• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እነ አባይ ጸሃዬ አሜሪካ ነበሩ፤ “ኦሮሞና አማራ ተባበሩብን፤ ሰግተናል”

August 10, 2016 05:11 am by Editor 3 Comments

የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራር አባይ ጸሃዬ፤ ሳሞራ የኑስን ጨምረው ሌሎች ከፍተኛ የህወሃት ባልደረቦቻቸውንና በመያዝ አሜሪካ አገር አጭር ቆይታ አድርገው መመለሳቸውን ጎልጉል አረጋግጧል። አሜሪካ በግል የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማነጋገር ውሉ ባግባቡ የማይታወቅ የሽግግር ሃሳብ ለመተግበር ማሰቧ ተሰምቷል። የሽግግር ሃሳቡ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) የያዘውን ስልጣን በተወሰነ መልኩ የሚያስቀጥል በመሆኑ ለአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ሃሳብ የሚያቀርቡ ተጽእኖ ፈጣሪዎች አሜሪካ ይህንን መሰሉን አቋም እንድትቀይር እየወተወቱ ነው። ለኦባማ አስተዳደር ፖሊሲ አውጪዎች ዕቅድ ለማቅረብ እነዚሁ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝግጅት አላቸው።

ከሁለት ቀን በፊት አሜሪካ አጭር ቆይታ ያደረጉት እነ አባይ ጸሃዬ “እንወድቃለን” ብለው እንደሚሰጉ ለአለቆቻቸው አስታውቀዋል። የጎልጉል የዲፕሎማት ምንጮች እንዳሉት ህወሃቶች አሁን የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ምን አልባትም ሙሉ በሙሉ ከቁጥጥራቸው ሊወጣ እንደሚችል፣ ከተቃውሞው ጀርባ ያሉት ክፍሎች በተለይም በኦሮሚያ በቀጣይ ህዝብ የራሱን ነጻ አስተዳደር እንዲመሰርት እቅድ መያዛቸውን፣ የመንግስት መዋቅር እየፈረሰና ተቃዋሚዎች ከጀርባ ሆነው የሚመሩት ነጻ ክልል እየበዛ ሲሄድ ጽንፈኛው አይሲስ አገሪቱን ሊቆጣጠር ይችላል ሲሉ የአሜሪካ ሹሞችን ማስጠንቀቃቸው ተነግሯል። ሁለተኛ አማራጫቸውም ሙሉ በሙሉ ወደ ቻይና መጣበቅ ሊሆን እንደሚችል የህወሃት መሪዎች በማስፈራሪያ መልክ ፍንጭ ሰጥተዋል። ቻይና ግን ከፖለቲካ የበላይነት ይልቅ የኢኮኖሚ ጥቅሟን የምታስቀድም በመሆኗ ይህ የህወሃት “ማስፈራሪያ” ምን ያህል ሊሠራ እንደሚችል ለህወሃት ሹሞችም ግልጽ የሆነ አይመስልም፡፡ oromo-amhara-protests

በ1997 ምርጫ ህወሃት ተሸንፎ ስለነበር ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲያደርግ አሜሪካኖቹ ሲጠይቁት መለስ “ሠራዊቴን በመያዝ ወደ ትግራይ አፈገፍጋለሁ፤ አገሪቱ የአሸባሪ መናኽሪያ ትሆናለች፣ ትፈራርሳለች፤ ተቃዋሚዎች ሃይል የላቸውም…” በማለት አስጠንቀቀው የአሜሪካንን ሃሳብ ካስቀየሩ በኋላ ወደ ግድያ መዛወራቸውና ድምጻቸው እንዲከበርላቸው የጠየቁ ንጹሃንን በአልሞ ተኳሾች እንዲገደሉ ቀጥተኛ ትዕዛዝ መስጠታቸው የሚታወስ ነው። መለስ ከአሜሪካኖቹ ጋር ያደረጉትን ድርድር በወቅቱ የወጣ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ዘግቦት ነበር።

ዛሬ 25 ዓመት ራሱን ተገንጣይ በማለት ሰይሞ አገር በነጻ አውጪ ስም የሚገዛው ህወሃት፤ በተመሳሳይ የማስፈራራት ልምምዱን አንድ ደረጃ በማሳደግ “እኔ ከሌለሁ አገሪቱን አይሲስ ይወራታል” ሲል በወኪሎቹ አማካይነት አሜሪካ የሕዝቡን ተቃውሞው በጥገና ለውጥ እንድታፋዝዝላቸው ጠይቀዋል። እስረኞችን ለመፍታት፣ የሚዲያ ነጻነትን ለማወጅ፣ በቀጣዩ ምርጫ ተቃዋሚዎች ፓርላማ እንዲገቡ ለመፍቀድና የመሳሰሉትን ማሻሻያዎች እንደሚያከናውን ማረጋገጡን የዜናው አቀባዮች አመላክተዋል። ዴሞክራሲ ሂደት ነው፤ ስለዚህ በዚህ መልኩ በቀስታ እየተለካ ከተሰጠ ይበቃል በሚል ዓይነት ህወሃቶችን አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ ጥገናዊ ለውጥ እንዲካሄድ ህወሃት ማስፈራሪ፣ ምልጃና ጭንቀት የወጠረው ጥያቄና ውትወታ ማቅረቡ ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡

እንደ ዜናው ሰዎች ገለጻ ከሆነ፣ ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ አውጪዎች የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርቡት ተጽዕኖ ፈጣሪ አካላት ይህንን ሃሳብ አልተቀበሉትም። ምክንያታቸውም ወያኔዎች ሲጨንቃቸው የሚገቡትን ቃል የመተግበር ልማድ የሌላቸውና የማይታመኑ በመሆናቸው ነው። እነዚህ ክፍሎች አነሰ ቢባል በሳምንቱ ማብቂያ አገሪቱ ላይ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት የሚያስገድድ የውሳኔ ረቂቅ ሃሳብ ያቀርባሉ ተብሎ ይገመታል። የኦባማ አስተዳደርም የስራ ጊዜውን ሳያጠናቅቅ ይህንን ጉዳይ በጥልቀት እንዲመለከተው እንደሚወተውቱ ለማወቅ ተችሏል።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና ህወሃት ለጊዜውም ቢሆን ከመንበሩ እንዲነሳ የማትመኘው አሜሪካ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አመራሮች በግል ለማነጋገር መጋበዟ ታውቋል። በተለያዩ መለያዎች የሚታወቁትን የኦሮሞ ድርጅቶች ለማነጋገርና ወደ ድርድር ሲቀርቡ አንድ ቅርጽ እንዲይዙ ለማድረግ ማሰቧ ተደምጧል።

አንድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር ለድርጅታቸው ከላይ የተጠቆመው አይነት ጥሪ መላኩን ለጎልጉል የአሜሪካ ዘጋቢ አረጋግጠዋል። የዚህ ጥሪ አካል ይሁን የሌላ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነትና የኦፌኮ ሊቀመንበር መረራ ጉዲና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን ራሳቸው በየፊናቸው ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ ክፍል (ECADF) የፓልቶክ መስኮት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት መረራ “አገሪቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ መክረናል” ሲሉ በሰለጠነ መንገድ አስቸኳይ ፖለቲካ መፈትሄ ሊፈለግ እንደሚገባ በመልሶቻቸው ወስጥ ሁሉ ሲያመላከቱ ተስተውሏል።hero

የሰማያዊ ፓርቲም መሪው ይልቃል ስላደረጉት ውይይት በፌስቡክ ገጹ ላይ አትቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ የመጣው የሕዝብ ተቃውሞ ለዓመታት የዘለቀ ግፍና መከራ ውጤት እንደሆነ የጠቀሱት ይልቃል፤ በአገዛዝ ላይ ያለው ኃይል ምንም ዓይነት ሕጋዊነት የሌለው በመሆኑ በሥልጣን ለመቆየት ባለፉት ዓመታት ሲያደርግ እንደቆየው መግደልና ማሰር እንደሚቀጥል ለአሜሪካውያኑ ሹሞች አስረድተዋል፡፡ አሜሪካ “የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦኛል” እያለች ለምታወጣው መግለጫ ሕዝቡ ምንም ግምት የማይሰጠው ደረጃ ላይ መድረሱን የተናገሩት ሊቀመንበር ይልቃል በማጭበርበር የተካነው ህወሃት ሥልጣን ላይ እያለ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ መካሄድ እንደማይቻል ፓርቲቸውም ሆነ ህዝቡ እንደማያምን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም “ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር የማድረጊያው ብቸኛ መንገድ ጊዜያዊ ባለአደራ መንግሥት ማቋቋምና በአዲስ በሚመሠረተው የምርጫ ኮሚሽን ባስቸኳይ ብሔራዊ ምርጫ ማካሄድ ነው” ማለታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ዜና መግለጫ አስታውቋል፡፡

እነ አባይ ጸሃዬ የኦሮሞና የአማራ መተባበር እንዳሰጋቸው ለአሜሪካ ባለሥልጣናት አስረግጠው መናገራቸውን፣ የሁለቱ ብሔሮች መተባበርና አማራ ክልል ህዝብ ነፍጥ ማንሳቱ ደግሞ አሜሪካንን እጅግ እንዳሳሰባት የሚናገሩት ምንጮች፣ የህዝብ ተቃውሞ እያየለ ከሄደ የአሜሪካ ውሳኔ ሰጪ ኃይሎች ሃሳባቸውን ሊቀይሩ እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ከዚህ ያለፈው ድርድር ግን የህወሃትን ዕድሜ ከማራዘም የዘለለ ትርጉም እንደማይሰጥ አክለው ተናገረዋል።

“ሕዝብ ላይ የተኮስህ ዕለት አለቀልህ፤ ሕዝብ ላይ መሳሪያ ያነሳህ ዕለት አበቃልህ” እያሉ በንጹሃን ደም ተጨማልቀው በድንገት የተሽቀነጠሩት መለስ ዜናዊ “ውርሳቸው” በደም ግብር እየጸና መሆኑን የሚጠቀሱ በርክተዋል። ስብሃት ነጋም “የመረረው ህዝብ ይነሳል። ይህ ዓለም አቀፋዊ እውነታ ነው” ሲሉ ለቅስቀሳ ፍጆታ ሲደሰኩሩ የተቀዳው ቅጂ በስፋት የማህበራዊ ገጾችን አጨናንቋል። እኒህ ሁለት የህወሃት ካስማዎች እንዲህ መሰሉን ስላቅ እየተጫወቱ ህዝብ ሲጨርሱ እንደነበር አይዘነጋም። በዚህ መልኩ የመቆመሪያ ካርዱን የጨረሰው ህወሃት ካሁን በኋላ ምንም ዓይነት “አስታራቂ ሃሳብ” ቢያመጣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የአንጋሾቹን ምዕራባውያን ቀልብ መሳብ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል የሚለው ብዙዎች የሚጋሩት አመለካከት እየሆነ ሄዷል፡፡pic1

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ከተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የክልሉ ኃላፊ የሆኑት ገዱ አንዳርጋቸው ቀለም የማይተፋ ብዕር እንደተሰጣቸው ተነግሯል፡፡ ከሥልጣናቸው ሳይነሱ የፖለቲካ ውሳኔዎችን የመፈረም ሥልጣን ለደመቀ መኮንን መሰጠቱን በህወሃት ወይም በሚዘውረው ሚዲያ በይፋ ባይነገርም በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ተበትኗል፡፡ በባህርዳር በተደረገው ተቃውሞ የብአዴን ባንዲራ ወርዶ በኢትዮጵያ ሠንደቅ መተካቱ፤ የብአዴን ንብረቶች መውደማቸው፤ ሰሞኑን “ህዝባዊ ወገንተኛ” ሆነዋል እየተባለ የሚነገርላቸው ገዱ ሁልጊዜ በኢህአዴግ ውስጥ “ሁለተኛነት” መጫወት የሰለቸውን ብአዴንን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እየወሰዱት ነው በሚል ፍራቻ ውሳኔው እንደተላለፈባቸው ተነግሯል፡፡ ሆኖም በኦሮሚያ ለዘጠኝ ወራት ያህል የኦህዴድ ንብረት ሲቃጠል፣ ሲወድም፣ … ሙክታር ከዲር ከስልጣናቸው ሳይነቃነቁ ገዱ ለዚህ መብቃታቸው ዜናውን ጥርጣሬ ላይ ከመጣል ባለፈ ህወሃትንና አሽከሩን ደመቀን ለበለጠ ጥላቻ በመዳረግ “ገዱ ለምን ተባረረ? ያለግምገማ ለምን ሥልጣኑን ተቀማ? …” በሚሉ አላስፈላጊ ንትርኮች ውስጥ ህዝቡን በማስገባት አቅጣጫ ለማስቀየር ሆን ተብሎ የታቀደ ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየትም ተሰጥቶበታል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. eunetu says

    August 11, 2016 06:16 am at 6:16 am

    ከታሪክ መማር የማያስችል ማንነት ተይዞ አገርን ለመምራት መሞከር፣ ወይም የትናንት ማንነትን እያዩና እየፈሩ አገርን / ሕዝብን ለመምራት መሞከር ፕሮፌሰር ቀደም ብለው በመጽሃፋቸው እንደጠቀሱት ሕዝቡን ጭኖ መሪውን የጨበጠው የኋሊት እያየ እንደሚነዳ ባቡር መሆን ነው ያሉት ትንቢት አሁን እየተፈጸመ አይመስላችሁም ወገኖቼ???

    Reply
  2. koster says

    August 11, 2016 11:51 am at 11:51 am

    TPLF fascists are terrorists, the al Qaida of the Horn of Africa bred and nurtured by UK/US/EU and their allies – the Arabs. It is a joke to try to have peace in the region with these fascists since they are propagating ethnic politics and use distability/war and famine as source of wealth to satiate their greed for wealth.

    Reply
  3. koster says

    August 11, 2016 11:54 am at 11:54 am

    I hope Samora Yunus will not return back to Ethiopia and be a Professor in one of the colleges in the USA.

    Reply

Leave a Reply to eunetu Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ላይ ጀብዱ ፈፀሙ August 11, 2022 03:04 pm
  • በኢትዮጵያ ግብርና ላይ ግብጽ ለዓመታት የፈጸመችው ሤራ August 10, 2022 10:58 am
  • የስሪ ላንካው “FamilyCracy” – ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ August 8, 2022 09:45 am
  • “አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”          July 19, 2022 04:57 pm
  • ሸኔ አመራሮቹንና ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ ነው July 19, 2022 01:55 am
  • የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች! July 18, 2022 03:13 pm
  • ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች July 17, 2022 05:36 pm
  • “ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ July 7, 2022 10:03 am
  • የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ July 6, 2022 01:38 pm
  • “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ July 6, 2022 01:53 am
  • “በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ July 5, 2022 12:57 pm
  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule