• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዎላይታ አመራሮች “ከህወሃትና ኦነግ ሸኔ አካላት ጋር በድብቅ ስብሰባ ያረጉ ነበር”

August 11, 2020 05:56 am by Editor 2 Comments

የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኮምቤን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ከትላንት በስቲያ በመከላከያ ሠራዊት መያዛቸው ተሰምቷል።

እሁድ አመሻሹን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊዎች ለደቡብ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ የዎላይታ ዞን አመራሮች በዞኑ ኮማንድ ፖስት ዛሬ ከሰዓት መያዛቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አለማየሁ ባውዲ እንዳሉት የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ህገወጥ አደረጃጀቶችን ፈጥረው ግጭት የመቀስቀስ ፍላጎታቸውን እንዲያስፈጽሙ እያደረጉ ነበር ብለዋል። 

አመራሮቹ በፓርቲ ደረጃ እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ሀገር ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመስራት ላይ ይገኛሉም ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ አለማየሁ ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩ በማለት ከገለጿቸው ህወኃትና ኦነግ ሸኔ አካላት ጋር በድብቅ ሰው እየላኩ ስብሰባ እንደሚያደርጉ እና ተልዕኮ እንደሚቀበሉ ተናግረዋል። ለዚህም ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት መረጃዎች ተገኝተዋል ብለዋል።

የኮማንድ ፖስቱ ትዕዛዝ በመተላለፍ ህገወጥ ስብሰባዎች እንዲሁም ሰልፎችን እንዳደረጉ ተገልጿል። ህብረተሰቡ የሰጡትን አመራር ቢቀበላቸው አካባቢው ግጭቶች ይፈጠሩ እንደነበር አቶ አለማየሁ ተናግረዋል።

አቶ አለማየሁ ከሕገ መንግሥት ውጭ በመንቀሳቀስ ክልሉን የግጭት ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ገልፀው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም በእኩይ ድርጊታቸው መቀጠሉን ምረጣቸውን አብራርተዋል። 

የዞኑ ህዝብ የአመራሩን የጥፋት ተልዕኮ ሳይቀበል መቆየቱን በመጥቀስ ሃላፊው ለህዝቡ ምስጋና አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት ዞኑ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ህዝቡ የሰላም እሴቱን እንዲያስቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

በዛሬው ዕለት (ዕሁድ) በወላይታ ሶዶ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮችን ጨምሮ 26 ግለሰቦች መሆናቸውን አል አይን ዘግቧል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ትናንት የዎላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ በሶዶ ከተማ የተከሰተው አለመረጋጋት ዛሬም ጠዋት አንዳንድ ቦታዎች ቀጥሎ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓት ከተማዋ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በወላይታ ዞን በአሁን ሰዓት ብጥብጥ አስነስታችኋል የተባሉ ሰዎች በመከላክያ ኃይል በቁጥጥር ሥር እየዋሉ እንደሆነና እስካሁን በተነሳው ግርግር ስንት ሰው እንደተጎዳ የታወቀ ነገር የለም ትላንት ምሽት ግን አንድ ሰው ሲሞት 14 መቁሰላቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ወላይታ ሶዶ ከተማ ሙሉ በሙሉ አለመረጋጋቷን ማረጋገጥ ችለናል። አሁንም አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሳውቀዋል።

በዛሬው ዕለት (ሰኞ) ሁለት (2) ሰዎች መሞታቸውን ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። ሌሎች ግን የሟቾች ቁጥር ከ20 በላይ ነው ይላሉ።

በተጨማሪም ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ የንግድ እንዲሁም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አለመኖሩን የቲክቫህ ኢትዮ አባላት አሳውቀዋል።

ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ተለያዩ ወረዳዎች የሚደረግ ጉዞ ተቋርጧል/የለም። አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊትና የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል በከተማ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

(ከተለያዩ መደበኛና የማኅበራዊ ድረገጾች የተጠናቀረ ዘገባ ነው)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News

Reader Interactions

Comments

  1. Tazabiw-sew says

    August 20, 2020 06:55 pm at 6:55 pm

    ” በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አለማየሁ ባውዲ . . . ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩ በማለት ከገለጿቸው ህወኃትና ኦነግ ሸኔ አካላት ጋር በድብቅ ሰው እየላኩ ስብሰባ እንደሚያደርጉ እና ተልዕኮ እንደሚቀበሉ ተናግረዋል። ለዚህም ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት መረጃዎች ተገኝተዋል ብለዋል”

    የጎልኡል አርታኢ ከላይ እንደተጠቀሰው ይንን ያሉት ዓለማየሁ ባውዲ ናቸው፤ ነገር ግን ይጎልጉል “ዜና” አርዕስት መሆኑ ለምን ይሆን? በጥቅስ ምልክት ቢቀመጥም! እንግዲህ የማትወጡት አዳላጭ ዳገት ላይ ስለሆናችሁ ሸርተት በሉና ተደመሩ፤ በልጥጉ፤ ድሮም ካለኛ የለም የዜና ዘላን ነበራችሁ፤ አሁን ጥሩ የመደመር ግጦሽ መሬት ተግኝቷል

    ታዛቢ

    Reply
    • Editor says

      August 31, 2020 03:57 pm at 3:57 pm

      That is what we did.

      Editor

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
Copyright © 2026 · Goolgule