• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፉን ቀን ወደ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም አስተላለፈ!!

September 6, 2013 05:41 am by Editor Leave a Comment

ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!!!

ሰማያዊ ፓርቲ ለነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጠርቶት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂ ኋይሎች ሕገ-አራዊት እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ፓርቲያችን ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ጳጉሜ 2 ቀን 2005ዓ.ም ሠልፉ በድጋሚ እንደሚካሔድ አስታውቋል፡፡ ሠልፉ የተሳካና ሰላማዊ እንዲሆን በፓርቲ በኩል ልዩ ልዩ ተግባራት ከመከናወናቸው ጎን ለጎን አስፈላጊው የጸጥታ ጥበቃና የአስተዳደር ድጋፍ እንዲሰጠን በህጉ መሰረትም ሠልፉ እውቅና እንዲያገኝ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሰወቂያ ክፍል ነሐሴ 27 ቀን 2005ዓ.ም ደብዳቤ ለማስገባት በአካል ተገኝተን ጠይቀናል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ክፍል ደብዳቢያችንን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡semayawi press release

በፓርቲው በኩል በሁኔታው ተስፋ ባለመቁረጥ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል የማሳወቂያ ደብዳቤውን ከላይ በተጠቀሰው ቀን የላክን ሲሆን ውጤቱ ግን አሁንም በፖስታ ቤት በኩል የተላከውን ደብዳቤ በእንቢተኝነት አለመቀበል ሆኗል፡፡

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በአስተዳደሩ ፅ/ቤት በመገኘት ከተለያዩ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር እረጅም ሰዓት የወሰደ ከቢሮ ቢሮ መንከራተት የተሞላበት ደጅ ጥናት ካደረጉ በኋላ በመጨረሻም በከንጺባ ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ም/ኃላፊ ጋር ለመነጋገር ተችሏል፡፡

በዚህም ውይይት የጳጉሜ አምስቱ ቀናት በከተማው አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ እድል ለመፍጠርና እራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ በየዓመቱ አስቀድሞ በከተማው ማዕዘናት ያሉ ቦታዎች ለዚህ አገልግሎት ስለሚያዙ በነዚህ ቀናት የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ የማይችሉ መሆኑን አበክረው ገልጸውልናል፡፡ ፓርቲው በከንቲባ ጽ/ቤቱ የቀረበውን ምክንያት ከመረመረ በኋላ የበዓሉ ዋዜማና የዘመን መለወጫ በዓል ካካፋ በኋላ ባሉት ቀናት ሰልፉን ለማድረግ በመወሰን ለጳጉሜ 2 ቀን 2005 ዓም ጠርቶት የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ የዚህን ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ክፍል በማቅረብ የሰልፉ ማሳወቂያ ደብዳቤ ቀሪ ላይ በማስፈረም ገቢ አድርጓል፡፡

በመሆኑም ከለይ በተጠቀሰው ምክንያት ሠልፉ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006ዓ.ም መተላለፉን እየገለጽን ከዚህ በፊት የጠራናቸው የተቃውሞ ሰልፎች የተሳኩ እንዲሆኑ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪክ ማሕበራትና በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ላደረጋችሁት ድጋፍ ፓርቲያችን ምስጋናውን እያቀረበ፤ አሁንም ቀጣዩ ሠልፍ በታሰበለት ዓላማ መሠረት የተሳካ እንዲሆን የተለመደ ድጋፋችሁን እንድታደርጉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ምንግዜም የተባበረ የሕዝብ ትግል ያሸንፋል!!!
ነሐሴ 30 ቀን 2005ዓ.ም
አዲስ አበባ

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule