“ለኦሮሞ ህዝብ በሙሉ የተላለፈ የሃዘን ቀን ጥሪ” የሚለውን ጥሪ ካተምን በሁዋላ ይህንን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተብሎ የተላለፈውን መረጃ ስላገኘን ከዚህ በታች ደብዳቤውን አቅርበናል። ስለተፈጠረው ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን፣ አስተያየት ለሰጣችሁን ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። (የደብዳቤው ፎቶ ምንጭ ኢሣት)
ለኦሮሞ ህዝብ በሙሉ የተላለፈ የሃዘን ቀን ጥሪ
(ከበቀለ ገርባና ቂሊንጦ እስርቤት ከሚገኙት ሌሎች የፖለቲካና የህሊና እስረኞች…ነሃሴ፤2008)
በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ፣ የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄ አንግበው በሰላም የወጡ በርካታ ዜጎች ከነዚ የህዝብ መብቶች ተቃርኖ በጉልበት እየገዛ ባለው የኢህአዴግ የጭቆና አገዛዝ ስርዓት (tyrannical regime) ተተኪ አልባ ህይወታቸውን አጥተዋል፤ እያጡም ነው። “የዲሞክራሲ ስርዓት ተገንብቷል፣ የዜጎች ህገ-መንግስታዊ መብት ተከብሯል” እያለ የአገዛዝ ስርዓቱ ካለምንም ሃፍረት ሲለፈልፍ በቆየባቸው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት፣ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን በሙሉ ሲያፍንና ሲገድል ኖሯል።
እንደ አለመታደል ሆኖ ባገራችን የገዳዮች ገድል እንጂ የሟቾች ጀግንነትና ሃቅን መዘከር አልተለመደም። ምንም እንኳን እንዲ ዓይነት ጥቂት ጀግኖች በህዝብ ዘንድ ሃሃቃቸውና ህዝባዊነታቸው ታውቆ የሚዘከሩ ያሉ ቢሆንም፣ ኣብዛኞቹ ግን በስርዓቱ “የአድኖ መብላት” (predatory) የውሸት ገድል ትርክት መርህ መሰረት እንደ ወንጀለኞችና ሃገር አፍራሾች ተደርገው ለስርዓቱ ባደሩ ሚዲያዎች የፕሮፕጋንዳ ሰለባ ሆነዋል።
ከ2006 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) ጀመሮ በኦሮሚያ ከማስተር ፕላኑ ጋር ተያይዞ፣ በአማራ ከወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ፣ በደቡብ ክልል እራስን በራስ ከማስተዳደር መብት ጥያቄ ጋር ተያይዞ እንዲሁም በጋምቤላ የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄ አንግበው የሃገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት በሚፈቅደው መሰረት በሰላማዊ መንገድ ለተቃውሞ የወጡ በርካታ ዜጎች በመንግስት የታጠቁ ሃይሎች ተገድለዋል። አሁንም እየተገደሉ ነው።
የእንስሳቶችን መብት ጥበቃ እንኳን ለማረጋገጥ አለም ሁሉ በሚረባረብበት በዚህ ወቅት፣ የዜጎቻችንን አንገት በመቁረጥና በሌሎች የጭካኔ መንገዶች በመግደል፣ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ማድረግ እጅግ አሳፋሪና አስነዋሪ ተግባር ነው። በታሪክም የማይረሳ ብቻም ሳይሆን ይቅር ሊባል የማይችል የአረመኔዎች ተግባር ነው።
አገዛዙ በዚሁ ዓይነት የጭካኔ መንገድ በተገደሉት ሰማዓቶቻችን ላይ በውሸት የቴሌቪዥን ዶክሜንታሪና በካድሬዎቹ በኩል በሚጠናቀሩ ዜናዎች ከማውገዝና እነዚ ንጹህ ሰማዕታት የከፈሉት መስዋዕትነትን በፕሮፓጋንዳ ጥላሸት ከመቀባት አልፈው፣ ለነዚሁ በግፍ ለተገደሉ ዜጎች ሃዘናቸውን ለመግለጽ እዚህ እስር ቤት ውስጥ ጥቁር ልብስ በለበስነው የግፍ ታሳሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባና የማሰቃየት (torture) እያደረሱ ነው። በእስር ቤቱ ሃላፊዎች ትዕዛዝ ልብሶቻችን ሁሉ ተቀምተው ተወስደዋል። በተጨማሪም ለነዚሁ በግፍ ለተገደሉ ዜጎች ሃዘናቸውን ለመግለጽ ጸጉራቸውን በተላጩት እስረኞች ላይ ከፍተኛ ድብደባና አሰቃቂ የማሰቃየት ተግባር (severe torture) ደርሶባቸዋል። በቀጠሮአቸው ቀንም ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ተደርገዋል።
እኛ አሁን በዚህ ዓይነት ሁናቴ ውስጥም እንኳን ሆነን እነዚህ የዲሞክራሲና የፍትህ እንዲሁም የእኩልነት ጥያቄን በሰላማዊ መንገድ አንግበው ለተሰውት ዜጎቻችን ያለንን ልባዊ ክብርና ህያውነታቸውን ለመግለጽ፣ እነሱ የተሰውለትን ዓላማ ለማሳካት ያለንን ቁርጠኝነት ለማሳየት እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው አጋርነታችንን ለመግለጽ ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ ብሄራዊ የሃዘን መርሃግብር (ከነሐሴ 18-21፣ 2008) ሁላችንም ባንድነት እንድናደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ስለሆነም በነዚህ ሶስት የብሄራዊ ሃዘን ቀናት፣ ሁሉም ዲሞክራሲና ፍትህ እንዲሰፍን የምትመኙና ለዚህ ዓይነቱ ትግልም አጋርነትን ማሳየት የምትሹ ዜጎች፥
1) ጥቁር ልብስ በመልበስ፣ በትግሉ የተሰውትን ሰማዕታት ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመለጠፍና በሰፊው እንዲሰራጩ በማድረግ፣ በታክሲዎች፣ በበጃጆችና በሌሎች የህዝብና የግል ትራንስፖርት መኪናዎች ላይ ጥቁር ጨርቅ በማንጠልጠል፤
2) በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር ያላቹ ዜጎች የሰማዕታቱን ስሞች በማጠናቀር የጋራ ጸሎት ወይም ህዝባዊ ውይይት ፕሮግራም ማድረግ፤ በተለይም ደግሞ ሃገር ውስጥ ያላቹ ወደ ሰማዕታቱ ቤተሰቦች ዘንድ በመሄድና በማጽናናት አብሮነታቹንና አጋርነታቹን ማሳየት፤
3) የሰማዕታቱን ሙሉ መረጃ፣ ከተቻለም ፎቶግራፎቻቸውን ጨምሮ ገደይና አስገዳዮቻቸውን ለፍርድ ለማቅረብ መረጃ እያጠናቀሩና ባለማቀፍ ደረጃ እየሰሩ ላሉት አካላት መረጃዎችን በተቀናጀ መልኩ በመላክ (ለዝርዝሩ ይሄንን ገጽ ይጎብኙ . . . ኮንታክት ያድርጉን https://daandii.com/)፤
4) እያደርግን ያለውን የዴሞክራሲና የፍትህ እንዲሁም የእኩልነት ትግል ለማስቀጠል ባለን ቁርጠኝነት ላይ ቃል በመግባትና ያንኑ የሚያሳዩ መልዕክቶችን፣ የአርት ወይም የሙዚቃ ስራዎችን በማሳየት … በማህበራዊ ሚዲያዎች በማሰራጨት፤
5) እንዲሁም ይሄን ማድረግ የምንችል ደግሞ ጸጉራችንን በቡድን በመላጨት ለንጹሃን የተሰው ሰማዕቶቻችንን እንድናስባቸው በነዚሁ ለነጻነት፣ ለእኩልነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ በተሰዉት ሰማዕታት ስም ጥሪ ልናደርግላችሁ እንወዳለን።
ህዝባዊና ሰላማዊ ታጋዮቻችን የተሰውለት ቅዱስ ዓላማ በህዝብ የተባበረ ትግል ግቡን ይመታል!!
እናመሰግናለን
(ምንጭ:#oromoprotests)
Yinegal Belachew says
ebakachihu yihen hizbin begosana bezer mekefafel tewut. ye’ethiopia hizb min bedelachihu endewoyane yemtkefaflut? hizbu aand nen eyale poletikegnoch beyegosa qirchat wust eyeketetu ye’oromo hazen yamara hazen yilutal. yihe akahed yibkan, ej ej blonal. bzuw hizbum teltotal. begzer yihunbachihu astesasebachin ke’afnchachin tinish kef yibelna wodeginbarachin enkuan yidres. woy meregem. woyane tkur wusha yiwuled!
አሰፋ says
መልዕክቱ ቆነጆ ነው። መልዕክቱ የሚገለጥባቸው መንገዶችና ዘዴዎችም ግሩመ ናቸው።
የበደል ሰለባዎቹም ዝርዝር ከሞላ ጎደል ሁሉንም ያካተተ ነው። ጎሽ!
“ለኦሮሞ ሕዝብ በሙሉ የተላለፈ የሃዘን ቀን ጥሪ” የሚለው
ለመልዕክቱ በርዕስነት እንዴት ተመረጠ? ጥያቄዬ ነው።
በተረፈ በአረመኔው የወያኔ እስር ቤትም ሆናችሁ መከራና ስቃይ እየተቀበላችሁም እንኳን
ለወገኖቻችሁ የምታሳዩት ጭንቀትና ጥበት፤ ለነጻነት ታጋዮች ጥንካሬ አጎናጻፊ ነው።
ለመለወጥ የማትችሉትን ለመቀበል መረጋጋቱን አይንፈጋችሁ።
Editor says
አሰፋ
ስለ አስተያየቱ እናመሰግናለን – ከይቅርታ ጋር አስተካክለናል!
አርታኢ
Editor says
Yinegal Belachew
ስለ አስተያየቱ እናመሰግናለን – ከይቅርታ ጋር አስተካክለናል!
አርታኢ
Aman says
ኢሳት ከሚነዛው የዘር ፖለቲካና እናንተ ከምታራግቡት ፕሮፐጋንዳ፡ ወያነን እናባርራለን ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ፡ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁነታ ወደ ህውላ ቀርታቹሃል።
የትግራይን ህዝብ በመስደብና በማግለል፡ ወያነ ከፈጸሙት የዘር ፖለቲካ የባሰ ስህተት እየፈጸማችሁ ነው። የትም ኣያደርስም። ጭንቅላታችሁ ማሳደስ ኣለባችሁ።