• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል!

September 6, 2013 09:48 am by Editor 1 Comment

ያለፈው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠርቶ በነበረው የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በህወሃት/ኢህአዴግ የተወሰደውን ጽንፈኛ፣ አክራሪና አጸያፊ የውንብድና ተግባር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ይኮንናል፤ ያወግዛል፡፡ ፓርቲው ሰልፉን ለማካሄድ ከሁለት ወራት በፊት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ቅዳሜ ነሐሴ 25፤2013 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የፓርቲውን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሃት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው፡፡

በዕለቱ እንደሆነው የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪ ፖሊሶች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከመውረራቸው በፊት ኤሌክትሪክ መስመሩን ቆርጠዋል፡፡ በቀጣዩም ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት እያደረጉ የነበሩትን አመራሮችና ፈቃደኛ ሠራተኞችን ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ከደበደቡና ካሰቃዩ በኋላ ለሰዓታት አስረዋቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ከተፈቱ በኋላ ለእሁዱ ስብሰባ ተመልሰው ዝግጅት እንዳያደርጉ የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪዎች የፓርቲዉን ጽ/ቤት እስከ እሁድ ድረስ በመቆጣጠር ኮምፒውተሮችን፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ ሠንደቅዓላማዎችን፣ መፈክሮችን፣ … በማውደም፤ የሚፈልጉት በመውሰድ ሰልፉ እንዳይካሄድ አድርገዋል፡፡ ይህንን ተግባር የሚመሰክር ከበቂ በላይ የፎቶግራፍ፣ የሰው፣ … ማስረጃ ቢኖርም ህወሃት/ኢህአዴግ ሁሉንም በመካድ ለዓለምአቀፍ ሚዲያ አንዳች ነገር እንዳልተደረገ semayawi flagsበመናገር የተለመደውን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ደግሟል፡፡

ጥያቄው ግን ሰላማዊ ሰልፍ እናድርግ ያሉ ቁርጠኛ ወጣቶች ያነሱት ይህ የመብት ጥያቄ ለምን ህወሃት/ኢህአዴግን ለምን አሸበረው? ለምንስ እንዲህ ያለውን ራሱን የሚያጋልጥ ተግባር እንዲፈጽም አደረገው? መልሱ ህወሃት/ኢህአዴግ ልምድ በሌለውና በማያውቅበት የሰላማዊ ትግል ጠንክረው ስለመጡበት ብቻ ነው! ለዚህ ደግሞ ለሁለት ዓመታት ያህል በጽናት መብታቸውን ለማስከበር የሚታገሉት ሙስሊም ወገኖቻችንና ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ የተጀመረው ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡

ህወሃት/ኢህዴግ ባስቀመጠው ትዕዛዝ መሠረት የሰማያዊ ፓርቲ ለእሁዱ ሰልፍ ከሁለት ወር በፊት ደብዳቤ አስገብቶ ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ባለፈው ሰሞን ህወሃት/ኢህአዴግ ባቀናበረው የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ “አሸባሪነትንና አክራሪነትን” ለማውገዝ ሕዝቡ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አድርጎ ነበር፡፡ በጥሪ ብቻ ያላበቃው ዘመቻ የከተማው ነዋሪ በግድ፣ በማስፈራራት፣ በጉቦ፣ … ሰልፍ እንዲወጣ የተቀናበረም ነበር፡፡ ይህ ሰልፍ በሚካሄድበት ቀን ታቅዶ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ትዕይንተሕዝብ ካልተጨናገፈ በስተቀር ህወሃት/ኢህአዴግ በጠራው በራሱ ሰልፍ ላይ የሚደርስበት ክስረት መራራ እንደሚሆን ግልጽ ነበር፡፡

ከሰልፉ ጥሪ በፊት በተካሄደው ጉባዔ ወቅት “በኢትዮጵያ ህዳሴ የሃይማኖቶች ተስማምቶ መኖር” አስፈላጊነት የተሰበከ ሲሆን ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ በወቅቱ “የሃይማኖት አክራሪነትን” እንዲያጋልጡ ተሰብሳቢዎቹን በመጠየቅ መንግሥት በዚህ ዙሪያ የሚወስደውን እርምጃ አንደሚቀጥልበት አስጠንቅቀው ነበር፡፡ ቅዳሜ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የተፈጸመው ተግባር አሸባሪና አክራሪ ራሱ ህወሃት/ኢህአዴግ መሆኑን ያጋለጠበት ነው፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉዳይ ያገባኛል በማለት ጉባዔ የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ “በሃይማኖታችን ጣልቃ አትግባ፤ የራሳችንን መሪዎች እንምረጥ፣ መብታችን ይከበር” በማለት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል እየጮሁ ያሉትን ሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ መመለስ ያልፈለገ ወይም ያልቻለ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን የራሱን ካድሬዎች በሃይማኖት መሪነት ሽፋን በመሾምና ሙስሊሙን ኅብረተሰብ በመከፋፈል የአፈናና የመብት ረገጣ ተግባሩን ቀጥሎበታል፡፡ ይህ የህወሃት/ኢህአዴግ አሠራር በሌሎች ሃይማኖቶችም የቀጠለ ለመሆኑ በሃይማኖት ተቋማት ስም የተጠራው ጉባዔና ሰልፍ በቂ ምስክር ነው፡፡

ህወሃት ገና ከጥንስሱ የሃይማኖት ጉዳይ የማይስበው፤ በበረሃው ቆይታ በተደጋጋሚ በአሸባሪነት ተግባር ላይ ለመሠማራቱ የተመሰከረለት መሆኑ፤ ራሱን በፈጣሪ የለሽ የሌኒኒስታዊ ፍልስፍና ያጠመቀ መሆኑ ራሱ የመሰከረውና በግልጽ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ አሁን “በኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉዳይ ያገባኛል፤ የሃይማኖት አክራሪነትን እታገላለሁ” ማለቱ ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ የአህያ ቁርበት አንጥፉልኝ ያለው ዓይነት ነው፡፡

በአመሠራረቱ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክለው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ካሉት “የድምጻችን ይሰማ” ሙስሊም ወገኖች፣ የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ፣ የሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች ወገኖች ጋር ያለውን ኅብረት ይገልጻል፡፡ የጋራ ንቅናቄው ባለው ዓለምአቀፋዊ ዕውቅናና ግንኙነት በመጠቀምም የህወሃት/ኢህአዴግን ቋት ለሚሞሉት ለለጋሽ አገራት፣ ለሕግ ተቋማት፣ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ለሚዲያ ተቋማት፣ ወዘተ በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የመብት ረገጣ ያሳውቃል፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ እስካሁን የፈጸመውን የሽብር ተግባርና ወደፊት ለሚያደርሰው ማንኛውም በደል በቀጥታ ተጠያቂ እንዲሆን መረጃው በሕግ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡

በአገራችን በ1997 የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ በሟቹ ጠ/ሚ/ር ቀጥተኛ ትዕዛዝ ህወሃት/ኢህአዴግ የፈጸመው የ193 ዜጎች ግድያ፣ የፖለቲካ መሪዎች እስር፣ አፈና፣ የመብት ረገጣ፣ … ያስከተለውን ፍርሃት ለመጀመሪያ ጊዜ በመግፈፍ የፖለቲካ ትዕይንተሕዝብ ያደረገው የሰማያዊ ፓርቲ ነው፡፡ “ድምጻችን ይሰማ” የሚያደርጉት በትክክለኛ የሰላማዊ ትግል መርህ ላይ የተመሠረተው እልህ አስጨራሽና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ትግል እንዳለ ሆኖ የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴም ከዚህ ጋር አብሮ ተጠቃሽ ነው፡፡semayawi party

አርቆአሳቢና ራሳቸውን በሰላማዊ ትግል ዲሲፒሊን ያነጹ ወጣቶች ተሰባስበው በሰማያዊ ፓርቲ ሥር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሰላማዊ ትግል በትክክለኛው መንገድ ከተከናወነ በኢትዮጵያ እንደሚሠራ በተግባር ያስመሰከረ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን “ሰላማዊ ትግል ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አንጻር አይሠራም” የሚለውን ስሜታዊ አስተሳሰብ ከሥሩ የመታ ትግል በመሆኑ የጋራ ንቅናቄው ለሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችንና አመራሮች ከፍ ያለውን አድናቆት ይሰጣል፡፡ በተለይም በሰላማዊ ትግል መስመር ስማቸው በዓለም የሚጠራው መሃትማ ጋንዲ፣ ዶ/ር ኪንግ፣ ማንዴላ፣ … በወጣትነታቸው ይህንን ዓይነቱን የትግል መስመር ከመምረጣቸው አኳያ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች የተጠና እንቅስቃሴና የዓላማ ጽናት ሌሎችም የእናንተን መስመር እንዲከተሉ የሚያደፋፍር እንጂ በምንም ዓይነት መልኩ የያዛችሁትን እርግጠኛ አቋም እንድትመረምሩ ሊያደርጋችሁ እንደማይገባ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በአጽዕኖት ያስታውቃል፡፡ ለመስከረም 12፤ 2006 ዓ.ም. የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም ሰላም ወዳድ ወገኖች ድጋፋቸውን እንዲሰጡት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ከዚህ በፊት በሊቢያ በቅርቡ በግብጽ አሁን ደግሞ በሶሪያ ሕዝብን እያስተላለቀና እጅግ ደም እያፋሰሰ ያለውን ዕልቂት ተመልክታችሁ አገራችሁን በምንም ዓይነት መልኩ ወደ ደም መፋሰስና ዕልቂት እንዳትገባ የሚደርግ ሰላማዊ የትግል መስመር መምረጣችሁ የጋራ ንቅናቄው ምስክርነት የሚሰጠው ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ከየትኛውም የአመጽና የሽብር ተግባር ጋር በግድ በማያያዝ ሊኮንናችሁ፣ ሊወነጅላችሁ፣ ወዘተ ቢሞክርና ወደፊትም ይህንኑ ለማድረግ ቢያስብ እስካሁን የፈጸማችሁት ሰላማዊ ሥራችሁና የትግል ስትራቴጂያችሁ በገሃድ የሚመሰክረው ከመሆኑ ባሻገር የጋራ ንቅናቄው ዓለም ሁሉ ይህንን ምስክርነት እንዲያውቅ በማስረጃነት የሚያስመዘግበው ነው፡፡

ትክክለኛውን የትግል መርሆ የተከተለ ሰላማዊ ትግል ከዚህ በፊት የሠራና አሁንም ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ መተግበር እንደሚችል ጠንቅቆ ያወቀው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ በሰላማዊ የትግል መስመር የሚነሱትን ሁሉ ገና በእንጭጩ ሲቀጭ ቆይቷል፡፡ ተስፋ በማስቆረጥ፣ በመከፋፈል፣ በማሰር፣ በማሰቃየት፣ በመግደል፣ ወዘተ የፓርቲ አመራሮችን ያስወግዳል፤ ትግሉ ወደ ተራው አባል ከመዝለቁና አባሉ በራሱ አመራርና የትግሉ ባለቤት መሆን ከመቻሉ በፊት ይበታትናል፡፡ ይህንን የሚያደርገው ከባህርይውና ከለመደው የደም ማፍሰስ አገዛዝና ትግል ውጪ ያለ አካሄድ ሥልጣኑን ስለሚያናጋውና መጨረሻውን ስለሚያቃርበው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የትግል መስመር ተጠናክሮ ወደ ሙሉ ህዝባዊ እንቅስቃሴና እምቢተኝነት ከተቀየረ ህወሃት/ኢህአዴግ መመከት የማይችልበት ደረጃ ስለሚደርስ ህልውናው ያከትማል፡፡ “ሥልጣን ወይም ሞት” በማለት የፖሊስና የመከላከያ ኃይሉን እስካፍንጫው በማስታጠቅ ዕድሜውን እየገፋ ያለው ህወሃት/ኢህአዴግን ወደ ሙሉ ህዝባዊነት የተቀየረ ሰላማዊ ትግልን መቆጣጠርም ሆነ ማጨናገፍ አይችልም፡፡ ለዚህ ነው ሰላማዊ ትግል በህዝቡ ዘንድ በሙላት ሳይሰርጽና መርሆዎቹ ተግባራዊ ሳይሆኑና ገና በጅምሩ ማጥፋት፣ ማውደም፣ ማሰቃየት፣ ወዘተ የሚፈልገው፡፡ በወጣቶች የተገነባው የሰማያዊ ፓርቲ ላይ እየረደሰ ያለው ሁኔታ ይህንኑ የሚያመለክት ነው፡፡

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ፍትሕ መስፈን የሚታገል እንደመሆኑ በሰላማዊ የትግል መስመር ላይ ያሉ ድርጅቶችንም ሆነ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ይደግፋል፤ ያበተረታታል፡፡ በሰላማዊ የትግል መስመር የሚመጣ ለውጥ በአገራችን ያለማቋረጥ ሲፈስ የቆየውን የደም ጎርፍ እንዲቀጥል፤ ቂምና በቀል እንዲስፋፋ፤ መጪውን ትውልድ በፍርሃትና በማያቋርጥ የደም መፋሰስ አዙሪት ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግ ሳይሆን፤ በፍትሕ ላይ የተመሠረተ ዕርቅ እንዲሰፍን፤ የአንዱን ነጻነት ብቻ የሚያስከብር ሳይሆን “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚል የጠነከረ ምሶሶ ላይ የሚገነባ ነው፡፡ በአገራችን ለዓመታት የተረጨውንና እስከ ቤተአምልኮዎች የዘለቀውን የዘር ፖለቲካና የዘረኝነት አመለካከት ማምከን የምንችለው በሌላ መንገድ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ” እንስጥ የሚለውን ታላቅ መርህ ከፍ ስናደርግ እንደሆነ የጋራ ንቅናቄው ያምናል፡፡ ይህንን አመለካከት ከሚጋሩ ሁሉ ጋር በጋር ይሠራል፤ ይንቀሳቀሳል፡፡

በአገራችን ላይ እስካሁን በበሽታ፣ በረሃብ፣ በድህነት፣ በእርስበርስ ጦርነት፣ … ብዙ ደም ፈስሷል፡፡ ከዚህ በኋላ የምንሄድበት መንገድ ይህንኑ እንዲቀጥል የሚያደርግ በጭራሽ ሊሆን አይገባውም፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግም ይህንኑ ሊያስተውልና “በለመድኩት የአፈና አካሄድ እቀጥላለሁ” ከሚለው ዕብሪተኛ አስተሳሰቡ ሊመለስ ይገባዋል፡፡ በውስጡ ያሉት የትግራይ ተወላጆችም ይሁኑ ሌሎች የአገራቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው ኢትዮጵያውያን በግልጽ የሚወጡበትና የህወሃት/ኢህአዴግ አሠራርን በግልጽ በመተቸት ሁላችንም ወደ ዕርቅ የምንመጣበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ሥርዓቱ “ከእንጥሉ መበስበሱን” ሟቹ ጠ/ሚ/ር የመሰከሩለት በመሆኑ ምንም የሚደበቅ ነገር ስለሌለ ጉዳዩን ይፋ ለማውጣት የሚያስፈራ ነገር የለም፡፡ የጋራ ንቅናቄው ይህንን የጥሪ ደወል እስካሁን ሲያሰማ ቆይቷል፤ አሁንም ይህንኑ ይደግማል፡፡ ሆኖም ይህ በህወሃት/ኢህአዴግ ውስጥ ላሉትና ለመሰል ድቃይ ድርጅቶች የምንሰጠው “ከሥርዓቱ ተለዩ” የሚለው ጥሪ የሚያቆምበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ምላሽ የመስጫው ጊዜ ነገ ወይም አንድ ቀን ሳይሆን ዛሬ፤ አሁን ነው፡፡ የአፈናና የጭቆና ሥርዓት ጸንቶ አይቆይም፡፡ እንኳን እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ያለው ዘረኝነትን መመሪያው፤ የአገር ውርደት ክብሩ የሆነ አገዛዝ ይቅርና በህዝባዊነታቸውና ብሔረተኝነታቸው የተመሰከረላቸው አገዛዞችም ጨቋኝ በመሆናቸው ብቻ እንደማይነሱ ሆነው ወድመዋል፤ ፈርሰዋል፡፡

ፈጣሪ ሁላችንንም የማስተዋልና ትክክለኛውን መንገድ የመምረጥ ጥበብ ይስጠን፡፡ የልቦና ዓይናችንን ከፍቶ የዘረኝነትን፣ የጥፋትን፣ የብቀላን፣ የውድመትን አስከፊነት እንድናስተውልና የሰላምንና የዕርቅን መንገድ እንድንመርጥ ይርዳን፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የመረጣችሁትን ሰላማዊ መንገድ በምንም አትቀይሩት፤ ከእርሱ የሚበልጥም ሆነ የሚሻል መንገድ የለምና!! ሌሎች የእናንተን ዓይነት መንገድ አስቀድመው ከጀመሩ ጋር በኅብረትና በመቻቻል ሥሩ፡፡

ለውጥ በአገራችን ይመጣል! ይህ የማይቀር ሃቅ ነው! ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች፤ ነጻ የምትወጣው ግን በሌላ ነጻ አውጪ ሳይሆን “ነጻ አውጪ ነኝ” የሚለውን ጭምር ነጻ በሚያወጣው እውነትና ፍትህ ነው፡፡

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

smne banner1

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. TEWBEL says

    September 6, 2013 10:19 pm at 10:19 pm

    መልካም ነዉ፤ ጎብዙ ጠንክሩ፤ ህብረት ካለ የማይሽነፍ ሃይል የለም፤ ዋናዉ ጠላት ፍርሃት ስለሆነ እሱን ከመንፈሳችሁ አዉጡ፤
    የወያኔዎች የኛ ደካማነት ነዉ፤
    የነገ የኢትዮጵያ ባለቤቶች እናንተ ስለሆናችሁ ላግሬ ለቤቴ ብላችሁ የማያቋርጥ ትግል ማድረግ አለባችሁ፤
    ያባቶቻችሁን ጋሻ ማንሳት ግዴታችሁ ነዉ፤
    መልካምና የድል ዓምት ይሁንልን እግዚያብሄር አይለየንም።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule