• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ . . .

May 26, 2015 05:25 am by Editor 5 Comments

የ”ምርጫው” ድራማ እየተተወነ ሳለ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ለአቦይ ስብሃት ስልክ ደወሉ።

“ሃሎ?”

“ሃሎ፣ አቦይ ስብሃት ኖት?”

“ነኝ፣ ምን ፈለግክ?”

“ዶ/ር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ነን።”

“ችግር መስማት አልፈልግም። የታዘዛችሁትን አደረጋችሁ?”

“99.8% ህዝብ አልመረጠንም። ግን በታዘዝነው መሰረት ውጤቱን ገልብጠነዋል!”

“0.2% ብቻ ነው የመረጠን ማለት ነው?”

“አዎን ጌታዬ። ሌላ ምን እንታዘዝ?”

“99.8% ህዝብ የስም ዝርዝሩን አንብብልኝ።” አሉ አቦይ ስብሃት እየተባለ ይወራል።

አንድ ወዳጄ ስለ አቦይ ስብሃት የነገረኝ ታወሰኝ። ሰውዬው ከግመል እንኳን የማይሻል እንስሳ ብጤ ነው። ግመል ሳትጠጣ ለቀናት ትሰራለች አቦይ ስብሃት ደግሞ ሳይሰራ ቀኑን ሙሉ ይጠጣል። አብዛኞቹ የህወሃት አባላት እድሜያቸው እንደ አስተሳሰባቸው ስላረጀ ጨዋታቸው ከውሃ ጋር ነው። ከውድ ውሃ ጋር!  ድንጋይን ውሀ ያስጮኸዋል!

ሜዳው የኢህአዴግ፣ ዳኛው ኢህአዴግ፣ ታዛቢው ኢህአዴግ፣ ድምጽ ቆጣሪው ኢህአዴግ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀው “ምርጫ” እነሆ ተጠናቀቀ። በአፈና የታጀበው ምርጫ ጸጥ–እረጭ ባለ ድባብ ተጠናቅቋል። ልክ አስገድደው እንደሚደፍሩ ወሮበሎች፤ በሃይል ጠልፈው ያላቻ ትዳር እንደሚመሰርቱ ጉልበተኞች፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለፍቃዱ እንደገና የአምስት አመት የትዳር ቁርኝት ውስጥ ገብቷል።  ሌላ አምስት አመት። ሌላ የህወሀት ዘመን። ሌላ የጥርነፋ ዘመን!  ሌላ የቁምራ ዘመን! ሌላ የመፈናቀል ዘመን! ሌላ የመሬት ነጠቃ ዘመን! ሌላ የስደት ዘመን!. . .

የህወሃት ሰዎች አሁን የጭንቀቱ ምእራፍ ሁለት ላይ ናቸው። በዛሬው እና በትላንቱ እለት የህወሃት ባለስልጣናት ተሰባስበው በፐርሰንቱ ምደባ ላይ ውይይት ይዘዋል። ዘረፋው ላይ ሁሉም በ 100% ይስማማሉ። ምደባው ላይ ግን ችግር አለ።  አንዳንዶቹ ይህ ጉዳይ ተአማኝነት እንዲኖረው ለተቃዋሚዎቹ ትንሽ መልቀቅ ይኖርብናል ሲሉ ለሎች ደግሞ ይህንን ሃሳብ ይቃወማሉ። ጥቂት ተቃዋሚዎችን ፓርላማ እንዲገቡ መፍቀድ አለብን የሚሉ ተከራካሪዎች “ሌባ ከሰረቀው ጥቂቱን ቢሰጥ” እንደማይጎዳው ይናገራሉ።  ይህንን የማይቀበሉት ግን የተቃዋሚዎች በፓርላማ መግባት ራስ ምታት እንደሚሆንባቸው በስፋት መክረዋል። 547 መቀመጫ የነበረው የቀድሞው ፓርላማ ውስጥ እውነትን የያዘ አንድ ተቃዋሚ ብቻ ጭንቅላታቸውን በጥብጦት እንደነበር ሁሉም አይዘነጉትም። ይህንን በድጋሚ መፍቀድ አልያም ውግዘቱን በመቀበል መሃል ባለ አጣብቂኝ ውስጥ ከርመዋል። ውጤቱን ከሰሞኑ ይፋ ያደርገዋል ዶ/ር መርጋ።

የዘንድሮው ዝርፍያ ጤናማ አይደለም።  ልክ እንደ ቦራት ዘ-ዲክታተር ፊልም ተወዳዳሪዎችን እግር እግራቸውን እየመቱ ለብቻ ሮጦ፤ በራስ ዳኛ የድል ዋንጫ መረከብ? ይህ በእውነት በዚህ በ21ኛው ዘመን እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው። ተቃዋሚ ሃይሎች በምርጫው ክርክር እና በትውልድ ስፍራቸው ላይ የነበራቸው የሕዝብ ድጋፍ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ በታየበት ሁኔታ ህወሃቶች 100% አሸንፈናል ሲሉ ከሌብነታቸው ይልቅ ንቀታቸው ጥርስ የሚያስነክስ መሆኑን ለአፍታ እንኳ አላስተዋሉትም። እጅግ ትንሽ ጭል ብላ የነበረችውን ዲሞክራሲ በምድረ ኢትዮጵያ ገድለው፣ ከፍነው ቀበሩት። አዲዮስ ዲሞክራሲ . . .

elect2007ፈረንጆች የሚሉት አባባል አለ። “ለነብሰ-ገዳዮች ትክክለኛ ዲሞክራሲ ማለት ፍጹም አምባገነን መሆን ነው።”

“በ100% ድምጽ ተመርጠናል!” አሉ።  የመረጣቸው ህዝብ የቱ ይሆን? በአዲስ አበባ በነቂስ ወጥቶ “ወያኔ በቃን! መንግስቱ ይግደለን” ያለው ህዝብ ነው ወይንስ ለም መሬቱን ተነጥቆ ለባእድ የተሰጠበት የገጠር ህዝብ? በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በሁመራ…ወዘተ የተፈናቀለው ህዝብ ነው የመረጣቸው? ወይንስ  አምቦ – ጉደርን እንደ ሱናሚ ያጥለቀለቀው ህዝብ ? የቱ ነው ወያኔን የመረጠው?  ከስርአቱ ጋር ሆድና ጀርባ የሆነው ሙስሊሙ እምነት ተከታይ ነው ወይንስ በእምነቱ ጣልቃ እየገቡ ካድሬ ጳጳስ የሚሾሙለት ክርስቲያኑ ህብረተሰብ?  ማን ነው ህወሃትን የመረጠው? እንደ ምጽዓት ለስደት እያኮበኮበ ያለው ስራ-አጥ ወጣት ነው ወይንስ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅቶ ድንጋይ የሚፈልጠው ወጣት ምሁር?  መብራት እና ውሃ በፈረቃ ያደረጉበት ህዝብ ነው የመረጣቸው?…  ለመሆኑ ስንት አመት ነው ህዝቡ ላይ እንዲህ የሚቀልዱት?

እነሱ ልባቸው በትእቢት ስለተወጠረ፤ ሌላው ህዝብ የማይመለከትና የማይሰማ ይመስላቸው ይሆናል። ትእቢት ደግሞ የውድቀት ምልክት ናት።  በመጀመርያ የውጭ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ተደረገ። ዝም!  በምርጫው ወቅት ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎችን አሰሯቸው። አሁንም ዝም ተባለ።  ከዚያ ኮሮጆ እየተሞላ ቀረበና በቁም ያሰሯቸው ታዛቢዎችን ምሽት ላይ ፈትተው እንዲፈርሙ አዘዝዋቸው። የተያያዙት አስገድዶ መድፈር ነውና አንዳንዱን አስገድደው በተሰረቀ የድምጽ ሳጥን ላይ አስፈረሟቸው።

ምርጫ 2007 በዚህ ሁኔታ “ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፤ ዲሞክራሲያዊና የህዝብ ተዓማኒነትን አግኝቶ” ተጠናቅቋል ሲሉ ፕ/ር መርጋ በቃና አበሰሩ። እኚህ ፕሮፌሰር ግን ህሊና ይኖራቸው ይሆን? ካላቸው በምን ለወጡት? በገንዘብ? ህሊና ስንት ያወጣል?

አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ከምርጫው በኋላ ስላለው ነገር ብዙም አላሉም።  ማን እንደሚያሸንፍ እና በምን ያህል ድምጽ እንደሚያሸንፍ አስቀድመው ዘግበው ስለነበር ውጤቱን መድገም የፈለጉ አይመስልም።  አስቀድሞ ውጤቱ የታወቀበት ምርጫ መሆኑን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ብቻ ሳይሆኑ፣ ራሱ የምርጫው ቦርድ በድረ-ገጹ ላይ በግልጽ አስቀምጦት ነበር። የምርጫው ቦርድ በድረ-ገጹ  እንዳስቀመጠው የኢሕአዴግ 501 ተወዳዳሪዎች የተመዘገበለት ሲሆን መድረክ 270፣  የሰማያዊ ፓርቲ 139 እጩዎች ብቻ እንዲኖራቸው ተደረገ። የሰማያዊ ፓርቲ 200 እጩዎች በምርጫ ቦርዱ ተሰርዘውበታል።  108 እጩዎች አስመዝግቦ የነበረው አንድነት ፓርቲም ስልታዊ በሆነ ዘዴ በቦርዱ እንዳይሳተፍ ታግዷል። ይህ እንግዲህ በሎተሪ ሰበብ የተገለሉትን ሳይጨምር ነው።

መቼም ይታገሉታል እንጂ አይታደሉትምና ቀኑ እስኪደርስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልፈለገው ሊገዛ፤ ባላመነበት ሊዳኝ፣ ባልመረጠው ሊተዳደር ነው። አሁንም ዝምታን መርጧል።  ዝምታ ራሱን የቻለ መልስ ነው። በዝምታ የተዋጠች እያንዳንድዋ ሰከንድ ቁርሾ ይዛ ማለፍዋም ግልጽ ነው። ማሰብ ላልተሳነው ሁሉ ዝምታ ያስፈራል።  ምጥና ውሃ ሙላት በድንገት እንዲሉ ዝም ያለ ወራጅ ሲወስድ አይታወቅም። ጽዋም ሲሞላ ይፈስሳል . . .

አለም-አቀፉ ህብረተሰብም ዝርፊያውን ስለለመደው ችላ ብሎታል። የእንግሊዙ “ዘ ጋርዲያን” ጋዜጣ “ምርጫውን ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደ አንድ ክስተትም አይቆጥረውም።” ሲል፣  ሂዉማን ራይትስ ዎች፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ፍሪደም ሃውስ፣ ሲፒጄ፣ የመሳሰሉት አለም አቀፍ የመብት ተከራካሪ ተቋማት አፈና የሰፈነበት እና ነጻ ሜድያ በሌለበት ሁኔታ የሚካሄደው ይህ ምርጫው ፍሱም ኢ-ፍትሃዊ እንደነ ገልጸዋል። አልጃዚራ፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ኒውዮርክ ታይምስ የመሳሰሉ ታላላቅ ሜድያ ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ ምርጫ ሲሉ ሂደቱን  በክፉ ኮንነውል።

ነገሩ ግልጽ ነው። ነጻ ሜድያ በሌለበት፣ ገለልተኛ ታዛቢዎች ባልተፈቀዱበት፣  ነጻ ዳኛ በልተመደበበት  ነጻ ምርጫ አይታሰብ። የዘንድሮው ክስተት ህወሃት የዘረፋ ደረጃውን ያወረደበት ምርጫ ነው። ከረቀቀ የዘረፋ ስልት ወደ ግልጽ የውንብድና ተግባር።

የጀርመን ድምጽ እንግሊዝኛው ክፍል ከምርጫው በኋላ ምንጮችን ጠቅሶ ሲዘግብ “ታዛቢዎ የቁም እስር ላይ ስለነበሩ ወደ ውጭ ወጥተው ምርጫውን መታዘብ አልቻሉም” ብሏል።  የሰራዊት እና የሚሊሽያ አባላት በየምርጫ ጣብያው እየተገኙ መራጮችን እያስፈራሩ የተካሄደ ምርጫ በአለም ላይ ይህ ብቻ ነው። የምርጫ ዘመቻም በታጠቁ ሃይሎች ወታደራዊ ትእይንት የተካሄደው በኢትዮጵያ ብቻ ነው።

30 አመት ሙሉ ያል ህዝብ ፍቃድ በስልጣን መቆየት ይሰለቻል። እነዚህ ሰዎች የምእተ አመቱን አንድ አራተኛ የሃገሪትዋን ሃብት ብቻ ሳይሆን የህዝብን ድምጽም እየዘረፉ ተቀመጡ።  ባለፉት 24 አመታት በአሜሪካ አምስት ግዜ መንግስት ተቀይሯል። በሆላንድ 7 ግዜ መንግስት ወርዶ በህዝብ ድምጽ ሲቀየር አይተናል። አፍሪካዊቷ ጋና አምስት ግዜ ፕሬዝዳንታዊ  ምርጫ ፣ ሶስት ግዜ ፓርላሜንታዊ ምርጫ አድርጋለች።…  ያልታደልን ወይንም ያልታገልን እኛ ግን ለ30 አመታት በአንድ አንባገነን ተይዘናል።

ህወሃቶች በሩን ሁሉ ዘግተው ህዝቡን ወደማይፈለገው አመጽ እየገፉት ነው። ያልተረዱት ቢኖር አንደኛው በር ሲዘጋ ሌላኛው በር መከፈት መቻሉን ነው። የ90 ሚሊዮን ህዝብን ድምጽ ሰርቀው፣ አንደበቱን ለጉመው ምን ያህል እንደሚዘልቁ የምናየው ይሆናል። መቶ አመት የዘለቀ አምባገነን በታሪክ አልተከሰተም።

ከዚህ ቀደም ባስነበብኳችሁ ቀልድ ጽሁፌን ልቋጭ። አንድ የህንድ ኢንቨስተር አዲስ አበባ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያንን የቀብር ስፍራ አይቶ በሊዝ ሊገዛ ፈለገ። የአዲስ አበባ ባለስልጣናትን ጠርቶ እንዲሸጡለት ጠየቀ። ባለስልጣናቱም መልሰው ሌሎች ቦታዎች ሳያልቁ የቀብር ስፍራ ለግዜው እንደማይሸጡለት ነገሩት። ህንዱ መለሰና መከራቸው። “እኛ አገር ሰው ሲሞት እናቃጥላለን እንጂ አንቀብርም። ለምን ይህን ለምን ቦታ ታባክናላችሁ?” አላቸው።  ባለስልጣናቱም መለሱ፣ “እኛ አገር ደግሞ ሰውን በቁሙ እንጂ ሲሞት አናቃጥልም!”

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. rasdejen says

    May 28, 2015 09:44 am at 9:44 am

    Not TPLF but USA/UK should be blamed because you don’t blame a child for his wrongs but the parents.

    Yes, the (post) cold war leaders of these two great nations(US/UK) installed/sustained the terrorist rather genocidal group (see clip below) in Ethiopia, causing vicious chaos and misery among the Ethiopians.

    https://www.youtube.com/watch?v=ZWhW34r0r

    Thus, post cold war states of USA and UK are terrorists in the eye of Ethiopians. They are fully responsible for the destruction of Ethiopia and for the sustained misery of its peaceful rather just people!

    Reply
  2. rasdejen says

    May 29, 2015 12:16 pm at 12:16 pm

    Yeap, it is time for the people to go for a neo-Adwa:
    https://www.youtube.com/watch?v=lFuk2PoKjYs –

    Reply
  3. Tilahun says

    May 30, 2015 04:24 pm at 4:24 pm

    ጥሩ ብለህ ነበር ሆኖም ግን “ወያኔ በቃን! መንግስቱ ይግደለን”ባልከዉ ቃል ጭንቅላትህን መረመርኩት እንደሚመስለኝ ምናልባትም የደርግ አባል ወይም የወታደር ልጅ ስለነበርክ ሊሆን ይችላል እንደዚያም ሆነህ ደርግ ይመረሃል ብዬ አልገምትም ለማንኛዉም የደርግን ግድያ እዚህ አሁን ለመግለጽ አስቸጋሪና ዉስብስብ በመሆኑ መግለጹ አስፈላጊ አይመስለኝም የማዝነዉ ግን እንዳንተ ያለዉን የደርግ ናፋቂ እድል ሰጥተዉ ሃሳብህን እንድትጽፍ ባደረጉት ላይ ነዉ
    እንደሚመስለኝ ኢህአዴግ ደስ አይበለዉ ብለህ እንደሆን ትክክል ነህ በተረፈ ይህንን ነገር ከጭንቅላትህ አዉጣዉ ሰዉ ይገምተሃል ትንታኔህ ብዙ እንዳልተማርክ ያሳብቅብሃል ደርግን ጭራሽ ልታነሳዉ አይገባህም የደርግን ያህል መንግስት እስከዛሬ አልታየም ወደፊትም አይታይም እዉነት እልሃለሁ

    Reply
  4. Dejene M says

    June 20, 2015 06:22 pm at 6:22 pm

    እንግህ ምርጫ ብለህ ዝም በል እንጅ አለዚያ ከጫወታ ዉጭ እንዳትሆን።

    Reply
  5. wizy says

    July 9, 2015 01:02 pm at 1:02 pm

    derg ayferedbetm min yaderg alaskemtew silu tegre kalhonk abatkin teyikew ewnetun yasredahal

    Reply

Leave a Reply to rasdejen Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule