• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አሸባሪው” የ72 ዓመት አዛውንት

December 8, 2014 09:30 am by Editor Leave a Comment

የ72 አመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢር የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ ናቸው፡፡ የሚኖሩት ከ10 አመት ልቻቸው ጋር ነው፡፡ ይህን ልጅ እሳቸው ብቻ ነው የሚያሳድጉት፡፡ ትናንት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከታፈሱ ከሰዓታት በኋላ ስራ ውለው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በደህንነቶች ታፈኑ፡፡ አቶ ቀኖ የጥበቃ ስራ ከመስራት ውጭ ሰልፉ አስተባባሪም ተሳታፊም አልነበሩም፡፡ ግን ታጥሮ ከሰነበተው የሰማያዊ ቢሮ የወጣ ሁሉ ሲለቀም ነበርና እሳቸውንም አፈኗቸው፡፡ ምን አልባትም ተደብድበው ይሆናል፡፡

ይህ ስርዓት እነ ይልቃልን፣ ብርሃኑን፣ አቤልን፣ በላይን፣ ጣይቱዎቹን . . . ሰማያዊን ብቻ አይደለም የሚፈራው፣ የሚያፍነው፣ የሚያፍሰው፣ የሚደበድበው፡፡ አቶ ቀኖንም የሆነ ነገር ያደርጋሉ ወይንም አድርገዋል በሚል (በራሱ ትርጉም) አፍኖ አስሯቸዋል፡፡ አሁን አቶ ቀኖ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ አይጠየቁም፡፡ ምን አልባትም ጨለማ ቤት ውስጥ ከታሰሩት መካከል ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡

ኢቲቪ ትናንት ታፍሰው የታሰሩትንም ሆነ የታፈኑትን “ከአሸባሪ ድርጅት ጋር በመስራት” ሲል የተለመደ ፍረጃውን አሽጎድጉዷል፡፡ እንግዲህ ለስርዓቱ የ72 አመቱ አቶ ቀኖም ከ”አሸባሪዎች” ጋር አሲረዋል ማለት ነው፡፡qeno abajobir

የአቶ ቀኖ መታፈን የስርዓቱን ቅጥ ያጣ ፍርሃት ደግሞም አረመኔነት የሚያሳይ ነው፡፡ ቀጣዩን ትውልድ ብቻ ሳይሆን አዛውንቶችንም ለማጥፋት እንደቆመ፣ ጥላውንም ማመን እንዳቃተው የሚያመለክት የእውር ድንበር እርምጃ ነው፡፡ ፍትህ፣ ሞራል፣ ምክንያታዊነት፣ ህግ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሰብአዊነት ጨርሶ ከስርዓቱ ጋር እንደሌለ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡

ትናንት ሴቶች፣ እናቶች፣ ወጣቶች፣ እንደ አቶ ቀኖ ያሉ አዛውንቶች ታፍነዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ይህን የሚመስል፣ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ፣ ደግሞም የሚያሳፍር፣ የሚያበግን ጭቆና ውስጥ ነች፡፡ እህቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እናቶቻችንና አባቶቻችን እያነቡ ነው፡፡ ይህን የህዝብ እንባ ልናብስ የምንችለው በቆራጥነት ደግሞም ተባብረን ስንታገል ነው፡፡

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም! (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule