በኢትዮጵያ ባሏቸው ኢንቨስትመንቶች መልከ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው የሚነገርላቸው ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን የካሩቱሪን የእርሻ መሬት ለመግዛት ከድርድር ላይ ናቸው ተባለ። ድርድሩ በስምምነት ከተቋጨ የሳዑዲን የምግብ አቅርቦት ለመሸፈን የሚንቀሳቀሱት “ባለሃብት” በጋምቤላ ብቻ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ድንግል መሬት ባለቤት ይሆናሉ። በድርድሩ መሰረት እስከዛሬ ከወሰዱት በተጨማሪ ብድርም ከንግድ ባንክ ያገኙበታል።
የሳዑዲን የምግብ ኮታ ለመሸፈን ታስቦ እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሳዑዲ ስታር አግሮ ኢንዱስትሪ በ2001 ዓ ም 10ሺህ ሄክታር መሬት ተረክቦ በጋምቤላ ስራ ሲጀምር ተጨማሪ 500 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት እንደነበር በወቅቱ የተለያዩ መገናኛዎች ዘግበው ነበር።
ሳዑዲ ስታር የስራ አቅሙ ተገምግሞ መሬት እንደሚጨመርለት ቃል ቢገባለትም የወሰደውን 10 ሺህ ሔክታር በቅጡ አልተጠቀመም በሚል የግብርና ኢንቨስትመንት ሃላፊዎች ተጨማሪ መሬት ለመስጠት ሲያቅማሙ ቆይተው ነበር። ሆኖም ግን በአቋማቸው መዝለቅ ያልቻሉት ሃላፊዎች ለሳዑዲ ስታር ተጨማሪ 120 ሺህ ሔክታር መሬት ፈቅደዋል። በቅርቡ ከወራት በፊት በተካሄደ ግምገማ አነስተኛ የስራ ትጋት ውጤት ያስመሰዘገበው ሳዑዲ ስታር አዲስ ጥያቄ ማቅረቡን በጋምቤላ የሚኖሩ የድርጅቱ ባልደረቦች ለጎልጉል ገልጸዋል። ስማቸውን መናገር ያልፈለጉ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊም በሰራተኞቹ የተጠቆመውን ዜና አጠናክረው አምነዋል።
በዚሁ መሰረት ንግድ ባንክ 62 ሚሊዮን ብር እዳ እንዳለበት፣ እዳውም በገባው ውል መሰረት እንዳልከፈለ፣ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም አለመሰካቱን፣ በዚህም የተነሳ ንብረት ለመውረስ መመሪያ መተላለፉንና ጉዳዩ ወደ ህግ መመራቱ ይፋ የሆነበትን ካሩቱሪ በተረከበው ማሳ ላይ ያስቀመጠው ንብረት ካለበት የሊዝ ዕዳ፣ የተለያዩ ክፍያዎችና የክልሉ ዓመታዊ ክፍያዎች ጋር ተዳምሮ እዳውን ይሸፍናል ተብሎ እንደማይገመት ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ።
በክልሉ ኢህአዴግ በጠመንጃ ሃይል እየተተገበረ ያለው የመሬት ንጥቂያ ጉዳዩን በውል የሚያውቁ ዜጎችን፣ እንዲሁም የክልሉን ነዋሪዎች ቁጭት ላይ የጣለ መሆኑ “ባለሀብቶች” ተብለው በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩትን በሙሉ እረፍት እንደማይሰማቸው የሚጠቁሙት የጎልጉል ምንጮች “ካራቶሪን በሳንቲም ሂሳብ ተቸብችቦለት ከባንክ ብድር ጋር የተረከበውን መሬት መልሶ ለመውሰድ ከፍተኛ ኪሳራ አለ። ኪሳራው የአገርና በተለይም ለዚህ ፋይዳ ለሌለው ኢንቨስትመንት ንብረቱንና ቀዬውን በጠመንጃ የተነጠቀው የክልሉ ሰላማዊ ህዝብ ነው” በማለት ቁጭታቸውን ይገልጻሉ።
“በአካባቢው ሕዝብ ተቀባይነት ያላገኘ ኢንቨስትመንት፣ በተለይም ሰፋፊ እርሻዎች ሁሌም አደጋ ላይ ናቸው” በማለት አሁንም ኢህአዴግና ባለህብቶች ከቀድሞው ጥፋታቸው እንዲማሩ የሚመክሩ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት “ካራቱሪ ከቀረጥ ነጻ ሲነግድና የተፈጥሮ ደን ሲያወድም ቆይቶ በእዳ ፋይሉ ሲዘጋ መሬቱን ለሳዑዲ የምግብ ዋስትና እንዲውል እየተደረገ ያለው ሩጫ ዳግም ስህተት እንዳይሆን” ሲሉ ይመክራሉ።
3.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማዘጋጀት የአገሪቱን ምርት 39 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ለማሳደግ አቅዶ እንደነበር የሚገልጸው ኢህአዴግ ባለበት እየረገጠ እንደሆነ ማስረጃ በማጣቀስ የሚተቹት ብዙዎች ናቸው። በተለይ በጋምቤላና በቤኒሻንጉል ክልል ያለውን ድንግል መሬት ከነዋሪዎቹ ጋር በመስማማት ለአገሪቱ ሕዝብ የምግብ ዋስትና ሊያውለው እንደሚገባ የግብርና ባለሙያዎች በየጊዜው የሚወተውቱት ጉዳይ ነው።
የጎልጉል ምንጮች አጠንክረው እንደሚናገሩት ካሩቱሪ የውጪ አበዳሪዎቹና የአክሲዮን ደንበኞቹ ስለከዱት ከጋምቤላ ለቅቆ ይወጣል። ካራቱሪ ቀደም ሲል 300 ሺህ ካሬ ሄክታር መሬት የነበረውና በሂደት ተቀንሶበት 100 ሺህ ሔክታር እንደቀረው፣ ከዚሁ ላይ ማልማት የቻለው አስር በመቶ ብቻ እንደሆነ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
በለው! says
” በአንድ ድሃ ሀገር ካድሬው ኢኮኖሚውን ሲዘውረው ድህነት ይፈተላል እንጂ የሀብት ልቃቂት አይወጣውም በለው!።
“ዓለም የሚቀዝፍበት ከሰሌንና ከገሳ የተሠራ ጀልባ “የነፃ ገበያ”(የፈለከውን አምርተህ፣ በፈለከው ዋጋ፣ እፈለከው ሀገር የመሸጥ)..ስንት ተከፍሎበታል?
ግሎባላይዜሽን፡- “አለም አንድ መንደር ሆነች!” እንኳን ዓለምና ህዝቦቿ የአሜሪካ ቆሻሻ ገንዳና የኢትዮጵያ የቆሻሻ ገንዳ አንድ ናቸውን?
(ሀ) ጉልቤ-አይዜሽን(በስው ሀገር ሃያል መሆን) የአንድን ሀገር መውረር፦ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በዳርድንበር ሉዓላዊነትን ለመስበር ወረርሽኝ ማድረግና አንድን ሕዝብ ማፈናቀል፣ ማሰደድ፣ እራሱንም፣ ልጆቹንም ፣መሬቱንም፣ ዕምነትና ባሕሉን እንዲተው እንዲበረዝ እንዲከለስ ብሎም ጨርሶ እንዲጠፋ ማዳቀል የሀገርን ዳር ድንበር እና የሀገርን ጥሬ ሀብት በቅድሚያ ለጎረቤት ሀገር መስጠት ገዢውን ፓርቲ ከውጭ ተቀናቃኝ እንዲጠብቁ መገበሪያ የምርት ውጤትና መብራት በገፍ በማቅረብ በመሳሪያ በወታደር መክበብ (…)
(ለ) ግልቤ-አይዜሽን (መግለብ) የሚያስተሳስሩ እሴቶቹን መበተን የሀገርን ውስጠ ሚስጥር ከሕዝቡ በበለጠ መመራመር ባሕልና አብሮ መኖርን ማናናቅ በእንዳንዱ ዘርፍ ተሳታፊ ሆኖ ያለውን ሥርዓት በማሞካሸት ህዝብን በሥነልቦና ጫና ማዳከምና ተገዢ ማድረግ፣ የትምህርት፣ ጤና፣ የሥራ ዕድልን፣ ለሥርዓቱ ደጋፊዎች በማመቻቸውት ሌላውን እያቁለጨለጩ የበይ ተመልካች ወይንም ተንበርካኪ ሁለተኛ ዜጋ ለማድረግ ማሕበራዊ ትስስሩን በልማት መለክ ማፍረስ (ዕድር፣ዕቁብ፣ጋብቻ፣መተዛዘን ፣አብሮ መብላት፣የቀብር ቦታን፣የቤት ይዞታ ውረስን መግታት፣ የሙታንን ሀውልት የታሪክ መዘክሮችን ማቃጥል መሸጥ መለውጥ (…)ይሆናል። በሀይማኖት ነፃነት ሥም የፓርቲ ደጋፎዎችን በመከፋፈል ተቀናቃኞችን የብጥብጥ እስትራቴጂ መቀየስ ናቸው።
*ዘመነኛው ሀገር በቀል ባለሀብት ዶ/ር ሼክ አላህሙዲን ለህወአት ባለሥልጣናት የውጭ ባንክ የተከሉና ከድሃ ሀገር ባንክ ገንዘብ እየተበደሩ ሀገሪቱን የሚያዘውሩት ለቀድሞ ታጋይ ወታደሮች አሁን በኪራይ ሰብሳቢነት በተሰማሩበት የጡረታ ገቢ የውጭ ምንዛሪን የሚያቀባብሉት ስንቱን ድሃ ኢንቨስተር አነጣጥረው እየገደሉ እንደሆነ ማወቅ ቀላል ነው። በጋምቤላ ክልል ከሚኖሩ ድሃዎች የተገኘውን ቃል በጎልጉል የድረገፅ ጋዜጣ እንዲህ አስነብቧል “የዘራሁትን ሳላነሳ በዶዘር ማሳዬን ጠረጉት፣ በዶዘር እርሻዬ ውስጥ ገብተው አረሱት፣ መሬቴን ለምን ትወስዳላችሁ? የት ልትወስዱኝ ነው? ያሸተውን በቆሎዬን መነጠሩት። ምን ላደርግ እችላለሁ። መሳሪያ የያዙ ወታደሮች ከበውኛል፣ ጠዋት ስነሳ ማሳዬ ባዶ ሆኖ አገኘሁት … ” የአካባቢው ነዋሪ “ሰላማዊ ህዝብ፣ በቅጡ የሚለብሰው እንኳን የሌለውን ህዝብ፣ አሮጊቶችን፣ አዛውንቶችንና ህጻናትን ሲገድሉና ሲያሰቃዩ የቆዩት ለዚህ ነው? ለዚህ ኢንቨስትመንት ነው ያ ሁሉ የተፈጥሮ ደን ወድሞ ከሰል እንዲሁን የተደረገው? ገንዘብ ሳይሆን የከሰል ጆንያ ይዘው ክልሉን እንዲቀራመቱ የሚፈቅዱት ክፍሎች ስለጊዜና ስለዘመን ለምን አያስቡም?” ሲል ይጠይቃሉ። በማያያዝም “፸ ከመቶ የሚሆኑት ባለሃብቶች የትግራይ ሰዎች መሆናቸውን እናውቃለን።
እንግዲህ ብሔር ብሔረሰብ በቋንቋህ ብቻ ተናገር ውጤቱ ይህ ነው። ለራስህ መቆም አትችልም ከሌላው ጋር አብሮ ለመቆምም እነታግባባ ወየንም እነድትፈራራ በቋንቋ አትግባባም ሥልጣንና ብር መሳሪያ አለው ቡድን ብቻ እነደፈለገ መኖርም ማድረግ መናገርም መፈፀምም ይችላል።”በዚህ ክልል አነድ መሁር አንድ የተጠየቁትን የመለሱት መልስ ድንቅ ነበር። “ባለፈው ሥርዓት መብታችሁ ተነፍጎ ነበር አሁን ፌደራሊዝም ነፃነትና እኩልነት አጎናፅፋችኋል..ድሮ ሙዚቃ እንኳን እንዳትጫወቱ ማይክርፎን አይሰጣችሁም ድምፅ መጉሊያውን ድማፃችሁ ይሰብረዋል ተብሎ ነበር ይባላል። ስለዚህ ምን ይላሉ፡፤ ጠያቂው ነፍሱን ይማር !ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የኢሳት ጋዜጠኛ ነበር። ግለሰቡ ሲመልሱ “ይህ ቀልድና አሁን የሚንቁን ፈጠራ ነው። ዛሬ ነው እኩልነት፣ ተሰሚነት፣ ባለሀብትነትና ማንነታችን የተገፈፈው። ለመሆኑ እኛ ድምፅ ማጉሊያ የተከለከልነው በዚያን ግዜ መንግስት ስንት ድምፅ ማጉሊያ ነበረው? በማለት ቀልድን በቁም ነገር መልሰዋል። ለመሆኑ ጡረተኛው የህወአት ታጋይ ሁሉ ይህንን ህንፃ ለማከራት ገንዘብ ከየት አገኘ? በእርግጥ መከላከያው በፌደራሉ ቁጥጥር ውር ነው ወይስ እራሱን የቻለ ተቋም ሆኗል? ለመሆኑ መነግስት ተበድሮና ለምኖ ይህ ሁሉ ሙስና ሲፈፀም ለምን የኢኮኖሚ ችግር አይኖርበትም? በእርግጥ በተከታታይ ፲፩ ነጥብ ለ፰ዓመት አድጎ የግብርና ምርት ሳይኖር እንዱስትሪው ምርታማ ሆነ ከቻይና ተሸምቶ ሀገር ውስጥ መንገድ ዳር ተቸርችሮ ነው? በፍፁም አደለም ከዔኩ ጥምጥም የተጠቀለሉ ብዙ ጥቃቅን ፀጉር ሥላሉ ነው። ” ሼኩ እንዳሉት ኢህአዴግ እስካለ እኖራለሁ”” አንዳንዴም እኛ ኢንቨስተሮች ሥንሠራ ስለምንሳሳት አይታችሁ እንዳላየ እለፉን ሲሉ ተማፅነዋል።
‘ ለራሷ ተስኗት ፈሷ ዘርጥ ይላል”ሼክ አላሙዲን የከተማ ቦታን እንደድንች መቸርቸሪያ ጉልት ድንጋይ አድርገው ባይሸጡም ባይለውጡም አጥረው የማለፍ አቅማቸው ከመንግስት ቁጥጥር ሆኗል። “ካራቱሪ ከቀረጥ ነጻ ሲነግድና የተፈጥሮ ደን ሲያወድም ቆይቶ በእዳ ፋይሉ ሲዘጋ መሬቱን ለሳዑዲ የምግብ ዋስትና እንዲውል እየተደረገ ያለው ሩጫ ዳግም ስህተት እንዳይሆነ ብዙ ሀገር ወዳድ ይናገራሉ” የሼክ አላሙዲንና ህወአት ኢንቨስተሮች ይህ የሌላውን ዕዳ ለእኛ በእኛ ተውት ሚስጥሩ ምንድነው?። ጨዋታው ታማኝ ሆድ አደር፣ አድርባይ ብሄርተኛ ሲገኝ ወይም አገልግሎቱን የጨረሰ ታጋይ ጡረታ ሲወጣ ንብረቱ በእርሱ ሥም ተሰይሞ የሚገኘው ገቢ በሼክ አላሙዲን ይሰበሰብና ለመከላከያው ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ መምሪያ እና ለወ/ሮ አዜብ ጎላ ለፋውንዴሽኑ የጥናትና ምርምር ዘርፍ በውጭ ሀገር ገቢ ይደረጋል። ለዚህ ነው አዲሱ ፕሬዘዳንት የውጭ በላተኞችን በብዛት ወደ ኢትዮጵያ በማምጣታቸው ምስጋና፣ ክብሩና ሙገሳው፣ የቀለጠው አሁንም የውጭ ንግድ የድለላ ሥራውን በሙያቸው ደርበው እንዲሰሩ ታዘዋል !!።
የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ከጭፈራ ቤት፤ ከፀጉር ቤትና ከመሳጅ ቤት የዘለለ ሀብት የላቸውም። ለዚያውም በዕድሜ በፆታ በዘርና ቋንቋ ተቃቅፈው እንኳን ገንዘብ ለመበደርና ሀብት ለማፍራት ኮብል እስቶን ለመጥረብ መመዘኛው ብሔርና የፓርቲ አባልነት ነው። “ካራቱሪ ከኢትዮጵያ ነግድ ባንክ እ.ኤ.አ በዲሴምበር ፳፻፲፩ ወደ ፷፪ ሚሊየን ብር ብድር ወሰወዶ ያልከፈለ…፫፻ሺ ሄክታር ለማልማት ከግብርና ሚኒስቴር መሬት ተረክቦ የነበረ ቢሆንም ባለፉት አምስት አመታት ከ፰፻ ሄክታር በላይ ለማልማት አልቻለም። ግብርና ሚኒስቴር ይህንኑ ደካማ አፈጻጸም በማየት ከአንድ ዓመት በፊት ፪፻ሺ ሄክታር መሬት የነጠቃቸው መሆኑ ተዘግቧል።ድርጅቱ ፻፶ ያህል ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዳሉት የሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ እስከ ፵፭ ቀናት እንደሚዘገይ፣ ለጡረታና ለግብር ከሰራተኛው የሚሰበሰበው ክፍያ በአግባቡ ለሚመለከተው አካል እንደማይገባ ፣የኩባንያው አመራሮች በውጪ ምንዛሪ የሚያስገቡዋቸውን ዘርና ማዳበሪያ በአገር ውስጥ እንደሚሸጡ፣ ከቀረጥ ነጻ ያስገቡዋቸውን ማሽነሪዎች በማከራየትና ለሶስተኛ ወገን በመሸጥ ያልተገባ ጥቅም በማካበት እራሱን ከሀገሪቱ ህግና ደንብ ውጭ ያደረገ ብቸኛ ክልላዊ የንግድ መንግስት እንደሆነ ማየት ይቻላል። ግን ሌባና ሌባ እንጂ ሌባና ፖሊስ የሌለበት ወሮ በላ ሥርዓት ነው በማለት አስቀድመን ተናግረናል ዘረኝነት የሀገር ዕድገት ጥላቻ አደለም እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል በለው!
በአንድ ድሃ ሀገር ካድሬው ኢኮኖሚውን ሲዘውረው ድህነት ይፈተላል እንጂ የሀብት ልቃቂት አይወጣውም በለው!። ፩/ኩባንያው ለማን አክሲዮን ይሸጣል? ፪/ተበድሮ ኢንቨስተር ለመሆን ኢትዮጵያዊው ትምህርት የለውምን? ወይስ ለህይወቱ ይፈራል?፫/የአካባቢው ብሔር ብሄረሰብ ጥቅሙ ምንድነው? ይህ ባዶውን የቆመ ፕሎኬት የጤና ጣቢያ ነውን? ኢህአዴግ የሕፃናት ሞትን ቁጥር ቀነስኩ ሲል የአዋቂዎችን ሞት በመጨመር እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።፬/በኩባንያው የተቀጠሩት ፻፶ ሰዎች እነማን ናቸው? የጋምቤላና ቤኒሻንጉል ብሔር ተወላጅ አላየሁም!?፭/የክልሉ ፖሊስና ካድሬ አማራን ለመግደልና ለማፈናቀል ነው የተቀጠረው? ፮/የተሰበሰበን ግብር የማይከፍል ኩባንያ መንግስትም በጥቅሙ ከሌለበት ከቁጥጥር ውጭ የሆነው ዜግነት አግኝቶ በነፃ መሬቱን እነዲወስደው ታስቦ ይሆን? ሼክ አላሙዲን ያለባቸውን ዕዳ ሁሉ ከፍለው ጨርሰው ነው የሌላ ኢንቨስትመንት የሚወስዱት? እንደእኔ አመለካካት የውጭ ዜጋ ሥምና ፎቶ እንጂ ምንም ህወአት ያላካተተ ምንም የውጭ ኢንቨስተር የለም!። ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የቴሌኮምንኬሽን ሠራተኞች ያለክፍያ ለማሰናበት ባለቤቱን ፈረንሳዊ አደረጉት፡ አካባቢው ሲረጋጋ ኢፈርት ቴሌኮምን ጠቀለለው። ካራቱሪን አስወጥቶ ሳውዲ እስታር ያጫል በህወአት ቀለበት በሼክ አላሙዲን ቅልጥ አለ ድግስ ሸራተን ከኢፈርት ጋር ጋብቻ ይፈፅማሉ።አራት ነጥብ። ሸዋ ቀለጠ በለው!! አሁን ምን ያደርጋል አስወስዶ ማልቀስ ቀድሞውኑ ነበር በር ዘግቶ መደቀስ….በለው! ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን