• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የደቡበ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ

September 4, 2013 07:29 pm by Editor Leave a Comment

የደቡብ ክልልን ከሚመሩት አራቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡

ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ  የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡

የአቶ አለማየሁ አሰፋና የአቶ ታገሠ ጫፎ መነሳት የተጠበቀና ውስጥ ለውስጥ ሲነገር የቆየ መሆኑን፣ ያልተጠበቀው ግን የአቶ ሳኒ ረዲ ነበር በማለት አስተያየት የሰጡት የደኢሕዴን አባልና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን፣ ሦስቱም ሹማምንት የተገመገሙት በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ‹‹አቶ ታገሠ በአመራር ብቃት ማነስ በተደጋጋሚ ይተቹ እንደነበር ገልጸው፣ አቶ አለማየሁና አቶ ሳኒ ደግሞ አላስፈላጊ ‹‹ኔትወርክ›› በመፍጠር ብልሹ አሠራር በማስፈናቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡

በግምገማው የተሳተፉ ምንጮች ደግሞ በተለይ አቶ አለማየሁ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በተወከሉበት ዳውሮ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲነሳባቸው የኃይል ዕርምጃ እንዲወሰድ ማድረጋቸው እንደ አንድ ምክንያት መነሳቱን ያስረዳሉ፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑ አንዳንድ አስተያት ሰጪዎች ለሦስቱም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኃላፊነት መነሳት የአመራር ብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን የኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና ችግሮች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡

በሥነ ሕይወት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በዓሣ ዕርባታ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ታገሠ ጫፎ እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ከ2000 እስከ 2003 ዓ.ም. መስከረም ድረስ ብቸኛው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፣ እንዲሁም ወደ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊነት እስከተዛወሩበት ህዳር 2005 ዓ.ም. ድረስ አራተኛው ምክትል ርዕስ መስተዳድር ሆነው ቆይተዋል፡፡ ከአምስት ዓመት በላይ በኃላፊነት የቆዩበት ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አንዳንድ ሠራተኞች፣ ‹‹ከአራት መቶ በላይ ሠራተኞች ያሉበትን ቢሮ ሲመሩ አንድም ቀን ሠራተኞችን ሰብስበው አናግረው ችግር የፈቱበት ጊዜ አልነበረም፡፡  ግንኙታቸው ከሥራ ሒደት ባለቤቶች ጋር ስለነበር ዕርምጃም የሚወስዱት ከነዚያ ሰዎች በሚያገኙት መረጃ ብቻ ነበር፤›› በማለት በርካታ ሠራተኞች ሳያውቁዋቸው እሳቸውም የሚያስተዳድሩዋቸውን ሠራተኞች በቅጡ ሳያውቁ መነሳሳታቸውን ይናገራሉ፡፡

እስከ መስከረም 2003 ዓ.ም. ድረስ የደኢሕዴን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን የክልሉን የፖለቲካ እንቅሰቃሴን ሲመሩ የቆዩትና ከዚያ በኋላ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ የነበሩት አቶ አለማየሁ አሰፋ፣ ‹‹ሜትሮ ፖሊታን›› የተሰኘውንና የሐዋሳ ከተማ አስተዳዳር 70/30 (ሰባ በመቶ ብሔር ብሔረሰቦች ተዋፅኦ፣ ሰላሳ በመቶ በሲዳማ ተወላጆች እንዲዋቀር) ባለፈው ሚያዚያ 2004 ዓ.ም. አዘጋጅተው ለውይይት ያቀረቡት መመርያ በተለይ በሲዳማ ተወላጆች ዘንድ ከፍተኛ ትችት እንዳስከተለባቸው ይታወሳል፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ አፈትልኮ የወጣውን ያንን መመርያ የዞኑ ሕዝብ ዘንድ በመድረሱ በወቅቱ ከፍተኛ ውጥረት ተፈጥሮ ነበር፡፡ በቅርቡ የትምህርት ሚኒስትር የሆኑት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የማረጋጊያ መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ነው፡፡

አቶ አለማየሁ አሰፋና አቶ ሳኒ ረዲ ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባለፈው ሐምሌ 2005 ዓ.ም. ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሥራ አመራር ሁለተኛ ዲግሪ አግኝተው የተመረቁ ሲሆን፣ በአመራር ብቃት ማነስ ስለመገምገማቸው የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡

ሦስቱም ከኃላፊነት የተነሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳደሮች ለሰላሳ ስድስቱ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ከተዋጡት ዘጠኝ አባላት ውስጥ የሚገኙ ቢሆንም፣ ኢሕአዴግ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ባህር ዳር ከተማ ባደረገው ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎና አቶ ደበበ አበራ በመተካካት መርህ መነሳታቸው ይታወሳል፡፡ አቶ ታገሠ ከንግድ ኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊነት ለወራት ብቻ ወደ መሩት ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የተዛወሩት ከባህር ዳር ጉባዔ በኋላ መሆኑ አይዘነጋም፡፡

ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው የተነገረላቸው እነዚህ ሦስቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች የካቢኔ አባላትም እንደሚኖሩበት ምንጮች ለሪፖርተር የገለጹ ሲሆን፣ በምትካቸው የሚሾሙትን ተተኪዎች አዲሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ በመጪው መስከረም 2006 ዓ.ም. በሚደረገው ጉባዔ ላይ ይፋ በማድረግ በምክር ቤቱ እንደሚያፀድቁ  ይጠበቃል፡፡  (ምንጭ፤ ሪፖርተር)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule