• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“‘ጭካኔ የተሞላበት አፈና’ – የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ”

June 16, 2016 08:03 am by Editor 3 Comments

ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በምንም ዓይነት መልኩ የማይተዋወቀው፤ መተዋወቅና መግባባትም የማይችለው ህወሃት ሰሞኑን “የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን” ብሎ ባቋቋመው ጽ/ቤቱ አማካኝነት “በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር” በማለት ዘገባ ካወጣ ጥቂት ቀናት በኋላ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት ማምሻውን የህወሃትን ቅጥፈት ርቃኑን የሚያወጣ ዳጎስ ያለ ዘገባ ይፋ አድርጓል፡፡ ከዘገባው ጋር በማያያዝ የተወጣው መግለጫ ከዚህ በታች ይገኛል፡፡

(ናይሮቢ፤ ሰኔ 9 ቀን 2008 ዓ.ም) – ከህዳር ወር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከ400 በላይ የሚሆኑ ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ከአስር ሺህ በላይ የሚቆጠሩትን ደግሞ ማሰራቸውን ሂዩማን ራይት ወች ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ እስራቶችንና ሌሎች የመብት ጥሰቶች በአስቸኳይ ተአማኒነት ያለውና ገለልተኛ የሆነ ማጣሪያ እንዲካሄድ ድጋፍ ማድረግ አለበት።

ይህ ባለ 61 ገጽ ሪፖርት “‘ጭካኔ የተሞላበት አፈና’ – የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ“ የተሰኘው ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት ተቃውሞሙን ለመቆጣጠር የተጠቀመውን ከመጠን ያለፈ ሀይል እርምጃና እስከ መግደል የሚያደርስ ሃይል፣ የጅምላ እስር፣ ጭካኔ የተሞላበት የእስር ቤት አያያዝ፣ እንዲሁም የተቃውሞ ሂደቶችን በተመለከተ መረጃዎች ለህዝብ እንዳይሰራጩ ማፈንን አጠቃሎ በዝርዝር አቅርቧል፡፡

ይህን ሪፖርት ለማጠናቀር ሂዩማን ራይትስ ዎች እ.ኤ.አ. ከህዳር ወር 2015ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም. ድረስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እንዲሁም ሀሳባቸውን በነጻነት በሚገልጹ ዜጎች ላይ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የተወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን፣ ከ125 በላይ የሚሆኑ የተቃውሞ ሰልፎች ተሳታፊዎችን፣ ጉዳዩን በአንክሮ ሲከታተሉ የቆዩ ግለሰቦችን፣ በተለያዩ ጊዜያት የመብት ጥሰት የተካሄደባቸውና ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ያካተተ ቃለ መጠይቅ አድርጓል።

“የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ በቀጥታ በመተኮስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ ገበሬዎችን እና ሌሎች የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎችን ገድለዋል።” በማለት የሂይውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ተናግረዋል። ሌፍኮው አያይዘውም “መንግስት ያለ አግባብ የታሰሩትን በአስቸኳይ መፍታት አለበት፣  ተአማኒነት ያለው እና ገለልተኛ የማጣራት ሂደት እንዲከናወን ድጋፍ ማድረግ አለበት፣ እንዲሁም ይህን ጥቃት የፈጸሙት የጸጥታ ሀይል አባላት ላደረሱት የመብት ጥሰት ተጠያቂ መሆን አለባቸው፡፡”

ሂዩማን ራይትስ ወች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ለወራት ያህል በኦሮሚያ ክልል  የተለያዩ አካባቢዎች በተካሄዱ ተቃውሞዎች ሰልፈኞችን ለመቆጣጠር ቀጥታ መተኮሱን እና  በእያንዳንዱ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ቢያንስ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የተቃውሞ ሰልፈኞችን መገደላቸውን አረጋግጧል። ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ሌሎች ድርጅቶች ከ300 በላይ የተገደሉ ሰዎችን ማንነት በስም ለይቷል እንዲሁም በተወሰኑት ጉዳይ ላይ  በፎቶ ለማረጋገጥ ችሏል።

እ.ኤ.አ. የህዳሩ ተቃውሞ የተቀሰቀሰው መንግስት የዋና ከተማውን የማዘጋጃ ቤት ድንበር በአደሲ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን መሰረት ለማስፋፋት ማቀዱን ተከትሎ በተፈጠረ አሳሳቢ ሁኔታ ነው፡፡  ተቃውሞ አድራጊዎቹ ማስተር ፕላኑ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ያፈናቅላል እንዲሁም በአካባቢው የእርሻ መሬት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፤ የሚጠቅመው ጥቂት የበላዮችን ብቻ ነው የሚል ስጋት ያደረባቸው ሲሆን የማፈናቀል ተግባሩ ባለፈው አስር ዓመት እየጨመረ የመጣ ጉዳይ ነው፡፡

እ.ኤ.አ. በታህሳስ ወር ተቃውሞው ሲስፋፋ መንግስት ተቃውሞውን ለማፈን የጦር ሀይሉን በመላው የኦሮሚያ ክልል ውስጥ አስፍሯል። የጸጥታ ሀይሎች ምንም አይነት ቅድመ ማስጠንቀቅያ ሳይሰጡ ወይም ጉዳት የማያስከትሉ የአድማ መበተኛ መሳሪያ ሳይጠቀሙ ወደ ሰልፈኖች በቀጥታ ተኩሰዋል። በዚህም አይነት ሁኔታ ከተገደሉት ሰልፈኞች መካከል አብዛኞቹ ተማሪዎችና እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

የፌደራል ፖሊስ እና የጦር ሰራዊት በጋራ በመሆን በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ ሙዚቀኞችን፣ የተቃዋሚ አባላትን፣ የጤና ባለሙያዎችን፣ እንዲሁም ለተቃውሞ ሰልፈኞቹ እርዳታ ያደረጉ ወይም በፍርሀት በመሸሽ ላይ ለነበሩ ተማሪዎች መደበቅያ ያዘጋጁ ሰዎችን በሙሉ አስረዋል። በርካታ ታሳሪዎች የተፈቱ ቢሆንም አሁንም ድረስ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ እስረኞች ምንም አይነት ክስ ሳይቀርብባቸው፣ ከህግ አማካሪዎች እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ፈጽሞ መገናኘት እንዳይችሉ ተደርገው ዛሬም ድረስ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ።

የአይን እማኞች የእስራቱን መጠንና ስፋት ‘ከዚህ በፊት ፈጽሞ ታይቶ የማይታወቅ’ ሲሉ ገልጸውታል። ነዋሪነቱ በወለጋ ዞን የሆነ ዮሴፍ የተባለ የ52 አመት ሰው “ሙሉ እድሜዬን እዚሁ ነው የኖርኩት። እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት የግፍ ድርጊት በህይወቴ አይቼ አላውቅም፡፡ በየቀኑ እስራት እና ግድያ በህዝባችን ላይ ይፈጸም የነበረ ሲሆን ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ቢያንስ አንድ ልጅ ታስሮ ነበር” ብሏል።

ከዚህ ቀደም ታስረው የነበሩ ግለሰቦች በእስር ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ ስቃይና የሰባዊ መብት ጥሰቶች እንደተካሄዱባቸው እንዲሁም ሴት ታሳሪዎች አስገድዶ መድፈር እና ጾታዊ ጥቃቶች ይፈጸምባቸው እንደነበር ለሂዩማን ራይት ወች ተናግረዋል። ጥቂቶች እግራቸው የፊጥኝ ታስሮ የቁልቁሊት በመዘቅዘቅ መደብደባቸውን የገለጹ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በኤሌክትሪክ እግራቸው ስር መነዘራቸውን ገልጸዋል፤ እንዲሁም በዘር ፍሬያቸው (ብልታቸው) ላይ ክብደት ያለው ነገር ታስሮባቸው እንዲሰቃዩ መደረጋቸውንም ተናግረዋል። በዩኒቨርስቲ ካምፓሶች ውስጥ ታማሪዎች ሲደበደቡ እንደነበር የሚያሳይ ቪዲዮም ታይቷል።

ከጅምላ እስራቱ ባሻገር የመንግስት ባለስልጣናት በጥቂት ግሰቦች ላይ ክስ በመመስረት ፍርድ ቤት አቅርበዋቸዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እና ጋዜጠኞች በአወአዛጋቢው የኢትዮጵያ ጸረ ሽብርተኝነት ህግ የተከሰሱ ሲሆን

አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ሰላማዊ ተቃውሞ ያደረጉ 20 ተማሪዎች በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ መሰረት ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በየትምህርት ቤቱ በመስፈራቸው እንዲሁም በርካታ መምህራንና ተማሪዎች በመታሰራቸውና ቀሪዎቹም ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ በፍርሀት በመዋጣቸው የተነሳ ተቃውሞው በተካሄደባቸው ብዙ ስፍራዎች ላይ የመማር ማስተማር ሂደቱ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። በአንዳንድ አካባቢዎችም ተቃውሞው እንዳይቀጥል በመስጋት ለስልጣን አካላት ትምህርት ቤቶችን ለሳምንታት ያህል እንዲዘጉ አድርጓል። በርካታ ተማሪዎች ለሂዩማን ራይት ወች እንደተናገሩት ወታደሮች በየትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሰፈሩ ከመሆኑም ባሻገር የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ለይተው ከመቆጣጠር አልፈው የመብት ጥሰት ሲያደርጉባቸው ነበር።

አንዳንድ ተአማኒነት ያላቸው ዘገባዎች እንደጠቀሱት በተቃውሞ ሰልፈኞቹም የተካሄዱ የወንጀል ድርጊቶች እንደነበሩ ተስተውሏል፤ ከእነዚህም መካከል የውጭ ሀገር ዜጎች ንበረቶች ወድመዋል፣ የመንግስት ህንጻዎች ተዘርፈዋል፣ እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ንብረቶች ወድመዋል። ይሁን እንጂ ሂዩማን ራይት ወች ባደረገው ማጣሪያ እ.ኤ.አ. ከህዳር ወር ጀምሮ በተካሄዱት ከ500 በላይ የተቃውሞ ሰልፎች አብዛኞቹ ፍጹም ሰላማዊ ነበሩ።

የኢትዮጵያ መንግስት በገለልተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማትና በመገናኛ ብዙሀን የጣለው ጽኑ እቀባ ምክኒያትችግሮቹ በሚታዩባቸው ስፍራዎች ላይ ስላለው ሁኔታ የሚወጡት መረጃዎች እጅግ አነስተኛ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የመገናኛ ብዙሀን ነጻነትን ለማፈን የሚያደርገውን ጥረት ጨምሯል። በዚህም ከመጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮ ፌስ ቡክንና ሌሎች ማህበራዊ ድረ ገጾችን ገድቧል። ከዚህም በተጨማሪ መቀመጫቸውን ከሀገር ውጪ ያደረጉና በሀገር ውስጥ የሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን አፍኗል።

በጥር ወር ላይ መንግስት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን ይፋ አድርጓል። ይሁን እንጂ በወቅቱ  መንግስት በወሰደው የሀይልና የግፍ እርምጃዎች ሳቢያ የተቃውሞው አድራጊዎቹ ብሶት ግንፍሎ ወጥቶ ነበር።

እንደ ሂዩማን ራይት ወች ጥናት ከሆነ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በተለያዩ ስፍራዎች ይካሄዱ የነበሩ ተቃውሞዎች እየተቀዛቀዙ  የነበረ ቢሆንም የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሚፈጽሙት አፈና ግን ቀጥሏል። ላለፉት ሰባት ወራት ያህል የታሰሩት በርካቶች አሁንም በእስር ላይ ያሉ ሲሆን ሌሎች በመቶ የሚቆጠሩት ደግሞ የት እንደደረሱ ለማወቅ አልተቻለም፤ ይህም በሀይል እንዲሰወሩ ሳይደረጉ አይቀርም የሚል ስጋት ፈጥሯል። መንግስት ስለቀረበበት በዚህ ሁሉ ውንጀላ ምንም አይነት ተአማኒነት ያለው የማጣራት ስራ አልሰራም። ወታደሮች አሁንም በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች እንደሰፈሩና በአካባቢውም ከፍተኛ ፍርሀት እንደነገሰ ነው። ተቃውሞ አድራጊዎቹ ምንም እንኳ በመጠኑ አነስተኛ ቢሆንም እ.ኤ.አ. በ2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ተነስቶ የነበረውን የተቃዎሞ ጥያቄ ነው ያስተጋቡት፣ እናም የመንግስት ምላሽ ለወደፊት ተቃውሞ የበለጠ እንዲባባስ ሊያደርግ እንደሚችል ሂማን ራይትስ ወች ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ጭካኔ የተሞላው የግፍ አያያዝን በተመከተ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ምክርቤትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግስታት እና መንግስታዊ ተቋማት ጠንካራና የተቀናጀ ምላሽ የሚጠይቅ ነው በማለት ሂዩማን ራይት ዎች አሳስቧል። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ድርጊቱን በማውገዝ ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ ያወጣና ይሄው መግለጫም ለአሜሪካ መንግስት የተገለጸ ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው የግፍ ድርጊት በአለማቀፍ ደረጃ በአብዛናው በዝምታ የታለፈ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክርቤት ይህን ከፍተኛ የመብት ጥሰት በአትኩሮት ሊያየው፣ ያለአግባብ ለእስር የተዳረጉት እንዲፈቱና አስቸኳይ ገለልተኛ የሆነ ማጣሪያ እንዲካሄድ ጥሪ ሊያደርግ ይገባል።

“የኢትዮጵያን መንግስት የሚደግፉ አብዛኛዎቹ የውጭ አጋር ተቋማት መንግስት በኦሮሚያ ክልል የወሰደውን አስከፊ አፈና በተመለከተ በዝምታ አልፈውታል፡፡” በማለት ሌፍኮው ተናግሯል። “የኢትዮጵያን ልማት የሚደግፉ ሀገራት በኢትዮጵያ በሁኒም መስኩ መሻሳሎች እንዲታዩ ጫና ማድረግ አለባቸው፤ በተለይም የንግግር ነጻነትና ለተጠቂዎች ፍትህ እንዲያገኙ መስራት ይጠበቅባቸዋል። ” ብለዋል። (ምንጭ፤ ሂዩማን ራይት ዎች ድረገጽ)

ሙሉ ዘገባውን በእንግሊዝኛ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

በአማርኛ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፤ የኦሮሚፋውን ለማግኘት ደግሞ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Kebe says

    June 17, 2016 02:44 am at 2:44 am

    Thank you golgul for making the document available to all

    Reply
  2. rirdih says

    June 18, 2016 12:34 pm at 12:34 pm

    ኦሮሞ ብቻ አደለም የተጎዳው እየተጨፈጨፈ ያለው እና እንዳይወልድ እየተደረገ ያለው አማራውሥ እባካችሁ አንድ ሆነን እንጩህ አንድነት ኃይል ነውና!!!!!!!

    Reply
  3. tesfai habte says

    June 24, 2016 04:01 pm at 4:01 pm

    ወያኔው ስልጣን በመጣበት ስዓት ኣንድ ፊልም ሰርቶ ለትይንት ኣሳይቶን ነበር። ”ንጋት” ይህ ፊልም ወያኔን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ ያካየደው ኢሰብኣዊ ተግባር ነበር። በገድል ተወረውረው የተገደለ ሰው፡ በሰው ኣንገድ ላይ ገመድ ኣጥልቆ ዛፍን ላይ በመስቀል፡ ብቢላዋ ኣንገቱን ቆርጦ ብዙ ሰው በምድር ላይ ጥሎ የዘገነነ ፊሊሙን ያየን ሰዓት ነበር። (እንደዛሬው ድኣሽ) isis ጭካኔ የተሞላ በደል በመፈጸሙ ለፍርድ መቅረብ ኣለበት። የወጋ እንጂ የተወጋ ጭካኔውን ኣይረሳውም። ያ ሁሉ የተፈጸመ ለኦሮሞ ነጻ ኣውጪ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለማራራቅ ሆን ብሎ የተደረገ ነብር። ለሰው ለማመንና፡ የፓርቲው ተፎካካሪ እንዳይኖር በማድረግ የተሰራ ፊሊም ነበር። ያ ሁሉ የክፋት ሴራ ወያነ ራሱ እንደሰራ ህዝብ ስለኣወቀ፡ ለወያኔ ተቃውሞ ኣሰማ። ወያኔ እና isis ለዶላር የሚሰሩ የኣንድ ሳንቲም ሁለት ምስል ናቸው። ይህ ሁሉ ዛሬ ብሌሎች የኢትዮጵያ ዜጎች እየተደረገ ነው። ወጣቶጭ ለምን ኣትነሱም? ይእንስሳት ባህሪይ ያለው፡ የጫካን ህግ የሚከተል ኣጭበርባሪ፡ የዶላር ቕጥረኛ ብሃይል እንጂ በሰላማዊ መንገን ኣያምንም። ሳም ታይም ሃይል (ውግያ) ሰላምን ያመጣል!!!!!!

    Reply

Leave a Reply to tesfai habte Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule