቡ ዓለም የፖለቲካ ዘዋሪዎች በኢህአዴግ ላይ አቋም እንዲወስዱ ተገቢውን ግብዓት በይፋ እየሰጡ እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል እና ድርጊቱም ያለምክንያት እንዳልሆነ የፖለቲካ ተንታኞች የሚስማሙበት ሃሳብ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በሚገኝ አንድ የትምህርት ተቋም የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር የሆኑ ለጎልጉል ይህንን ጉዳይ ሲገልጹ “የምዕራብ ፖለቲከኞችና ጋዜጦች በቁርኝት ነው የሚሰሩት፤ ፖለቲከኞች የሚፈልጉትን ለማድረግ ሲፈልጉ በጋዜጦች በኩል ሃተታ እንዲሰራ ያደርጋሉ ከዚያ ያንኑ ዘገባ መልሰው እንደማስረጃ በመጠቀም የፖሊሲ ለውጥ ለማድረግ ይጠቀሙበታል፤ ሰሞኑን የምዕራብ ጋዜጦች እየወሰዱ ያለውን የተለየ አቋም ከዚህ አንጻር ከተመለከትነው በእርግጥ ምዕራባውያን በኢህአዴግ ላይ ስሉሱን ሊያዞሩ ነው እንዴ በሚል ሊታይ የሚችል ሲሆን ይህ አካሄድ ምን ያህል ለውጥ ሊያመጣ ይችላል የሚለው በሂደት የሚገለጽ ነው፤ በውጭ አገር ያለው ኢትዮጵያዊ የሚያደርገው ግፊትና ተጽዕኖም ከዚሁ ጋር በተዛማጅ ሊጠቀስ የሚገባው ነው” ብለዋል፡፡

የምዕራቡ ዓለም ጋዜጦች በኢህአዴግ ላይ የጀመሩት “ዘመቻ” ወደ የትኛውም አቅጣጫ ይሂድ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ሁኔታ ግን “ስሉሱ” ቢዞርም ባይዞር የሕዝቡ ምሬት ከምንግዜውም በበለጠ እየጨመረ መምጣቱን ነው፡፡ ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች የዕርቅን አማራጭ በተደጋጋሚ እያቀረቡ ያለ ቢሆንም ከኢህአዴግ በኩል የሚሰማው ግን “እንደጀመርን እንጨርሰዋል” የሚል ቀረርቶ ብቻ ነው፡፡

ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም “የወያኔ የጥላቻ ፍሬ” በሚል ርዕስ የዛሬ ዓመት አካባቢ ባወጡት ጽሁፍ ላይ እንደጠቆሙት ግፍ ማብቂያ እንደሚኖረውና አልሰማ የሚል ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ በግድ እንዲሰማ እንደሚደረግ ይህም ደግሞ ለማንም እንደማይበጅ ሲገልጹ እንዲህ ብለው ነበር፡- “ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ ጥላቻ ወደ ንዴት፣ ንዴት ወደ ቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደ አውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።”

በመጪው ግንቦት ወር ይካሄዳል ከሚባለው ምርጫ አኳያ ኢህአዴግ እየተጓዘበት ያለው የዕውር መንገድ፤ በልማትና ዕድገት ስም በሕዝቡ ላይ እየጫነ ያለው ቀንበር፤ “እኔ ከሌለሁ አገር ትፈርሳለች” የሚለው ቅኝት፤ በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርሰው ዓይን ያወጣ በደል፤ አፈና፣ እስራት፣ ግድያ፣ … የግፉን ሸክም እያገዘፈው ብቻ ሳይሆን የሚሄደው መሸከም የሚችል ወገብ እንዳይኖርም ያደርገዋል፡፡ የዚያን ጊዜ የግፉን ቀንበር ተሸካሚው መውደቁ የማይቀር ይሆናል፡፡ ይህ ሲሆን “ስሉሱ” ቢዞርም ባይዞርም አሸካሚው ግፈኛም ሚዛኑን ስቶ መውደቁ የማይቀር ነው፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. እምሩ ዘለቀ says

    March 16, 2015 02:47 am at 2:47 am

    Foreign governments are well aware of the prevailing total corruption and and of the massive illicit transfer of funds from developing countries. This has been reported broadly by the organizations such as the Oakland Institute, Global Financial Integrity, and other organs including the world media. For political considerations and for what is considered national donor governments, including World Financial Institutions have deliberately ignored the issue, at the cost to their own constituencies and to the poor people of the countries.
    According to a report made by the Indian Express of March 15, 2015, with the collaboration of Le Monde and the Consortium of Investigative Journalists, amongst 140 countries
    Ethiopia counts for US$ 9.987.629.910 in the name of 19 personal names
    Eritrea counts for US$ 699.598.731.31 with this Bank alone.
    In think that the recent articles denoncing such practices are caused by the possible public outcrie that happened by these revelations.
    I

    Reply
  2. LK says

    March 16, 2015 01:10 pm at 1:10 pm

    we trust not foreign media. if they have any good opportunity from tplf for themselves they will restore (fix) the story again. so to bring an end the tplf killing, smuggling, abuse, torching on Ethiopian people trust only in Ethiopian people and good friends of us and the the help of our great God.

    Reply

Leave a Reply to እምሩ ዘለቀ Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule