• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ፀሎታችን በቤታችን”

June 19, 2014 03:17 am by Editor 3 Comments

በተለያዩ ግዜያት ህጋዊ እና ህገወጥ በሆነ መንገድ ተሰደው ወደ ሳውዲ አረቢያ ከሚገቡ ኢትዮጵያውያን መሃከል ጥቂት የማይባሉ  የኦርቶዶክ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የህዝብ ሙስሊሙን ሃይማኖታዊ ደንብ እና ስረአት  አክበረው እንደሚኖሩ ይታወቃል። እነዚህ በሃገሪቱ ግዛቶች ሪያድ፣ ጅዳ፣ ደማም እና ጅዛን በሚባል ክፍለ ግዛቶች ውስጥ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚኖሩ የሚነገረው የእምነቱ ተከታዮች በደስታም ሆነ በሃዘን ግዜ ሃይማኖታቸው የሚያዘውን የፀሎት ስረአት ሃይማኖታዊ ወግ እና ስረአት ጠብቀው ለፈጣሪያቸው ጸሎት ማድረስ እንደማይቸሉ የሚገልጹ ምንጮች ሳውዲ አረቢያ በእስላማዊ ህግ የምትመራ እንደመሆኗ መጠን ሌሎች ሃይማኖቶችን ማራመድ በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ በመንግስት ዘንድ በይፋ ከሚታውቀው ሃይማኖት ውጭ ምንም አይነት አማራጭ የጸሎት ስፍራዎች ባለመኖራቸው  በኢትዮጵያውያኑ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ መንፈሳዊ ተጸዕኖ እንዳሳደረባቸው ይነገራል።

እንደ ኢትዮጵያውያኑ በሳውዲ አረቢያ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች እንዳሉ የሚጠቅሱ ምንጮች እንደ ፊሊፒንስ፣ ኔፓል፣ ህንድ፣ ወዘተ የክርስትና እምነት ተከታይ እና ሌሎች መንፈሳዊ እምናተ ተከታይ  የውጭ ሃገር ዜጎች በኤምባሲያዎቻቸው በኩል በሚደረግላቸው ሁለንተናዊ ትብብር እና ድጋፍ ህይወቱ ያለፈች ዜጋን አስክሬን ተባብረው ለሃሀገሩ አፈር ሲያበቁ ከፈጣሪው ተማጽኖ የራቀውንፈሪሃ እግዚአብሄር  በየሃገሮቻቸው ኮሚኒቲ ተቋማት ሰር ተሰባስቦ በሳምንት አንዴ «ከፈጣሪው ጋር ተገናኝቶ» ፀሎት የሚያደርስበት ስፍራ እንደተዘጋጀለት የሚገልጹ እንዚህ ወገኖች  በሪያድ እና በጅዳ የሚገኙ የመንግስት ተወካዮቻችን  ለዜጎቻቸው ደህነት የሚጨነቁ ከሆነ  በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በጂዛን የኮሚኒቲ ግቢ እና በሪያድ የኢትዮጵያ የኮሚኒት ካፍቴሪያ አዳራሾች ለዚህ የተቀደሰ ተግባር የሚውል ቤቶቻቸው የማይለየው ግቢ ውስጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የፀሎት ቦታ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ  ይናገራሉ።

በየአመቱ በኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ምዕመናን ዘንድ የሚከበሩ በአላትን ከሳውዲ አረቢያ ህግ አንጻር አንድ ቦታ ተሰባስቦ ማክበር እንኳን እንደማይችሉ የሚናገሩ እነዚህ ወገኖች ኤምባሲውን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ዲፕሎማቶች አብዛኛዎቹ የእልምና ሃይማኖት ተከታዮች በመሆናቸው ዲፕሎማቱ ለኢትዮጵያውያኑ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ትኩረት እንደማይሰጡዋቸው ይገልጻሉ። ይህ በዚህ እንዳለ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መካነ መቃበር ባለመኖሩ በተለያየ ምክንያት ህይወታቸ የሚያጡ የዕምነቱ ተከታዮች እስከሬኖቻቸውን ወደ ሃገር ለመላክ አቅም ስለማይፈቀድ በዲፕሎማቱ ፊርማ እና ሃላፊነት ሆስፒታል «ተላጃ» ገብቷል እየተባለ ሃይማኖታዊ ስረአትን ባልጠበቀ ምንገድ በአቦጀዴ እይተጠቀለለ ወደ አልታውቀ ስፍራ እንደሚወሰድ ምንጮች አክለው ይገልጻሉ።

ቀደም ሲል አንዲት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ በሚገኝ ግዜያዊ መጠለያ ውስጥ ታማ ያለህክምና እርዳታ ስትሰቃይ ከርማ  ህይወቷ በማለፉ በዲፕሎማቱ ት ዕዛዝ በሳውዲ ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች አስከሬኗ የት እንደደርሰ እንደማይታወቅ የሚናገሩ የልጅቷ የቀርብ ቤተሰቦች  እናት  የልጃቸውን ሞት ሳይረዱ ሳውዲ አረቢያ ለስራ የሄደቸው ልጄ ከዕለታት አንድቀን ጥሪት ቋጥራ ትመጣልኛለች በሚል ተስፋ የልጃቸው ሬሳ በወግ በመአረግ ለአፈር መብቃቱን ሳይረዱ መቅረታቸውን በሃዘን የሚገልጹ ምንጮች በተመሳሳይ መልኩ ህይወታቸው አልፎ መርዶ ነጋሪ ያጡ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ብዛት ቤት ይቁጠረው ብለዋል።

“ፀሎታችን በቤታችን” በሚል መሪ ቃል ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጎናችን ሊቆም ይገባል የሚሉ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እስካሁን ሳውዲ አረቢያ ምድር ላይ ህይወታቸው አልፎ የቀብር ስረአታቸው በወጉ ሳይፈፀም የቀሩ ወገኖችን ሰም ዝርዝር ዲፕሎማቱ ለቤተሰቦቻቸው በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት በኩል ይፋ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸው ወድፊት እንደዚህ አይነቱ አሳዛኝ ታሪክ በዜጎቻችን ላይ እንዳይደገም ኤምባሲው ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር የጋራ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በአሰቸኳይ እንዲቋቋም ጠይቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ቀደም ሲል ጅዳ ከተማ አንድ የግል መኖሪያ ቤት ውስጥ ተሰባስበው በጋራ ፀሎት ሲያደርሱ በነበሩ የኦርቶዶክ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ላይ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ከ39 በላይ ኢትዮጵያውያን ለእስር መዳረጋቸው አይዘነጋም። ይህንን እርምጃ የሚያስታወሱ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች በአመታዊ በአላትም ሆነ በሳምንት አንዴም ዕመናኑ ተስባስበው በጋር መንፈሳዊ ፀሎታቸውን ያለምንም ስጋት የምናደርሱበትንም ሆነ የእምነቱን ተከታዮች  ሃይማኖታዊ ግንዛቤ እንዲዳበር የሚያስተምሩበት  መንፈሳዊ ማዕከል በኤምባሲው ስር ከሚገኙ ተቋማት ውስጥ ጅዳ፤ ሪያድ፤ እና ጂዛን ከተሞች እንዲፈቀድላቸው ተማጽነዋል።

ለህዝበ ክርስቲያኑ ምዕመናን ጥያቄ መስካት በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከጎናቸው እንደሚቆሙ ከኢትዮጵያን ሃገሬ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ  በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ የሁኑትን አቶ ሸሪፍ ኬሬ +96626653444 እና ተቀማጭነታቸው ሪያድ የሆኑትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን በዚህ ዙሪያ ለመነጋገር ያደርኩት ሙከራ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን አልተሳካም ።

Ethiopian Hagere ጀዳ በዋዲ ለጎልጉል የላኩት

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Hibret says

    June 22, 2014 10:02 pm at 10:02 pm

    The solution is simple: If Saudi Arabia does not allow churches to operate, its religion, should not be allowed to function elsewhere.

    Reply
    • aradaw says

      June 25, 2014 01:10 am at 1:10 am

      This is absurd. Saudis are Muslims and in your case you mean you do not allow mosques to function elsewhere. You want to punish the world Muslims because of the Saudis. This is logic and this is justice.

      Reply
  2. አንዬ says

    July 21, 2014 08:33 pm at 8:33 pm

    በመጀመሪያ አስተያየቴን ከመስጠቴ በፊት አቋሜን ግልፅ ለማድረግ ያህል የማንኛውም ወገን የመብት ጥያቄ አልቃወምም። ነገር ግን በዚህ ርዕስ ላይ ጉዳዩ ሀይማኖታዊ ከመሆኑ አንፃር አንዳንድ ብዥታ ይፈጥራሉ ወይም በከፊል ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎች ናቸው የምላቸውን ለመጠቆም እወዳለሁ።በመጀመሪያ በህጋዊም ሆነ በህገወጥ መንገድ ሳኡዲ አረቢያ ገብተው የሞቱ ወገኖቻችን ቤተሰብ ነኝ የሚል እስካለ ድረስ ለማስቀበር አስቸጋሪ አይመስለኝም። በየሆስፒታሉ ማቀዝቀዣ ውስጥ ተረስተው ያሉ አስከሬኖች በወጉና በወቅቱ ላለመቀበራቸው የኤምበሲው ድክመት ለመሆኑ እኔም እስማማለሁ፣ ነገር ግን ያልተቀበሩት ሙስሊም ስላልሆኑ አስመስሎ ማቅረብ ተገቢ አይመስለኝም። እዚህ ላይ ለክርስትና አማኞች የተዘጋጀ የቀብር ስፍራ መኖሩን አትዮጵያ ሀገሬ ያውቃል ብዬ እገምታለሁ። ብዙ አትዮጵያውያን ወደዚህ የመጣነው በኡምራና በሀጅ ስማችንና ሀይማኖታችንን ቀይረን ስለሆነ የሞት አጋጣሚ ሲፈጠር ክርስቲያን ለመሆኑ ምንም አይነት የወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ስለማንችል የቀብሩን ቦታ አንጠቀምበትም።
    ሌላው ሙስሊም ዲፕሎማቶች ስለበዙ ለጉዳዩ ትኩረት አይሰጡም የሚለው አካሄድ ብዙም ሚዛን አይደፋም። ምክንያቱም ሙስሊም ዲፕሎማቶች ወደዚህ አካባቢ መመደብ ከጀመሩ ሁለትና ሶስት አመታት ቢሆን ነው። ያለፉትን ሁለት አስርት አመታትና ከዚያም በላይ ኤምባሲውን ሲመሩ የነበሩት ሀላፊዎች የክርስትና እምነት ተከታዮች ነበሩ። አንድም ሰው በነሱ ጊዜ ይህን መሰል ሀሳብ ያነሳ አይመስለኝም። ስለዚህ ሙስሊሞቹን ለጉዳዩ ያለመሳካት ምክንያት አድርጎ ማቅረብ ተገቢ አይመስለኝም ። ለመሆኑ እነኝህ ሙስሊም ሀላፊዎች ለሙስሊሙ ህ/ሰብ ምን የተለየ ነገር አደረጉለት? በወቅታዊ የሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ሳቢያ በሚነሱ አለመግባባቶች ላይ እየወሰዱ ያለው እርምጃ (ኢትዮጵያ ሀገሬ) ከሁላችንም በላይ መረጃው አለው ለኛም ተርፎናል።

    Reply

Leave a Reply to አንዬ Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule