• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ውሃ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው”፤ መፍትሔ መፈለግ “የግድ” ነው፤ አል-ሲሲ

May 7, 2014 08:14 am by Editor Leave a Comment

በቅርቡ በግብጽ ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸንፋሉ እየተባለ የሚጠበቁት ዕጩ ተወዳዳሪ አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ “የውሃ ነገር” ለግብጽ “የህይወትና የሞት ጉዳይ” ሲሉ ገለጹ፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን መፍትሔ መፈለጉ “የግድ” እንደሆነ አስታወቁ፡፡ በቅርቡ በግድቡ ዙሪያ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ በውጭ የሚገኙ ሦስት ኢትዮጵያውያን ምሁራን የግድቡ መሠራት ግብጽን “በማይቀር አደጋ” ላይ እንደማይጥላት አስረዱ፡፡

በግብጽ በተላለፈ የቴቪ ስርጭት ትላንት ቃለመጠይቅ የሰጡት የቀድሞው የግብጽ ጦር መሪ ፊልድ ማርሻል አል-ሲሲ ግድቡን አስመልክቶ ሰፊ ትንተና እንዳልሰጡ አልሃራም የቲቪ ስርጭቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ሆኖም ዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ተወዳዳሪ “የሌሎችን ፍላጎትና ጥቅም የምንረዳ መሆናችንን ማሳየት ይገባናል፤ (የዚያኑ ያህልም) የራሳችንን ጥቅም ለማስጠበቅ ጽኑ መሆን አለብን፤ (ምክንያቱም) ውሃ ማለት ለእኛ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡

አል-ሲሲ በአባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሊደረግ የሚገባው ንግግር ትኩረት ሳይሰጠው ለረጅም ጊዜ የቆየ መሆኑና ውይይቱም የተጀመረው ዘግይቶ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “ለኢትዮጵያና ለሌሎች አፍሪካ ወንድሞቻችን ተገቢውን ጥረትsisi አለማድረጋችንን ማመን አለብን፤ በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ለመተባበርና መፍትሔ ለማግኘት ድርድርና የጋራ መግባባት ቁልፍ ናቸው” በማለት አል-ሲሲ የግብጽን ፍላጎት አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል በዚሁ የአባይ ግድብ ዙሪያ በቅርቡ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡና በውጭ የሚገኙ ሦስት ምሁራን የግድቡ መሠራት ግብጽን “የማይቀር አደጋ” ላይ እንደማይጥላት አስታውቀዋል፡፡ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ፣ ፕሮፌሰር ሰይድ ሃሰንና ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ “Misplaced opposition to the Grand Ethiopian Renaissance Dam” በሚል ርዕስ ባቀረቡት በዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ታላላቅ ግድቦችን በተመለከተ የሚቀርቡ የተቃውሞ ሃሳቦች መኖራቸውን ዓለምአቀፋዊ መረጃዎችን በማጣቀስ ይተነትናሉ፡፡ ከእነዚህም ሃሳቦች መካከል ጥቂቶቹ የሕዝብ መፈናቀል፣ ሙስና፣ ከኮትራት ውሎች ጋር በተያያዘ ሊኖር የሚገባ ግልጽነት፣ የግንባታና የጥገና ወጪ፣ ወዘተ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በግድቡ ዙሪያ ያላቸውን ሕጋዊ ጥያቄ የማንሳትና የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ምሁራኑ ያስረዳሉ፡፡

በመቀጠልም በቅርቡ ከዓለምአቀፍ የባለሙያዎች ፓናል አምልጦ የወጣ መረጃ በመጥቀስ ግድቡ ከኢኮኖሚ አንጻር መቀጠል የሚችል መሆኑን፣ ዲዛይኑ አንዳንድ መጠነኛ “ማስተካከያዎች” ሊደረግበት የሚገባ ቢሆንም ዓለምአቀፍ ደረጃን የጠበቀ መሆኑን፣ ሥራውን እያካሄደ ያለው ኮንትራክተር ታላላቅ ግድቦችን በመሥራት ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ያለው መሆኑን፣ ወዘተ በመጥቀስ የግድቡ ሥራ በግብጽ ላይ መቅሰፍትን የሚያመጣ አለመሆኑን ኢትዮጵያውያኑ ምሁራን ባለ 48 ገጽ ምሥጢራዊ ሰነዱ በመጥቀስ ማጠቃለያ ሰጥተዋል፡፡ የግድቡ ሥራና መጠናቀቅ ግብጽን “የማይቀር አደጋ” ውስጥ እንደማይከታትም ሦስቱ ምሁራን ይናገራሉ፡፡abay and church

በ“ህዳሴው” ግድብ ዙሪያ በግብጽና ኢትዮጵያ መካከል ያለው መካረር ቀጥሎ ከጥቂት ቀናት በፊት ለሁለተኛ ጊዜ ግብጽን ለመጎብኘት ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበረው አቡነ ማቲያስ የግብጹ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ በላኩላቸው መልዕክት ምክንያት ጉብኝቱ መሠረዙን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ዘግቦ ነበር፡፡ የግድቡ ጉዳይ ወደ ሃይማኖት መንደር መዝለቁ የሁኔታውን አሳሳቢነት የሚያሳይ መሆኑን ጎልጉል በወቅቱ የገለጸ ሲሆን በሥራው ላይ የሚገኙ መሃንዲስ ኢህአዴግ የአገር ሃብት የሆነውን ግድብ ሥራ ለራሱ ርካሽ የፖለቲካ መሣሪያነት መጠቀሙ አግባብ የሌለው መሆኑን መናገራቸውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ግብጽን በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ እየተባለ የሚጠበቁት አል-ሲሲ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው የተባረሩትን ሙርሲን የሚተኩና የምዕራባውያን ከፍተኛ ድጋፍ ያላቸው “ሥዩመ-ፕሬዚዳንት” የመሆናቸው ጉዳይ የበርካታዎችን ትኩረት የሳበ ነው፡፡ ፊልድ ማርሻል አል-ሲሲ የአባይን ግድብ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር መፍትሔ መፈለጉ “የግድ” እንደሆነ ቢጠቅሱም ውሃ ለግብጻውያን “የህይወትና የሞት ጉዳይ” ከመሆኑ አንጻር የግብጽን ጥቅም አስጠብቃለሁ ብለው መናገራቸው እንዴት ሊታረቅ እንደሚችል ወደፊት በሂደት የሚታይ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያና ግብጽ በአባይ ጉዳይ ገና ብዙ የሚቀራቸው መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule