ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ጃዋር ሲራጅ መሃመድ የተከሰሰበት ጉዳይ “ፖለቲካዊ ነው፤ ይህ ችግር የሚፈታው ቁጭ ብሎ በመወያየት ነው” በማለት ለፍርድ ቤቱ ተናገረ። የወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ከጃዋር ጋር አብሮ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎችም ተጠርጣሪዎች ሐሙስ ዕለት ነው ልደታ ምድብ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እና አራዳ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት። ይህንንም ተከትሎ የጃዋር ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ከእስር ቤት ውጪ ሆኖ ጉዳዩን መከታተል እንዲችል እንዲፈቀድለት ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ተቀብሎታል። በዚህ … [Read more...] about በወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር ለፍርድ ቤቱ፤ “ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው፤ የሚበጀው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው” አለ
ችሎት
ኦኤምኤን ሕጋዊ ክስ ተከፈተበት፤ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል
በአሜሪካ አገር በትርፍ አልባ ድርጅትነት የተቋቋመውና ለበርካታዎች ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ተጠያቂ ነው የሚባለው ኦኤምኤን (የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ) ክስ ተመሥርቶበታል። ከሚዲያው ጋር ታደለ ኪታባ (የሚዲያው ሹም እንደመሆኑ)፤ እንዲሁም አያንቱ በከቾ በግል የክስ ተመሥርቶባቸዋል። ክሱን ያቀረቡት ጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ እንደሚሉት ይህ ፋይል የማስከፈት ዓይነት ተግባር ነው እንጂ በትክክል በዐቃቤ ሕግ ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ክስ አልተመሠረተባቸውም። የጉዳዩ ባቤት የሆኑት አቶ ጥበበ ሳሙኤል እንዲህ ይላሉ፤ ከበርካታ ሰዎች እና የሚድያ አውታሮች፤ 'OMN and its employees are Charged in District Court የሚል የዜና ዘገባ እየተራገበ መሆኑ እና እንዳብራራ ጥያቄ እየተጠየቅኩ ነው። በአጭሩ ለማብራራት "they are sued not … [Read more...] about ኦኤምኤን ሕጋዊ ክስ ተከፈተበት፤ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል
የሃጫሉ ተኳሽ፣ አስተኳሾችና የአስከሬን ድራማ ጸሐፊ ተውኔቶች የግፍ ሥራ
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ጸጋ ቅዳሜ ሐምሌ 5፤ 2012 ከፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጋር በሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ የሃጫሉ ሁንዴሣ ግድያን አስመልክቶ የተቀናበረውን ድራማ አስረድተዋል። የድራማውን ጸሐፍትና የድራማ ትወናቸውንም በዝርዝር ተናግረዋል። ቃታ ሳቢው ጥላሁን (ተኳሽ) “የአርቲስቱ ግድያ ግብ ነበረው” ያሉት አቶ ፍቃዱ ጸጋ “አርቲስቱ የግድያ ዛቻ ይደርስበት እንደነበር ለጓደኞቹ ተናግሯል” ብለዋል። ወደ ግድያው አፈጻጸም ዝርዝር ትንታኔ በመግባትም ገዳዩ ጥላሁን ያሚ በሚኖርበት የገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ ሁለት የማያቃቸው ሰዎች ስሙን ጠርተው እንዳናገሩት ራሱ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል አስረድቷል። ይህንን የእምነት ክህደት ቃል የሰጠውም ሕገመንግሥታዊና የወንጀል ሕግ በሚፈቅደው መሠረት መብትና ግዴታው … [Read more...] about የሃጫሉ ተኳሽ፣ አስተኳሾችና የአስከሬን ድራማ ጸሐፊ ተውኔቶች የግፍ ሥራ