• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አገራችንን በእርቅ እንታደጋት” ዶ/ር ተጋ

August 24, 2013 03:00 am by Editor 4 Comments

የኢህአዴግ ባለስልጣኖችና ደጋፊዎች ከየትኛውም ዜጋ በላይ ዋስትና እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ። በአገራቸው ጉዳይ ላይ በተለይም በዕርቅ ዙሪያ በርካታ ጽሁፎችን ሲያቀርቡና ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ በኃላፊነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከአገራቸው ውጪም በኬንያ፣ በሞዛምቢክ፣ በስዊትዘርላንድና በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በከፍተና ኃላፊነት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በተለይም በዎርልድ ቪዥን፣ በተባበሩት መንግሥታ፣ በዓለምአቀፍ አብያተክርስቲያናት ካውንስል፣ … የሰጡት የዓመታት አገልግሎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በአገር ውስጥና በውጪ አገራት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ዶ/ር ተጋ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የዕርቅ፣ የሰላምና የፍትሕ ሒደት ውስጥ የተጫወቱት መጠነኛ ሚና በአገራቸው ተግባራዊ ሆኖ ለማየት የሚመኙና ለዚያም የሚቻላቸውን ጥረት ሁሉ ሲያደርጉ መቆየታቸው እስካሁን የሠሩት ሥራ ምስክር ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ የአገር ውስጥና የውጭ ስድስት ቋንቋዎችን አቀላጥፈው የሚናገሩ ናቸው፡፡

“እውነተኛ እርቅ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን” የሚሉት ዶ/ር ተጋ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት አገራችን ከምትገኝበት አደጋ መታደግ የሁሉም ዜጋ ግዴታ እንደሆነ አመልክተዋል። በማያያዝም በደል ሲበዛ ህዝብ እንደሚያምጽ በመጠቀስ ሳይረፍድ ሁሉም ወገኖች ለእርቅ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጠይቀዋል።

እርቅና ሰላም ለማውረድ የሚችሉ ዜጎች አድፍጠው መቀመጣቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ተጋ “የፖለቲካ መናኞች” ያሉዋቸውን እነዚህ ዜጎች ከተደበቁበት በመውጣት ባገራቸው ጉዳይ ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።

እውነተኛ እርቅ ቢጀመርና፣ ለማስታረቅ የሚመጥን ስብእና ያላቸው ወገኖች የሚካተቱበት አስታራቂ ቢሰየም ህዝብ እውቅና ለመስጠት እንደማይቸገር ያስታወቁት ዶ/ር ተጋ “ከኢህአዴግ ወገን እርቅ የሚፈልጉና ለልቡናቸው የቀረቡ ሰዎች አሉ። እነሱም ሰው ናቸውና ሰላም ይፈለልጋሉ። ራሳችሁን መናኝ ያደረጋችሁ ከተደበቃችሁበት ውጡና ኢትዮጵያን እናድን” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ሙሉ ቃለ ምልልሳቸው እንደሚከተለው ተቀናብሯል።

ጎልጉል፦ በተደጋጋሚ ስለ እርቅ ይናገራሉ። በርግጥ መፍትሔ ይኖረዋል?
ዶ/ር ተጋ፦ ከእርቅ ውጪ ምንም አማራጭ የለም። አለ?

ጎልጉል፦ አሁን ኢህአዴግ ከያዘው አቋም አንጻር “እርቅ ዋጋ የለውም” የሚሉ አሉ፤
ዶ/ር ተጋ፦ ስለነዚህ ወገኖች በተለይ የምለው ነገር የለም። በኔ እምነት እርቅ፣ ትክክለኛው የእርቅ መንገድ ተሞክሯል የሚል እምነት የለኝም። ስለዚህ ትክክለኛው እርቅ፣ እውነተኛው አርቅ መሞከር አለበት። እኔ እንደምረዳው ከሁሉም ወገን ትክክለኛ እርቅ ከቀረበ ተቀባይ የማይሆንበት ምክንያት የለም።

ጎልጉል፦ትክክለኛ እርቅ ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?
ዶ/ር ተጋ፦ ከፍቅርና የሚመነጭ ፍርሃት ሰዎች አምነው እንዲገዙ ያደርጋቸዋል። ፍርሃት ስል አምነው ለሰየሙት መንግሥት ክብር መስጠትና መገዛትን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መሳሪያ ያላቸውና ህግ ያረቀቁ ክፍሎችም ህዝብን መግዛት ይችላሉ። እነዚህ ክፍሎች እኔን ምሰል። እኔ የምልህን አድርግ። አንተ ቦታ የለህም። የአንተ ድርሻ መገዛትና መገበር ብቻ ነው። አንተ ዝም ብለህ ከመገዛት ውጪ ሌላ ተግባርና ድርሻ የለህም በማለት በጉልበት ይገዛሉ። ልክ አሁን እንደሚደረገው ማለት ነው። በሌላ ወገን “አማራጭ ነን”  ብለው በጉልበት እየገዛ ያለውን ለመገልበጥ የሚታገሉ አሉ። ገለልተኛ ሆነው የሚኖሩና የሸሹ ወገኖች አሉ። እነዚህ የሸሹ ሰዎች “የፖለቲካ መናኞች” ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሌሎችንም አካትቶ ለመታረቅ ሲስማሙ ትክክለኛው እርቅ ይመጣል። ሳይሞከር አይሳካም ማለት አይቻልምና እንሞክረው።

ጎልጉል፦ ያልተቻለው እኮ እነዚህን ወገኖች ማሰባሰብ ነው? በተለይም ኢህአዴግን ወደ እርቅ የሚገፋው ጉዳይ የለም የሚሉም ወገኖች አሉ። ኢህአዴግ ምን አስፈርቶት ወደ እርቅ ይመጣል? የሚሉ አሉ፤
ዶ/ር ተጋ፦ ለጊዜው ሃይል አለኝ ብሎ ከተራራ ላይ አልወርድም። መሳሪያ አለኝና እርቅ አይበጀኝም። ጡንቻ አለኝና ሰላም አያሻኝም በማለት ኢህአዴግ የሚያከር ከሆነ የተጎዱ፣ የተረገጡ፣ የተገፉ፣ የከፋቸው፣ የባሰባቸው ቀኑ ሲደርስ “አታስፈልግም” ብለው ይነሳሉ። ዓለም ብዙ አሳይታናለች። የህዝብ ቁጣ ሲነሳ የሚደርሰው አደጋ የከፋ ነው። እኔን ዘወትር የሚያስጨንቀኝ ይህ ነው። የኢህአዴግ ሰዎችም ቢሆኑ ሰዎች ናቸውና ከደጋፊዎቻቸው ጭምር ይህንን ሳያስቡት ውለው ያድራሉ ብዬ አላስብም። ደግሞም ያስባሉ። እንደውም ከማንኛቸውም በላይ የኢህአዴግ ደጋፊዎች እውነተኛ እርቅ የሚመኙበት ወቅት ላይ ለመሆናቸው ጥርጥር የለውም። ዋናው ጉዳይ ግን እንዴት …

tegga
ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ

ጎልጉል፦ ኢህአዴግ እርቅ ይፈልጋል እያሉ ነው?
ዶ/ር ተጋ፦ በሚገባ። የኢህአዴግ አመራሮችና ደጋፊዎች እኮ ሰዎች ናቸው። አሁን አገሪቱ ላይ ያለው አደጋ ያሰጋቸዋል። ከሁሉም በላይ ሰላም ለነሱም ያስፈልጋቸዋል። ያለ ስጋት ተራ ሰው ሆነው መኖር የሚፈልጉ አሉ። የግፍና የጭቆና መጠን ሲያልፍ ህዝብ እንደሚነሳ ጠንቅቀው ያውቃሉ። የግፈኛ መሪዎች መጨረሻ ምን እንደሚመስል ይረዳሉ። ችግሩ ያለው እነሱና ደጋፊዎቻቸው ወደ እርቅ እንዲመጡ የሚኬድበት መስመር አግባብ ያለው መሆኑ ላይ ነው። የመተማመን ችግር አለ።

ጎልጉል፦ እርቅ የጀመሩና አሁንም እየሰሩ ያሉ አሉ?
ዶ/ር ተጋ፦ ካሉ ጥሩ ነው። እኔ ግን የማወራው ሌሎች ስለጀመሩት እርቅ አይደለም። እኔ የምናገረው የእውነተኛው እርቅ መንገድ ለገባቸው፣ የእርቅ ሃሳብ ላላቸው፣ ያልተነካኩና ለእርቅ ተግባር ቢነሱ የህዝብ ይሁንታና አመኔታ ማግኘት ለሚችሉ፣ ኢህአዴግም አክብሮ ሊያነጋግራቸው ፈቃደኛ ይሆናል ብዬ ለማምንባቸው ክፍሎች ነው። እርቅ ጀመሩ የሚባሉትን እነዚህን ሰዎችም ሆኑ ክፍሎች አላውቃቸውም። የምናገረው ቢጀምሩት ይሳካላቸዋል ብዬ ለማምንባቸው ሰዎች ለህሊናቸው ነው። የአገራችን ጉዳይ ያገባናል ለሚሉ ጨዋ ስብዕና ላላቸው ወገኖች ነው። እንግዲህ ይህንን ስል ከሁሉም ወገን ኢህአዴግን ጨምሮ ነው። አሁን አገራችን ያለችበት አሳሳቢ ወቅት ጤና ለነሳቸው፣ የወደፊቱ ትውልድ እድልና እጣ ፈንታ ግራ ላጋባቸው የኢትዮጵያ ልጆች ነው።

ጎልጉል፦ እውነተኛ እርቅ ምንድ ነው?
ዶ/ር ተጋ፦ ስለ አቀራረቡ መናገሩ የሚሻል ይመስለኛል። ከላይ የጠቀስኳቸው ክፍሎች ውስጥ አገራችንን ሊታደጉ የሚችሉ፣ የመጪውን ትውልድ መከራ ሊገፉ የሚችሉ ነገር ግን ዝምታን የመረጡ የተከበረ ስብእና ያላቸው ወገኖች አሉ። እነዚህ ዝምታን የመረጡ ወገኖች ዝምታን የመረጡበት በርካታ ምክንያቶች ይኖራቸዋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከውስጥም ሆነ ከውጪ ስድድብ ነው። አንዳንዴ ቃላት እንኳ አይመረጥም። ሰው በስድብ ፖለቲካና ባለመከባበር የሚደረገው አተካሮ የሰለቸው ይመስለኛል። አንግዲህ እንዲህ ያለው መንገድ አልመች ብሏቸው ዝም ያሉትን ከተሸሸጉበት እንዲነሳሱ ማድረግ የመጀመሪያው ስራ ነው። ሌላው እርቅ የምትጠይቀውን ክፍል ማክበር ነው። እየዘለፍክና እያዋረድክ እርቅ መጠየቅ በባህላችንም ቢሆን አያስኬድም። በመከባበር ልዩነትን ማሳየትና ተቃውሞን መግለጽ የሚቻልበት መንገድ ሲፈጠር አድማጭ ማግኘት ይቻላል። በዚህ መልኩ መነጋገር ይጀመራል። እውነተኛ እርቅ የሚጀመረው የእርቁ አጀማመር ክብር የተሞላበት ሲሆን ነው። ሲጀመር መከባበርና የህዝብን ይሁንታ ማግኘት ከተቻለ የቀረው ጉዳይ ሂደት ነው የሚሆነው። ራሳቸውን ያከበሩና የጸዳ ማንነት ያላቸው ወገኖች ከየትኛውም ወገን ድጋፍ አላቸው። ከበሬታም አይነፈጉም። ኢህአዴግ ራሱም ቢሆን ሊገፋቸው አይችልም። አላማቸውና መሰረታቸው እርቅ ማውረድ መሆኑ ከተረጋገጠ ሊገፉ ወይም እምቢ ሊባሉ የሚችሉበት መንገድ የለም። ሁሉም ነገር የሚመነጨው ከስብዕናቸው ነውና ስብዕናቸው ያማረ ሰዎች ተሰባስበው እርቅ ላይ ቢሰሩ የሁሉም ስጋት ተቀረፈ ማለት ነው። ሌላ ትርጉም ካልተሰተው በቀር እርቅ አሁን ላለችው ኢትዮጵያ ፈውሷ ነው።

ጎልጉል፦ የሐይማኖት መሪዎች ሚና ምን ሊሆን ይችላል?
ዶ/ር ተጋ፦ የሐይማኖት መሪዎች ነው ያልከው? እንደው ለመሆኑ እዛ ደረጃ የደረሱ አሉ? ካሉ ጥሩ ነው። እኔ ግን እስካሁን አላየሁም። የራሳቸው የግል አመለካከት ቢኖራቸውም ለጊዜው እሱን ወደ ጎን አድርገው ለእርቅ ቢሰሩ ደግ ነው። ግን …

ጎልጉል፦ ቄስ ገመቺስና ቄስ ኢተፋ ጎበና የጀመሩት እርቅ ነበር፤
ዶ/ር ተጋ፦ ለትግል መንስዔ የሆኑ ሰዎች የእርቅ አፋላላጊ መሆን የሚችሉ አይመስለኝም። ከጅምሩ የህዝብን ይሁንታ ማግኘትና አለመነካካት ያልኩት እዚህ ጋር ይመጣል። ከቤተክርስቲያን ሃላፊነት በላይ በእርቅና በሰላም ፍልስፍና ማመን ይቀድማል። ራሳቸውን ለሰላምና ለእርቅ ፍልስፍና ያስገዙ ሰዎች የእርቅን ሂደትና የሚያስከፍለውን ዋጋ ስለሚረዱ እንዲህ አይነት ሰዎች ቢሆኑ ይመረጣሉ ባይ ነኝ። አሁን የጠቀስካቸው ወገኖች የጀመሩት ስራ ድጋፍ የሚያሻው ደረጃ ከደረሰም ማገዝ ነው።

ጎልጉል፦ በአንድነት ያምናሉ?
ዶ/ር ተጋ፦ አንድነት የተሰጠን ነው። እምነት ነው። በፍጹም ሊፋቅ አይችልም። አንድነት ውስጥ ልዩነት፣ በልዩነት ውስጥ ደግሞ አንድነት አለ። የምናምረው በልዩነታችን ነው። በልዩነታችን ውስጥ የሚፈጠረው አንድነት ደግሞ ያደምቀናል። ልዩነት በየጊዜው የሚያድግ፣ ወደፊትና ወደኋላ የሚለጠጥ የላስቲክ ይዘት ያለው ነው። ስለዚህ ይህንን እንደ ላስቲክ የሚለጠጥ ልዩነት ስንይዘው፣ “ያንተ ማንነት እኔን አይረብሸኝም” የሚለው እሳቤ ውስጥ ሁልጊዜም መኖር እንችላለን። ያንተ ቋንቋ፣ ማንነት፣ አስተሳሰብ፣ አያስፈልገኝም የሚል ጉዳይ ከተነሳ የላስቲክ ይዘት ያለውን ልዩነት ባህሪውን ወደሚሰበርና የሚቀነጠስ ቁስ ይቀይረዋል። እንዲህ ያለው እርምጃ አደጋ አለው። እኔ እንግዲህ እንዲህ ያለውን አስተሳሰብ ከሚቃወሙ የአንድነት አማኞች ውስጥ ነኝ …

ጎልጉል፦ ስለ እርቅ እንመለስና የውጪ ሃይሎች /መንግስታት/ ካልገቡበት አይሆንም የሚሉ አሉ፤ በተለይም ተጽዕኖ ፈጣሪ አገሮች፤
ዶ/ር ተጋ፦ እስከማውቀው ሕዝብ እውቅና የሰጠው እርቅ ስለመከናወኑ አልተሰማም። እኔ በግል ህዝብ እውቅና የሰጠው እርቅ ስለመኖሩ መረጃ የለኝም። በመጀመሪያ እርቅ በጓዳ ሲሆን ክብር የለውም። እርቅ በግልጽና ባደባባይ መሆን አለበት። ከላይ የገለጽኳቸው ወገኖች ከተሸፈኑበት መጋረጃ ከወጡና ለእርቅ ከሰሩ ብዙ ርምጃ መራመድ ይቻላል። የውጪ ሃይሎችን ማካተት ተገቢ የሚሆንበት አግባብ ብዙ ነው። እንደውም በገሃድ እርቁ ሲጀመር ለእርቁ ስራ የሚተባበሩ አገራትም አብረው መገለጽ አለባቸው። ለምሳሌ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ኖርዌይ ብዙ ሚና ተጫውታለች። በወቅቱ ሚናዋ ደስተኛ ባልሆንም አስፈላጊ የሆኑ አገሮች እንዲካተቱ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል።

ጎልጉል፦ በተደጋጋሚ ዝምታን የመረጡ እንዲነሱ ይጠይቃሉ። በውል ስም ጠርተው ለዚህ ተግባር ተነሱ የሚሏቸው ወገኖች ካሉ?
ዶ/ር ተጋ፦ ብዙ ታሪክ መለወጥ የሚችሉ ወገኖች አሉ። ራሳቸውን ከአገራቸው ፖለቲካ አግልለው የመነኑ አሉ። ራሳቸውን የፖለቲካ ባህታዊ ያደረጉ አሉ። እነዚህ ባህታዊ ፖለቲከኞች እንዴት እንዲቀሳቀሱ ማድረግ እንደሚቻል ያሳስበኛል። ብዙ እርቅ ላይ መስራት የሚችሉ ወገኖች አሉ። እነዚህም ወገኖች ከሸፈቱበት የ”አያገባኝም” መንገድ ተመልሰው ማየት እፈልጋለሁ። ስለዚህ ድንገት ቢሰሙኝ ብዬ ነው ደጋግሜ የጠቀስኳቸው።

ጎልጉል፦ ፖለቲከኛ ነበሩ? አሁንስ?
ዶ/ር ተጋ፦ ፖለቲከኛ አይደለሁም። አጥብቄ የምጠየፈው ነገር ነው። አንዴ እዚህ፣ አንዴ እዚያ የመርገጥ ባህሪ የለኝም። የመገለባበጥ ነገር አይገባኝም። አቋራጭ ብሎ ነገር አላውቅም።

ጎልጉል፦ ግን በቂ ልምድ ያለዎት ይመስላል፤
ዶ/ር ተጋ፦ (ሳቅ ብለው) … ልምድ!! ስለ አገራችን ፖለቲካ አንድ ነገር ልበል። የእኛ ህዝብ ቦይ ነው። መንገድ ካሳየኸው ዝም ብሎ ይጎርፋል። አሁን ታዲያ ቦዩ በዛ። ቦዮቹ ደግሞ ትንንሽ ሆኑ። ትንንሽ ስም ያላቸው ሆኑና እንደ ስማቸው ትንሽ፣ ትንሽ ሰዎችን ይዘው ቀሩ። እነዚህ ትንንሽ ቦዮች የጥቂት ብልጣብልጦች መጠቀሚያ ሆኑ። ባህሪያቸውና ተፈጥሯቸው ትንሽ በመሆኑ ጥቂቶች አትራፊ ሆኑና አብዛኞች ከሰሩ። ይህ አካሄድ ያላስደሰታቸው አብዛኞች ራሳቸውን አቀቡ። አድፋጮች በዙና /silent majority/ ተባሉ። ከስማቸው እንደምንረዳው እነሱ ይበዛሉ። አሁን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት እነዚህ ዝምተኛ፣ ባህታዊ ፖለቲከኞች፣ የመነኑ ዜጎች ተመልሰው ለእርቅና ለሰላም እንዲሰሩ ማሳሰብ የሁሉም ቀና ዜጋ ተግባር ሊሆን ይገባል። እኔ እንግዲህ እንደዚህ አስባለሁ። የተደበቁ ተመራማሪዎች አሉ። ሌሎች አገራትን የሚጠቅሙ ክቡር ዜጎች አሉን። አገራቸውን የሚወዱ ህዝብን የሚፈሩ አሉ። ከሁሉም በላይ ለህሊናቸው የሚኖሩ ዜጎች አሉ። ኢትዮጵያ የልጆች ደሃ አይደለችም። እነዚህ ዜጎች ለህዝብ ሲሉ፣ አገራቸው ሰላምና እርቅ እንዲወርድላት ሲሉ ከተደበቁበት ሊወጡ ይገባል።

ጎልጉል፦ ከህወሃት ሰዎች ጋር ይተዋወቃሉ?
ዶ/ር ተጋ፦ የቀድሞውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍንን አውቃቸዋለሁ፤ አብረን ተምረናል። ባለስልጣን ከሆኑ በኋላ ተገናኝተንም ነበር። በግል በእርቅ ዙሪያ ላነጋግራቸው እችላለሁ። ሌሎችም ሰዎች አሉ። ኢህአዴግ ውስጥ ቀና ሰዎች እንዳሉ መታመን አለበት። ቀና የትግራይ ልጆች አሉ። የወደፊቱ ችግር የሚያሳስባቸው ጥቂት አይደሉም። ደጋግሜ እንደነገርኩህ ዋስትና የሚናፍቁ ባለስልጣኖች ብዙ ናቸው። ሰላም የሚመኙ ብዙ ናቸው። መንገዳቸውን መመርመር የሚፈልጉ ጥቂት አይደሉም። ግን በስድብና በጥላቻ ሊሆን አይችልም። በመከባበር የሚመሰረት መቀራረብ ወደ አንድ የእርቅ ሃሳብ ያመጣል። ጊዜ ቢወስድም መጀመር አለበት። ሲጀመር ግን በክብር መሆን አለበት። ህዝብም እውቅና የሚሰጠው ሊሆን ይገባል።

ጎልጉል፦ እርስዎ የሚያምኑበት እርቅ በዋናነት ምን መያዝ አለበት?
ዶ/ር ተጋ፦ እርቅና ሰላም ከፍትህ ጋር። ፍትህ የሌለበት እርቅ ዋጋ የለውም። ሰላምም አያመጣም። ግብጽ ጥሩ ምሳሌ ናት። አሁን የተነሳውን የፕሬዚዳንት ሙርሲን ደጋፊ ምን ታደርገዋለህ። ፍትህ ካላገኘ ለመሞት ተነስቷል። በሌላ በኩል ሙርሲን አውርደው የተቀመጡ አሉ። ለሙርሲ ደጋፊዎች ምላሽ ቢሰጥ አውርደው የተቀመጡትና የፈለጉትን ለመምረጥ ጊዜ ገደብ የተቀመጠላቸው ይነሳሉ። ሲጀመር ፍትህና እርቅ ተጣምረው ባለመከናወናቸው ችግሩ እየተባበሰ ሄደ። ስውር ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ማለቴ ነው። ስለዚህ እርቅና ፍትህ የሚለያዩ ነገሮች አይደሉም። ፍትህ ያለበት እርቅ እንዲሰፍን ተግተን መስራት አለብን። አገራችን ያለችበት ሁኔታ ቸል የሚባልበት አይደለም። በኋላ ሁላችንንም ይቆጨናል። እርቅ ላይ ትኩረት ማድረግ ግድ ነው። የፖለቲካ ለውጥ እንኳን ቢኖር የተዘራውን ክፉ ዘር ለማክሰም እርቅ ግድ ነው።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Interviews Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    August 24, 2013 10:42 am at 10:42 am

    A South African type of soluton is no solution to be recommended for Ethiopia. First and foremost in South Africa the economy is illegally controlled by the Whites and the political power is transferred to the blacks and that will not be bread and butter for the millions of poor South Africans. Secondly the Whites of South Africa are “civilized” and abide by rules even after giving power and this is not possible under arrogant home grown fascists in Ethiopia. EFFORT should be nationalzed because it is all stolen Ethiopian Money. Those who looted the bank and built high storey buildings should be nationalized and all criminals should face justice.

    Reply
  2. Alem Akliku says

    August 25, 2013 02:16 am at 2:16 am

    Dr Tega, thank you for your thoughtful message about reconcilliation. I do agree and with God’s help, we as Ethiopians should be reconciled and own our future. Thank you for making your stand known as a man of faith. We should have more people like you Dr Tega. A lot of current spiritual leaders treat their calling as a job and choose to remain silent for fear of upsetting some segment of their congregation. However, their actions sadden the Almighty God, the same God they claim to serve and obey. May the Lord give our spiritual leaders the courage to speak the truth in the way of the old prophets. I hope you are the trail blaizer for men of God to boldly speak to authority and say “Thus says the Lord”. Thank you again Dr Tega.

    Reply
  3. MASRESHA says

    August 27, 2013 12:09 am at 12:09 am

    የሃይማኖት አባቶች አሉ ወይ …… ለተባሉት ጥያቄ ምላሻቸው እውነት ቢመስልም ለኢትዮጵያ ሰላም የሚጸልዩ አበባቶች ኢትዮጵያ አሏት…….. አዎ በእርግጥ ኢትዮጵያ የልጆች ደሃ አይደለችም፡፡ ንፁኋን ልጆችዋን እርሱ እግዚአብሔር በእውነት ለእርቅ የሚተጉ የሚሰዉ ልጆችዋን ያስነሳልን፡፡ በእርግጥ እርሱ እግዚአብሔር ካስነሳ ሁሉም ተሸናፊ ነውና አሁንም የድንግል ማርያም ልጅ መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለኢትዮጵያ ለዓለም ሁሉ ሠላምን ይስጥልን፡

    Reply
  4. MASRESHA says

    August 28, 2013 12:01 am at 12:01 am

    የሃይማኖት አባቶች አሉ ወይ …… ለተባሉት ጥያቄ ምላሻቸው እውነት ቢመስልም ለኢትዮጵያ ሰላም የሚጸልዩ አበባቶች ኢትዮጵያ አሏት…….. አዎ በእርግጥ ኢትዮጵያ የልጆች ደሃ አይደለችም፡፡ ንፁኋን ልጆችዋን እርሱ እግዚአብሔር በእውነት ለእርቅ የሚተጉ የሚሰዉ ልጆችዋን ያስነሳልን፡፡ በእርግጥ እርሱ እግዚአብሔር ካስነሳ ሁሉም ተሸናፊ ነውና አሁንም የድንግል ማርያም ልጅ መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለኢትዮጵያ ለዓለም ሁሉ ሠላምን ይስጥልን፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule