የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ይድነቃቸዉ ተክሉ በወልቂጤ ከተማ በጉብሬ ክፍለ ከተማ አባፍሯንሷ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪ ነዉ። ከ10 በላይ የተለያዩ የሳይንሰና የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች ስራ ባለቤት ሲሆን ከነዚህ የፈጠራ ስራዎች መካከል የእናቶች ጉልበትና ጊዜ ማስቀረት የሚያስችል የእንጀራ መጋገሪያ ቴክኖሎጂ ፈጥሯል። ይህ የእንጀራ መጋገሪያ ቴክኖሎጂ እራሱ ያቦካል ፣ እራሱ ያሟሻል፣ እራሱ ይጋግራል እንዲሁም እንጀራዉ ሲደርስ እራሱ ከምጣዱ ላይ ያወጣል። የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ባዘጋጀዉ 3ኛዉ ዙር የሳይንስና የሒሳብ ትምህርቶች ቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽንና ዉድድር ላይ እናቶችን ከጭስ የሚገላግለዉ የእንጀራ መጋገሪያዉና ሌሎችም በርካታ ቴክኖሎጂዎች ይዞ የቀረበዉ የአባ ፍሯንሷ ፈርጥ ይድነቃቸዉ ተክሉ በውድድሩ 1ኛ ደረጃ በመውሰድ … [Read more...] about ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ