አቃቤ ሕግ በእነ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ላይ ክስ የሚመሰርትበት ቀን አርብ መስከረም 8፤ 2013ዓም ነበር። ሆኖም በዚህ ክስ ይመሰረታል ተብሎ በሚጠበቅበት የመጨረሻው ቀን ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። በዚህም አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ የነ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ተናግረው ነበር። ሆኖም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት ጃዋርና ሲራጅ መሐመድና ግብረአበሮቹ በ10 ተደራራቢ ክሶች ፋይል እንደከፈተባቸውና የክስ ቻርጁም መስከረም 11፤2013ዓም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደሚደርሳቸው አስታውቋል። ዐቃቤ ሕግ ያወጣው ጽሁፍ ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድ፤አቶ በቀለ ገርባ፤አቶ ሀምዛ አድናን እንዲሁም በሌሉበት የተከሰሱትን የኦሮሚያ ሜዲያ … [Read more...] about ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
ችሎት
እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
በእነ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ላይ ተከፍቷል ከተባለው የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ በመጪው ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ ዐቃቤሕግ አስታወቀ። ጃዋር ሲራጅ መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ በ24 ሰዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 260215 በ10 ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን ያስታወቀው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን በማስመልከት በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት መግለጫ እንደሚሰጥ ተገለፀ። “ክስ መመሥረት ባለበት ጊዜ ውስጥ ባለመመሥረቱ ተከሳሾቹ ከሰኞ ጀምሮ ከእሥር ሊለቀቁ ነው የሚል ወሬ በሕዝብ ዘንድ ተሰራጭቷል” መግለጫው ዐቃቤ ሕግ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ሥራ ማኅበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ መከፈቱን በተመለከተ ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አጭር ጥቅል መረጃን ሰበር በሚል ርዕስ ሰጥቷል። “ፍርድ ቤት ራሱ ክሱ በዝርዝር … [Read more...] about እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
ለጌታቸው አሰፋና መሰሎቹ ክስ ምስክር ማሰማት ተጀመረ
በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በተከሰሱ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የዐቃቤ ህግ ምስክር ማሰማት ጀመረ። በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች በተከሰሱበት በአዋጅ ከተሰጣቸው ስልጣን ውጪ ሰዎችን በመያዝና በማሰር ስልጣንን ያለ አግባብ መገልግል ወንጀል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከመጋረጃ ጀርባ ማንነታቸው የማይገለፅ ምስክሮችን ዛሬ ማሰማት ጀምሯል። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አጠቃላይ 22 ተከሳሾች ሲሆኑ፥ ጌታቸው አሰፋ፣ አፅበሃ ግደይ፣ አሰፋ በላይ እና ሺሻይ ልኡል በሌሉበት ነው ጉዳያቸው የታየው። ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በምስክር ጥበቃ አዋጅ 699/ 2003 መሰረት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው እና ማንነታቸው የማይገለፅ 29 ምስክሮችን … [Read more...] about ለጌታቸው አሰፋና መሰሎቹ ክስ ምስክር ማሰማት ተጀመረ
እነ እስክንድር፥ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት
እነ አቶ እስክንድር ነጋ የአስተዳደሩን ሥልጣን በኃይል ለመያዝና ለሽብር ወንጀል መሰናዳት ወንጀሎች ተከሰሱ ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለው የቆዩት እነ አቶ እስክንድር ነጋ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀና ለ)፣ 35፣ 38፣ 240(1ለ) እና የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 6(2) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ መንግሥትን ሰላም በመንሳትና እንዳይረጋጋ በማድረግ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥልጣንን ኃይልና አመፅ ተጠቅመው ለመያዝ በመንቀሳቀስና ለሽብር ወንጀል በመሰናዳት ወንጀሎች ክስ ተመሠረተባቸው። የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጳጉሜን 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ መንግሥትና የሽብር ወንጀሎች አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት፤ በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ … [Read more...] about እነ እስክንድር፥ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት
“ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” ሊባሉ ነው
እነ ጃዋር መሐመድ መንግሥትን ኮንነው የፍትሕ ተቋማትንና ፍርድ ቤትን አመሠገኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግሥት ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 71 ቀናት በእስር ላይ ያሉት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የጊዜ ቀጠሮና የቅድመ ምርመራ የፍርድ ቤት ሒደቶች መጠናቀቃቸውንና የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱን አስመልክቶ፣ “ያለ ጥፋታችን እንድንታሰር አድርጎናል” ያሉትን መንግሥትን ኮንነው የፍትሕ ተቋማትንና ፍርድ ቤትን አመሠገኑ። ተጠርጣሪዎቹ ቅሬታቸውንና ምሥጋናቸውን የገለጹት ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱን ሒደት ሲያይ የነበረው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት፣ ሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በምርመራ መዝገቡ ላይ የተለያዩ ትዕዛዞችን ሰጥቶ ሲዘጋ በሰጡት … [Read more...] about “ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” ሊባሉ ነው
ደጀኔ ጣፋ፥ ከ “ተጠርጣሪ” ወደ “ተከሳሽ”!
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ በሕገ መንግስት እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓት ላይ በሚፈጸም ወንጀል ተከሰሱ። አቶ ደጀኔ ክስ የቀረበባቸው ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 26፤ 2012 ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ነው። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በአቶ ደጀኔ እና አቶ መስተዋርድ ተማም በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ባቀረበው ክስ፤ ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ከሚገኙ እና ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን እንደነበር ጠቅሷል። ሁለቱ ተከሳሾች “በኃይል፣ በዛቻ፣ በአድማ ወይም ህገ ወጥ በማናቸውም መንገድ በሕገ መንግስቱ የተቋቋመውን ስርዓት ለማፍረስ በማሰብ ከሰኔ 2012 ዓ.ም. በኋላ መንግስት የስልጣን ዘመኑ የሚጠናቀቅ በመሆኑ መንግስት ሆኖ … [Read more...] about ደጀኔ ጣፋ፥ ከ “ተጠርጣሪ” ወደ “ተከሳሽ”!
እነ ጃዋር መሐመድና ተቋማቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናል አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ
“በግል ሐኪሜ ካልሆነ አልታከምም ማለታቸው እንድንጠራጠር አድርጎናል” ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ “አዕምሮዬን ብስት እንኳን በማላውቀው ሐኪም መነካት አልፈልግም” ተጠርጣሪ አቶ ጃዋር መሐመድ “ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ የሚሰጠው ትዕዛዝ እየተከበረ አይደለም” ተጠርጣሪዎች “መርህ አክብረን ሁሉንም ነገር በአግባቡ እየፈጸምን ነው” የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በተጠረጠሩበት የአመፅ ጥሪ ማድረግ፣ የሰው ሕይወት ማጥፋት፣ የእርስ በርስ ግጭት መፍጠር፣ የንብረት ውድመትና ሌሎችም የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኘው እነ አቶ ጃዋር መሐመድና ሁለቱ የመንግሥት ተቋማት (ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ፌዴራል ፖሊስ) የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናልና አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ። ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች “ፈጽሜያለሁና አልፈጸሙም” በሚል … [Read more...] about እነ ጃዋር መሐመድና ተቋማቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናል አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ
የፍርድ ቤት የችሎት ውሎ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት እንዲተላለፍ ምክረ ሐሳብ ቀረበ
በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ጨምሮ በርካታ ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ለሕዝብ ተደራሽ እንዲደረግ ምክር ሐሳብ ቀረበ። የፍርድ ቤት ውሎ በቀጥታ ሥርጭት ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆንና ሌሎች አማራጮችን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው፣ የኢፌዴሪ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ነው። በተቋሙ ዋና እንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ (ዶ/ር) ተፈርሞ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ለዳኞችና ዓቃቢያነ ሕግ፣ ለተጠርጣሪዎችና ለችሎት ታዳሚዎች ደኅንነትና ጥበቃ አመቺ በሆነ ሰፊ አዳራሽ ችሎት ማስቻልን የመጀመርያ አማራጭ አድርጓል። የፍርድ ቤቱን ውሎ ሁሉም የመንግሥትና የግል፣ የሕትመትና የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ አካላት ብቻ እንዲዘግቡት ማድረግና በዘገባዎቻቸው የችሎቱን … [Read more...] about የፍርድ ቤት የችሎት ውሎ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት እንዲተላለፍ ምክረ ሐሳብ ቀረበ
ልደቱ የ98 ምርጫ ወቅት ከህወሓት ደኅንነት ሽጉጥ መቀበሉን ለፍርድ ቤት አመነ
ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ አያሌው በህክምና ምክንያት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ፥ መርማሪ ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የሰባት ቀን ጊዜ ፈቅዷል። በምስራቅ ሸዋ ዞን የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ በቀረቡት አቶ ለደቱ አያሌው ላይ መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው ተጨማሪ 14 ቀናት ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን የምርመራ ስራዎች ገልጿል። አቶ ልደቱ እጅ ላይ የተገኙ ሁለት ሽጉጦች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም የተላላኳቸውን የስልክ መልዕክቶች በፎረንሲክ እያስመረመረ መሆኑን ተናግሯል። በእጃቸው ላይ የኢትዮጵያ ህዳሴ እርቅና አንድነት የሽግግር መንግስት ማቋቋም የሚልና ሌሎች የፖለቲካ ሰነዶችን ማግኘቱን የገለፀው መርማሪ ፖሊስ በሰኔ 23 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን … [Read more...] about ልደቱ የ98 ምርጫ ወቅት ከህወሓት ደኅንነት ሽጉጥ መቀበሉን ለፍርድ ቤት አመነ
ጃዋርና በቀለ ገርባ ለቅድመ ምርመራ የተሰየመው ዳኛ ይነሣልን ሲሉ አመለከቱ
አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የ14 ተጠርጣሪ ጠበቆች ለቅድመ ምርመራ የተሰየመው ዳኛ ገለልተኛ ሆኖ ጉዳያችንን ሊመለከትልን ስለማይችል ይነሣልን ሲሉ ማመልከታቸው ተገለጸ። አሥራ አንዱም የተጠርጣሪ ጠበቆች በሰባት ገጽ ባቀረቡት አቤቱታቸው ሕግ ጠቅሰው ዳኛው ገለልተኛ ሆኖ ጉዳያችንን መመልከት አይችልም በማለት ነው ያመለከቱት። የምርመራ መዝገቡን ሲመለከቱ የቆዩት የዕለቱ ዳኛ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ 25/88 አንቀጽን በመጥቀስ የቀረበው አቤቱታ ተጨባጭነት የሌለው፣ በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ልነሣ አይገባም በማለት ወስነዋል። ይሁን እንጂ በአዋጁ መሠረት መዝገቡ በሬጅስትራር በኩል ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ በተመሳሳይ ሌላ ዳኛ አይቶ ውሳኔ እስኪሰጥበት እና መጥሪያ እስከሚደርሳቸው ድረስ ተጠርጣሪዎቹ ባሉበት በፖሊስ ማረፊያ እንዲቆዩ የፌዴራል … [Read more...] about ጃዋርና በቀለ ገርባ ለቅድመ ምርመራ የተሰየመው ዳኛ ይነሣልን ሲሉ አመለከቱ