• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የስለላ ሰራተኞች መሯቸዋል፤ በጽናት የሚሰራ የለም”

March 28, 2015 01:16 am by Editor 1 Comment

በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ። ለዓመታት የስለላ ሠራተኛና የአዲስ አበባ ቀጠና ኦፊሰር የነበረች የህወሃት አባል መክዳቷ ታወቀ።

የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው።

አዲስ አበባ የሚገኙ ባልደረቦቿ “እርሷ ዕድለኛ ናት” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳሳበቁት፣ ኦፊሰሯ ስፔን አገር ከባልደረቦቿ ተለይታ ያመራችው ወደ አሜሪካ ነው። እዚያም እንደ ደረሰች እንደማትመለስ አረጋግጣለች። የትግራይ ክፍለ ሃገር ተወላጅና ታማኝ የህወሃት አባል የነበረችው የስለላ ሰራተኛ፣ ከቀበሌ ተነስታ ለከፍተኛ ሃላፊነት የበቃች ታማኝ ነበረች።

በብሔራዊ የደህንነት መዋቅር ውስጥ መሰላቸት፣ አለመተማመን፣ ጫና እንዲሁም ነጻ ሰዎች ሳይቀሩ የሚደረግባቸው ክትትል ጤና የነሳቸው ተበራክተዋል። በተለይም የህወሃት ያልተማሩ ነባር /አንጋፋ ባለሥልጣናት/ ታጋዮች የሚሰጡት ቅጥ ያጣ መመሪያና ወሬ ለቃሚዎቸ ከየመንደሩ ለብር እያሉ የሚያቀረቡት የሰላማዊ ሰዎችን ህይወት የሚያናጋ መርጃ ዕረፍት እንደነሳቸው የዜናው ምንጮች አመልክተዋል።

“በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ ተቀምጠው የሚያገለገሉ ባብዛኛው ደስተኛ አለመሆናቸው በገሃድ ስለሚታወቅና የመውጫው ቀዳዳ ስለተዘጋ” በሁሉም አቅጣጫ መሹለኪያ ፈላጊውና በሰላም መኖር የሚመኘው ክፍል እንደሚያይል ያመለከቱተ ዜና አቀባዮች “የኢህአዴግ ዙሪያ መለሱ ቆሽሾዋል፤ የእርስ በርስ መተማመኑም ኮስሷል” ብለዋል። በማያያዝም በርካታ አመራሮች አገር ለቅቀው መውጣት እንደማይችሉ አስታውቀዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (ሚያዚያ 2፤2006ዓም/April 10, 2014) “ከአገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣናት በጭንቀት ውስጥ ናቸው፤ “አሁን ያለው ኢህአዴግ ላዩ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል”” በሚል ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ለአንባቢያን እንዲረዳ ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል፡፡

ኢህአዴግ በሙስና ስም የ”ማጥራት ዘመቻ” ማካሄዱን ተከትሎ የተከሰተው አለመተማመንና እርስ በርስ በጥርጥር የመተያየት ችግር ካድሬውን ማስጨነቁ ተጠቆመ። ኢህአዴግን ለመሰናበት የሚፈልጉ በርካታ ካድሬዎች “ለምን” በሚል የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በመፍራት የግድ ፓርቲውን መስለው እንደሚኖሩ ተገለጸ።stressed

የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ቀደም ሲል ኢህአዴግን ተሰናብተው የወጡና በተለያዩ የውጪ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው በማገልገል ላይ ካሉ ያገኘውን መረጃ በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የቀድሞ የትግል ጓደኞቻቸው “በደህና ጊዜ ተገላገልክ” በሚል በፓርቲው ውስጥ ችግር ስለመኖሩ እየነገሯቸው ነው። አብዛኞቹ ኢህአዴግን ተለይተው በሰላም ስለመኖር እንደሚያስቡ ነው የተሰማው።

የቤተሰቦቻቸው የወደፊት እድልና የነሱ በፍርሃትና በጭንቀት መኖር አሳዛኝ እንደሆነ የነገሩት የቀድሞ የኢህአዴግ ሰዎች “አሁን ያለው ኢህአዴግ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል” በማለት አንድ በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ እያገለገለ ያለ የቀድሞ ጓደኛቸው እንደነገራቸው ገልጸዋል።

ለስራ እንኳን ካገር መውጣት የማይችሉ ባለስልጣኖች እንዳሉ ዘጋቢያችን አመልክቷል። በተቀመጡበት ሃላፊነት ወደ ውጪ የሚያስኬድ አጋጣሚ ሲኖር የሚከለከሉ እንዳሉም ያገኛቸውን መረጃዎች ጠቅሶ ዘግቧል። ለሃላፊዎቹ ደህንነት ሲባል የሚሰሩበትን ተቋምና ስም መናገር እንደማይችሉ በመጥቀስ መረጃውን የሰጡት ክፍሎች “ባለስልጣኖቹ በመካከላቸው እርስ በርስ መተማማን ስለማይችሉ ችግራቸውን መወያየት እንኳን አይችሉም” ብለዋል፡፡

“በጣም የሚቀርቡኝ ጓደኞቼ ገንዘብ ወደ ውጪ እንድወስድላቸው እስከመጠየቅ ደርሰዋል” ሲሉ የገለጹት የቀድሞ የኢህአዴግ ባለስልጣን፣ ፓርቲው በሙስና ስም ያካሄደው የሽግግር ወቅት የማጥራት ርምጃ የፈጠረው ስሜት አሁን ድረስ እንዳለ ጠቁመዋል።

ሰሞኑንን ወደ አሜሪካ ያቀኑ የቀድሞ የኢህአዴግ ሰው በማግኘት ተመሳሳይ መረጃ ያሰባሰበው ዘጋቢያችን “ኢህአዴግ በከፍተኛ የመበስበስ አደጋ ውስጥ ይገኛል። በዚህም የተነሳ ካድሬው ተዥጎርጉሯል” ሲል ሪፖርት አድርጓል። ኢህአዴግ በውስጥ ያለበትን ችግር ለማድበስበስ የአባይ ግድብ ላይ ትኩረት በመስጠት “የንቅናቄ ሃይል” በማስፋፋት ላይ እንደሆነም ጠቁሟል።

ድፍን ህዝብ የአባይ ግድብን አስመልክቶ ያለው ስሜት በበጎ መልኩ የሚታይ በመሆኑ ኢህአዴግ ይህንኑ የህዝብ ስሜት ለቅስቀሳና ለበሽታው መደበቂያ ለማድረግ እየተጠቀመበት እንደሆነ ተጠቁሟል። የህጻናት ፕሮግራሞች ሳይቀሩ አባይ ላይ ያነጣጠሩ ቅስቀሳዎች እያስተላለፉ መሆናቸውን ያመለከቱት ሰው፣ “ስለ አባይ ግድብ የሚባለውና የሚሰራው ፕሮግራም ችግር የለውም። በአግባቡ ቢሰራበት ብሔራዊ ስሜት ሊገነባበትም በተቻለ ነበር። ይሁን እንጂ ዓለማው የችግር ማለባበሻ እንዲሆን መደረጉ ነው” ብለዋል።

“መለስ ኢትዮጵያን ቢወድ ኖሮ ከባድመ ጦርነት በኋላ የፈረሰውን ብሔራዊ አንድነትና መግባባት መልሶ መትከል ይቻል ነበር” በማለት የተናገሩት እኚሁ ሰው “በወቅቱ ይህንን ሃሳብ ያነሱ ሰዎች ነበሩ” ሲሉ ቁጭታቸውን ይሰነዝራሉ። በማያያዝም ኢህአዴግ የአባይን ግድብ ተንተርሶ ብሔራዊ አንድነት የሚገነባበት፣ መቀራረብና በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር ብሔራዊ መግባባት የሚደረስበት፣ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ መሰረት የሚጣልበት ቢያደርገው እውነተኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ለመተካት ህዋሀቶች የሚያደርጉት ሽርጉድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ሪፖርት መቅረቡ ተሰምቷል። ይኽው ሪፖርት የቀረበላቸው ክፍሎች ቀደም ሲል እንዳደረጉት የህወሃትን ከፍተኛ አመራሮች በማነጋገር ስህተት እንዳይሰሩ እየወተወቱ ነው።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Adaffufi Dangglassa says

    March 30, 2015 01:16 am at 1:16 am

    Ethiopians never had trusted the Hiwahat with their country, children, and the resources that are available above and below the lands in Ethiopia.

    Yes, right from the beginning, the foundation of this mafia regime has been showing a gradual crack from the bottom up and now the crack is deepening and the gap is widening and the paint that masked the wickedness of those who built the system is peeled off and clinging by a tread leading to the point where its structures from bottom up can neither be repaired nor renovated, only needs to be demolished to its ruin.

    Although it might be unlikely that the grand robbers from the top hierarchy in the Hiwhat would draw guns on one another, they might throw feasts on each other and would get bruised, but would not abandon the house that they built collectively and risk of creating a battlefield where one group becoming actors and the other one villains. What is clear now is that system is sick enough to dye; all it is needed is to quicken the fall of this criminal regime and leave it under the pile of its own ruin.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule