• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ” ደምቢ ዶሎ የተገደለ ወጣት እናት

September 7, 2016 08:18 pm by Editor 1 Comment

በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ ትናንት ማክሰኞ ማምሻው ላይ ከመንግሥት ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። የአንደኛው ወጣት ወላጅ እናት እኔንም የልጄ አስከሬን ላይ ጥለው ደበደቡኝ ብለዋል።

በመንግሥት ታጣቂ ጥይት ህይወታቸው ያለፈው ሁለቱ ሃይሉ ኤፍሬም እና ኢብሳ ሩንዴ የሚባሉ ሲሆኑ የ16 ዓመቱ ወጣት ሃይሉ ኤፍሬም ከተማዋ ውስጥ ተኩስ በመከፈቱ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ከተኩሱ ለማምለጥ ሲሮጥ መትተው ገደሉት ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

“ደሞቢ ዶሎ መሃል ከተማ ነበር ተኩስ የተጀመረው። ወደ ቀበሌ ዜሮ አምስት አካባቢም ተኩስ ነበር ። ልጆቹን እያባረሩዋቸው ሲመጡ ወጣት ሃይሉ ኤፍሬም በቅጽል ስሙ ቦጌ ነው የሚባለው ቀበሌ ዜሮ ሰባት በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ ነው የተገደለው” ብለዋል የአሜሪካ ድምፅ ያነጋጋራቸው የከተማዋ ነዋሪ።

ሌላው ወጣት ኢብሳ ሩንዴ ደግሞ ግቢው ውስጥ ቆሞ እንዳለ ተኩሰው ገድለውታል ሲሉ የደምቢ ዶሎ ነዋሪ አስታወቀዋል። አስከሬኑን ወደ ሆስፒታል በመውሰድ ላይ እንዳሉ የመንግሥት ታጣቂዎቹ አስቁመው ወደቤት መልሷቸው ሲሉ ነዋሪው አክለው አመልክተዋል።

ከሟቾቹ መካከል የአስራ ስድስት ዓመቱን ወጣት የሃይሉ ኤፍሬም እናንት ወይዘሮ ታደሉ ተማምን በስልክ አግኝተን የልጃቸውን መገደል ሰምተው እንደሆነ ጠየቅናቸው።

“ቤት ውስጥ ነበርኩ። እሱ ደግሞ ከልጆች ጋር ሊጫወት ወጣ ብሎ ነበር። ከተማ ውስጥ ብጥብጥ ተነሳ ሲባል መሯሯጥ ጀመሩ። ከፊት ይሮጥ የነበረውን ልጄን መትተው ጣሉብኝ። ጓደኞቹ መጥተው ሲነግሩኝ ሮጬ ሄድኩ።ስደርስ ልጄ ሜዳ ላይ ተዘርግቷል። አንድ ያለኝ ተስፋ እሱ ነበር። እንደ አባትም ሆኖ በባሌም ምትክ የቀን ሥራ እየሰራ የሚረዳኝን ልጄን ነው ያጣሁት” ብለዋል።

ታጣቂዎቹ ጥለውኝ ሲሂዱ ብጮህ ሰዉ ሁሉ ፈርቶ ሸሽቷል። እኔና ሴቷ ልጄ ሜዳ ላይ ብቻችንን አለቀስን ያሉት የሟቹ ወጣት እናት አንገቱ ላይ መትተው ነው የገደሉብኝ ብለዋል። በኃላም ጎረቤቶች ተሰብሰበው ረድተውኝ ልጄን ሸኙልኝ። የአስከሬን ሳጥን መግዣ እንኳን አልነበረኝም ብለዋል።

ከቂለም ወለጋ የፖሊስ አዛዥ ምላሽ ለማግኘት ደውለን ነበር። ይሁን እንጂ አዛዡ ኮማንደር ቦደና ስልኩን ካነሱ በኃላ ዘግተውታል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል እዚህ ላይ ያድምጡ። (ምንጭ: የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)

ፎቶ: ከግራ ወደ ቀኝ ኢብሣ ሩንዴ እና ኃይሉ ኤፍሬም (ቦጌ) ከጃዋር ፌስቡክ የተገኘ

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Lusif says

    September 9, 2016 09:12 pm at 9:12 pm

    I can’t say it did not happen. I am still troubled by the nature of human beings particularly the so called law enforcers or military personals. They are supposed to protect citizens against criminals and oppressive government.
    It is natural, no matter what,a mother cry for her dead son. Why on earth, however I am cynical, force a mother to sit on her son’s dead body and bit hear down. Those military personnel must be sadistes evil in human appearance. I still doubt it, that a human person do such evil deeds.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule