• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለአዲስ አበባ የውሃ ድርቅ “ፈረቃ” መፍትሔ ሆኖ ተበሰረ

March 23, 2016 08:44 am by Editor 4 Comments

ራሱን “ልማታዊ” እያለ የሚጠራው ኢህአዴግ በውሃ ድርቅ ሳቢያ በአዲስ አበባ በዝርዝር ባልተገለጹ ቦታዎች ውሃ በፈረቃ ማቅረብ መፍትሔ ሆኖ ተበሰረ። በአገሪቱ በይፋ ያልተገለጸ የውሃ ችግር አለ። አዲስ አበባን በተመለከተ የከርሰ ምድር ውሃ ችግር እንደሌለ ባለሙያዎች ሃሳብ ሲሰጡ ኖረዋል። ኢህአዴግም ቢሆን ከ1997 ምርጫ በኋላ የአዲስ አበባን የውሃ ችግር ለመፍታት የከርሰ ምድር ውሃን እንደሚያጎለብት በተደጋጋሚ ሲገልጽ ነበር።

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነትን ጠቅሶ ቪኦኤ እንደዘገበው የፈረቃው አሠራር የተጀመረው የካቲት 24 ነው። ፈረቃው መፍትሔ ሆኖ የቀረበው የድሬና የለገዳዲ ግድቦች በቂ ውሃ ባለመያዛቸው ሲሆን ፈረቃውም የሚያካትታቸውን ቦታዎች “የተወሰኑ” ከማለት ሌላ ዝርዝር አልቀረበም። በከፊል አዲስ አበባ ተብሎ በደምሳሳው ውሃ በፈረቃ እንደሚታደል ሲገለጽ ፈረቃው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይም የተሰማ ነገር የለም።

የፈረቃውን ብስራት ተከትሎ በከተማዋ የውሃ ችግር ሥር የሰደደና መፍትሔ ያልተገኘለት ጉዳይ ሆኖ ሳለ ችግሩ ቀደም ሲል የሌለ በማስመሰል ፈረቃ መጀመሩን ማወጅ “ከልማታዊ አስተዳደር” አንጻር አሳፋሪ በመሆኑ ለሦስት ሳምንታት ያህል ይፋ ሳይሆን ቆይቷል። የውሃ ችግር አዲስ አበባን ሰፈር እየለየ ሲጠብሳት መቆየቱን ያወሱት ክፍሎች፣ ችግሩ የዝናብ እጥረት ከመፈጠሩ በፊትም ያለና የነበረ ነው። አሁን አዲስ ጉዳይ ሆኖ ከአየር መዛባትና ከኤልኒኞ ጋር ተዛምዶ ሊነሳ አይገባም ባይ ናቸው።

የአዲስ አበባ አስተዳዳሪ የሆነው ኢህአዴግ በተደጋጋሚ የከተማዋን የውሃ አቅርቦት እናሟላለን በማለት በርካታ ፕሮጀከቶች በሥራ ላይ መሆናቸውን ሲገልጽ እንደነበርና ከመሬት በታች ያለ ውሃ በመጠቀም “የውሃን እጥረት ተረት እናደርጋለን” በማለት ባዶ ተስፋ ሲሰጥ መቆየቱን በክስተቱ የተጠቁት ወገኖች በማስረጃ ያመላክታሉ።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያ እንደሚሉት አዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውሃ ችግር የለባትም። አዲስ አበባ እንጦጦ ላይ ሰፋፊ የውሃ ፕሮጀከቶች ቢዘረጋላት በውሃ ምርት ልትጥለቀለቅ እንደምትችል የሚጠቁሙት ከፍሎች “አዲስ አበባ ውሃ ጠማት፣ የውሃ ድርቅ መታት” ብሎ መናገር ለአንድ አገር አስተዳድራለሁ ለሚል ክሽፈት መሆኑን ይጠቁማሉ።

አዲስ አበባ ውሃ በጉቦ ይሰራጭ እንደነበር፣ ድራማውም የሌሎችን መስመር በመዝጋት ጉቦ ለሚከፈሉት በመልቀቅ ገንዘብ ያላቸውን በማንበሻበሽ፣ ገንዘብ ያላቸው ባኟቸው እንዳይደርቅ፣ የሆቴል ትርፋቸው እንዳይስተጓጎል፣ በቀን ሁለቴ ሻወር የሚውስዱ ልማዳቸው እንዳይቀር ወዘተ ድሆችን በውሃ ጥም በማቃጥል ሲከናወን እንደነበር በራሱ ሸንጎ ይፋ መገለጹን በማስታወስ “አዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውሃ ችግር ከሌለባት፣ ኢህአዴግም ይህንን ካመነ የውሃ ችግር አዲስ አበባን ለምን ያቃጥላታል?” ሲሉ ይጠይቃሉ። አያይዘውም “ይህ የመልካም አስተዳደር እጦት ብቻ ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን ግልጽ ክሽፈት ነው። ሕዝብ የሚበላው እና የሚጠጣው ካጣ እንደ አንድ አገር ይህ ውድቅት ነው። የፖሊሲ መኮላሸት ነው። የብቃትና አርቆ በማሳብ የመምራት ድርቅ ነው” በማለት ሃዘናቸውን ይገልፃሉ።

“ይህ ኢህአዴግ የሚባለው ግንባር ቢያንስ በወሳኝና ማህበራዊ በሆኑ አገልግሎቶች ላይ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ቢያሰራ ምን አለበት? ፖለቲካውን ራሱ ህዝብ መፍትሔ እስኪፈልግለት ድረስ ባለሙያዎች አገልግሎት ዘርፎች ላይ እንዲሠማሩ በሩን ቢከፈትላቸው ምን ችግር አለው?” በማለት የኮታና የታማኝነት ሹመት አገሪቱን እያሰመጣት እንደሆነ አሁንም እኚሁ ባለሙያ የተማጽኖ ድምጻቸውን ያሰማሉ። የአዲስ አበባው የጎልጉል ዜና አቀባይ ያነጋገራቸው የውሃ ባለሙያ በዘርፉ በተደጋጋሚ ለመደርደሪያ ሲሳይ የሆነ ጥናት ያቀረቡ ናቸው።

ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኝ ገጠር አንድ ሴትዮ ውኃ በእንስራ ቀድተው ሲሄዱ /ሮይተርስ-REUTERS/
ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኝ ገጠር አንድ ሴትዮ ውኃ በእንስራ ቀድተው ሲሄዱ /ሮይተርስ-REUTERS/VOA

የአዲስ አበባው ችግር ሊደበቅ የማይችል ድረጃ በመድረሱ ፈረቃን ተንተረሶ ይፋ ሆነ እንጂ በየክልሉ ያለው የውሃ ችግር አሳሳቢ ነው። ያልተጣራ ውሃ በመጠጣት ለውሃ ውለድ በሽታ ተጋልጠው ያሉና እድሜ ልካቸውን ጭቃና የማይጠጣ ንጥረ ነገር እየጠጡ የሚኖሩት ወገኖች ችግር የተከደነ ነው። ጎልጉል ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለይም ከሰሜን ምስራቅ አካባቢ የሚደርሱት የህዝብ ምሬቶች ይህንኑ የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡

በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የፍሎራይድ ማዕድን የሞላበትን ውሃ እየተጋቱ አልጋ ላይ ደርቀው የቀሩ፣ አካላቸው የማይታዘዝ፣ ጥርሳቸው ተፈርፍሮ አልቆ ማላመጥ የማይችሉ፣ አሁንም እነሱም ልጆቻቸውም ይህንኑ ውሃ እየጠጡ የሚኖሩትን ወገኖች ሚዲያውም ገዢያቸውም አያውቋቸውም።

መጠነሰፊና መፍትሔ አልባ በሆኑ ችግሮች ከየአቅጣጫው የተወጠረችውን ኢትዮጵያ ላለፉት 25 ዓመታት በነጻ አውጪ ስም እየገዛ የሚገኘው ኢህአዴግ መሠረታዊ የሕዝብ ፍላጎቶችን ሳያሟላ ልማታዊ፣ ሕዳሴ፣ መልካም አስተዳደር፣ … እያለ እባካችሁ እመኑኝ ቢልም እውነታው ግን የሚያሳየው እንደ መንግሥት ከከሸፈ መቆየቱንና ይህም በራሱ ሰዎች ሳይቀር የሚታመንበት ሃቅ መሆኑን ነው፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Yikir says

    March 23, 2016 09:39 pm at 9:39 pm

    Hizibu :-mekakelegna gebi kalachew hageroch terta new yeteselefew .100 % simertenim kezih belay teselifo neber.

    Reply
  2. geresu says

    March 24, 2016 01:53 pm at 1:53 pm

    ወያኔ ልማታዊ መንግስት ሳይሆን ”ጥፋታዊ መንግስት” ለመሆኑ መገለጫዎቹ: 1ኛ.ሀገሪቱ በተለይም ኦረሚያ: አማራ: ጋምቤላ ወዘተ… በወታደራዊ አስተዳደር ቁጥጥር ስር መሆናቸው: 2ኛ. ምርጫ ያካሄደው ምርጫ ጣቢያዎችን በፌደራል ፖሊሶች በመቆጣጠር መሆኑ: 3ኛ. ወያኔ የፈለገውን መሬትና ህዝብ የትግራይ ክልል ነው በማለት በወታደር የሚመራ የግዛት ማስፋፋት በአማራ ክልል እያካሄደ መሆኑ: 4ኛ. አንዱን ብሄር ከሌላው ብሄር ለማጋጨትና እድሜውን ለማራዘም ታማኝ ጀሌና ካድሬዎቹን በማሰማራት ተማሪዎችን: ሰላማዊ ኗሪዎችን: በድብቅ በማስገደል አማራው ኦረሞውን ገደለ: ኦረሞው አማራውን ገደለ በማለት ጥላቻ በዜጎች መካከል እንዲፈጠር ማድረጉ: ቤተክርስቲያኖችን መስጊዶችን: የግጦሽ ሳር እና የማሳ ሰብሎችን: መኖሪያ ቤቶችን ወዘተ… እራሱ በማቃጠል ሰላማዊ ሰልፈኞችና ተቀዋሚዎች አቃጠሉት በሚል ፕሮፓጋንዳ የተቃውሞ ትግሉን ለማጣጣል እየጣረ መሆኑ: 5ኛ. ከውጭ መንግስታትና ረደኤት ድርጅቶች ለትምህርት: ለጤና: ለግብርና: ለረሀብ ተጎጅዎች የሚሰጡ ድጋፎችን ወደሹማምንቱ ኪስ እገባ መሆኑ: 6ኛ. የሀገሪቱ የመሰረታዊ ተቋማት ግንባታ 50% ወጭ ወደ ሹማምንቱ እጅ በመግባቱ ከፍተኛ የጥራት ችግር መኖሩ:7ኛ. የትምህርት ጥራቱ በሀሰት የሪፖርት ቀመር የታጀበ በመሆኑ ጥራቱ ክፉኛ በማሽቆልቆሉ የመምህራን: የሀኪሞች: የሹፌሮች: የአመራሮች:ወዘተ…የከፋ የብቃት ችግር መኖሩ ሰው አልባ ሀገር እየተፈጠረች መሆኑ: 8ኛ. ሰው በችሎታውና በብቃቱ ሳይሆን በፖለቲካ አባልነቱ እየተለካ መሆኑ: 9ኛ. ጦር ሀይሉ:ሚዲያው : ታላላቅ የኢኮኖማ ተቋማትና መላ የፖለቲካ አመራሩ 90% በአንድ ብሄር ተወላጅ ትግሬዎች ብቻ የተያዘ መሆኑ: 10ኛ. የሀገርን ልኡዋላዊነት በመጣስ ድንበር ቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት ጫካ በነበረበት ወቅት የገባውን ቃል ለ…

    Reply
  3. gud says

    March 24, 2016 06:52 pm at 6:52 pm

    The question is

    Are you part of the problem or the solution
    Just read back your posts of the past one year
    And you know the answer . People in addis call u
    MERDO NEGARI s

    Reply
  4. gud says

    March 28, 2016 08:16 pm at 8:16 pm

    Geresu

    You r fool of garbage . All u wrote was what poisonous medias told u .

    There is no better day for ethiopia than today .
    All these ill wishers will vanish when they understand that they can not stop the unstoppable .

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule