• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ተቦርነ በየነ “አንተ አልክ?” – ቴዲ አፍሮን

May 11, 2017 01:54 pm by Editor 3 Comments

እንዲህም ሆነ። የይሁዳ ገዥ የነበረው ጲላጦስ ክርስቶስን አስጠርቶ “አንተ የአይሁድ ንጉስ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ክርስቶስም መልሶ “አንተ አልክ?” አለው። ሰማይን ያለ ምሰሶ ያቆመው ክርስቶስ “ጥፋ” የምትል ቃል ብቻ ከአንደበቱ ቢያወጣ ኖሮ ጲላጦስ አይደለም መላው ቂሳር ክምድረ-ገጽ በጠፉ ነበር።

ታዋቂዎች በአዋቂዎች ላይ የሚቀልዱበት ይህ የገሃዱ አለም እውነታ ግብረ-ገብ ወደ ግብግብ በተቀየረበት በዚህ ዘመን ባሰበት እንጂ አልጠፋም። ጥንት አንቺ-ትብሽ፣ አንተ-ትብስ ይባል የነበረው ብሂል አሁን በ“አንቺ ብስብስ አንተ ብስብስ” ተቀይሯል ሲል አንዱ አጫወተኝ። ከቶውንም ስድብን እንደ ስንቅ በከረጢት ቋጥረው በሚጓዙበት የፌስቡክ ዘመን መስመር የመልቀቁ ነገር አዲስ ሊሆን አይችልም። “አንተ አልክ?” ብሎ ማለፍ ምን ይጎዳል?

ብላቴናው ላይ አንዳች እንከን ሲያጡ፣ የጠወለገን የጥላቻ ህያሴ ለማንጠባጠብ የሚሞክሩትን እንዲህ ማለቱ ይበጅ ይመስላል፤ “አንተ አልክ?”። እንግሊዞች “Cover before you discover” ይላሉ። “አወቅኩ ከማለትህ በፊት፣ እወቅ” እንደማለት ነው። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አንደራደረም ከሚሉ ወገኖች ያልሆኑትን-እነሱ ልንላቸው ነው። ከእኛ ሳይሆን ይልቁንም ከነሱ ወገን፣ አንገት አርዝመው፤ ምላስ አሹለው የቴዲን ስራ ለማጣጣል ብቅ ያሉ ሃያሲ ተብየዎች ግራ ቢገባቸው፣ “ቴዲ ስለ አባይ ስላልዘፈነ ግብጻዊ ነው” ሲሉ አስደምመውናል። “ህዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍቷል” ይላል ቃሉ። “ስለ አባይ ስላልተቃኘ ግብጻዊ ነው!” የሚለውን የድንቁርና ዝባዝንኬ ሲቀባጣጥሩ፣ የ”ፈለገ ግዮን” ምስጢራዊ ቅኝት ሊገባቸው አይችልምና እንደነዚህ አይነቱን ለማስረዳት መጣር ግዜ ማባከን ይሆናል። አባይ የወንዞች ሁሉ ታላቅና ንጉስ ስለሆነ፣ በታላቁ መጽሃፍ ፈለገ-ግዮን በሚል ስም ይጠራል።

እርግጥ ነው። ቴዲ አባይን ያየበት መንገድ ከባህላዊው ቅኝት ትንሽ ለየት ይላል። ስለ አባይ ያነሳው ቅኝት ለጸጸት፣ ለቁጭት እና ለፕሮፓጋንዳ ከተነሱት ዘፋኞች ሁሉ የላቀ ነው። ስለ አባይ ብዙ ተዘፍኗል። አንዳንዶች ግጥምን ከጉልት እንደሚሸመት ሸቀጥ እየገዙ አዚመውታል። ይኽኛው ከነዚያ ስራዎች ጋር የሚነጻጸር አይደለም። በረቀቀ መልኩ “…ፈለገ ግዮን ያንቺ ስም ሲጠራ” ሲል በእናትነት፤ ከፍ ሲል ደግሞ ከሃገር ጋር አቆራኝቶ ተቃኝቶለታል።

ስለ ወዳጃችን ተወልደ/ተቦርነ በየነ የከተፋ ወግ ከመግባቴ በፊት በቴዲ አምስተኛው የአልበም ስራ የተሰማኝን ልግለጽ። አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ ይህንን ስራ በአንድ መስመር ሲያስቀምጠው፣ “እኔ ማለት ምችለው ቴድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የጠፋውን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የመለሰ ልብ አስታራቂ ልጅ ነው” በማለት ነበር።

የሃይሌ ገብረስላሴን ገጽ ያነበበ ሁሉ በእርግጥ “የኢትዮጵያዊነት መንፈስ” ጠፍቶ ኖሯል የሚል ጥያቄ ማንሳቱ አይደንቅም። የኢትዮጵያን ባንድራ እያውለበለቡ ስምዋን በአለም መድረክ የሚያስጠሩም ሳይቀሩ ኢዮጵያዊነታቸው በሰላቢዎች ተሸልቶ የበጠፋበት ግዜ መሆኑ ግን ያስደነግጣል። በእናት እየመሰለ የተቀኘላት ይህች ሃገር የሚያቆስሏት እንጂ የሚቆስሉላት በጠፉ ግዜ፣ የሚጮሁባት ሳይሆን የሚጮሁላት በመነመኑበት ግዜ፣ በድብቅ ሳይሆን በገሃድ የ”እናፍርሳት” አፈርሳታ የሚዶልቱ በበዙበት በዚህ ዘመን፣ እናቱን ከነ ችግርዋ የሚወድዳት፣ በሲቃና በደስታ መሃል የተቀኘላት የጠላት፣ የሚጠላትን ደግሞ በድፍረት የሚረግም ጀግና ብቻ ነው።

ከ“ሰምበሬ” … እስከ “ናት ባሮ” እናትን እናይበታለን፤ ከቴዎድሮስ እስከ አደይ ኢትዮጵያን እንቃኝበታለን።

“አደይ”ን እያሰማን ከመረብ ወንዝ በላይና ታች አድርጎ ታቹን በጀግናው አጼ ቴዎድሮስ ወደ ጎንደር ያስገባናል፤ ከዚያም “ማሬ” እያለ በጎጃም አውርዶ ወሎ እና ሸዋ ላይ ያወጣናል። “ኦላን ይዞ” እያለን ወደ ደቡብ ይወስደንና “በአናኛቱ” ምስራቅንና ምእራብን ያስጎበኘናል። በሙዚቃው ቅኝት ኢትዮጵያን ከጫፍ እስከጫፍ የማስጎብኘት ጥበብን መሰለኝ ሃይሌ ለማንሳት የፈለገው። ይህ የድምጻዊነት ደረጃውን ጣራ ያደረሰው ብቻ ሳይሆን፣ የተነጠቀን ኢትዮጵያዊነት የማስመለስ ምትሃት ይመስላል። ይህ ስራ በውቀት ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ልቆ የሚገኝ ስለመሆኑ ሚሊዮኖች መስክረዋል። ሚሊዮኖች  “ኢትዮጵያ” እያሉ አብደዋል።

የቴዲ ስኬት ያሳበዳቸውም አልጠፉም።

አንድን ስራ ስነ ምግባር መተሞላ መልኩ መተትች አንድ ነገር ነው። በሙያው የተካኑ ይህንን ቅንብር ቢተቹ ጥቅም እንጂ ጉዳት አይኖረውም። ከግል ጥላቻ ብቻ ተነስቶ ይህንን ድንቅ ስራ ጥላሸት ለመቀባት መሞከር ደግሞ ሌላ ነገር ነው። ስኬቱ ያበገናቸው ሁሉ ዘልለው የማይይዙትን ተራራ ለመንካት ከቁመታቸው በላይ መንጠራራትን ይዘዋል።

ተቦርነ በየነ የኢሳት ራዲዮ ላይ ስለ “መተቸት መብት” ይናገራል። መብትም እኮ “መብት” ስለሆነ ብቻ ፋይዳ አለው ማለት አይደለም። አጋጣሚ እየፈለጉ እንደ Crusades የማያቋርጥ ማጥላላትን በአንድ ብላቴና ላይ ማናፈስ ግን መብት አይደለም፣ ፍጹም ጭፍን የሆነ ጥላቻ እንጂ። ጥላቻና ማን-አለብኝነት ደግሞ የደካማነት እንጂ የጥንካሬ ምልክት አይደለም። ለሃገር ቆምኩ የሚል ሰው በሃገር ጉዳይ ላይ አይደራደርም። ለነገሩ እንጂ “ሺ ዝንብ መሶብ አይከፍትም” እንዲሉ፣ እነዚህን በእውቀት እና በጥበብ ከፍታ ላይ የተሰሩ ስራዎች የማውረድ አቅም ያለው ሊኖር አይችልም።

ይህች ሀገር አሽቃባጭ እና ጥሩምባ ነፊ አላጣችም። ሊያጠፉዋት የሚዶልቱትን እንኳ ሳይቀር በአንዲት ዜማ ማስመለስ የሚችሉ፣ ከችሎታው በላይ ደግሞ ዝምታን ደፍረው የሚሰብሩ ናቸው ኢትዮጵያ የሚያስፈልጉዋት። ይህንን ቴዲ ሲያደርግ አልጋ ባልጋ ሆኖ አይደለም። ከሚነደው እሳት ጥግ ሆኖ ወላፈኑ እየገረፈው ይህንን አደረገ። ከውጭ ሆናችሁ ሌላ እሳት መለኮስ የምትሹ ሁሉ፤ እባካችሁ ተወት። ወላፈኑ ይበቃዋል።

ተወልደ/ተቦርነ በየነ በቴዲ ስራዎች ላይ ያሻውን የማለት መብት አለው። በአመክንዮ ሳይሆን በጥላቻ ስራውን ለማጥላላት እንደሚሞክረው OMN ቲዩብ ማለት ነው። ተቦርነ ቲዩብ ብሎ መልቀቅም ይችላል። ኢሳትን ምርኩዝ አድርጎ ሲሰራው ግን የ”ትችቱ” ትርጉም ይቀየራል። “ቀላል ይሆናል” ይላል ቴዲ – ነገሮች መስመር ሲስቱ። ይህ ዘመቻ – የ”ሙዚቃ ሃያሲ”ው ትራስ እያደረገ የሚነሳበት ተቋም ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ ግን “ቀላል አይሆንም”። የኢትዮጵያን ማልያ ለብሶ ለOMN መጫወት ይመስላል። አንድ ግለሰብ ከሚሊዮኖች ጋር ለመላተም ከቶውንም አይደፍርም። አእምሮውን ቆልፎ ይህንን ድፍረት የሚሰጠው ትራስ ካልተማመነ በስተቀር። … አካሄዱ “ሹሩባ ልትሰራ ሄዳ ጠጉሩዋን ተላጭታ መጣች” እንዳይሆን ነገሩ የገባው ሁሉ ይወቅበት።

አዎ ቴዲ ስለጎንደር የተቃኘውን ስራ “የይርጋ ዱባለ ሰራ ነው” ሲል ተቦርነ አሹፎበታል። “የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ” እንዲሉ ከዚህ ቀደም እንደሚለው “ለምን ይዋሻል”ን አልጨመረበትም እንጂ ሙዚቃው ከሌላ ድምጻዊ እንደተወሰደ በድፍረት ተናግሯል። በኢሳት ራዲዮ የተናገረው ቃል በቃል እንዲህ ይላል።

“በቴዎድሮስ ካሳሁን አዲሱ ‘ኢትዮጵያ’ የሙዚቃ አልበም ውስጥ የአንጋፋውን የባህል ድምጻዊ የይርጋ ዱባለን ጎንደር የተሰኘ ስራ ጨምሮ 14 ያህል የሙዚቃ ስራዎች ተካትተዋል።”

ከዚያም ይደግምና “ከአንጋፋው ይርጋ ዱባለ ጎንደር የተሰኘው ስራ ውጭ ሌሎች አስራ ሶስት የሙዚቃ ስራዎች ግጥም እና ዜማ ድርሰቶች የድምጻዊ የቴዎድሮስ ካሳሁን ናቸው” ይለናል።

አልበሙ ላይ የምናየው የዚህ ስራ ግጥም ጸሃፊ “በቴዎድሮስ ካሳሁን” ይላል። በዜማው ላይ ጎንደርኛ ቅኝት የቀባበት መሆኑንም በግልጽ አስቀምጦታል። ቴዲ በጠራራ ጸሃይ ሊዋሽ እንደማይችል ግልጽ ነው። ለከተፋው ይህ ስራ የተመረጠበት ምክንያትም፣ ሙዚቃው በህዝብ ልብ ውስጥ እጅግ ዘልቆ መግባቱ ይመስላል።

የሚደንቀው ደግሞ የቴዲን አልበም ሽያጭ ለማኮሰስ ሲል የተጠቀመበት የንጽፅር መነጽሩ ነው። የአልበም ሽያጭ ሰልፉን ከሌሎች ድምጻውያን ሰልፎች ጋር ለማወዳደር የሞከረበት መንገድ ቴዲን ሳይሆን ይልቁንም አድማጩን ሕዝብ የመስደብ ያህል ነው። ከጅምሩ ይህ አልበም ከሌሎች ድምጻውያን አልበም ጋር ለንፅፅር መቅረብም የለበትም። በሚሊዮን አይደለም በመቶ ሺዎች ያሳተመ ድምጻዊ በኢትዮጵያ ታሪክ አልነበረም፣ የሙዚውቃ ሲዲ እንደ ቀበሌ ስኳር በሰልፍ እና በሽሚያ የተገዛበት አጋጣሚም የለም፤ አዟሪዎች ሲዲን በእጥፍ የሽጡበት ወቅት አላየንም። እስከዛሬ በማንም ድምፃውያን ያልተከሰተን ነገር ነው ለንፅፅር ሊያቀርብ የሞከረው።

ለወንድሜ ተቦርነ የምለው አንድ ነገር ብቻ ነው። ልቦና ይስጥህ። በጥላቻ እና በትችት መሃል ያለን ልዩነት መቀበል እና ማመን ይገባሃል። ጥላቻ ደግሞ እንዲሁ አይመጣም። ምክንያቶች አሉት። ግላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ባህላዊ እና ማህበራዊ ምክንያቶች። ጥላቸው ከየትም ይምጣ ከየት – ግን አንድ የምመክረው ነገር አለ። አበው እንደሚመክሩት “ቆዳ ሲወደድ በሬህን እረድ።” እጅህን ከቴዲ አንሳ!

(ንግግሩን ለማድመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ ከ10ኛው ደቂቃ ጀምሮ)

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. getachew fuafuate says

    May 12, 2017 08:04 pm at 8:04 pm

    ወንድሜ ክንፉ አሰፋ ተወልደ የሚባል አንድ የኢሳት ጥውር በቴዎድሮስ ካሣሁን አዲስ አልበም ላይ የሰጠውን አስነዋሪ ትችት በሚመለከት ያስነበብከን ፁሑፍ በጣም ተገቢና ሚዛኑን የጠበቀ እርምት ነው እጅግ በጣም ወድጀዋለሁ አንድ ነገር ግን ግልፅ መሆን ይገባዋል ኢሳትም ሆነ የኢሳቱ ቀጣሪ ድርጅት ላይ ላዩን ስለኢትዮጵያ ይወሻክቱልህና ጠበቅ አድርገህ ስትይዛቸው ከኢትዮጵያ ጋር የሉም ስነልቦናቸው ሆነ ስነአእምሯቸው የተሰለበው በኤርትራ ጉዳይ ላይ ነው ይህ ደግሞ ትልቅ ውርደት ነው እነሱ ወርደው ሀገርን እያዋረዱ ለጥቅም ተገዥ መሆን ይኸውም እያደገና ሰር እየሰደደ ሲሄድ ራስን ለባንዳነት ያዘጋጀ ኃይል ኤርትራ አገኘች ማለት ነው ስለዚህ የተወልደ በየነ ሆነ የሌሎች የኢሳት ጋዜጠኛ ነን ባዮች ክህደታቸውንና መንጠርዘዙን ትተው ተቋሙን ነፃና የሁሉም መገልገያ እንዲሆን በጎ ተፅእኖ ማሳደር ያስፈልጋል በኋላ እናቴ በእንቁላሉ እንዳይመጣ።

    Reply
    • Michael says

      May 20, 2017 08:20 pm at 8:20 pm

      Thank you friend you right. We will not forget Professor Berhanu Nega was the one who sponsors the book of Ethiopian enemy Tesfaye Gebreab by the name of G7. Esat Radio is also interviewed Tesfaye many times and Tesfaye was also applying to be Esat’s news broadcaster. We can’t say Esat is a free Media but is a hijacked media served G7 propaganda. Even they are afraid to speak concerning Ethiopiawinet. That’s why to disdain the good work of Teddy. Since their master, Shaebia dislikes Amara and Ethiopia, Esat remains quiet for long even during the fierce fight of the Amara people did quietly.

      Reply
  2. ገረመው says

    May 25, 2017 09:47 am at 9:47 am

    ክንፉ እድሜህን ከፍ ያርገው ተወልደ ይህን ማለቱ አልስማሁም ገልቱ ነኝ የቴዲ ስሪ ግን ለኔ የነበረ, የሚኖር,ያለና የሚመጣ የሚዘምር መዝሙሬ ነው::

    Reply

Leave a Reply to ገረመው Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule