• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ብሶት የወለደው የኦሮሚያ አመጽ ተቆንጥሮ አስመራ ላይ ተላከከ!

February 29, 2016 06:39 am by Editor Leave a Comment

በኦሮሚያ የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኛነትና ዓመጽ ተከትሎ ስለጠፋው የሰው ህይወት እርግጠኛ አሃዝ የሚጠቅስ አልተገኘም። ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና የአገር ውስጥ ቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደሚሉት የህወሃት አንጋቾች ከ200 በላይ ንጹሃንን ገድለዋል። በነጻ አውጪ ስም አገሪቱን እየመራ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር – ህወሃት፣ አመጹን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ ቆይቶ በስተመጨረሻ ችግሩን ቆንጥሮ አስመራ ልኮታል። ወታደርና ከባድ መሣሪያም ወደ ድንበር አስጠግቷል። መፍትሔው ጭፍን ብሔረተኝነት ሳይሆን ሁሉንም በሰብዓዊ ፍጡርነት ማየት ነው የሚሉ አካላት “ጆሮ ያለው ይስማ፣ ልቡና ያለው ያስተውል” እያሉ ነው፤ ርምጃቸውንም ከጊዜ ጋር አዋዝተዋል። ህወሃት የትጥቅ ትግልን የራሱ “ንግድ ምልክት” አድርጎ መውሰዱ የማይዋጥላቸው “ለህወሃት ብቻ የትጥቅ ትግልን ህጋዊ ያደረገው ማን ነው?” በማለት ይጠይቃሉ፡፡

“ታዛዥ” በሚል ስያሜ የሚጠሩትና ብዙም ከበሬታ የሌላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ “የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን” ባሉ ማግስት የተምታታ መግለጫ በመስጠት ዝነኛ እየሆኑ የመጡት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ የምዕራብ አርሲውን ችግር አስመራ ላይ ለጥፈውታል። ሠራዊት አዝምቶ ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ያለው ህወሃት፣ በሃይለማርያም ደሳለኝ አንደበት “የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን” ማለቱን ተከትሎ “እየገደሉ ነው፣ እያሰሩ ነው፣ እየገረፉ ነው፣ እያቆሰሉ ነው፣ የማያዳግም ሲባል ነፍሰጡር ከመግደል የዘለለ ምን አይነት ርምጃ ሊሆን ነው?” ሲሉ አስተያየት የሰጡት የአርሲ ኮፈሌ ነዋሪ ናቸው።

ሌላ ገለለተኛ አስተያየት ሰጪ “እኔ በግሌ ስርዓቱን የማላምንበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ፣ ብዙ ሰዎች ራሳቸው ኢህአዴጎቹን ጨምሮ ከነባለሥልጣኖቻቸው ልባቸው ሸፍቷል። አገር የሚመራ ድርጅት ካልታመነ አደጋው የከፋ ይሆናል” ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ማሳያ በማቅረብ ሲቀጥሉም ሙሽሮች ቀስቃሽ ዘፈን አሰሙ በማለት ተኩስ በመክፈት ሠርገኞችን አቆሰሉ፤ ሙሽሮቹ ሸሽተው ጫካ ገብተው ከሁለት ቀን በኋላ ተገኙ፤ ህዝብ ተቆጣና ጠመንጃ አንግተው የሚገሉትን ገደለ፤ ይህን እውነት ለምናውቅ “ጉዳዩ ከሰላማዊ ተቃውሞ ያፈነገጠ ሽብር ነው ተብሎ ሲነገረን ምን እንበል? ከዚህ በላይ እምነትን የሚሸረሽር ምን አለ?” በማለት ይጠይቃሉ፡፡

ኢህአዴግ ከበረሃ ወደ ቤተመንግስት ሲዛወር የእድሜ ልክ ጠላቱ አድርጎ የሚያሰቃየውን አማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ማስፈጀት የጀመረው አርሲ እንደሆነ የሚያስታውሱ ከፍሎች አሁን ህወሃት “ምዕራብ አርሲ ላይ የታየው የተለየ ሽብርና ስልጣንን ኢ-ህግመንግስታዊ በሆነ መልኩ ለመጨበጥ ያለመ ነው፣ በጉዳዩ ላይ የአስመራው መንግስት እጅ እንዳለበት ማስረጃ አለ” በሚል ለውጭ ሚዲያዎች መግልጹን በርካቶች አይቀበሉትም።

የቬንዝዊውላ አምባሳደር የሆኑት ራፋኤል ዳርዮ ራሚሪዝ ካሬኖ የማዕቀቡን ኮሜቴ ስራዎች አስመልክተው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ሲያስረዱ፣ “ቡድኑ የኤርትራ መንግስት አልሸባብን እንደሚደግፍ የሚያሳይ ማስረጃ አላገኘም” ባሉ ማግስት ህወሃት ይህንን መሰል መረጃ ይፋ ማድረጉ መረጃውን የተዛባ እንደሚያደርገው እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ።

ከዚሁ ጋር በተያያዝ ይሁን በሌላ ህወሃት በሰሜን ጎንደር ሱዳን ድንበር ኤርትራ ላይ ያነጣጠረ ሰራዊትና ከባድ መሳሪያ ከወትሮ በተለየ መልኩ ማሰለፉ ተሰምቷል። ኢሣትና አንዳንድ ድረገጾች ዜናውን ይፋ ከማድረጋቸው ውጪ ከህወሃት በኩል በይፋ የተባለ ነገር የለም።

ኢሳያስ አፈወርቅን በማስወገድ ራሱ ያደራጀውን መንግስት ኤርትራ ላይ ለመትከል ደፋ ቀና ማለት ከጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረው ህወሃት፣ ይሳካ አይሳካ ባይታወቅም በተመሳሳይ መልኩ ህወሃትን ለማሰወገድ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ሻዕቢያ ማገዙ እንደወንጀል ይቆጠርበታል። ተቃዋሚዎችን ማደራጀት የሽግግር መንግሥት መመሥረት ለህወሃት ህጋዊ ሲሆን፣ ለሻዕቢያ ወንጀል ተደርጎ ተወስዷል።

ህወሃት በተገንጣይ ስም የሚጠራበትን “ታላቅ የመሆን” ህልሙን እውን ለማድርግ ኤርትራ ላይ የራሱን ስሪት መንግስት ለማቋቋም ሌት ተቀን ሲሰራ፣ ሻዕቢያ ብዙም ሲከሰው አይሰማም። በኢትዮጵያ የውስጥ ችግር ሲባባስ ሻዕቢያን መወንጀል፣ ማስፈራራት፣ ማሳጣት፣ ተቃዋሚዎችን “ተላላኪ” በማለት ለማሳነስና ክብረቢስ አድርጎ ለመሳል መሞከር፣ ወዘተ የተለመደ የህወሃት ተግባር መሆኑ በተደጋጋሚ የሚሰማ ጉዳይ ነው።

ለዚህም ይመስላል የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ ባለፈው ዓርብ ለቪኦኤ ሲናገሩ ይህንን ጉዳይ ያሰመሩበት። የሳዳም ሁሴን የማስታወቂያ ሚኒስትር የአሜሪካ ወራሪ ጦር ባግዳድን ሲቆጣጠር እሳቸው የመድፍ ድምጽ በሚሰማበት ስልካቸው “ችግር የለም” ዓይነት መልስ ይሰጡ ነበር። በሰሞኑ መግለጫቸው ከእኚሁ ሚኒስትር ጋር የተመሳሰሉት አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ ለሰነዘሩት ክስ መልስ የሰጡት አቶ ቶሌራ “ስልጣን ላይ በመቆየታቸው የነበሩበትን ሁኔታ የዘነጉ ይመስላሉ። ለህወሃት የትጥቅ ትግልን ህጋዊ አድርጎ ኦነግን የሚከለክል ህግ የለም” ብለዋል።

ተመሳሳይ ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖች በምዕራባውያን ዕርዳታ፣ ድጎማና በኢትዮጵያ ላይ ባላቸው ጥላቻ እየተደገፈ “የትጥቅ ትግል አካሂጄ ድል አደረኩ” የሚለው ህወሃት የትጥቅ ትግልን የራሱ ብቸኛ “የንግድ ምልክት” አድርጎ መውሰዱ የማይሠራና አሁን ኢትዮጵያ ካለችበት ሁኔታ አኳያ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ይከራከራሉ፡፡ እነዚሁ ወገኖች እንዲያውም ይህ የህወሃት አስተሳሰብ ነጻነትን የመጎናጸፊያው ብቸኛ መንገድ የትጥቅ ትግል ነው ብለው እንዲያምኑ በርካታዎችን እያደረጋቸው እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

ከፋሽስት ጣሊያን ባልተናነሰ ሁኔታ ህጻናትን፣ ነፍሰጡርን፣ አዋቂዎችን፣ አረጋውያንን፣ የሚጨፈጭፍው ወያኔ ወንጀሉን ለመሸፋፈን የሚያደረገው መፍጨርጨር መሆኑንን በመግለጽ የቀረበባቸውን ክስ ያጣጣሉት የአርበኞች ግንቦት 7 የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ነዓምን ዘለቀ “ጌታቸው ረዳና መሰሎቹ ለፍርድ የሚቀርቡበት ቀን ሩቅ አይሆንም” ሲሉ ህወሃትን ራሱ “መንግሥታዊ አሸባሪ ነው” ሲሉ ጠርተውታል።

ኦፌዴንም ከፊል አባሎቹ አሸባሪ ተብለው መከሰሳቸውን አስመልከቶ ድርጅቱ ከሽብር ጉዳዮች ጋር ግንኙነት እንደሌለው፣ አምባገነንነትን እንደሚዋጋ፣ ሕዝብ ለሚያቀርበው ጥያቄ አግባብነት ያለው መልስ መሰጠት እንዳለበትና ብቸኛውም አማራጭ ሕዝብን ማክበር መሆኑንን በመግለጽ የጌታቸው ረዳን ስሞታ አጣጥለውታል።

በአገር ውስጥ የተከሰተውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ወደ አስመራ መውሰድ እና ከኤርትራ ጋር ማዛመድ በኦሮሚያ ላይ “የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን” የሚለውን የህወሃት አካሄድ “ሕጋዊ” ሽፋን ለመስጠት የታሰበ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በአገር ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ታዛቢ ለጎልጉል በሰጡት አስተያየት መሠረት “ኤርትራ አሸባሪ ከተባለች በኋላ የኦሮሚያ ተቃውሞን ከኤርትራ ጋር ማዛመድ በቀጣይ ለመውሰድ ለታሰበው እርምጃ “አሸባሪነትን ለመከላከል የተወሰደ” የሚል የአገር ውስጥና ዓለምአቀፋዊ ሕጋዊ ሽፋን ለመስጠት ያስችላል፤ አሜሪካ አፍጋኒስታንን አሸባሪ ካለች በኋላ ድንበር አልፋ፤ ባሕር አቋርጣ አፍጋኒስታንን ለመደብደብ ሕጋዊ ሽፋን እንዳገኘች ሁሉ ይኼኛውም የህወሃት አካሄድ ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት አለው” ብለዋል፡፡ (ፎቶ: ተስፋዜና)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule