በአሜሪካ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር መገናኘታቸውን ማምሻው ላይ የኋይት ሃውስ ጽህፈት ቤታቸው ባወጣው አጭር መግለጫ አስታውቋል። በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ያለውን የተሃድሶ ጥረት እንደሚያደንቁ ሚስተር ፔንስ ተናግረዋል። ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ በትላንትናው ዕትም ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከምክትል ፕሬዚዳንት ፔንስ ጋር እንደሚገናኙ በዘገበ ወቅት ግንኙነቱ ወሳኝና ጠቃሚ እንደሆነ መጥቀሱ ይታወሳል። ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ዐቢይ “ሰብዓዊ መብቶችን በማክበር፣ የንግዱን ማኅበረሰብ ሁኔታ በማሻሻል እና ከኤርትራ ጋር ሰላም በመፍጠር ረገድ” እያካሄዱ ያሉትን ለውጥ በማድነቅ አገራቸው የተሃድሶ ለውጡን እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል። ከዚህ ሌላ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ … [Read more...] about “ታሪካዊውን የተሃድሶ ጥረት” እናደንቃለን – ማይክ ፔንስ
mike pence
ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ጋር ይገናኛሉ
ሐሙስ ዕለት የአሜሪካ ጉብኝታቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ጋር ነገ (አርብ) እንደሚገናኙ ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ ያገኘው መረጃ ጠቁሟል። ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት ማክሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ወይም ሰኞ ይዘልቃል ተብሎ ታስቦ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጉብኝት ባጭር ቀናት እንደሚጠናቀቅ ከተሰማ ወዲህ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወገኖች ቀናቱ እንዲረዝሙ ብዙ ሲጥሩ ቆይተው ነበር። በተለይ የጠ/ሚ/ሩ ጉብኝት ዋናው ዕቅድ ከኢትዮጵያውያን ጋር መገናኘት ነው ተብሎ ከአገር ቤት ከተነገረ ወዲህ እነዚሁ ወገኖች ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መገናኘት አለባቸው በሚል ሲጥሩ ቆይተው ነበር። የጠ/ሚ/ር ዐቢይ ጉብኝት ከኢትዮጵያውያን ጋር ብቻ ከሆነና በዚህ የመጀመሪያ በሆነው ጉብኝት ከትራምፕ አስተዳደር … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ጋር ይገናኛሉ