• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መፍትሔ የራቀው የአሸባሪው ሕወሓት የዘረፋ ሱስ

August 30, 2022 04:44 pm by Editor Leave a Comment

ባሳለፍነው ሳምንት አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ሰብዓዊ ርዳታዎችን ለሚያመላልሱ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውልና በዓለም ምግብ ፕሮግራም መቀሌ መጋዘን የተከማቸ ነዳጅ መዝረፉ ይፋ መሆኑ አይዘነጋም። በወጣው መረጃም ቡድኑ 12 የነዳጅ ቦቴዎችን በአጠቃላይ 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉ ነው የተመላከተው።

የፖለቲካና ፌዴራሊዝም ምሁሩ ሀይለየሱስ (ዶ/ር) አዲስ ልሳን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ አሸባሪው ሕወሓት ከጅምሩ አንስቶ የተለያዩ የስርቆት ወንጀሎችን ሲፈፅም የኖረ መሆኑን አውስተው፤ በተለይ በከፍተኛ የዕለት ደራሽ ድጋፍ ላይ ሲፈፅም የነበረው ዝርፊያ ህዝቡ በረሀብ እንዲያልቅ ከመፍረድ ለይተው እንደማያዩት ነው የገለፁት።

አንድ ፓርቲ፤ አንድ ህዝብ የሚል አስተሳሰብ የቆየና ኮሚኒስታዊ አመለካከት እንደሆነ የሚያስረዱት ምሁሩ አክለው እንዳስገነዘቡት፤ አሸባሪ ቡድኑ አሁን ላይ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በየትኛውም አግባብ ህዝባዊ ውግንና የሌለውና ስልጣንና ስልጣንን ብቻ ያስቀደመ ነው። ይህንንም “እኛ ስልጣን ካልያዝን ሁሉም ይውደም” የሚል ዓይነት እኩይ ተግባራቸው ማሳያ ነው ይላሉ ምሁሩ።

የሽብር ቡድኑ ከሰሞኑ የፈፀመው የነዳጅ ስርቆት ተግባር አስቀድሞም ሲፈፅመው የነበረ የእኩይ ባህይሪው መገለጫና የነውረኛነቱ ማስታወሻ መሆኑን ያነሱት ሀይለየሱስ (ዶ/ር) የውጭ መንግስታት ተግባሩን ለማውገዝ የሄዱበት ርቀት ግን ለትችት የሚዳርግ ነው ይላሉ። በእርግጥ ዘግይተውም ቢሆን በራሳቸው ላይ ሲደርስ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ቢሆንም ከጉዳዩ ክብደት አንፃር በቂ አይደለም ነው የሚሉት።

በመቀሌ ለሰብዓዊ ድጋፍ ተከማችቶ የነበረ ነዳጅ በሽብር ቡድኑ መዘረፉን አስመልክቶ የዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃውን ይፋ ከማድረጉ ጋር ተያይዞ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ቢሆንም በትክክል የዚህ ጥፋት ተጠያቂው አሸባሪዉ ሕወሓት ነውና ከድርጊቱ ሊቆጠብ ይገባል የሚል መልዕክት በሁሉም የውጭ አካላት አልተላለፈበትም፤ ይህ መሆኑ ደግሞ ምን ያህል የውጭ ጣልቃ ገብነት እንዳለበት የሚያስገነዝብ ነው ይላሉ።

ያም ሆነ ይህ ግን በአሁኑ ሰዓት ሕወሓት ላይ እየደረሰበት ያለው ውግዘት የመጣውም በቀጥታ በተራድኦ ድርጅቶች አማካኝነት በመሆኑ ተሰሚነቱ ከፍ ይላልና የኢትዮጵያ መንግስት አጋጣሚውን ቸል ሊለው እንደማይገባም መክረዋል። በእንግሊዝኛ ቋንቋ በስፋት እየተሰራጨ ያለውን የቡድኑን የዘረፋ መረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች በማስተጋባት የዓለም ማህበረሰብ እንዲረዳ ማድረግ ይገባል ሲሉም መክረዋል።

ህዝቡም ቢሆን ለሀገር መዳን ቅድሚያ ሰጥቶ አሸባሪውን ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አደብ ለማስገዛት የሚደረገውን ርብርብ ሊደግፍ ይገባልም ሲሉ ነው ምክራቸውን የለገሱት።

ይህ አሸባሪ ቡድን የትግራይ ህዝብን መበደል ከጀመረ ረጅም አመታትን አስቆጥሯል። ገና ወደስልጣን ለመምጣት ሲያልም ጀምሮ ጦሩን ሊደግፍልኝ ይችላል ያለውን ወንጀል ሁሉ ሲፈፅም እንደነበር ነው ዶ/ር ሀይለየሱስ ያስታወሱት።

ህይወትን ያለምግብና ውሃ ለማቆየት ትግል በሚደረግበት በ1977 ዓ.ም በሕወሓት ታጣቂ ቡድንና በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት መካከል ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱ የሚታወስ ነው። ይህ ወቅት ለበርካቶች የስቃይ ወቅትም ነበር። ሀገሪቷም ምድር ላይ ያለች ሲዖል የሚል ስያሜ ተሰጥቷት እንደነበር ታሪክ ያወሳል። ይህንን የተረዱት አለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶችም የህይወት አድን ስራን አንድ ብለው ቢጀምሩም መልካም ምግባራቸው ለፅንፈኞች ሲሳይ ነበር የሆነው። የሕወሓት የሽብር ቡድን ተላላኪ የሆኑ ሰዎች ረሀብተኛ አርሶ አደር መስለው በመቅረብ ለትግራይ ህዝብ የዕለት ደራሽ መግዣ እንዲውል የታቀደውን አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር ወደ ህወሓት ካዝና እንዲገባ አድርገዋል።

የፖለቲካ ተንታኝ አንድሪው ቆሪብኮ እኤአ ሰኔ 9 ቀን 2022 ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ ላይ እንዳመለከቱት፤ አሸባሪው ህወሓት ወደ ቀድሞ የተንኮል ተግባሩ የተመለሰበትን ለሰብአዊ እርዳታ የቀረበን ንብረት ለጦርነት ማዋል ነው። በ1985 በኢትዮጵያ በተከሰተው ረሃብ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሃብ ለመዋጋት ከተሰበሰበው 100 ሚሊዮን ዶላር 95 በመቶውን የጦር መሳሪያ መግዛቱን አስታውሰዋል።

በድርቅ ለተጎዱና ለረሀብ ለተጋለጡ ኢትዮጵያውያን የተሰጠው ይህ ገንዘብ ለዚያን ጊዜ አማፂው ህወሓት የጦር መሳሪያ መግዣ መዋሉን የተለያዩ የፅሁፍና የድምፅ ማስረጃዎች ያመላክታሉ። በመረጃዎቹ መሰረትም አሸባሪው ሕወሓት በረሀብ ለተጎዱና በሞት አፋፍ ላይ ላለዉ የትግራይ ህዝብ ከመጣው የነፍስ አድን እህል መግዣ ውስጥ 95 በመቶ ያህሉን ለጦር መሳሪያ መግዣነት አውሎታል። በዚህ ሳቢያም በርካታ ህፃናትና አዋቂዎች እንደቅጠል እንዲረግፉ ሆነዋል። ይኸን ድርጊት ከፈፀመው 37 ዓመት ቢያልፉትም የተጣባው የዘረፋና ለዜጎች ቅንጣት ታህል አለማሰብ አባዜውን ዛሬም ደግሞታል።

የሽብር ቡድኑ የትግራይ ህዝቦች ይህንና ሌሎች በርካታ የሰቆቃ ጊዜያትን እንዲያሳልፉ ፈርዶባቸዋል። እየፈፀማቸው የመጡ የግፍ ተግባራትም በታሪክ ተከትበዋል።

የዛሬ ዓመት ገደማ የተፈፀመ ሌላ የእለት ደራሽ እህል ምዝበራ የቅርብ የአሸባሪው ህወሓት ነውራዊ ተግባር ማሳያ ነው። አሸባሪው ቡድን ከተሞችን አውድሞና የነዋሪዎችን ሀብት ከዘረፈ በኋላ የዩኤስ ኤይድ የእርዳታ እህል ማከማቻን በመስበር የእለት ደራሽ እርዳታን ዘርፎ ወስዷል።

ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ ደግሞ ሰብዓዊ ርዳታዎችን ለሚያመላልሱ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውልና በዓለም ምግብ ፕሮግራም መቀሌ መጋዘን የተከማቸ ነዳጅ መዝረፉም ይፋ መሆኑ አይዘነጋም። ዳግም ከተቀሰቀሰው ውጊያ ጋር በተያያዘ ነሀሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ማለዳ ላይ መቀሌ የሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በትግራይ ኃይሎች ዘረፋ መፈፀሙንም ያመላከተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ነው።

የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪው ማርቲን ግሪፊዝም፤ በመቀሌ በሚገኘው የዓለም የምግብ ፕሮግራም መጋዘን ላይ የተፈፀመውን የነዳጅ ዝርፊያ አውግዘዋል።

ዋና ፀሀፊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ሃሳብ፤ በትግራይ ክልል መቀሌ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ውስጥ የነበረው ነዳጅ በችግር ውስጥ ላሉ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት ለማድረስ የሚያስችል ነበር ብለዋል። የነዳጁ መዘረፍ የምግብ ዋስትና እጦት እየጨመረ ባለበት በዚህ ወቅት መዘዙ አስከፊ ሊሆን እንደሚችል አመላክተዋል።

በወቅቱ በወጣው መረጃም ቡድኑ 12 የነዳጅ ቦቴዎችን በአጠቃላይ 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉ ነው የተመላከተው። ቡድኑ ድርጊቱን የፈፀመው በኃይል በመሆኑ በስፍራው ያሉ አካላት ለመከላከል እንዳልቻሉ ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት።

ይህ ሁሉ ሲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የሚመለከታቸው ሃላፊዎቻቸው ድርጊቱ አሳስቦናል ከሚል መግለጫ በስተቀር አንዳች ርምጃ ሲወስዱ አልታዩም። አሸባሪው ሕወሓት አሁን ከፈፀመው ኢሰብአዊ ድርጊት አንጻር አለም አቀፋዊ ጫናዎች እንደሚደረጉ የሚጠበቅ ቢሆንም እስከአሁን በዚያ ደረጃ የተወሰዱ ርምጃዎች የሉም። በዘረፋ ሱስ የተጠመደዉ አሸባሪዉ ሕወሓትም ከኢትዮጵያ መንግስት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ በመተዉ በመንግስት ላይ ጦርነት ከፍቷል። (አዲስ ሚዲያ-በየሺ ወልዴ)



Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Right Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule