• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኛና የነሱ ኢትዮጵያ

April 3, 2014 06:50 pm by Editor 5 Comments

እኛ የምናውቃት ኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ ህዝቧ በመብራትና በውሃ እጦት የሚሰቃይባት ፣ በስልክና በኔትወርክ ችግር የሚማረርባት ፣  በመልካም አስተዳደር እጦት አሳሩን የሚበላባት ፣  አብዛኛው ህዝቧ የዛሬን እንጂ የነገን ማቀድ የማይችልባት፣ የተለያዩ ተንታኞችና አለማቀፍ ድርጅቶች “ችግር አለ” ብለው የሚያስጠነቅቋት ፣ ለዲሞክራሲ ፈር ቀዳጅ መሆን የሚገባው የፖለቲካ ስርዓት የሚያስፈራና ደም ደም የሚሸትባት ፣ ብዙ ዜናና ትንታኔ ስለ አንዲት የመንግስት ፕሮጀክት ለአመታት የሚነገርባት ፣ ከአንዲት ፕሮጀክት ብዙ ሚሊዮን ብር በሙስና ተዘርፎ ጥቂቶች የሚከብሩባት ፣ መንግስት ተብየው ሃገርና ህዝብ ከማስተዳደር ይልቅ ስልጣኑን ለማደላደል ተግቶ የሚሰራባት ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቿን በየአመቱ በስደት የምታጣ ፣ ለቁጥር በሚታክቱ አሰቃቂ የመኪና አደጋዎች በየቀኑ ዜጎቿ የሚረግፉባት ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቿ በህክምና እጥረት በሞት የምትነጠቅ ፣ ችግሮቿ ለቁጥር የሚታክቱ ነገር ግን ኩሩ ታሪክ ያላት ጥቂት ሆዳሞች በፈጠሩት ችግር አንገቷን የደፋች ሃገር ናት።

እነሱ ግን ልክ እንደማናውቃት ሌላ ሃገር ኢኮኖሚዋ አለምን ባስገረመ መልኩ ለተከታታይ ብዙ አመታት የተመነደገባት ፣  የአለማችን መዓት ሃገራት የሚቀኑባትና ልምድ የሚቀስሙባት ናት ይሉናል። ለመሆኑ ይህች እነሱ የሚሏት ሃገር የት ነው ያለችው? ለምን ይሆን ስለገዛ ሃገራችን ከአመት አመት ልክ እንደማናውቃት በሞኝ ውሸት የሚሰብኩን?

ሃገራችን ችግር ላይ መሆንዋን ችግርዋም ከግዜ ወደ ግዜ እየተወሳሰበ ለመፍታት ወደሚያስቸግር ሂደት ውስጥ እየገባ መሄዱን የተለያዩ ምሁራን ፣ ፖለቲከኞች ፣ ተንታኞች እንዲሁም አለማቀፍ ድርጅቶች ሲወተውቱ በአንፃሩ ደግሞ መንግስት ነኝ ብሎ የተቀመጠው አካል የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ እያለ ነው። ሁላችንም የምናውቀው አንድ እውነት ከጥቂት ሆዳሞች በስተቀር ኢትዮጲያዊ ሆኖ ሃገር እንድታድግለት የህዝቡም ኑሮ እንዲሻሻልለት የማይፈልግ የለም። ነገር ግን መንግስት ተብየው የሃገራችንን ችግር ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ የባሰ እያወሳሰበውና ጭርሱንም እየሸፋፈነ ወደ መፍትሄ አልባነት እየገፋው ይገኛል። የችግሩንም መኖር የሚጠቁሙ ዜጎችና አለማቀፍ አካላት እንደመንግስት ተቀራርቦ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ እንደሃገር ጠላት እየፈረጀ ይገኛል።

ሃገራችን ለዘመናት ለተጫናት ችግር የህወሃት መንግስት በጉልበት መመካት መፍትሄ ሳይሆን ሌላ ችግር ፈጣሪ መሆን ነው። ይህንንም መንግስት ተብየው በሚገባ ያውቀዋል። ነገር ግን ሃገር ወዳድነት ወደጎን ተብሎ በራስ ወዳድነትና አድር ባይነት ውድ ሃገራችን ኢትዮጵያ ወደ አጓጉል ሁኔታ ውስጥ እየተገፋች ነው። ጥቂት ራስ ወዳዶችና በግለኝነት የተዋጡ ተራ ብልጣ ብልጦች ለሃገር እድገት ከመጣር ይልቅ አንዲት ነገር እየተቀባበሉና ቅርፅ እየቀያየሩ ትንታኔ በመስራት የማናቃት ኢትዮጲያ በመፍጠር ህዝባችንን የህልም ዳቦ እየበላህ ኑር እያሉት ነው።

የሃገራችን ህዝብ ከመቼውም ግዜ በበለጠ የለት ተለት ኑሮው እጅግ አስቸጋሪ እስኪሆን ድረስ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ተይዟል። በመንግስት ቴሌቪዥን የሚያይዋት ኢትዮጵያ የት እንዳለች አያውቁም። ደስተኝነት ከአብዛኛው ህዝባችን ርቋል። የሃገራችን ህዝብ  በመንግስት ሚዲያ የሚነገረው የህልም የኢኮኖሚ ትሩፋት የት እንዳለ አያውቅም። በዋና ከተማ እየኖረ የሚጠጣው ያጣን ህዝብ ፣ በዋና ከተማ እየኖረ ለወራት በመብራት እጦት ሳቢያ በሻማ ለሚኖር ህዝብ ፣ በትራንስፖርት እጦት እየተሰቃየ ለሚኖር ህዝብ ፣ በመኪና አደጋ ፍራቻ በሰቀቀን ውሎ ለሚገባ ህዝብ በጥቂት ሆድ አደር ብልጣ ብልጦች ስለ ሃገር ኢኮኖሚ መመንደግ ፣ ስለ ከተማ ውበትና ስለትራንስፖርት መትረፍረፍ ይነገራዋል።

ናትናኤል ካብቲመር
ናትናኤል ካብቲመር

ሃገራችን ችግር ላይ ነች። ይህን ማለት ችግር መፍጠር አይደለም። መንግስት ነኝ ብሎ የተቀመጠው አካል የተሞላው በራስ ወዳዶች ፣ ብልጣ ብልጦችና የህዝብ ብሶት በማይሰማቸው ሆዳም ግለሰቦች ነው። ይህንን የሃገራችንን ችግር ከነችግር ፈጣሪዎቹ ማስወገድ የማንኛውም ሃገር ወዳድ ዜጋ ሃላፊነትና ግዴታ ነው። ሃገራችን ጭርሱን የማይፈታና ወደውሃላ የማይመለስ አደጋ ውስጥ ከገባች በውሃላ ጣት መጠቋቆሙ ከክፉ ፀፀት ውጪ የሚፈይደው ነገር አይኖርም። እኛም ሆነ እነሱ የምናወራው ስለ አንድ ሃገር ነው። ስለ ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያን ከችግር የማውጣት ግዴታ ያለብን ደግሞ እኛው ኢትዮጲያውያን ነን። አዎ ኢትዮጵያችን ከመቼውም ግዜ በላይ ችግር ላይ ነች።

natnaelkab@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Akalu says

    April 7, 2014 10:19 pm at 10:19 pm

    deg bilehal! yezih hulu yetewesasebe chigir yalebatin hager new beyeametu ye2 ahaz economy ediget eyasmezegebech new eyalu 23 amet mulu yihen miskin hizib game sichawetubet yenorut! dergin yaswegedelin fetari kesemay yiyen. fetari hageren yasbat amen!)

    Reply
  2. Saron says

    April 9, 2014 01:09 am at 1:09 am

    I donot understand why you focus on the dark side rather than on the positive side. you need to get up and work hard along your people to improve the living standard of your people including yourself. Remember what was happening 23 years ago let alone 50 years ago. We have now different Ethiopia except those who want to reverse the equality of all ethnic groups in Ethiopia. we have to accept the truth we can no more living by deceiving ourselves. we need to be realistic. Today the southerner thinks more critical than the former rulers and fellow country men. Narrowism have no place. I believe you agree with me. I support your idea in light of improvement rather than making ethiopia one ethnic designed country. EPRD is working around the clock despite the cry outside ethiopia and changed the mind set of the people living in ethiopia. We saw PM Meles funeral which was a good example in ethiopian history. No former ethiopia rulers barried like PM MZ in ethiopian history. Ask grand fathers and check history.

    Reply
    • xxxx says

      April 12, 2014 08:06 am at 8:06 am

      ሌባ ለአመሉ …..በጣም ያሳዝናል…ምናለ ሌቦች አርፋችሁ ብትበሉ….አኛ ብቻ ነን በጅብ መንጋ ውስጥ ተከበን እየኖርን እንደሆነን የምናውቅ …ጥላቻችን እንኳን ለመግለጽ አቅቷናል!!!

      Reply
    • abudalis says

      April 13, 2014 01:40 am at 1:40 am

      saron anchi hodam !

      Reply
  3. xxxx says

    April 12, 2014 07:58 am at 7:58 am

    እኛ የምናውቃት ኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ ህዝቧ በመብራትና በውሃ እጦት የሚሰቃይባት ፣ በስልክና በኔትወርክ ችግር የሚማረርባት ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት አሳሩን የሚበላባት ፣ አብዛኛው ህዝቧ የዛሬን እንጂ የነገን ማቀድ የማይችልባት፣ የተለያዩ ተንታኞችና አለማቀፍ ድርጅቶች “ችግር አለ” ብለው የሚያስጠነቅቋት ፣ ለዲሞክራሲ ፈር ቀዳጅ መሆን የሚገባው የፖለቲካ ስርዓት የሚያስፈራና ደም ደም የሚሸትባት ፣ ብዙ ዜናና ትንታኔ ስለ አንዲት የመንግስት ፕሮጀክት ለአመታት የሚነገርባት ፣ ከአንዲት ፕሮጀክት ብዙ ሚሊዮን ብር በሙስና ተዘርፎ ጥቂቶች የሚከብሩባት ፣ መንግስት ተብየው ሃገርና ህዝብ ከማስተዳደር ይልቅ ስልጣኑን ለማደላደል ተግቶ የሚሰራባት ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቿን በየአመቱ በስደት የምታጣ ፣ ለቁጥር በሚታክቱ አሰቃቂ የመኪና አደጋዎች በየቀኑ ዜጎቿ የሚረግፉባት ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቿ በህክምና እጥረት በሞት የምትነጠቅ ፣ ችግሮቿ ለቁጥር የሚታክቱ ነገር ግን ኩሩ ታሪክ ያላት ጥቂት ሆዳሞች በፈጠሩት ችግር አንገቷን የደፋች ሃገር ናት።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule