• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአዲስ አመትም ያላባራው ስቆቃ

September 12, 2013 09:32 am by Editor Leave a Comment

በግልም ቢሆን አዲሱን አመት በሰላም እና በደስታ መቀበሌ እውነት ነው! መስከረም ጠብቶ ብዙ ቀናት ሳንቆጥር ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርሰኝ የስደተኛ ወገን መከራ ግን ከአዲሱ አመት ዋዜማ ጀምሮ እስከ መባቻው አላባራም … አያንዳንዱን የወገን ስደት ሰቆቃ መከራ ጨክኘ ከመናገር ለመቆጥብ ያደረግኩት ትግል ላንዲት ቀን ቢሳካም ህሊናየ ግን እረፍት አላገኘም! በተለይ በአዲሱ አመት ዋዜማ “ብሪማን” ተብሎ በሚጠራው የጅዳው ትልቅ ማረሚያ ቤት የደረሰኝ መረጃ ያማል …

ያሳለፍነው ሮመዳን ወር እንደገባ ጅዳ ውስጥ የትዳር ጓደኛውን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ በአሳር በመከራ ከተያዘ በኋላ ዘብጥያ የወረደው አዕምሮውን የሳተ ኢትዮጵያዊ ከጤነኛ ታሳሪ ሃበሾች ጋር ነብሰ ገዳይ ከተራ ወንጀለኛ ጋር ደባልቀው በማሰራቸው ደም እንዲፈስ ምክንያት ሆኗል በማለት ታሳሪዎች እያነቡ ገልጸውልኛል። ይህ ነፍሰ ገዳይ ከአንድ ፍርዱን ጨርሶ በተወካይ ጉትጎታ እጦት ከእምስት ወራት በላይ  እስር ይንገላታ የነበረን በእስር ቤቱ ተደብቆ ሲጋራ የሚሸጥን ወጣት ኢትዮጵያዊን ታሳሪ “አንዲት ሲጋራ ለምን አልሰጠህኝም” በሚል ቂም በብረት ዘንግ አይኑን አፍስሶ የመደብደቡ ወንጀል ሊናገሩት የሚከብድ አሰቃቂ እንደነበር “ተደብዳቢው ከሞት አይተርፍም” ያሉኝ እማኝ ታሳሪዎች በሃዘን ገልጸውልኛል … በአዲሱ አመት ዋዜማ!

በአዲስ አመት መባቻ  ዛሬ ምሽት … ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እና ፍትህ!

ሀገር ቤት የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የርሃብ አድማ መምታት ዜና ከአሜሪካ ራዲዮ የግማሽ ሌሊት የሳተላይት ስርጭት እያዳመጥኩ በወጣቷ ጋዜጠኛ የእስር እንግልት ዙሪያ እንደ ዜጋ የሚሰማኝን ለማለት በሃሳብ ላይ ነኝ፣ ከኮምፒውተሬ ጋር ተፋጥጨ በሃሳብ ከርዕዮት አለሙ አልፊ ከእስክንድር ከውብሸት እና ከአንዷለም የእስር ፈተና ርቄ ፍትህን ፍለጋ ሄጃለሁ … “አሸባሪዎች!” አልኩ ለራሴ ውስጤ እየተቆጣ! ግን ዝም አልኩ … ጭጭ  … ዝም! ምን ይባላል!

ወጣቷ ጉብል ትፈታ ግን እላለሁ!

ከምሳ የተረፈችንን ራት አድርገን ከባለቤቴ ጋር እየቀማመስኩም ርዕዮትን አስታውሸ  ፍትህን ፍለጋ በሃሳብ ነጉጃለሁ … ምሽት ላይ አብረውኝ ሲጫዎቱ ያመሹትን ሁለት ታዳጊ ግረምሳ ልጆችን  በአመት በአል ተጠራርተን በአሉን ያደመቁ ዘምድ ጓደኛ ጎረቤቶችን አንዳፍታ ከነርዕዮት ጋር አዛምጀ ሳያቸው አመመኝ! በአውደ አመት ከልጅ ወላጅ ወዳጅ ዘመድ ተራርቀው የከረሙ እና እንዲከርሙ የተፈረደባቸው ወንድም እህቶች ጉዳይ በእርግጥም ያሳስባል ያማል! የሰረቀ፣ የገደለ በምህረት በሚፈታበት ሃገር የህዝብን በሶት በተናገረ መቀመቅ መውረድ አግባብ አይደለም ማለቱ በዘመኑ ባያዋጣም፣ ይቅርታ ምህረት ጠይቆ መነፈግ ልብ የሚሰብረውን ያህ ስብራት አጣሁለት! የእነ ርዕዮትን ስቃይ፣ እስራት! የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ! ሰላማዊ እርቅ ይበጀናል እላለሁ!

መንገድ ላይ ተጥላ የተገኘችው የኮንትራት ሰራተኛ …

ብዙ ርቄ ስጓዝ ስልኬ አቃጭሎ ከነጎድኩበት ሃሳብ ተመለስኩ … ከአንድ ወዳጀ የደረሰኝ የስልክ ጥሪ አዲሱን አመት ዳግም በአሳዛኝ መረጃ ቅበላ እንድጀምር አስገደደኝ፡፡ (እየተኮላተፈ አማርኛ የሚናገር ወዳጁ መንገድ ላይ አንዲት አትዮጵያዊት በአሰሪዎቿ ተጥላ እንዳገኘና ሃበሻ የሚያውቅ እሱን በመሆኑ እንዲረዳት መረጃ አቀብሎት ይህችን እህት እንዴት መርዳት እንደሚቻል “የተሻለ መረጃ ካለህ” ብሎ ሊያማክረኝ መደወሉን አጫወተኝ!  እኔም ከሁሉ አስቀድሞ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎችን እንዲያነጋግር በመምከር አድራሻ ጭምር አቀበልኩት እና በጉዳዩ ዙሪያ አማክሬው ስልኩን ዘጋን …

ወዳጀ በደረቁ ሌሊት መልሶ ደውሎ የደረሰበትን መረጃ አቀበለኝ … ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ደውሎ ቆንስል ሙንትሃን በማግኘት ችግሩን አስረድቶ መፍትሔ ጠየቀ። ከዚያም ቆንስል ሙንትሃ ልጅቱን ወደ ቆንሰሉ መጠለያ በመውሰድ ለመጠለያው ሃላፊ ለወ/ሮ አዜብ እንዲያስረክባት መክረውት ወደ ጅዳ ቆንሰል መጠለያ መሄዱን ገለጸልኝ፣  በቆንስላው ሲደርስ የተባሉት የመጠለያ ሃላፊም ሆኑ የሚመለከታቸው በቦታው አለማግኘቱን ወዳጀ በአግራሞትና በብስጭት የሆነውን ሁሉ ገልጾልኛል! ለመጠለያውን እና ለኮሚኒቲውን ጠባቂዎች ጉዳዩን በማስረዳት ይህች መንገድ ላይ ተጥላ ያገኟት እህት የቀሩትን  ከ140 የዘለቁ ተፈናቃዮች ለመቀላቀል ይቻላት ዘንድ የቆንስል ሃላፊዋን መልዕክትና ቃል ቢገልጹም ከጠባቂዎች ጋር መግባባት አልተቻለም!

ይህች ምስኪን እህት ለሃገር ምድሩ ባዳ በሆነችበት ሰማይ ስር መንገድ እንደመጣሏ ወገኖቿ የደረሱላት መሆኑ ቢያስደስትም ወደ መጠለያው ለመግባት ፈቃድ አለማግኘቷ ያበሳጨው መረጃውን ያቀበለኝ ወንድም እልህ እና ቁጭት እየተናነቀው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ስልክ ደውሎ እንዲህ ነበር ያለኝ “አቶ ነቢዩ ዘበኞች አትገባም አሉን፣ ወደ ጅዳው ቆንስል ሃላፊ አቶ ዘነበ ደወልን ስልካቸው ዝግ ነው! መልሰን ለቆንስል ሙንትሃ ደወልን፣ ቅድም ውሰዷት እና ለወ/ሮ አዜብ አስረክቧት ያሉኝ እመቤት ደጋግምን ብንደውልም ስልካቸውን አያነሱም፣ ምን ማድረግ ይቻላል? ግን … ወገናችን ይህን መከራ ላለማየት እህታችን ሜዳ ላይ አይተን እዳላየን በጭካኔ ጥለን መሄድ ነበረብን? …”  ብሎ ጠየቀ!  ብዙ ተነጋግረን ስልኩ ተዘጋ … አንደምንም  በግል አስጠግቶ አሳድሮ ነገ የሚሆነውን ለማድረግ ተስማምተን ከተሰነባበትን በኋላ መልሸ አሁንም የደረሰበትን ሁኔታ ለመረዳት ስደውልለት መልካም የምስራች አበሰረኝ ፣ እንዲህ ሲል “አዎ ተሳካ! የቆንስል ሃላፊዎች ስልካቸውን ማንሳት ባይችሉና የምናደርገው ጠፍቶን ብንንገላታም በፍቃድ ማግኘት ያልቻሉትን ወደ መጠለያ የማስጠጋት ሙከራ ሰው በሰው (በዋስጣ) ይህች አንጀት የምትበላ እህት ወደ ቆንስሉ መጠለያ ልትገባ ችላለች!” ብሎኛል!

በየሜዳው እየተጣሉ ያሉ የኮንትራት ሰራተኛ እህቶቻችን ከችግር ብዛት እስከ ማበድ ራሳቸውን እስከ ማጥፋት እንዳደረሳቸው እያየን ነው!  ሰብዕናው ቢገደን ገጽታችን እንዳያጠፉት እህቶቻችን ወደ መጠለያ በመሰብሰቡ ረገድ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ዛሬም ድምጻችን ሰምተው ሳይሆን ግፉአኑን ከደጃቸው ተመልክተው አንድ ቢሉን መልካም ነው!

የአዲሱ አመት የማለዳ ወግ  በመራራው ሮሮ ጀመርኩት … በአዲስ አመትም ያላባራው ሰቆቃ እና ልናገረው የከበደኝ ሮሮ! አልኩት … ልተንፍሰው በሚል ከብዙ ጥቂቱን ነካክቸ … ምን ላድርግ  ! የአረብ ሃገር ስደት  ኑሯችን እንዲያ ሆኗል!

እሰኪ ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule