• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የሃይማኖት አባቶች” የሰላም ጥሪ

January 29, 2018 10:57 am by Editor 4 Comments

  • “ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?” ዳንኤል ክብረት

በትናንት ምሽቱ የ“ሰላም ዋጋ” ዲስኩር አፈሙዝ ሳይሆን “ዘመናዊ መገናኛ ብዙሃን” ተወግዟል። የሃገሪቱ እድገት እና ትራንስፎርሜሽንም ተወድሷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ዻዻስ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴያስ ፓትሪያሪክ፣ ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአክሱም ወጨጌ፣  ዘመንበረ ተክለሐይማኖት….  ወዘተ  “… (ሃገሪቱ) ለሁሉም ልጆችዋ የምታበላው ከሌላት ከየት ታምጣ?” ብለውናል።

“ሕዝቡ ቢያገኝም አይረካም” የሚሉን አቡነ ማቴያስ እዚያች ቦታ ላይ እንዴት እንደተቀመጡ የታወቀ ነውና ከእርሳቸው ከዚህ የተለየ ነገር ፈጽሞ አንጠብቅም።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሃጂ ከድር ሁሴንም እንደ ገለልተኛ ሰው ተሰይመዋል። የአብያተክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ እና የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ መጋቢ ዘሪሁን ደጉም በቀጥታ ስርጭት ቀርበው ሰለ ትርጉም አልባዋ “ሰላም” ያልተነገሩት ነገር የለም።

ዳቦ እና መብት ለጠየቀ፣ ጥይት ሲርከፈከፍበት ግድያውን የማውገዝ ድፍረት እና ሞራል ሳይኖራቸው በብሄራዊ ቴሌቭዥን ቀርበው ስለ ሰላም መደስኮር ምንም ትርጉም የለውም።

የንጹሃን ዜጎች መገደልን ለማውገዝ የሃይማኖት ሰው ወይንም የተቋም መሪ መሆን አያሻም። ይህንን ለማድረግ ልብ እና አንጀት ያለው፣ አእምሮው ማሰብ የሚችል ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።

አጋዚ መግደል ሲሰለቸው፤ እነዚህን  “የሃይማኖት አባቶች” በቴሌቭዢን እያቀረበ የ”ሰላም” ጥሪ ሲያስተላልፍ ነበር። ከተወያዮቹ የምንረዳው አንድ ነገር አለ። ግድያ መፍትሄ ሳይሆን ይልቁንም ቤንዚን ሆኖ ችግሩን እንዳባባሰው የተረዱት አርፍደው ነው። ሕዝብ እንደ ቅጠል ሲረግፍ ጀርባ ሰጥተው የነበሩ “አባቶች”፤ ወያኔ  ጭንቅ ሲይዛት  ብቅ ብለው ስለ ሰላም ዋጋ ተናገሩ። ማንን ሊያሳምኑ እንደሚሞክሩ ግን አልተገነዘቡም።

ስለክቡር ህይወት ዋጋ አንዳች ያልተነፈሱ ሰዎች ስለ ሰላም ዋጋ ለመደስኮር መነሳታቸው ምን ያህል እንደሚፋጅ የሚገነዘቡት ግን የቆሰሉት ብቻ ናቸው።

ስለ ሞራል እሴቶች ለማስተማር”፤ በመጀመርያ ሞራል ያስፈልጋል። ስለ ሰላም ለመናገርም ድፍረት ይሻል። “ግድያው ይቁም” ለማለት ድፍረቱ ሳይኖር በገዳዮቹ አንደበት የሚወጣውን  የሰላም ዜማ ማስተጋባት ሲበዛ ግብዝነት ነው።

አራቱ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች በመሃሙድ አህመድ “ሰላም ባለም ዙርያ ሁሉ” መዝሙር ታጅበው ኢቢሲ ላይ የተሰየሙት በእርግጥ የ 100 ሚሊዮን ሕዝብን ብሶት ለማስተጋባት ሳይሆን፣ ወጌሻ  ሆኖ ወያኔን ለመጠጋገን ነው። “አፈሙዙ ይውረድ” ብለው ወያኔን ያወግዛሉ ብለን ስንጠብቅ “ለሰላም ዋጋ እንስጥ” ይሉናል። ለሞቱ ወገኖች የተሰማቸውን ሃዘን ይገልጻሉ ስንል ከጀርባቸው “የውጭ ሃይሎች አሉ” ይላሉ። ከምስላቸው ጀርባ የነጭ እርግብ ምስል አለ። “ሰላም” የሚል ጽሁፍም ጎልቶ ይታያል። ሰላም እነሱ ሲፈልጉ ብቻ የሚመጣ፣ ሳይፈልጉት ደግሞ የሚሄድ ግዑዝ ነገር ያደረጉት ነው የሚመስለው። “የሰላም ዋጋ ስንት ነው?” ይሉናል። የህይወትስ ዋጋስ ስንት ነው?

የሃይማኖት አባት ተብለው፣ አልባሳቱን ለብሰው፣ ቆብ አጥልቀው ከመቀመጣቸው ውጪ ንግግራቸው ከማጽናት ይልቅ የሚያበግን፣ ከማቅናት ይልቅ የሚያቃጥል፣ ቋንቋቸውም ኢሃዴግኛ ነው። ብዝህነት፣ እድገት ፣ ጸረ-ሰላም፣ የውጭ ሃይሎች፣ ወዘተ የሚሉ ወያኔ እንኳ ሰልችቶት የተዋቸውን ቃላት ይጠቀማሉ። እነ ደብረጽዮን፣ “ለችግሩ ጠተያቂዎች እኛ ነን” ማለት በጀመሩበት ሰዓት አባ ቆባቸውን አጥልቀው – መስቀላችውን እንደጨበጡ “ቀስቃሾቹ ሰላማችንን እና ልማታችንን የማይሹ የውጭ ሃይሎች እንደሆኑ” ሊነግሩን ሞከሩ። ፓስተር ጻድቁ ስለ አካባቢው ጂኦ ፖለቲካም ሁኔታና ስለ ውጭ ሃይሎች ተጽእኖም ይተነትኑ ነበር።

የፖለቲካ እውቀታቸው ይህን ያህል ከጠለቀ በነካ እጃቸው ስለ አንቀጽ 39 ጀባ ቢሉን ምን ይላቸዋል? የህዝብ ድምጽ ዘርፎ ፓርላማውን 100 እጅ የለያዘው ቡድንስ ጽድቅ ነው? የእምነት መጻህፍት በሙስና የበለጸጉ ሰዎችን አውግዙ አይልም? ዝሙትስ ነውር አይደል? በዚህ ተግባር ስለተሰማሩት መሪዎች ለመናገር ለምን አልደፈሩም?

እነዚህን ጥያቄዎች ለህሊናቸው ትተን ወደ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መልእክት እንሂድ።

“ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?” በሚል ርዕስ  በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተለቀቀውን ጽሁፍ አነበብኩ። መልዕክቱን በአንድ ትንፋሽ አንብቤ እንደጨረስኩ፤ የጀርመኑ ቄስ ማርቲን ኒሞለር ንግግር ታወሰኝ።

ናዚ ጀርመኖች 6 ሚሊየን የሚሆኑ አይሁዶችን የጨረሱት በአንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ ፤ በየተራ ነበር። መጨረሻ ላይ  የተያዘው ፓስተር ማርቲን ኒሞለር ሊታረድ ከገባበት የማጎርያ ካምፕ ሆኖ እንዲህ አለ።

“ናዚዎቹ በመጀመሪያ ወደ ኮሚንስቶች መጡ፥ እኔ ኮሚንስት ስላልነበርኩ ዝም አልኩ። ቀጥሎ ወደ ሠራተኛ ማኅበራት መጡ። እኔ የሠራተኛ ማኅበራት አባል ስላልነበርኩ ዝም አልኩ። ከዚያ ወደ አይሁዶች መጡ። እኔ አይሁድ ስላልሆንኩ ዝም አልኩ። በመጨረሻ ወደ እኔ መጡ። በዚህን ግዜ ስለ እኔ የሚናገርልኝ አንድም ሰው አልነበረም።”

ወገናችን በአጋዚ እንስሶች ጭንቅላቱ እና ደረቱ ላይ እየተተኮሰ መውደቅ ከጀመረ እነሆ 27 ዓማታት አለፉ። የወልድያው ግድያ ቃላት ባይገልጸውም ከጎንደሩ ግድያ፣ ከባህርዳሩ ጭፍጨፋ፣ ከአምቦው እና  ከእሬቻው እልቂት የተለየ አይደለም። ጨለንቆ ላይም ይፈስስ የነበረው የእንስ ሳይሆን የሰብአዊ ፍጡር ደም ነው።… እንዲህ እያለን የ27 ዓመቱን የግፍ ግድያ ብንዘረዝር መሽቶ ይነጋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ ቄሱም ዝም! መጽሃፉም ዝም እንዲሉ፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሲቃወሙ አልሰማንም።

ሲኖዶሱም ቢሆን  ከ”ጥልቅ ተሃድሶ” በኋላ  ሁለት ወይንም ሶስት ትግርኛ ተናጋሪዎች  ሲገደሉ ብቻ ጩኸት ሲያሰሙ ብቻ ነው የምናስታውሰው።

ከዲያቆን ዳንኤል ጽሁፍ ያስደመመችኝ ነገር “መንግስትም ወደ ልቡናው ይመለስ” የምትለዋ ቁልፍ ሃሳብ ናት።  አባባልዋ ዘይትን ከውሃ እንደመቀየጥ ሆነችብኝ። እምነቱ እንደሚለው  “ፈጣሪ ፍርዱን ይስጣችሁ” ብሎ ማለፍ አንድ ነገር ነው። በፖለቲካ መነጽር ካየነው ግን እየገዛ ያለው መንግስት ሳይሆን አንድ ትውልድን የበላ አውሬ ነው። በሕጻናት፣ በካህናትና  በጽላት ላይ ይተኩስ የነበረ አውሬ ላፈሰሰው ደም ተጠያቂ  ይሆናል እንጂ ምክር ያሻዋል?

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: eprdf, Right Column - Primary Sidebar, tplf, Woldiya Massacre

Reader Interactions

Comments

  1. Tadesse says

    January 30, 2018 01:54 am at 1:54 am

    Yehem yetaweke anti Tigray yemilut sew new,yekerta adregulign negative sibeza hoden yamegnal.

    Reply
  2. Tadesse says

    January 30, 2018 01:55 am at 1:55 am

    aferku bezih hager huletegnam hagere beye alterawm,thanks to the civilized world.

    Reply
  3. Tadesse says

    January 30, 2018 01:58 am at 1:58 am

    gena yemeslen neber alu,Revelation.

    Reply
  4. በለው ! says

    February 1, 2018 02:01 am at 2:01 am

    የሁለት ታዛዦች ወግ….
    *የአማሮች ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንድአርጋቸው በወሎ ከፍለ ሀገር ወልዲያ ከተማ “የተፈፀመው ጥፋት ነው” “ከሕዝብ ጋር ተወያይተናል፣ ችግሮችን በየደረጃው እንፈታለን” የጭፍጨፋው ምክንያት ባሻገር ሕዝብ በርካታ ችግር እንዳለበት፣ እሱም በየደረጃው መፈታት እንደሚገባው ገልፀዋል።”

    * የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አማረ ጎሹ “ያጠፋነው አጥፊዎችን ነው፣ አሁንም እናጠፋቸዋለን” “ጦር እየተጨመረልን ነው፣ አሁንም እንገድላቸዋለን” አይነት መግለጫ ይሰጣል። የችግሩ ምንጭ የፖለቲካ አላማ ያላቸው አካላት ናቸው። መፍትሄው “መደምሰስ” ነው።
    *******************
    “ወልዲያ ውስጥ የተፈጠረው የከተማዪቱን ማኅበራዊ ስብጥርና ግንኙነቶች የማያንፀባርቅ አሣዛኝ ሁኔታ መሆኑን በሰሞኑ ግርግር የንግድ ተቋማቸውና መኖሪያ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደሙባቸው በጓደኛቸው ልጅ ሞት ያዘኑት “ከእኔ ንብረት የሰው ሕይወት ይበለጣል” የኃይላይ ሕንፃ ባለቤት አቶ ኃይላይ ንጉሴ።
    __________________________________________
    ”ተገዳይ ወንድሜ ገብረመስቀል ጌታቸው እንዳይተርፍ ነው ፭ ጊዜ በጥይት የመቱት” ሲል በምሬት ይናገራል። ኪዳኔ ዕለቱን ሲያስታውስ ”ግርግር እንደተነሳ ደጋግሜ ስልክ ደወልኩለት አያነሳም። ብጠብቀውም መልሶ አይደውልም። በጣም ስለተጨነኩኝ ወደ ሆስፒታል ልፈልገው ሄድኩኝ፡ አንገቱ ላይ፣ ደረቱ ላይ፣ ሆዱ ላይ እና ብልቱ ላይ አምስት ጊዜ በጥይት የተመታ እና በደም የተሸፈነውን የወንድሜን አስከሬን ሆስፒታል ውስጥ አገኘሁ”ኪዳኔ ጌታቸው

    >› “ተመጣጣኝ እርምጃ!” የሚሉ ጨዋታ በህወሓት/ኢህአዴግ ተጀምሮ ነበር። ያውም ሱሪ ባስታጠቀው አባቱ ሻዕቢያ ላይ ግን የድሃ ልጅ መሐል ለጦር ማግደው እነሱ ኑሮአቸውን ዙሪያውን በመፎከርና በመፎካከር እንዲሁም በስውር ልዩ ጥቅማጥቅም ይደጋገፋሉ።” ብልጥ ልጅ እየበላ ያለቅሳል” ህወሓት ኤሌትሪክ ለሱዳን ሸጠች ሱዳን ለሻቢያ አቀበለች ያው ግሎብላይዜሽን ዓለም አንድ መንደር ሆነች ማለት ይህ አደለምን። ሁለቱም የአዞ እንባ ያነባሉ.. አንዱ በሌላው ላይ እጅ ይቀስራሉ፡ የአካባቢው ቀጠና አተራማሽነታቸውን ቀጥለዋል!
    * ህወሓት/ኢህአዴግ ተሰብስበው ለጦመሩም ይሁን፡ ለዘመሩ፡ ወይም ድማፃቸውን ላሰሙ ‘ተመጣጣኝ እርምጃው’ ግንባርና ደረቱን በአልሞ ተኳሽ ማስበርቀስ ነው።ድሮስ የተናቀ ሠፈር..!የመጀመሪያ ሞታችን ወደብ አልባ እንደከብት ስንከለል።
    *የአማራና ኦሮሞ ወጣት ወንድምና እህቱ ከጎኑ እንደቅጠል ሲረግፍ የሚሰጠው ተመጣጣኝ እርምጃ …የካድሬና የክልል(ባንዳ) ተላላኪ ጣራ በድንጋይ ደበደቡ ነው። ቢያንስ ድሃ ተቀጠሮ የሚሰራበትን አቃጥሎ ዓመድ ከመታቀፍ፡ በሕገወጥ የሚዘዋወር የሙሰኛና ልዩ ተጠቃሚ ንብረትን ወርሰው ለድሃ አከፋፈሉ የሚለው እጅጉን ይመረጣል!።
    __ ከዚህ በኋላ ወልድያ ላይ የቃና ዘገሊላ በዓል ቃና ዘገሊላ ብቻ ሆኖ የሚታሰብ ይመስለናልን? ገና ይዘፈንበታል፣ ይፎከርበታል፣ ይተረትበታል፣ ሙሾ ይወረድበታል፣ ውሎ ለቅሶ ይዋልበታል፡፡ገና ተዝካር፣ሙት ዓመት፣ ሰባት ዓመት፣ ሃያ አንድ ዓመት የሙታን በዓል አለ፡፡ በነዚህ ዘመናት ሁሉ ምን የሚባል ይመስላችኋል?
    * አሁን ያለው በተናጠል እየለየህ በለው የህወሓት የመቀሌው ስብሰባ ውሳኔ በእየክልሉ ቦታና ግዜ እያመቻቹ ለሚደረግ የመንገድ ላይ ግድያ፡ ወጣቱ ያለማቋረጥ በአንድነት ቆሞ ያሰበና ያሳሰበውን፡ የገደለና ያስገደለውን፡ እየለየ ተንበርክኮ ማፅዳት ይጠበቅበታል። “እያንዳንዱና ሁሉም አካባቢውን ቢያፀዳ ከተማችን ንጹሕ ትሆን ነበር። ”እንደሚለው ሁሉ ” እያንዳንዱና ሁሉም በቀበሌው የተሰገሰገን ሌባ፡ አስመሳይ፡ አድርባይ፡ አውርቶ አደር፡ ባንዳ፡በእየቀኑ ቢያፀዳ የነጻነት ጎዳናው ቀና፡ ተከብሮና ታፍሮ ለመኖር ግዜው ብሩሕ ይሆን ነበር። አራት ነጥብ። እንበለ፲፪ ግዜ!

    Reply

Leave a Reply to Tadesse Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule