• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትህነግ አዲሱ ሤራ – አማራን በውክልና እልህ ውስጥ መክተት

October 19, 2020 04:46 am by Editor 8 Comments

* የአማራ ክልል ሰላም መሆን ለትህነግ ሤራ ስኬት ዕንቅፋት መሆኑ ተገመገመ  

ስብሃት ነጋ የሚባለው የትህነግ (ህወሃት) ማፊያ ቡድን አውራ ገና ወደ በረሃ ከመግባቱ በፊት አዲስ አበባ ፒያሳ ከገብረ ትንሳኤ ኬክ ቤት ዝቅ ብሎ ፍሎሪዳ ቡና ቤት መጠጥ ጠግቦ ሲወጣ ሽንት ያዘው። ከዚያም ከፍሎሪዳ እንደወጣ ያለው አደባባይ ላይ ለመሽናት አብሮት ከነበረው ባልደረባው ጋር በመሆን በሞቅታ እያወጋ ተጠጋ። አደባባዩ ላይ ሲሸና እየገለፈጠ “አማራ ላይ እንሽና” ማለቱን በወቅቱ አብሮት ከነበረው ሰው በጀብድ ሲወራ መስማቱን የመረጃ ምንጫችን ይናገራል።  

ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ብሎ በመሰየም አገር ሲያተራምስና ሲዘርፍ ኖሮ መንግሥት እንዲሆን ባዕዳን ኢትዮጵያ አናት ላይ አስቀምጠውት የነበረው የጥቂት ወንበዴዎች ጥርቅም ከጅምሩ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት የተነሳ በመሆኑ ከላይ የተገለጸውን ሃሳብ መጠራጠር አይቻልም።  

የሕዝብ ቁጣና መንገፍገፍ፣ አጋር ሆነው አብረውት ይሠሩ በነበሩ ለኅሊናቸው የቀረቡ ታጋዮች ኃይል የተሽቀነጠረው ትህነግ፤ “ዲጂታል ወያኔ” በሚል አንድ በገሃድ የተደራጀ ኃይል ይዞ ብቅ አለ። ይህ በበጀት፣ በሰው ኃይልና አጀንዳ በሚያዘጋጁ የትህነግ ቧለሟሎች የሚመራና በበላይ ጠባቂነት ደብረጽዮን የሚቆጣጠረው የሳይበር ጦር፤ ትህነግ ተመልሶ ኢትዮጵያን እንዳሻው እንዲጋልብ አልሞ ዘመቻውን ጀመረ። በሺህዎች በሚቆጠሩ የዲጂታል ወያኔ አባላት አማካኝነት የፈጠራ መረጃውን በማሰራጨት አገር ማተራመሱን ተያያዘ። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በየዕለቱ አገራዊ መረጃ የሚሰበስበው ሕዝብ የዚህ የሐሰትና የተዛባ መረጃ ሰለባ ሆነ።  

ቀደም ብለን ለዚሁ የሳይበር ወንበዴዎች ቡድን ቅርብ የሆነ ወጣት ጠቅሰን እንደዘገብነው ዋናው የዘመቻው ማጠንጠኛ የአማራ ህዝብና ዶ/ር ዐቢይ ናቸው። በተመሳሳይ አጀንዳ ቀደም ሲል ይህንኑ የመረጃ ምንጫችንን ጠቅሰን እንደዘገብነው “እረኛውን ግደል መንጋው ይበተናል” በሚለው የወንበዴው የሳይበር ዘመቻ ዶ/ር ዐቢይን ከሕዝብ ለመነጠል የተረጨው የማጠልሸት ዘመቻ በውጤት ደረጃ እጅግ ስኬት ማስመዝገቡን በግምገማ አረጋገጡ።  

ከግምገማው በኋላ እንደ አቅጣጫ የተቀመጠው “ሕዝብ ወያኔ ይሻላል እያለ ነው። ዳግም ወደ አመራር ተመልሰን አገሪቱን እንድናረጋጋ ጥያቄ ቀርቦልናል” የሚሉና ሌሎች ተመሳሳይ ቅስቀሳዎችን በማሰራጨት ወደ ቀጣዩ የትግል ምዕራፍ ለመሸጋገር ተወሰነ።  

ትህነግ ለይቶ ዶ/ር ዐቢይ ላይ ዘመቻ መክፈቱ፣ ዘመቻውም በስኬት መገምገሙ የራሱ እንደምታ ያለው ጉዳይ ቢሆንም፣ ትህነግ ከዚሁ ጎን ለጎን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የውክልና አተራማሾችን በዘረፋ ያከማቸውን ከፍተኛ ሃብት በማሰራጨት አሰማርቶ ህዝብ ሰላም እንዳይሰማው ማድረጉንም በተመሳሳይ በስኬት እንደገመገመ ይኸው የጎልጉል መረጃ አቀባይ አስታውቋል።  

በአማራ፣ በኦሮሞና በታቦትና ቅዱሳን መገለጫዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የተበተኑት የሳይበር ጭፍሮች፣ ታልሞና ታስቦበት ከበላዮቻቸው የሚሰጣቸውን የዓላማ ማስፈጸሚያ አጀንዳ “ሳያኝኩ የሚውጡ” ሼር ማድረጋቸው ትልቁ ችግር መሆኑ ቢገለጽም ዜጎች ሊማሩ አለመቻላቸው አሳዛኝ እንደሆነ ጉሊና ይሄይስ የተባሉ ተከታታያችን በወቅቱ በአጭር መልዕት ሳጥን ልከውልን እንደነበር መግለጹ ለአሁን አስፈላጊ በመሆኑ ጠቅሰነዋል።  

ጉሊና አንድ ገጠመኛቸውን አክለዋል “አንድ የማውቃት የትህነግ ደጋፊና ጽንፈኛ አቀንቃኝ ጓደኛ ነበረችኝ። ከትህነግ ታዋቂ ሰዎች የአንዱ ሚስት ነበረች። እንዴት እንደተመቻቸላት ሙሉ መረጃ ባይኖረኝም ዛሬ አሜሪካ ንብረት ገዝታ ትኖራለሽ። አመጹ በተቀጣጠለበት ወቅት ‘ኦሮሞ በትግሬዎች ዘንድ እንደ ሰው አይቆጠርም። አንድ ትግሬ ኦሮሞ ካገባ ይናቃል’ ትለኝ ነበር። አንድ ቀን በድንገት የኦሮሞ ተቆርቋሪ ሆና አገኘኋት። ምን ተገኘ በሚል ስጠይቃት ‘ፖለቲካ ነው። እኛ በስሜት አንነዳም። የትግልና የግንኙነት መስመር አለን’ አለችኝ። ግንኙነታቸን ብዙ ስለሚያጫውተን በርካታ ነገር ብላኛለች። ይህንን ቀንጥቤ የላኩት የሚሰማ ካለ ከስሜት እንዲላቀቅ ብታደርሱ ብዬ ነው” ሲሉ በመልዕክት ሳጥናችን አስፍረዋል።  

የጎልጉል መረጃ አቀባይ ሰሞኑንን በነገሩን መሠረት የህወሃት ደጋፊዋ ሴት “እኛ በስሜት አንነዳም” ከማለቷ ጋር ዝምድና ያለው ነው። እንደ መረጃው ሰው ዲጂታል ወያኔ የሚባለው የሳይበር ወንበዴዎች ጭፍራ አማራን አልሞ አዲስ ሤራ ተግባራዊ እያደረገ ነው።  

ይህ የሆነው አንዱ የዲጂታል ወያኔ ጭፍራ የመስመር መኮንን ዳንኤል ብርሃኔ “ከመስከረም በኋላ የሚሆነውን ጠብቁ፤ ዐቢይ በዘር ማጥፋት በቅርቡ ለፍርድ ይቀርባል…” እያለ ሲያሰራጭ እንደነበረው፣ ልደቱና እነ ጃዋር በተደጋጋሚ እንዳስረዱት ከመስከረም በፊት መንግሥትን ለማሽቀንጠር በትሥሥር ከፍተኛ ሃብት ፈስሶ የተነደፈው ዕቅድ እንዴት ከሸፈ በሚል ግምገማ ከተደረገ በኋላ ነው።  

በዚሁ ግምገማ መሠረት የትህነግ ኃላፊዎች በስብሃት ነጋ መሪነት ባደረጉት ግምገማ “አማራው ክልል ሰላም መሆኑ ዕቅዳችን እንዳይሳካ አድርጓል” የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። እንደ መፍትሄ ያቀረቡት ይህን ከጅምሩ ሊያጠፉት በመታገያ ደብተራቸው ላይ በጠላትነት የፈረጁትን ሕዝብ በግድያ፣ በጥቃት፣ በትንኮሳ፣ ወዘተ ትዕግስቱ እንዲያልቅ ማድረግ ነው። ትዕግስቱ ሲያልቅና በተለይ በማንነቴ ላይ የተቃጣውን እመክታለሁ በማለት ወደ ኃይል ርምጃ ሲገባ አገሪቱ ትተራመሳለች። ስለዚህም ይህ ይሆን ዘንድ ምን መደረግ አለበት ተብሎ አዲስ ዕቅድ በማፊያው ቡድን ህወሃት ተነድፏል።  

እነ ጃዋርን አቅፎ የተነደፈውና እነ በቀለ ገርባ ትግራይ የተመላለሱበት፣ ዳውድ ኢብሳ አመራራቸውን ትግራይ ድረስ ሲያመላልሱ የነበረበት፣ አንዳንዶቹ የወጣት ሊግ አመራሮቻቸውን ወደ መቀሌ የላኩበት፣ በወላይታ፣ በቅማንትና በአገው ሕዝብ ውስጥ ሲሠራ የነበረው የተቀነባበረ ሤራ ህወሃት የበጀተውን ሃብት ቀርጥፎ ህልም በመሆኑ አማራ ክልልን ካልተተራመሰ ትህነግ ያሻውን እንደማያሳካ ታምኗል።  

ለዚህ ነው በቤኒሻንጉል ንጹሃን የአማራና የአገው ተወላጆች የሚገደሉት። በተደጋጋሚ ንጹሃን ላይ ዕልቂት እንዲፈጸም የሚያቀናብሩት ቤኒሻንጉል የተቀመጡ የትግራይ ኢንቨስት አድራጊ ተብዬዎች እንደሆኑም የሁለቱም ክልል መሪዎች በይፋ መናገራቸው የመረጃውን ሰው ትክክለኛነት ያሳያል። ሌላው ማሳያ በቤኒሻንጉል የሚፈጸመውን ግድያ በምስል በማስደገፍ የትህነግ ሚዲያዎችና የዲጂታል ወያኔ ጭፍራዎች መበተናቸው ነው። ጉሊና እንዳሉት መረጃ ሳያኝኩ የሚወጡ ግማሹ ለከንቱ ክሊክና ሳንቲም ለቀማ፣ ሌሎች ደግሞ በቁጭትና ሀዘን ሼር እያደረጉ ያሰራጩታል። በውጤቱም የአማራ ህዝብና አመራሮች አሁን እየታየ እንዳለው ወደ ንዴትና እልህ እያመሩ እርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ላይ መድረሳቸውን በማወጅ ላይ እንዲደርሱ እያደረጋቸው ሆኖ ታይቷል።  

ይህ ብቻ አይደለም አማራውን ወደ እልህ የሚከቱ በርካታ ዕቅዶች አሉ። አንዱን ዕቅድ በሌላኛው በማጀብ የሚተገበረው ይህ አማራውን አበሳጭቶ ወደ ግጭት የመንዳት አካሄድ ከፍቼ እስከ ሱሉልታ ባለው መንግድ በቅርቡ የታጠቁ የኦሮሚያ ኃይሎች ፈጸሙት የሚባለው ህገወጥ ድርጊትና ግድያ ሌላው ዕቅድ ነው።  

ከቅርብ ወራት ወዲህ ከአማራ ክልል በደጀን መስመር ወደ አዲስ አባባ የሚሄዱና የሚመለሱ ከባድ የደረቅ የጭነት ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከጎሐጽዮን ደብረጉራቻ ባለው መስመር ማለፍ ፈተና ሆኖባቸዋል።

አስተያየታቸውን ከሰጡት አሽከርካሪዎች መካከል አንዱ “ከፍቼ ከተማ የቅርብ ርቀት ከምትገኝ ‘አሊ ዶሮ’ ከተባለች ቦታ ላይ መስከረም 30/2013 ዓም የክልሉን የፀጥታ ኃይሎች የደንብ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው የቆሰሉና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሽከርካሪዎችና ከ10 በላይ የተሰባበሩና የተቃጠሉ መኪናዎች አሉ” ብሏል። የሞቱም እንዳሉ ተዘግቧል።

“ጠላትም ወዳጅም ይስማ” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን በፌስቡክ ገጻቸው ከትናንት በስቲያ እንዳሉት ካሁን በኋላ ማንም ይሁን ማን አጸፋ እንደሚመለስ መናገራቸው፤ የጸጥታው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ በተደጋጋሚ ስሜታቸው መጎዳቱንና እርምጃ እንዲወሰድ የሚገፋፉ ሃሳቦችን በአማራ ሚዲያ ማሰራጨታቸው ምናልባትም ሳያስቡት ትህነግ ባስቀመጠው የመጨረሻው ባቡር መሳፈር እንዳይሆን የመረጃው ምንጫችን ስጋቱን ይገልጻል።

ከሃጫሉ ሁንዴሣ ግድያ በኋላ በሻሸመኔና ሌሎች አካባቢዎች ሰዎች በማንነታቸው በግፍ መጨፍጨፋቸው “አማራው ራሱን ይከላከል” የሚለውን ሃሳብ እያጎላው ከመጣ ሰነባብቷል። ይህንንም ተከትሎ ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ቤተክርስቲያን ራሷ መከላከል አለባት በማለት ሲናገሩ በአዳራሹ የነበረው ተሰብሳቢ ሞቅ ባለ ጭብጨባ ማገዙ ፓትርያርኩ በጉዳይ ፈጻሚነት ይሁን ከቁጭት በመነሳት መናገራቸው ባይታወቅም ትኩረት የሳበ ሆኗል።

የመተከሉን በህወሃት የተቀነባበረና በሎጂስቲክስ የታገዘ የግፍ ግድያ ተከትሎ ምክትል ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን “ልብ ሰባሪ” ነው ያሉትን ጥቃት ለመከላከል የአካባቢው ሕዝብ ተደራጅቶና ታጥቆ ራሱን መከላከል አለበት ማለታቸው “አማራን እልህ በማስጨረስ የአጸፋ ጥቃት ውስጥ ማስገባት” ወደሚለው የህወሃት የሤራ ቀለበት በቁጭት ሰበብ አስገብቷቸው ይሆን የሚያስብል ሆኗል።    

የገንዘብ ለውጡን ተከትሎ ትህነግ ጉሮሮው እየታነቀና እንደ ቁስል እየነቃ ስለሆነ ይህ የመጨረሻው ዕቅድ ሊሆን እንደሚችል በርካቶች ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። በዚህም ሳቢያ የአማራ ክልል የሚያደርገውን ሁሉ ከስሜት በጸዳ አግባብ እንዲያከናውን ምክር የሚሰጡም ጥቂት አይደሉም።  

ትህነግ ይህንን ዓላማ ለማሳካት በርካታ ርቀት ልትሄድ እንደምትችል የሚጠቁመው የጎልጉል የመረጃ አቀባይ በቅርቡ በሃይማኖት ተቋማት የቀረበው ተነስ ታጠቅ ምን አልባትም የዚሁ አማራውን ጎትጉቶ ቃታ እንዲስብና አገሪቱ እንድትወላልቅ ማድረግ፣ ከዚያም በሰላም ማስከበር ስም ትህነግ ዳግም ህልሙን ዕውን ሊያደርግ ያሰበበት ረቂቅ ሤራ ሊሆን የመቻሉ ጉዳይ በጥንቃቄ መታየት የሚገባው ነው።

የኅልውና ጉዳይ፤ የመኖርና ያለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ ያለው የአማራ ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲህ ተደራጅቶና ታጥቆ ራሱን መከላከል እንዳለበት በመርህ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ጉዳይ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ርምጃ ሲወስድ ግን ለዚህ ሁሉ ግፍ ያበቃውንና “ጠላቴ ነህ” ብሎ የሰየመውን ህወሃትን፤ “አማራ ላይ እንሽና” በማለት ከተናገረው የበረኻ ወንበዴዎቹ ዋና አምበል ስብሃት ነጋን ታሳቢ በማድረግ፣ በሰከነ እና ጥቅምና ጉዳቱን፤ ግራና ቀኙን በጥሞና ባገናዘበ መልኩ ሊሆን እንደሚገባው የሚስማሙ ጥቂቶች አይደሉም።   


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

  

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics, Slider Tagged With: amhara, amhara region, sebhat nega, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Esubalew Chekol says

    October 19, 2020 07:24 am at 7:24 am

    ይህ ሴራቸው እንዳይሳካ፤ ሁላችንም አንድ መሆን ይጠበቅብናል።

    Reply
  2. Mussie Abraha says

    October 19, 2020 07:51 am at 7:51 am

    ባለፉት ዓመታት በናንተና እናንተ መሳይ መዲያዎች የተረጨ መርዝ ኣልሰራም።ኣሁንም ከዛው ኣልወጣችሁም። እኔ የምለው
    ይህ ትህነግ የሚባል የትግራይ ገጂ ድርጅት ምን ያክል ሓይለኛ ቢሆን ነው ሃገርን ሙሉ የሚያተራምሰው?
    ትህነግ ትርፍ ግዜ፡ ትርፍ ገንዘብ፡ ትርፍ የሠው ሓይል ኣለው’ዴ?
    የኣማራ ሕዝብ በራሱ የሴራ ፖለቲከኞች እየታመሰ ነው።
    ሌላው ደግሞ፡ የትግራይ ሕዝብ ሲገደል ፈንጠዝያ፡ የኣማራ ሕዝብ ሲገደል ለቅሶ፡ ምን ዓይነት ሳይኮሎጂ ነው?
    የሴራ ጉንጉናችሁ ኣቆሙና ሕዝቡን ከሽግር እንዲወጣ ኣግዙት። ብያንስ የምትረጩት መርዝ ያንድን ኣከባቢ ሕዝብ ብቻ እንደማየጠቃ እንዴት መገብዘብ ኣቃታችሁ?

    Reply
  3. ታዛቢ says

    October 19, 2020 08:18 pm at 8:18 pm

    ይሄ በሱሪው የሚሸና ሰካራም ኢትዮጵያን የሚያህል ታላቅ ሀገር ለመምራት ዕድል ማግኘቱ የሚያስዝን ቢሆንም በታዋቂው ክፍት አፍ ባሕርዩ ልንደነቅ አይገባም!
    ያም ሆነ ይህ እኛ ወያኔ ካዘጋጀልን የዛገ የዘር ጣሳ ውስጥ እንውጣ!
    በየጊዜው በተነሳው አጀንዳ ስንባላ ወያኔ ሥሩ ጠንክሮ: ብሩ ወልዶና በሀብት ከብሮ ለመነቅነቅቅ ከማዳገቱ በፊት የቆምንበትን አንጻራዊ ነፃነት መናዱን እናቁም!!
    ከገለበው እየገልብን እስከዘላለሙ እራቁታችንን እንዳንቀር!
    የምናጣው ስው አይደለም
    ሀገርና ዜግነት ንው!!!!

    Reply
  4. miko says

    October 20, 2020 03:39 am at 3:39 am

    የአማራ ህዝብ ጠላት ትናንትም ዛሬም ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው።የወያኔ ስትራቴጅያዊ ግብ የአማራን ህዝብ በሂደት አዳክሞ ወደ ምንምነት በመቀየር የሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀይል ሁኖ መውጣት ነው።ወያኔ ከትግራይ መሬት እግሩን እስካልነቀለ ድረስ አማራ መቼም ሰላም አይኖረውም።ስለዚህ የወያኔን ጉዳይ ሳይሰለቹ መከታተል ያስፈልጋል።

    Reply
  5. wonde says

    October 20, 2020 01:00 pm at 1:00 pm

    tikat bederese kutir tateku eyalu yemizebarikutin beyifa satikawemu bemedegef simet mazem tegebi new???? tatekuna erasachihun tekelakelu malet genocide mawej mehonun tegenzebu.yanne manim ayinorim,hagerim ayinorim!! beteley yehayimanot abat ena keftegna balesiltan yihenin sisebik yamal . tadiya jawar min atefa?? bekele gerbas?? kristiyanis min atefa?? eskindiris min atefa?? wey enezihin tasariwoch meftat wey degimo tateku eyalu yesebekkutin vice prime minister ena patriarch mekses new !!!!!

    Reply
  6. Tesfa says

    October 23, 2020 09:12 am at 9:12 am

    የሃበሻው ፓለቲካ ባለበት የሚሄድ ተለዋጭ በስፍራው የሚተካበት እንጂ ለህዝባችን ከዚህ ግባ የሚባል ነገር ያመጣው የለም፡፡ ብቻ ያለፈውን እየኮነነ ራሱን እያገነነ በጊዜው ቦጥቡጦ በሌላ ራብተኛ ይፈነገላል፡፡ በተለይ ደግሞ ወያኔና ሻቢያ በምድራችን ላይ ከበቀሉ ወዲህ የዘር ፓለቲካ ያለ ልክ ተለጥጦ አብሮ የኖረውን ህዝብ ለራሳቸው የመኖሪያ ብልሃት ሲያጫርሱት አይተናል እያየንም ነው፡፡ አሁን በለውጥ መልክ ወያኔን ገሸሽ አርጎ በስልጣን ላይ ያለው የኦሮሞ ብሄርተኛ ስብስብም ያው በዘሩና በቋንቋው ተለክፎ ሽማግሌን፤ ነፍሰ ጡርን በቢለዋ አራጅና ቤት አቃጣይ ሆኗል፡፡ ባጭሩ በጠ/ሚሩ የሰላም ጥሪ የገቡ የብሄር የዝንተ አለም ተፋላሚዎች ዛሬም ከመተናኮስና ተንኮል ከመሸረብ አላለፉም፡፡ ከመስከረም 30 በህዋላ መንግስት አይኖሩም ያሉት አሁን በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ወተው ሲገቡ ማየት የእብደቱ ፓለቲካ ምን ያህል ናላቸውን እንደ በወዘው ያሳያል፡፡ ዘረኝነት ህመም ነው፡፡ ቋንቋ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ ሂሳብ የሚያሰራ፤ ከሳይንሱ ጋር የሚያገጣጥም፤ በአለም መድረክ ላይ እኩል የሚያደርግ ቢሆን እሰየው ይባላል፡፡ ከበሮ ለመምታትና ክራር ለመከርከር አልፎ ተርፎም ሌላውን ያዘው ጥለፈው ግደለው የሚለው የቋንቋና የክልል ፓለቲካ የውሻ ፓለቲካ ነው፡፡ ሃገሪቱ በተኩላዎች ተከባለች፡፡ የትላንቱን ከመሳደብ ይልቅ ዛሬ ምን እያደረግን ነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነበር፡፡ ግን እንደ እንቁራሪት አንድ ሲጮህ አብሮ የሚጮህ የመንጋ አስተሳሰብ ተከታይ የራሱ እይታ የለውምና አብሮ መንጎድ ነው፡፡ ወያኔ የመከራ ቋት ነው፡፡ ወያኔዎች ስብእና የላቸውም፡፡ በ 27 ቱ አመት የተሰወሩትን፤ ብልታቸው የተጎተተውን፤ ብልታቸው ውስጥ እንጨትና ስለት የገባባቸውን፤ እግራቸው የተቆረጠውን፤ አንገታቸው ተቆርጦ ቤ/መንግስት በራፍ ላይ የተንጠለጠለውን አስከሬን እያሰቡ ጭካኔአቸው ከሰው ባህሪ ውጭ እንደሆነ ያስረግጣል፡፡
    አሁን ትግራይ ትግራይ የትግራይ ህዝብ የሚለው ወያኔ የአለምን የፓለቲካና የኢኮኖሚ ኡደት አልተረዳም፡፡ ወደፊት ፓለቲካው ሳይሆን አለምን የሚያሽከረክረው ቴክኖሎጂው ነው፡፡ ልክ 911 ኣለምን ባልተፈለገ መልኩ እንደቀየራት ሁሉ ኮቪድ 19 የትምህርት አሰጣጥን፤ የኢኮኖሚ ስሪትንና መስፈርትን ከሞላ ጎደል ይለውጣል፡፡ ባጭሩ አለም ክብ መሆኗ ቀርቶ ጠፍጣፋ ትሆናለች እየሆነችም ነው፡፡ የአንዲት ሃገር ባንዲራ ማውለብለብ፤ በጦር መሳሪያ ጋጋታ ይህንና ያን ማለት ሁሉ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ ዛሬ ሁሉም የጦር መሳሪያ አምራች ነው፡፡ ለዛ ነው ሃገራችን ከቱርክ በተሰራ መሳሪያ የተጥለቀለቀቸው፡፡ በህንድ፤ በብራዚል፤ በአርጅንቲና፤ ሁለቱ ኮሪያዎች፤ የእስያ ሃገሮች ሁሉ የጦር አምራችን ናቸው፡፡ በመሆኑም በሩሲያና በአሜሪካ ወይም በሌሎቹ ሃያላን መንግሥታት ጫና የሚያጎበድድ ብዙ አይኖርም፡፡ ትምህርትን በተመለከተ እንደ በፊቱ ይህ ዲግሪ አለው ያ ትምህርት ቤት ነው የተማረው ተብሎ መቀጠርም ይቀራል፡፡ ሥራው ገሚሱ reality augmentation (AR) and Artificial Intelligence (AI) ሲከወን ቀሪው ሰው በችሎታው እቤቱ ተቀምጦ የሚሰራው ይሆናል፡፡ ስለሆነም ሃገር ሃገር እኔ ለእኔ ብቻ የሚለው የጠባብ ብሄርተኞች ፓለቲካ አፈር ድሜ ይበላል፡፡ ነገሩ የትም ፍጪው ድቄቱን አምጪው ነውና! የወያኔም የአማራን ህዝብ እስከ ዝንተ ኣለም ማስለቀስ ያበቃል፡፡ እስከዚያው ይሁን ይሸርቡ፤ ያፍርሱ፤ ይግደሉ፤ ዋ ለሁሉም ቀን እንደሚመጣ ግን አይርሱ፡፡ በቃኝ!

    Reply
  7. ዘረ-ያዕቖብ says

    November 2, 2020 11:13 pm at 11:13 pm

    “Ethiopia’s Tigray blocks general’s appointment in blow to Abiy
    October 30, 2020”

    Reply
  8. ዘረ-ያዕቖብ says

    November 4, 2020 01:40 am at 1:40 am

    ጦርነት ጥፋትን እንጂ ልማትን አያስከትልም፣ ከመዋጋት ይልቅ መግባባት ይመረጣል!

    Reply

Leave a Reply to Tesfa Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule