እማሆይ ሲሳይ ዋጋው የደብረ ዘቢጥ ከተማ ነዋሪ ናቸው። የዛሬን አያድረገውና በየዓመቱ የዘመን መለወጫ በዓል ሲመጣ ቤት ያፈራውን በማዘጋጀት በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር። “የዘመን መለወጫ ለእኔ ልዩ በዓል ነበር” ያሉት እማሆይ ሲሳይ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ከተማቸውን በወረረበት ወቅት ሀብትና ቀለባቸው በመዝረፉ በዓልን አስፈላጊውን ነገር አዘጋጅቶ በደስታ ማሳለፍ ቀርቶ የዕለት ጉርስ ማጣታቸውን ተናግረዋል። እማሆይ ሲሳይ እንዳሉት የእሳቸው ንብረት ብቻ ሳይሆን የቀበሌው ነዋሪዎች ሁሉ በሽብር ቡድኑ በመዘረፉ ችግሩን የበለጠ የከፋ ያደርገዋል። “ይህ ክፉ ጊዜ ይለፍ እንጅ በዓል ሁሌም ይደረሳል። ብቻ ሀገራችንን ሰላም ያድርጋት” ነው ያሉት። አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ከተማቸውን በወረረበት ወቅት አቅም በሌለው ጉልበታቸው ወደ ጫካ ገብተው … [Read more...] about ሃብትና ቀለባቸው በትህነግ ወራሪ ተዘርፎ የዕለት ጉርስ አልባ የሆኑት እማሆይ ሲሳይ ዋጋው